መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ፌብርዋሪ 6/2025


የትምህርት ቦርድ ለ 2026 የበጀት አመት የስራ ማስኬጃ በጀት በጊዜያዊነት ተቀብሏል።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS) 2026 የበጀት ዓመት የስራ ማስኬጃ በጀት በጊዜያዊነት ለመቀበል በአንድ ድምፅ ወስኗል። ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የመጀመሪያቸው የሆኑት ሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ W. ቴይለር ያቀረቡት $3.6 ቢሊዮን ዶላር በጀት፣በቀጥታ በት/ቤቶች ኢንቨስት በማድረግ የተማሪዎችን የትምህርት ስኬት በመደገፍ እና መዋቅራዊ ክፍተቶችን በመቅረፍ መሰረታዊ ነገሮችን በማሟላት ላይ ያተኩራል። ሙሉውን ዘገባ ያንብቡ።


"Girls With Impact Spring Program" የተጽዕኖ ፈጣሪ ልጃገረዶች ፕሮግራም አሁን ለምዝገባ ክፍት ነው።


Annelise Allport,፣ በስተግራ እና Jaylin Adames በስተቀኝ

Annelise Allport፣ በፑልስቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲንየር ተማሪ ናት፣አንድ ቀን የራሷ ቢነስ እንደሚኖራት እቅድ አላት። እንዴት የቢዝነስ ባለቤት መሆን እንደምትችል ለመማር ወደ "Girls With Impact (GWI)" የመጣችው ባለፈው ፎል ነው።

"ከኮርሱ በጣም የወደድኩት ያቀረብኩት የቢዝነስ እቅዴ በመጨረሻ ትርጉም ያለው መሆኑን ማየት መቻሌ ነበር" ብላለች:። "ይህ ፕሮግራም በሙያ ጉዞዬ የምፈልገውን አቅጣጫ እንዳጠናክር ረድቶኛል" ትላለጭ

Annelise በፕሮግራሙ በቆየችባቸው 10 ሳምንታት ውስጥ ብዙ እንደተማረች ተናግራለች፣ ይህም በጀት ማዘጋጀትን፣ ደንበኞችን መሳብ እና ግንኙነት መገንባትን፣እና ስለ ፋይናንስ አያያዝ ጭምር ትምህርት አግኝቼበታለሁ ብላለች።

GWI ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ልጃገረዶች 10-ሳምንት የስራ ፈጠራ ትምህርት ይሰጣል። ይህ ፕሮግራም የሚያተኩረው ወሳኝ የቢዝነስ እና መሪነት ክህሎቶችን የቢዝነስ ዕቅድ፣ ማርኬቲንግ እና ፋይናንሺያል እውቀትን ጨምሮ ሌሎች ርዕሶችን በሚያካትት በትግበራ ስርዓተ ትምህርት በመጠቀም ነው።

በዊንስተን ቸርችል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁንየር፣ Jaylin Adames የአመራር ልምድ ለማግኘት እና ስለ ቢዝነስ ምክር ለመውሰድ GWI ጋር ስትሳተፍ ቆይታለች። የቢዝነስ ሥራዋን ለማቅረብ ከተመረጡት አምስት ተማሪዎች መካከል አንዷ ስትሆን—በዋጋ ተመጣጣኝ የሆኑ የዞማ ፀጉር ምርቶችን አቅርባለች። የቢዝነስ ሥራ ውጤቷን ማቅረብ መቻሏ የፕሮግራሙ ተወዳጅ ክፍል እንደሆነ እና ከሌሎች ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ጋር መተባበር ያስደስታት እንደነበር ገልጻለች።

GWI የቢዝነስ አቀራረብ ክህሎቱን ለማሳደግ እንደጠቀማት እና ስለ ቢዝነስ አስተዳደር ለመማር እንደረዳት ተናግራለች።

ማርች 3 በሚሆንበት ሳምንት ለሚጀመረው GWI ለስፕሪንግ ክፍለ ጊዜ ለመመዝገብ ክፍት ነው። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ እና ይመዝገቡ


BOE የማህበረሰብ መሪዎች እና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የአማካሪ ኮሚቴን እንዲቀላቀሉ ይፈልጋል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ማህበረሰብ መሪዎች እና በኮሙኒኬሽን እና በተሳትፎ ረገድ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በትምህርት ቦርድ አዲስ የተቋቋመውን የግንኙነት እና የማህበረሰብ ተሳትፎ አማካሪ ኮሚቴ እንዲቀላቀሉ ተጋብዘዋል፣ ይህ ጠቃሚና ቁልፍ የሆነ ተነሳሽነት ያስፈለገበት ምክንያት በቦርዱ እና በማህበረሰብ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር ነው።

ይህ ኮሚቴ የማህበረሰቡን ትስስር በማጠናከር፣ ግልጽነትን በማሻሻል፣ እና በጣም አስፈላጊ በሆኑ የቦርዱ ተነሳሽነቶች ዙሪያ ትርጉም ያለው ተሳትፎን በመምራት ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። አባላት ከትምህርት ስርዓቱ ጋር በቀጥታ በመተባበር የዲስትሪክቱን የግንኙነት ስልቶች/ስትራቴጂዎች ለማጠናከርና ለማጎልበት እና ትምህርት ቤቶችን እና ማህበረሰቦችን በሚመለከቱ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ሁሉም ድምፆች እንዲሰሙ እገዛ ያደርጋሉ።

ለ 2025 የትምህርት አመት፣ የኮሚቴው ትኩረት የክራውን፣ የዉድዋርድ፣ እና የደማስክስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክቶችን በሚመለከት በመጪው የድንበር ጥናቶች ላይ መሣተፍ ይሆናል።

ቦርዱ በተለይም ከተለያዩ ማህበረሰቦች መካከል በኮሙኒኬሽን እና በተሳትፎ ልምድ የተካኑ ግለሰቦችን ይፈልጋል። ጠንካራ እና የማህበረሰብ አጋርነት ትብብር ለመገንባት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው የማህበረሰብ መሪዎች ለኮሚቴው ስራ ጠቃሚ ይሆናሉ። የኮሚቴው አላማ ሁሉም ማህበረሰቦች—በተለይ በኮሚቴው ትኩረት በቀጥታ የሚመለከታቸው — በንቃት እንዲሳተፉ በማድረግ የዲስትሪክት ግንኙነቶችን ተደራሽነት እና ተፅእኖ ማስፋት ነው።

ኮሚቴው እንደ አስፈላጊነቱ ዓመቱን በሙሉ ስብሰባዎችን ያካሄዳል። አባላት በበጎ ፈቃደኝነት ለአንድ አመት የሚያገለግሉ ሲሆን የቦርዱ ምክትል ፕሬዝዳንት ከኮሚቴው ጋር ቋሚ የቦርድ ተወካይ ሆነው ያገለግላሉ።

ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች የማመልከቻ ቅጹን እስከ አርብ፣ ፌብሩዋሪ 28 ድረስ ሞልተው እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ።

ለበለጠ መረጃ፣ የግንኙነት እና የተሳትፎ አማካሪ ኮሚቴየሚለውን ይጎብኙ።


ለተመራቂ ሲንየር ተማሪዎች NAACP ስኮላርሺፕ ሽልማት

የሞንትጎመሪ ካውንቲ NAACP ቅርንጫፍ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተመራቂ ሲንየሮች $1,000 ስኮላርሺፕ ይሰጣል። ማመልከቻ ለማቅረብ የመጨረሻው ቀን አርብ፣ ማርች 21 ነው። አመልካቾች 3.0 ወይም ከዚያ በላይ GPA ሊኖራቸው ይገባል፣ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎች ላይ የሚሳተፉ፣ እምነትን መሰረት ያደረገ፣ ሀይማኖታዊ፣ ወይም የበጎ ፍቃደኝነት ተግባራት ላይ መሳተፍ እና “The Fight for Justice Continues!”/“ለፍትህ ትግሉ ይቀጥላል!” በሚል መሪ ሃሳብ 300 ቃላት ድርሰት ማቅረብ አለባቸው።

ማመልከቻዎችን በሚከተለው አድራሻ ማቅረብ አለባቸው፦ Rebecca Gibson, Board of Education office, 15 W. Gude Drive, Suite 100, Rockville, MD, 20850

የነፃ ስኮላርሺፖቹ እሁድ፣ ሜይ 18 በዓመታዊ "Freedom Fund Dinner" የእራት ግብዣ ወቅት ይሰጣል።

2025 NAACP ስኮላርሽፕ ሽልማቶች ማመልከቻ ቅጽ

ተጨማሪ መረጃ


የተማሪ እድሎች እና ማሳሰቢያዎች

በታሪክ የጥቁሮች ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች (HBCU) ትርኢት አርብ፣ ፌብሩዋሪ 14 ከቀኑ 6–8፡30 ፒ.ኤም በሼዲ ግሮቭ ዩኒቨርስቲዎች (USG) ይካሄዳል። ከ 8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው/አሳዳጊዎቻቸው ከ 50 HBCUs በላይ ተወካዮች ጋር የመገናኘት እድል ይኖራቸዋል። ስንየር ተማሪዎች ከ (National Pan-Hellenic Council) የሚሰጡ የስኮላርሺፕ ዕድሎችን በቦታው ማግኘት ይችላሉ፤ እንዲሁም ስለ ኮሌጅ ህይወት እና ወርክሾፖች ውይይት ይደረጋል። ተጨማሪ መረጃ

FAFSA/MHEC One Application Completion Event፦ፌብሩዋሪ 14 ከቀኑ 6–8:30 p.m. በዚህ አድራሻ ይካሄዳል፦ USG ይህ ዝግጅት ለሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየር ተማሪዎች እና ለወላጆቻቸው ክፍት ነው። በስፓንሽኛ ቋንቋ አስተርጓሚዎች ይኖራሉ። FAFSA ወይም MHEC One ማመልከቻ እርዳታ ከፈለጉ፣ቀጠሮ ለመያዝ ይመዝገቡ። ያለቀጠሮ ቢመጡም ሊስተናገዱ ይችላሉ።
ተጨማሪ መረጃ
FAFSA, MHEC ማጠናቀቅ ዝግጅት በራሪ ወረቀት፣ ፌብሩዋሪ 14፣ 2025

Summer RISE 2025 የተማሪዎች ምዝገባይህ ፕሮግራም በሠመር ወቅት ተግባራዊ ልምድ መቅሰም ለሚፈልጉ በአሁኑ ወቅት የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሶፎሞር ተማሪዎች እና ለጁንየር ተማሪዎች ክፍት ነው። ተሳታፊ ተማሪዎች ከጁን 23 እስከ ጁላይ 25 ድረስ በአካል፣ በ ቨርቹዋል፣ ወይም በስብጥር ዕድሎች በኢንዱስትሪ ምርጫዎቻቸው መሰረት የሙያ ልምድ ያገኛሉ። ምዝገባ ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 18 ይዘጋል።

የመኪና እና የኮምፒውተር ሽያጭ፡ በአውቶሞቲቭ ትሬድስ ፋውንዴሽን እና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፋውንዴሽን ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ያገለገሉ መኪናዎችን እና ኮምፒውተሮችን ቅዳሜ፣ ፌብሩዋሪ 22 ከሰአት በፊት 9-11 a.m. በደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Damascus High School, 25921 Ridge Road in Damascus. ይሸጣሉ። ለሽያጭ የቀረቡ መኪናዎችን ዝርዝር ለማየት፣ፌብሩዋሪ 22 ሲቃረብ አውቶሞቲቭ ትሬድስ ፋውንዴሽን ድረገፅ ይጎብኙ።

የተንቀሳቃሽ ስልክ ቪዲዮ ውድድር፡ ለሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍት ነው፣ ይህ ውድድር ትኩረት ባለመስጠት ስለሚደረጉ የእግር ጉዞዎች እና የማሽከርከር አደጋዎች ግንዛቤ ይሰጣል። በመንገድ ላይ ሳሉ በስልክዎ ላይ ሳይሆን በዙርያዎ ላይ ማተኮር ያለውን ጠቀሜታ ለማሳወቅ 30 ሰከንድ የሚፈጅ ቪዲዮ ፍጠሩ። በቡድን አዘጋጅተው የሚያቀርቡ ተማሪዎች "Apple MacBook Air, Apple Watch ወይም እስከ $800" ዶላር ሽልማት ማሸነፍ ይችላሉ በተጨማሪ (SSL ሠአቶችን ያገኛሉ)!። ቪዲዮዎችን በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ማቅረብ ይቻላል። ማስረከቢያው ጊዜ አርብ፣ ፌብሩዋሪ 28 ያበቃል።


የጥቁሮች ታሪክ የሚዘከርበት ወር

ከዚህ በታች ያለው ዝግጅት ለተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት ክፍት ነው። ተማሪዎች እስከ ሁለት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶች ማግኘት ይችላሉ፡-

ጥቁር ተማሪዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመማሪያ ቦታዎችን ስለመፍጠር በተማሪዎች የሚመራ ማቀንቀን፡

በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሚማሩ የጥቁር ተማሪዎች ህብረት አባላት ጥቁር ተማሪዎችን የሚያቅፍ ደህንነት የሠፈነበት የመማሪያ አካባቢዎችን ለመፍጠር በማቀንቀን ሀሳብ ያካፍላሉ። 

ሐሙስ፣ ፌብሩዋሪ 20 ከቀኑ 6፡30-8 ፒ.ኤም
ዙም መመዝገቢያ አገናኝ/Zoom Registration Link
በራሪ ጽሑፍ


የደቡብ እስያ አሜሪካውያን ወላጆች፣ ተማሪዎች የዳሰሳ ጥናትን እንዲያጠናቅቁ ተጋብዘዋል

የበደቡብ እስያ አሜሪካውያን ጉዳዮችን በሚመለከት የሜሪላንድ ገቨርነር ኮሚሽን ወላጆች እና የደቡብ እስያ ዝርያ ያላቸው ተማሪዎች ስለ ልምዳቸው እና ስለትምህርት ያላቸውን አመለካከት የዳሰሳ ጥናት ምላሽ እንዲሰጡ ይጠይቃል። ይህ ግብረመልስ ኮሚሽኑ በደቡብ እስያ አሜሪካ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ተማሪዎችን፣ ቤተሰቦችን እና አስተማሪዎች በተሻለ ሁኔታ ለመደገፍ እርምጃዎችን/እቅዶችን እና ስልቶችን እንዲያዘጋጅ/እንድታዘጋጅ ይረዳዋል/ይረዳታል። የዳሰሳ ጥናቱን ሞልተው ይመልሱ


በቀን መቁጠርያዎ ላይ ምልክት ያድርጉ!

ለመደነቅ ይዘጋጁ "MCPS County Bocce" ሻምፒዮና ቅዳሜ፣ ፌብሩዋሪ 8 ከሰዓት በፊት 10 a.m. ላይ  Watkins Mill High School, 10301 Apple Ridge Road in Gaithersburg.   ይካሄዳል።

60ኛው አመታዊ የዋሽንግተን ሜትሮፖሊታን ኢንተርስኮላስቲክ የዋና እና በጥልቀት የመስመጥ/ዳይቪንግ ሻምፒዮና ከፌብሩዋሪ 5-8 ይካሄዳል። ይህ ዝግጅት ወጣት አትሌቶች በጀርመንታወን የቤት ውስጥ ዋና ማእከል ውሃ ውስጥ ጠልቀው የመግባት ህልሞችን እያሳዩ በሁላችንም ውስጥ ያለውን ስሜት በመቀስቀስ መንፈስን የሚያድስ ጠንካራ ትዕትንት የሚታይበት ነው። ከእኛ ጋር ይቀላቀሉ!


ድል አድራጊዎችን ማበረታታት! 

28ኛው አመታዊ Pompons የካውንቲ ውድድር ከ 25 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተውጣጡ ቡድኖች ለከፍተኛ ክብር ሲወዳደሩ ከፍተኛ ፉክክር ፈጥሯል። የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አራተኛውን የካውንቲ አሸናፊነት ማዕረግ በማግኘት ከአንደኛ ዲቪዝዮን 1ኛ ሲሆን ክላርክስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ 2ኛ እና 3ኛ ዲቪዝዮን ድል አግኝተዋል። ስለ አሸናፊዎቹ ተጨማሪ ያንብቡ፤ የፎቶ ክምችት ይመልከቱ። 


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)