መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሀሙስ ኖቨምበር 14 2024

የMCPS ተማሪዎች የ44ኛው የወጣት አሜሪካዊ ቤትን/Young American House ግንባታ ጀምረዋል

በህንፃ ስራዎች በጎ-አድራጎት ፕሮግራም/Construction Trades Foundation program ውስጥ ያሉ የMCPS ተማሪዎች በሲልቨር ስፕሪንግ ለሚገኘው ለ44ኛው የወጣት አሜሪካዊ ቤት/Young American House ግንባታ የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ጠንክረው በመስራት ላይ ናቸው። ይህ አስደሳች ፕሮጀክት፣ ይህን ቤት ከስር መሰረቱ ህይወት እየዘሩበት ያሉት የግንባታ ቴክኖሎጅ ተማሪዎቻችንን ክህሎት እና ቁርጠኝነት አጉልቶ ያሳያል። በግንባታው ላይ ያሉትን የቅርብ ጊዜ ፎቶዎችን ይመልከቱ እና በሂደት ላይ ያለውን የእደጥበብ ሥራ ይመልከቱ። ይህንን ከመጋረጃ በስተጀርባ ያለው የአጭር ጊዜ እይታ እንዳያመልጥዎ - ሙሉውን ታሪክ እና ተጨማሪ ምስሎችን ለማግኘት ድህረ ገጻችን ይጎብኙ


የMCPSን የሥራ ማስኬጃ በጀት መገንዘብ

ሁሉም ባለድርሻ አካላት የስራ ማስኬጃ በጀቱን እንዲመረምሩ ለማድረግ ተደራሽ፣ ለተጠቃሚ ምቹ እና ግልፅ መንገድ ለማቅረብ MCPS አዲስ የስራ ማስኬጃ ባጀት ዳሽቦርድ ፈጥሯል።

በዳሽቦርዱ ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች ያለውን ቪዲዮ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ይውሰዱ።

MCPS የ2026 የበጀት ዓመት የስራ ማስኬጃ በጀት ላይ ለመወያየትበተከታታይ በሚካሄዱ የማዳመጥ ክፍለ ጊዜዎች እያስተናገደ ነው። እያንዳንዱ ዶላር በትምህርት ቤት ስርዓት ውስጥ እንዴት እንደሚመደብ ለማሰስ፣ ስለቀጣይ ለውጦች ለማወቅ/ለመማር፣ እና ግንዛቤዎን ለማካፈል የMCPS አመራርን ይቀላቀሉ።

የእርስዎ ድምጽ ዋጋ አለው እና ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ እና በውይይቱ ላይ እንዲሳተፉ እናበረታታዎታለን። በቀጣይ የሚካሄዱ መድረኮች፡ 

የመጀመሪያው የበጀት ፎረም አምልጦዎታል? እዚህ ጋርመመልከት ይችላሉ


የዊንተር አየር/ወራት እየተቃረበ ነው (ምናልባት)፡ ዝግጁ ኖዎት?

ዊንተር እየተቃረበ ነው እና MCPS የሚያስፈልጎትን ሁሉ ያቀርባል። ከአየር ሁኔታ ጋር በተገናኘ ስለሚኖሩ መዘግየቶች እና መዘጋቶች ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ግንኙነትዎ እንዲቀጥል የሚረዱ መሳሪያዎች ለማግኘት Stay Connected ድረ-ገጻችንን ይጎብኙ። በዚህ ዊንተር ወቅት ደህንነትዎን ይጠብቁ! 

የበላይ ተቆጣጣሪው/ዋ ቪዲዮ እንዳያመልጥዎት

ቪዲዮውን በዚህ ይመልከቱ፡https://youtu.be/ugfu7nIDpuk 


ለትምህርት ቤቱ ካላንደር/ቀን መቁጠሪያ የእርስዎ ግብረ መልስ ያስፈልገናል!

MCPS የ2025–2026 መደበኛ የትምህርት ዓመት ካላንደር/የቀን መቁጠሪያ ማዘጋጀቱን ቀጥሏል። ዲስትሪክቱ ከሰራተኞች፣ ከቤተሰቦች፣ ከተማሪዎች እና ከማህበረሰብ አባላት ተጨማሪ ግብረመልስ ይፈልጋል። በዳሰሳ ጥናቱ 2ኛ ዙር ላይ ግብረ መልስዎን ለመስጠት ጥቂት ጊዜ ይውሰዱ ። የዳሰሳ ጥናቱ እሁድ፣ ዲሴምበር 1 ይዘጋል።

የዳሰሳ ጥናቱን ለማግኘት   እዚህ ጋር ይጫኑ። 


ለኮርስ መጨረሻ ፈተናዎች ይዘጋጁ። 

የባዮሎጂ B እና ብሔራዊ፣ ስቴት፣ እና አካባቢያዊ (NSL) የመንግስት ቢ ኮርሶች የኮርስ መጨረሻ (EOC) ፈተናዎች እየተቃረቡ ነው። ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ ከዲሴምበር 9, 2024, እስከ ጃንዋሪ 22, 2025 ድረስ ክፍት ነው። እነዚህ ፈተናዎች የተማሪዎችን   የሁለተኛ ሴሚስተር ኮርስ ውጤቶች 20% ይይዛሉ። 

ለምን እንደሚተቅም፡

የEOC ፈተናዎች በሁለቱም ሴሚስተር A እና ሴሚስተር B የባዮሎጂ እና የNSL የስነ-መንግስት ኮርሶች ላይ የተማሪ እውቀትን የሚገመግሙ በስቴት የተደነገጉ ግምገማዎች ናቸው። በተማሪው የመጨረሻ ውጤት ላይ በቀጥታ ተጽዕኖ ያሳድራል። 

የበለጠ ለማወቅ የት መሄድ እንዳለብዎት፡

ስለ EOC ሂደት ለማንበብ እና በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ለማግኘት የMCPSን ድህረ ገጽን ይጎብኙ። 


የተማሪ እድሎች

በብሄራዊ C-SPAN ዘጋቢ ፊልም ውድድር ላይ ይሳተፉ

ብሄራዊ የC-SPAN ዶክመንተሪ ውድድር ከ6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ስለ ጠቃሚ የማህበረሰብ ጉዳይ በጥልቀት እንዲያስቡ እድል ይሰጣል። ተማሪዎች "ለፕሬዝዳንቱ የሚያስተላልፉት መልዕክት" ከሚለው መሪ ሃሳብ ጋር በሚገናኝ ርዕስ ላይ አጭር የቪዲዮ ዘጋቢ ፊልም እንዲሰሩ ተጠይቀዋል።

ዝርዝር:

ቀጣዩ እርምጃ ምንድን ነው፡

የበለጠ ለማወቅ የት መሄድ እንዳለብዎት፡

ውድድሩ ላይ እንዴት እንደሚሳተፉ እና የውድድሩን ህጎች ጨምሮ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት{C-SPAN StudentCam ድረ-ገጽን መጎብኘት ይችላሉ።


ለRales-O’Neill ስኮላርሺፕ ያመልክቱ  

በሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ፋውንዴሽን (MCPSEF) የሚሰጠው የ Rales-O'Neill ስኮላርሺፕ ማመልከቻዎች አሁን ላይ ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲኒየሮች/የመጨረሻ ዓመት ተማሪዎች ክፍት ናቸው። ስኮላርሺፖቹ ለወደፊት ትምህርቶች 10,000 ዶላር የሚሰጡ ሲሆን ይህም ለሁለት መቶ ተማሪዎች ይሰጣል።

ማመልከቻዎች እስከ ቅዳሜ፣ ጃንዋሪ 25, 2025 መቅረብ ይኖርባቸዋል። ብቁነትን እና ህጎችን በተመለከት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት MCPSEF ድረ-ገጽን ይጎብኙ።


የMPSSAA Football Playoff ትኬቶች በሽያጭ ላይ ናቸው

ለአስደሳች ፕሮግራም ይዘጋጁ! የMaryland Public Secondary Schools Athletic Association (MPSSAA) Football State Quarterfinals ትኬቶች ኖቬምበር 19, ማክሰኞ እኩለ ቀን ላይ ለሽያጭ ይቀርባሉ

አስደሳች ጊዜ እንዳያመልጥዎ-ቀኑን መዝግበው ይያዙ እና ቡድንዎን ለመደገፍትኬትዎንይግዙ!


የአካባቢ ጥበቃ የአገልግሎት ቀን! 

ቅዳሜ፣ ኖቬምበር 23 ከ1-4 p.m. ለሚካሄድው የአገልግሎት ቀን Lathrop E. Smith Environmental Education Centerን ይቀላቀሉ።በሁሉም የክህሎት ደረጃ ያሉ ቤተሰቦች ማዕከሉን ለማሻሻል እና ለማስዋብ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ በሆኑ ፕሮጀክቶች ላይ እንዲሰሩ ተጋብዘዋል። ከወላጆቻቸው ጋር የሚሳተፉ ተማሪዎች የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ። ለመሳተፍ እና ለውጥ ለማምጣት ቀድመው ይመዝገቡ! 


ግንኙነትዎን ይቀጥሉ



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)