ርእሰ ጉዳይ

የትምህርት ቦርድ ወቅታዊ መረጃ፦ኦክቶበር 11, 2024

የትምህርት ቦርድ በተለይም በሊተርሲ ትምህርት ላይ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ዲስትሪክቱ እንዴት እየሰራ እንዳለ መፈተሽ እና ክትትል ማድረጉ እንደቀጠለ ነው። በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ተማሪዎችን የምንደግፍበትን ሁኔታ በተመለከተ በዚህ ሳምንት ቦርዱ ትኩረት በመስጠት ተወያይቷል። በተጨማሪም ቦርዱ የሜሪላንድ የወደፊት ብሉፕሪንት እንዴት በተግባር ላይ እንደሚውል እና የጸደቁ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን በተመለከተ ወቅታዊ መረጃ አግኝቷል። 

የሁሉንም ተማሪዎች ሊተርሲ ማበልፀግ፡ በት/ቤቶቻችን ውስጥ የሚማሩ የተለያዩ ተማሪዎችን መደገፍ

የማንበብ እና የመጻፍ ችሎታን ማዳበር ለሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ስኬት ወሳኝ ነው። ጀማሪ የብዝሃ ቋንቋ ተማሪዎች እና የልዩ ትምህርት አገልግሎት የሚያገኙ ተማሪዎች የተለየ የትምህርት ፍላጎቶች አሏቸው። ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ እና የትምህርት ውጤቶቻቸውን ለማሻሻል እነዚህን ተማሪዎች መደገፍ አስፈላጊ ነው። በሊተርሲ አፈጻጸም ረገድ የቅርብ ጊዜ መረጃ እንደሚያመለክተው በእነዚህ ቡድኖች መካከል ያሉ ክፍተቶችን ለማጥበብና ለመዝጋት የታለሙ ስልቶችን አስፈላጊነት አጉልቶ ያሳያል።

ሙያዊ/ፕሮፌሽናል ትምህርት የተማሪዎችን ስኬት ይደግፋል

ለምን፦ በዲስትሪክት ደረጃ የሚሰጥ ሙያዊ ትምህርት የነዚህን ተማሪዎች የተለየ የትምህርት ፍላጎት በማሟላት ረገድ ለአጠቃላይ ትምህርት መምህራን እና ለመሪዎቹ አስፈላጊ ክህሎቶችን እና እውቀትን ያስታጥቃቸዋል። የአስተማሪዎችን እውቀት ማበልፀግ ላይ ኢንቨስት ስናደርግ፣ተማሪዎቻችን በተሻሻሉ የመማር ማስተማር ልምዶች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

እንዴት? MCPS በግላዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ትምህርት መስጠት፣ ምላሽ ሰጭ ባህልን ማጎልበት፣ እና አካታች የማስተማር ልምምዶችን የመሳሰሉ ቁልፍ የሙያ ዘርፎች ላይ መምህራንን እያሰለጠነ ነው። አስተማሪዎች ያገኙትን እውቀት ለጀማሪ የብዝሃ ቋንቋ ተማሪዎች እና የልዩ ትምህርት አገልግሎቶችን የሚያገኙ ተማሪዎችን ፍላጎቶች ለማሟላት ይተገብራሉ። 

የተለያዩ ተማሪዎችን የመደገፍ ስልቶች

ለምን? አስፈላጊ ግብዓቶችን እና ድጋፎችን በመስጠት በልዩ ቡድኖች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችን የቋንቋ ክህሎቶቻቸውን፣ የንባብ ግንዛቤአቸውን፣ እና አጠቃላይ የአካዳሚክ አፈጻጸማቸውን እንዲያሻሽሉ ልንረዳቸው እንችላለን። 

እንዴት? የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አስተማሪዎች የተለያዩ ተማሪዎችን የትምህርት ፍላጎቶች ለማሟላት ልዩ ልዩ የማስተማር ስልቶችን ይጠቀማሉ። እነዚህ ስልቶች ለአጋር ወይም ለትንንሽ ቡድን ተግባራት የሚሰጡ አስተያየቶችን፣ ለሚያስፈልጋቸው ተጨማሪ ልምምድ እና በእያንዳንዱ ተማሪ የእንግሊዘኛ ቋንቋ የብቃት ደረጃ ላይ የተመሠረተ የመረዳት አቅማቸውን የሚፈትሹ ዘዴዎችን ያካትታሉ።

ማሻሻል ማለት ቀጣይነት ያለው ሂደት ነው

ለምን? የተማሪዎች የመማር ፍላጎት፣ የአስተማሪዎች ችሎታ፣ እና ውጤታማ የማስተማር ዘዴዎች ሁልጊዜ የሚሻሻሉ ልምምዶች ናቸው። 

እንዴት? MCPS በየጊዜው ያለውን እድገት ይፈትሻል፥ እና ለቤተሰቦች ያሳውቃል። ይህ ቀጣይነት ያለው ሂደት ለተማሪዎች የትምህርት ፍላጎቶች ምላሽ እንድንሰጥ እና የትምህርት አቀራረብ ዘዴዎቻችንን እንድናሻሽል ይረዳናል፣ይህም ሁሉም ተማሪዎች የአካዳሚክ ስኬት እንዲኖራቸው ያደርጋል።

ይህ ውይይት በተለይም በሊተርሲ ትምህርት የተማሪዎችን ውጤት ከማሻሻል አንጻር የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS) ተጠያቂ ለማድረግቦርዱ የገባውን ቃል ይደግፋል። በተጨማሪም፥ በመካሄድ ላይ ያለውን መሻሻል በማንፀባረቅ፣በየጊዜው ያለውን እድገት በመፈተሽ፣ ውጤቶችን መገምገም እና እንደ አስፈላጊነቱ የታሰቡ ለውጦች መከናወናቸውን ከማረጋገጥ አንጻር የቦርዱን ትኩረት ያካትታል።

በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ የተለያዩ ተማሪዎችን እንዴት እንደምንደግፍ የበለጠ ለማወቅ እዚህ ላይ የቀረበውን እንዲመለከቱ እናበረታታዎታለን።

ለብሉፕሪንት ትግበራ ዲስትሪክቱ በጥረት ላይ ነው

ብሉ ፕሪንት ስለ ሜሪላንድ የወደፊት ዕጣ የተነደፈ በመላ ስቴቱ በትምህርት ላይ የሚከናወን ትልቅ ማሻሻያ ነው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰራተኞች ዲስትሪክቱ በትክክለኛው መንገድ እየሠራ መሆኑን ወይም በትምህርት አቀራረብ ለውጥ ከሚጠበቀው በላይ እየተሠራ መሆኑን ለቦርዱ ወቅታዊ መረጃ አጋርተዋል።

2023-24 እና 2024-25 የትምህርት ዓመት ላይ የተከናወኑ ቁልፍ ክንውኖች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-

  • 2023-24 የትምህርት አመት ላይ 260 አዲስ የሙሉ ቀን የቅድመ መዋለ ህፃናት ተማሪዎች ተጨምረዋል።

  • 268 የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዲፕሎማ እና ከሞንትጎመሪ ኮሌጅ በተጓዳኝ አሶሽዬት ዲግሪ በማግኘት ተመርቀዋል።

  • 2024-25 የትምህርት አመት ለመምህራን የመነሻ ደመወዝ $62,588 እንዲሆን ተወስኗል።

  • 2024-25 የትምህርት አመት 19 የህዝብ ትምህርት ቤቶች ተጨምረዋል፥ ይህም አጠቃላይ ቁጥሩን ወደ 53 ያሳድገዋል።

ቦርዱ በብሉፕሪንት ላይ የተዘረዘሩትን ግቦች በመተግበር ያምናል፥ ይህንንም ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር ከመለወጥ አኳያ የዲስትሪክቱን ጥረት ይደግፋል። ይህንን እውን ለማድረግ የገንዘብ ድጋፍ፣ መሠረተ ልማት፣ እና የአቅም ጉዳዮችን የመሳሰሉ ተግዳሮቶች አሉ። ዲስትሪክቱ ወደፊት እንዲራመድ ለማገዝ ቦርዱ 2025 የህግ አውጭዎች መድረክ ላይ ከእነዚህ ተግዳሮቶች መካከል አንዳንዶቹን ለይቶ አቅርቧል።

አቀራረቡንበመመልከት ብሉፕሪንት MCPS ውስጥ እንዴት ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል የበለጠ ይረዱ። 

የጸደቁት የፖሊሲ ማሻሻያዎች ግልጽነትን እና የትኩረት አቅጣጫዎችን ያሳያሉ 

ቦርዱ በፖሊሲ ACF፣ ስለ ፆታዊ ጥቃት እና በተማሪዎች ጾታዊ ትንኮሳ ላይ የፖሊሲ አርቃቂ ኮሚቴው ያቀረበውን ማሻሻያ አጽድቋል። የፌደራል ህጉን ለማስከበር ቴክኒካዊ ማሻሻያ ማድረግ ያስፈልግ ነበር። ለውጦቹ የሀረጎቹን ትርጓሜ ግልፅ በማድረግ፣ የመዋቅር ለውጦችን በማንፀባረቅ ረገድ ግልጽነት አላቸው። 

በዚህ ሰነድ (pdf) ላይ የተደረጉትን ማሻሻያዎች ይገምግሙ እና ለበለጠ መረጃ ውይይቱን ይመልከቱ

ቀጣይ ስብሰባዎች

  • ኦክቶበር 22, ማክሰኞ - መደበኛ የስብሰባ ቀን

አጀንዳዎችን፣የስብሰባ ግብአቶችን ለመከታተል በቀጥታ ስርጭት ወይም የተቀዳ የስብሰባ ውይይት ለመመልከት የእኛን ድረ ገጽ ይጎብኙ።

የመሳተፍ እድሎች

ማህበረሰቡ ከቦርዱ ጋር እንዲሳተፍ እና እንዲተባበር እናበረታታለን። በእኛ ድረ ገጽ ላይ መሳተፍ ስለሚችሉባቸው መንገዶች ያንብቡ።

ግንኙነትዎን ይቀጥሉ

በፌስቡክ እና X  ላይ ይከታተሉን

ኢሜል ያድርጉልን፦ boe@mcpsmd.org


ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org