አበይት ጉዳዮች

የትምህርት ቦርድ ወቅታዊ መረጃዎች
ፌብሩዋሪ 6, 2026

የትምህርት ቦርዱ ፌብሩዋሪ 5 ባካሄደው የሥራ ክፍለ ጊዜ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማካለል ምክረሃሳቦችን፣ የካውንቲ አቀፍ የአንደኛ ደረጃ የወሰን ጥናት እና ከቅድመ-መዋዕለ ሕፃናት እስከ 12ኛ ክፍል የሂሳብ ትምህርት አዲሱን ዕቅድ ገምግሟል። ፌብሩዋሪ ወር የጥቁሮች ታሪክ የሚዘከርበት ወር ነው፣ ቦርዱ በሞንትጎመሪ ካውንቲ የጥቁር ታሪክ በ "Scotland A.M.E. Zion Church" ጽዮን ቤተክርስቲያን ውስጥ የትምህርት መሠረት የተጣለበትን በማስታወስ አክብሯል። ቦርዱ ጃንዋሪ 22 ባካሄደው የሥራ ስብሰባ ላይ 2026–2027 የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያዎችን እና የሠመር ወቅት የትምህርት ክፍያ ተመኖች ላይ የቀረቡትን ማሻሻያዎች አጽድቋል፣ የፊስካል እና የኢንቨስትመንት ፖሊሲ ለውጦችን አጽድቋል፣ 2026 የተዘጋጁ ደንቦችን ገምግሟል፣ እና የተማሪዎችን እና የትምህርት ቤት ስኬቶችን እውቅና በመስጠት አክብሯል።


Black History Month=የጥቁሮች ታሪክ የሚዘከርበት ወር | Proposed Boundary=አስተያየት የቀረበበት የት/ቤቶች ማካለል | Elementary Boundary=የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ክልል/ወሰን | Math Pathway=ስለ አዲሱ የሂሳብ ትምህርት | 2026–27 School Calendar=ስለ ትምህርት አመት 2026–27 ቀንመቁጠሪያ | Summer School=የሠምረ ወቅት ትምህርት ቤት | Policy DAA | Policy DIG | Policy GIG | Legislative Update=የተሻሻሉ ደንቦች | Distinguished Service to Public Education Honors=በትምህርት ዘርፍ የላቀ አገልግሎት ላበረከቱ ስለሚሰጥ እውቅና እና አክብሮት | Celebrations=ክብረ በዓላት


የጥቁሮች ታሪክ የሚዘከርበት ወር፡ የሞንትጎመሪ ካውንቲን ታሪክ ማክበር

Black History Month Video

የጥቁሮች ታሪክ የሚዘከርበት ወር ነው፣ በሞንትጎመሪ ካውንቲ እና ከዚያም በላይ ያሉ የጥቁር ግለሰቦች እና ማህበረሰቦች ጥንካሬ፣ ፈጠራ፣ እና የፀና ትግልን የምናከብርበት ጊዜ ነው።

በዚህ ወር ለትውልድ ትምህርትን፣ የአመራር ሚናን፣ እና ለማህበረሰብ መሰረት የጣሉትን ታሪኮች እንድታስቡ የትምህርት ቦርድ ይጋብዛችኋል። ከባርነት ነጻ በወጡ ሰዎች እና ማሕበረሰቦች 1924 ዓ.ም በተገነባው በፖቶማክ በሚገኘው " Scotland A.M.E. Zion Church" ጽዮን ቤተክርስቲያን ነበር የጀመርነው። መደበኛ ትምህርት ቤቶች ከመፈጠራቸው ከረጅም ጊዜ በፊት ነበር፣ ይህች ቤተክርስቲያን የትምህርት ዕድል በመስጠት አይነተኛ ሚና በመጫወት አገልግላለች፣ ከእኛ በፊት የነበሩትን ሰዎች ቁርጠኝነት እና ህልም የሚያስተጋቡ መታሰቢያዎችም አሏት።

ያለፈውን ታሪካችንን የቀረጹትን የቀደምት አባቶቻችንን ታሪክ፣ የአሁኑን ሕይወታችንን የምንመራበትን ትምህርቶች እና ወደፊት ለምንመራበት መነሳሻ የሆነውን የአባቶቻችንን ታሪክ እና ተጋድሎ በጋራ ለመዘከር ይቀላቀሉን። ያደረጉትን ተጋድሎ በማስታወስ ብቻ ሳይሆን በትምህርት ቤቶቻችን፣ በሰፈሮቻችን እና በልባችን ውስጥ ተግባራዊ በማድረግም እናክብር።


ሱፐርኢንቴንደንቱ ስለ ትምህርት ቤቶች ወሰን ማስተካከያዎችን እና የወደፊት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዕቅዶችን ማሻሻያ አቅርበዋል።

ሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴይለር ስለ ት/ቤቶች ድንበር ምክረ ሀሳቦችን አቅርበዋል፣ ይህም የቻርለስ W. ዉድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን እንደገና ስለመክፈት የተሻሻለ አማራጭ B እና የቶማስ S. ዉተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ስለማዛወር የተሻሻለ አማራጭ ሀሳብ ያካትታል። የትምህርት ቦርዱ አሁን እነዚህን ተሻሽለው የቀረቡ እቅዶችን እየገመገመ ሲሆን ከማህበረሰቡ ግብዓት በማሰባሰብ ላይ ይገኛል።

የማህበረሰብ አባላት አስተያየቶችን እንዲያቀርቡ እና በሚመጡት የህዝብ አስተያየቶችን በምንቀበልባቸው ስብሰባዎች ላይ እንዲሳተፉ ይበረታታሉ፡ 

  • የሕዝብ አስተያየት የሚሰጥበት ስብሰባ #1 - ክራወን/ደማስከስ፡ ሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 23, 2026 | 5:00 PM

  • የሕዝብ አስተያየት የሚሰጥበት ችሎት #2 - ዉድዋርድ/ኖርዝዉድ፡ ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 24, 2026 | 5:00 PM

  • የስራ ክፍለ ጊዜ #2፡ ማክሰኞ፣ ማርች 3, 2026 | 10:00 AM

  • የሕዝብ አስተያየት የሚሰጥበት ችሎት #3 - CIP: ሰኞ፣ ማርች 9, 2026 | 5:00 PM

  • የሕዝብ አስተያየት የሚሰጥበት ችሎት #4 – CIP፡ ማክሰኞ፣ ማርች 10, 2026 | 5:00 PM

  • የስራ ክፍለ ጊዜ #3፡ ሐሙስ፣ ማርች 12, 2026 | 10:00 AM

ቦርዱ የመጨረሻውን እርምጃ የሚወስደው ማርች 26 ላይ ድምጽ በመስጠት ነው። 

ፌብሩዋሪ 5 የስራ ክፍለ ጊዜ ላይ የቀረበውን ይመልከቱ።  


MCPS በካውንቲ አቀፍ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶችን የተማሪዎች ምዝገባ ሁኔታ ለማሻሻል የወሰን ጥናት ሀሳብ አቅርቧል

MCPS ለትምህርት ቦርድ የካውንቲ አቀፍ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የወሰን ጥናት አቅርቧል፣ ይሄውም የተማሪዎች ቁጥር መቀነስ፣ በተገቢ ሁኔታ ጥቅም ላይ ያልዋሉ የአንደኛ ደረጃ እና የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሕንፃዎች እና የረጅም ጊዜ የፋይናንስ ጫናዎችን በማካተት ነው።  በዚህ ዓመት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከአቅም በላይ ተማሪዎችን በመቀበል ቢቀጥሉም፣ በትምህርት አመት 2027 መኸር (ፎል) ላይ ጀምሮ በዚህ አይነት አይቀጥሉም። MCPS በትምህርት አመት 2032 በአንደኛ ደረጃ እና በመካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች ወደ 20,000 የሚጠጉ ተጨማሪ መቀመጫዎችን ይኖራቸዋል የሚል ግምት አስቀምጧል፣ በዚህም ምክንያት ሰራተኞች ሊሆኑ የሚችሉ የማጣመር፣ የወሰን ማስተካከያዎችን እና የትምህርት ቤት ሞዴሎችን እንዲያጠኑ ሀሳብ እንዲያቀርቡ አድርጓቸዋል።

የተመከረ የጊዜ ሠሌዳ፦

  • ጸደይ 2026፡ ቦርዱ ከሕዝብ ችሎቶች በኋላ የጥናት ወሰንን አጽድቋል

  • ሜይ 2027፡ ቦርዱ የትምህርት ቤቶችን ጥምረት በተመለከተ ውሳኔ ይሰጣል

  • ሜይ 2028፡ ቦርዱ የመጨረሻ የወሰን ምደባዎችን ውሳኔ ይሰጣል

  • ኦገስት 2029፡ የትምህርት አመት 2029–30 አዳዲስ ወሰኖች ተግባራዊ ይሆናሉ

ግልጽነትን እና የማህበረሰቡን ተሳትፎ ለማረጋገጥ በየደረጃው የህዝብ ተሳትፎ ይካሄዳል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ


አዲሱ ከቅድመ መዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል የሂሳብ ትምህርት

MCPS ከቅድመ መዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል የሂሳብ ትምህርትን ዘመናዊ ለማድረግ እቅድ አቅርቧል፣ ይህም የተቀናጀ የአልጀብራ ትምህርት፣ በየቀኑ 60 ደቂቃ የሚፈጅ ከመዋእለ ህጻናት እስከ ስምንተኛ ክፍል (K-8) የሂሳብ ብሎኮች እና ተማሪዎችን ለላቀ የትምህርት ስራ እና ለወደፊት ስራዎች ለማዘጋጀት ባለብዙ ደረጃ የትምህርት ድጋፍ የሚሰጥበትን አሠራር ያካትታል።

ቦርዱ ስለ ቀድሞ የትግበራ ተግዳሮቶች፣ ጠንካራ የመምህራን ስልጠና አስፈላጊነት፣ ስለ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ጣልቃ ገብነት እገዛ ጊዜ እና ለቤተሰቦች በግልጽ ሪፖርት ማድረግን በተመለከተ ስጋቶችን በማንሳት በቀረበው እቅድ ላይ ተወያይቷል። አባላቱ የተማሪዎችን የጊዜ ሰሌዳዎች ለመጠበቅ ትኩረት ሰጥተው በመሥራት የሂሳብ ትምህርት ጊዜ መጨመር የምርጫ ኮርሶችን ወይም የልዩ ፕሮግራሞችን ተደራሽነት እንዳይቀንስ መደረግ እንዳለበት ተነጋግረዋል።

MCPS ያቀረበውን ይመልከቱ። 


ቦርዱ ስለ 2026–2027 የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያዎች የቀረበውን ቴክኒካዊ ማሻሻያዎች አጽድቋል

ቦርዱ ጃኑዋሪ 22 ባካሄደው የሥራ ስብሰባ፣ በማርክ መስጫ ወቅቶች የትምህርት ቀናትን በተሻለ ሁኔታ ለማመጣጠን በፀደቀው የትምህርት አመት 2026–2027 የቀን መቁጠሪያዎች ላይ ቴክኒካዊ ማሻሻያዎችን አጽድቋል። ለውጦቹ ቀደም ሲል የታቀደውን ትምህርት የማይሰጥበት ቀን ሴፕቴምበር 11, 2026 ለተማሪዎችና ለሠራተኞች መደበኛ የትምህርት ቀን እንዲሆን፣ እና ኤፕሪል 21, 2027 ጀምሮ ትምህርት የማይሰጥበትን ቀን ወደ ኤፕሪል 22, 2027 ያሸጋግራል።

በዚህም ምክንያት፣ የማርክ መስጫ ጊዜ ርዝመት ለመደበኛው እና ኢኖቬቲቭ ካለንደር ላላቸው ትምህርት ቤቶች የተስተካከለ ሲሆን፣ አጠቃላይ የትምህርት ቀናትን ቁጥርም አስጠብቋል። 

መደበኛው የቀን መቁጠሪያ / ኢኖቬቲቭ የቀን መቁጠሪያ 


2026 የሠመር ወቅት ትምህርት ቤት የትምህርት ክፍያ ተመን ጸድቋል

2026 የሠመር ትምህርት ቤት ፕሮግራም ክፍያዎች በቦርዱ ጸድቀዋል። የዚህ ዓመት ዕቅድ በአካዳሚክ ማካካሻ፣ በክሬዲት ማሟያ፣ እና Title 1 ትምህርት ቤቶች እና በልዩ ትምህርት አገልግሎቶች ውስጥ ላሉ ተማሪዎች ድጋፍ በመስጠት ላይ ያተኩራል።   

2026 የሠመር ትምህርት ክፍያ ተመኖች

የፀደቁት የትምህርት ክፍያዎች ፕሮግራሞች ተደራሽ ሆነው መቀጠላቸውን ለማረጋገጥ ደረጃ በደረጃ የተዘጋጁ አማራጮችን ያካትታሉ፡   

የፕሮግራም ደረጃ

ሙሉ የትምህርት ክፍያ

ደረጃ 1 ቅናሽ ተደርጓል

ደረጃ 2 ቅናሽ ተደርጓል

ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

$364.25

$145.75

$102.00

መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

$100.00

$40.00

$28.00

እነዚህ ፕሮግራሞች የተነደፉት ተማሪዎች ለመመረቅ በሚያስችላቸው በትክክለኛው መንገድ ላይ እንዲቀጥሉ እና MCPS የወደፊት ዝግጁ ስትራቴጂክ ዕቅድን ተከትሎ ለድህረ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስኬት መሰረታዊ ክህሎቶችን እንዲገነቡ ለማድረግ ነው። 


የተሻሻለ የፊስካል ቁጥጥር ፖሊሲ(Policy DAA)

ቦርዱ በይፋ የቦርድ ፖሊሲ DAA፣ የፊስካል ኃላፊነት እና ቁጥጥር ማሻሻያዎችን አጽድቋል። ይህ የማሻሻያ ጥረት የተደረገው የህዝብን ገንዘብ በመጠበቅ ላይ በማተኮር ነው፦

  • የተሻሻለ ቁጥጥር፦ አዳዲስ የውስጥ ቁጥጥሮች በትክክል መተግበራቸውን በከፍተኛ ደረጃ ክትትል ይደረጋል።

  • አስቀድሞ ጥንቃቄ እና ክትትል ማድረግ፦ ሱፐርኢንቴንደንቱ የበጀት ስጋቶችን በሚመለከት ቀደም ብለው ለመለየት እና ለመፍታት ወርሃዊ የትንታኔ ሪፖርቶችን ያቀርባሉ።

  • ጥብቅ መመዘኛዎች፦ የበጀት ዝውውሮችን እና ተጨማሪ ገንዘቦችን ለመጠቀም የበለጠ ግልጽ የሆኑ ፕሮቶኮሎች ተዘጋጅተዋል።

  • የማህበረሰብ ግብዓት፦ የመጨረሻው ፖሊሲ ከተማሪዎች፣ ከሰራተኞች፣ እና ከህዝብ የተሰበሰበውን አስተያየት ያንፀባርቃል።


የኢንቨስትመንት ስትራቴጂዎችን ዘመናዊ የማድረግ ፖሊሲ (Policy DIG)

ቅልጥፍና እና ደህንነትን በሚመለከት የቦርድ ፖሊሲ DIG የሥራ ማስኬጃ ፈንድ ኢንቨስትመንቶች አዲስ የጸደቁ ማሻሻያዎች ዋና አንቀሳቃሾች ናቸው። ዋና ዋና ነጥቦቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • የቅድሚያ ትኩረት በመስጠት ላይ የተመሰረተ ኢንቨስትመንት፦ አሁን ሁሉም ኢንቨስትመንቶች ስለ ጥንቃቄ፣ ደህንነት፣ ተአማኒነት፣ እና ስለ ገበያ ሁኔታ ጥብቅ መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው።

  • ማዕከላዊ አስተዳደር፦ MCPS የአስተዳደር እና የዋጋ አቅርቦት ቅልጥፍናን በማሻሻል ቀሪ የገንዘብ ሂሳቦችን ክትትል ያጠናክራል።

  • ሥነ ምግባር እና ስጋትን መቆጣጠር፦ ፖሊሲው የጥቅም ግጭትን የመከላከል ደንቦችን ያጠናክራል እንዲሁም ለኢንቨስትመንት ዓላማዎች ብቻ የሚደረግ የገንዘብ መበደርን ይከለክላል።


የጡረታ ገንዘብ አያያዝ ፖሊሲ (Policy GIG)

የሰራተኞች ጥቅማ ጥቅሞችን የረጅም ጊዜ ዘላቂነት ለማረጋገጥ፣ ቦርዱ የቦርድ ፖሊሲ GIG፣ የጡረታ እና የጡረታ ገንዘብ ስርዓት ማሻሻያዎችን አጽድቋል። የተደረጉት ጉልህ ለውጦች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • ስልታዊ/ስትራቴጂያዊ ቁጥጥር፡ ንብረቶች የሚተዳደሩት ለተሳታፊዎች ብቻ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማረጋገጥ በኢንቨስትመንት ቦርድ ባለአደራዎች ነው።

  • Actuarial Rigor፦ ከተመሰከረላቸው ድርጅቶች የሚቀርቡ ዓመታዊ የግምገማ ሪፖርቶች የበጀት ምክረሃሳቦችን እና የገንዘብ መጠን በመቶኛ ማረጋገጥ አለባቸው።


የተሻሻሉ ደንቦች፦ ስለ ትምህርት አመት 2026 የትምህርት ረቂቅ ህጎች ላይ የቦርዱ አቋም

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ 2026 ደንቦችን የማውጣት ስብሰባ ላይ የተነሱ በርካታ ቁልፍ ረቂቅ ደንቦችን ገምግሟል። ቦርዱ ለተማሪዎች፣ ለሠራተኞች፣ እና ለሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ ለመሟገት የሚከተሉትን አቋሞች ወስዷል፦

ከማሻሻያዎች ጋር የቀረቡ ረቂቅ ደንቦች

  • HB 14፡ የጉልበተኝነት እና የትንኮሳ ሪፖርት - የውሂብ ትክክለኛነትን ለማረጋገጥ የህዝብ ሪፖርት ማቅረቢያ ጊዜን ከስቴት ማረጋገጫ ሂደቶች ጋር ለማጣጣም የማሻሻያ ድጋፍ መስጠት።

  • HB 64፡ የትምህርት ፋይናንስ ግብረ ኃይል – ከአጠቃላይ የተማሪዎች ምዝገባ እድገት በተጨማሪ ግብረ ኃይሉ ለተወሰኑ የተማሪዎች ብዛት ላላቸው (ለምሳሌ፦ የልዩ ትምህርት እና የእንግሊዝኛ ተማሪዎች) የገንዘብ ድጋፍን ማብራሪያ መስጠት እንዲችል በሚቀርብ ጥያቄ ድጋፍ መስጠት።

  • HB 102፡ ወታደራዊ አገልግሎት ለሚሰጡ ቤተሰቦች ቅድመ ምዝገባ – ተማሪ በትምህርት ቤቱ በአካል ከተገኘ(ች) በኋላ፣ ከስቴት እና ከፌዴራል ህጎች ጋር ሙሉ በሙሉ በሚጣጣም መልኩ የልዩ ትምህርት አገልግሎቶች ወዲያውኑ መጀመራቸውን ለማረጋገጥ የቀረቡ ማሻሻያዎችን መደገፍ።

  • HB 128 / SB 299፡ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የቴራፒ ውሾች – የአካባቢ ቦርድ የቴራፒ ውሾችን እንዲፈቅዱ "ከመጠየቅ" ይልቅ "መፈቀድ" አለበት የሚለውን መስፈርት ለመቀየር ማሻሻያ ድጋፍ መስጠት። ይህ ለውጥ በስቴት ውስጥ የትምህርት ቤቶችን የአካባቢ ቁጥጥር በመጠበቅ ረገድ የቴራፒ ውሾችን ከተማሪ እና ከሰራተኞች የአእምሮ ደህንነት ጋር በተያያዘ ያለውን ጥቅም ያስገነዝባል።

ድጋፍ ያገኙ ደንቦች

  • HB 340፡ የትምህርት ቤት የሥነ ልቦና ባለሙያ የኢንተርስቴት ፈቃድ ስምምነት - የትምህርት ቤት የሥነ ልቦና ባለሙያዎችን የሥራ እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮችን ለመቀነስ በኢንተርስቴት ስምምነት ውስጥ የመሳተፍ ድጋፍ። ይህ ከአባል ስቴቶች (እንደ ዌስት ቨርጂኒያ እና ዴላዌር የመሳሰሉ) ባለሙያዎች በሜሪላንድ ውስጥ በቀላሉ እንዲሰሩ እና ወሳኝ የሆኑ የሰራተኞች እጥረትን ለመቅረፍ ያስችላል።

  • HB 160፡ የኮንፌዴሬት ስም መስጠትን መከልከል - የህዝብ ንብረትን በኮንፌዴሬት አባላት ስም መሰየምን በመከልከል፣ ቦርዱ ለፍትሃዊነት እና ለአካታችነት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ የስቴት አቀፍ ድጋፍ ይሰጣል።

  • HB 288/SB 218፡ የስቴት ሱፐርኢንቴንደንት የአደጋ ጊዜ ባለስልጣን – ለረጅም ጊዜ በሚከሰቱ መስተጓጎሎች ወቅት ከትምህርት ጋር የተያያዙ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታዎችን የማወጅ ስልጣን ለስቴት ሱፐርኢንቴንደንት የሚሰጥ ድጋፍ።

  • HB 326፡ ስም-አልባ/ማንነትን የማይገልፅ የሪፖርት አቀራረብ ስርዓት – ተማሪዎች እና ሰራተኞች የደህንነት ስጋቶችን ስም–አልባ ሪፖርት እንዲያደርጉ በመንግስት የሚተዳደር ስርዓት ለማቋቋም ድጋፍ ማድረግ።

  • HB 352፡ የስነጥበብ ባጀት ምደባ ተለዋዋጭነት - በከፍተኛ ድህነት ውስጥ ባሉ አካባቢዎች ያሉ ትምህርት ቤቶች ወደፊት የስነጥበብ ትምህርት ፕሮግራሞችን ለመደገፍ የተወሰነ የገንዘብ ድጋፍ እንዲጠቀሙ የሚያስችል ድጋፍ።  በአሁኑ ጊዜ ያለው ገንዘቡን ለዚህ ዓላማ የመጠቀም ችሎታ የሚፈቀደው እስከ 2027 ድረስ ብቻ ነው።

ድጋፍ ያላገኙ ደንቦች

  • SB 158፡ ስለ አስተማማኝ አማራጭ መንገዶች ሪፖርት ––  ቦርዱ ከፍተኛ የሆነ የፋይናንስ ተጽእኖ እና ከትምህርት ቤት ቁጥጥር ውጭ ባሉ የእግር ጉዞ መንገዶች ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ የተጠያቂነት ስጋቶች ስለሚኖሩ ይህንን ረቂቅ ደንብ (5 ተቃውሞ እና 3 ድምጸ ተአቅቦ) በመቃወም ውድቅ ተደርጓል።

  • የአካባቢውን የራስ ገዝ አስተዳደር መጠበቅ – ቦርዱ የአካባቢውን የውሳኔ አሰጣጥ ለመጠበቅ ሲባል የተጣሉበትን በርካታ ግዴታዎች ይቃወማል፣ ከእነዚህም ውስጥ HB 73 (የውኃ ዋና ሥርዓተ ትምህርት)፣ HB 163 (የግል የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ አጠቃቀም ፖሊሲ)፣ SB 51 (በልዩ ትምህርት ክፍሎች ውስጥ የቪዲዮ ካሜራዎች አጠቃቀም)፣ እና HB 140 እና HB 355 ይገኙበታል። (ስለ ቦርድ ክፍት የሥራ ቦታዎች እና ሥርዓተ ትምህርት ላይ የስቴት ኃላፊነቶች)። 

የእነዚህ ረቂቅ ህጎች ዝርዝር ውይይቶች ጃኑዋሪ 22 ስብሰባ እና ፌብሩዋሪ 5 ስብሰባ ላይ ሊታዩ ይችላሉ። 


በትምህርት ዘርፍ የላቀ አገልግሎት ላበረከቱ የክብር ሽልማት ለመስጠት እጩዎችን ለመጠቆም ክፍት ነው

የትምህርት ቦርድ በካውንቲው ውስጥ ባለው የትምህርት ልምድ ላይ ዘላቂ የሆነ አዎንታዊ ተጽዕኖ የፈጠሩ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችን፣ እና የንግድ ማህበረሰቦችን እውቅና ለመስጠት 2026 ለሕዝባዊ ትምህርት የላቀ አገልግሎት ሽልማት የእጩዎችን ጥቆማ እየተቀበለ ነው። ሽልማቶቹ የሚቀርቡት በሚከተሉት ምድቦች ነው።

የቢዝነስ አጋር

የማህበረሰብ አጋር

የት/ቤት አገልግሎት በጎ-ፈቃደኛ

የተማሪ አገልግሎት ሽልማት

 እጩዎችን እስከ ሰኞ፣ ማርች 9 5 p.m. ድረስ መጠቆም ይቻላል።

 Nomination forms: English | español | français | 中文 | Portuguese | 한국어 | tiếng Việt | አማርኛ

ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ


በቦርድ የሥራ ስብሰባ ላይ የተከናወኑ እውቅናዎች ጃኑዋሪ 22, 2026

ዓለም አቀፍ የትምህርት ቀን

የቦርዱ አባል ካርላ ሲልቬስትሬ/Karla Silvestre ትምህርትን እንደ መሠረታዊ የሰብአዊ መብት እና የፍትሃዊነት ዕድል አንቀሳቃሽ አጽንዖት በመስጠት በዓለም አቀፍ የትምህርት ቀን በተከበረበት ወቅት ንግግር አድርገዋል። ቦርዱ አካታች የሆኑ ልምዶችን በመተግበር እና ለብዝሃ ቋንቋ ተናጋሪ ተማሪዎች ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት ተደራሽነትን በማስፋፋት ላሳዩት አመራር ለዳንኤል ዪፕ/Daniel Yip የአክብሮት እውቅና ሰጥቷል።

የሜሪላንድ ብሉ ሪባን ትምህርት ቤት – ዳይመንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

የቦርድ አባል ጁሊ ያንግ/Julie Yang የዳይመንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሜሪላንድ ብሉ ሪባን ትምህርት ቤትን ስያሜ በማግኘቱ፣ የትምህርት ልቀቱን እና የስኬት ክፍተቶችን በማጥበብ ረገድ ስኬቱን በማድነቅ እውቅና ሰጥተዋል። የዳይመንድ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት 50ኛ ዓመቱን ሲያከብር የአስተማሪዎቹን፣ የተማሪዎቹን እና የቤተሰቦቹን ቁርጠኝነት እና ጠንካራ የመሳተፍ ባህልን ስኬት ያንፀባርቃል።

የሜሪላንድ ብሉ ሪባን ትምህርት ቤት – ዊልሰን ዊምስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

የቦርዱ ፕሬዝዳንት ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን/Grace Rivera-Oven የዊልሰን ዊምስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጠንካራ የትምህርት አፈጻጸሙን፣ አካታች የትምህርት ቤት ባህሉን እና ለተማሪዎች ስኬት ያለውን ቁርጠኝነት በማድነቅ የሜሪላንድ ብሉ ሪባን ትምህርት ቤት እውቅና ሰጥተውታል። እውቅናው የአመራር ብቃትን እና በፍትሃዊነት እና በማህበረሰብ እሴት ላይ የተመሰረተ ተግባርን ያንፀባርቃል።

ሙስሊም አሜሪካውያን የሚዘከርበት ወር

ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ቶማስ ቴይለር የሙስሊም አሜሪካውያንን የሚዘከርበት ወር በማክበር፣ የሙስሊም አሜሪካውያንን ታሪክ፣ ባህል እና አስተዋጽኦ አክብሮት በመስጠት እና MCPS ለትብብር እና ለባለድርሻ አካላት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። የማህበረሰብ መሪዎች (Jewru Bandeh, Samira Mohammad Hussein, እና Mumin Barre) MCPS ውስጥ ላሉ ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች ላሳዩት አመራር፣ ተሟጋችነት እና አገልግሎት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።


ቀጣይ ስብሰባዎች

ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 10፣ የፊስካል አስተዳደር ኮሚቴ (5:30 p.m.)

ረቡዕ፣ ፌብሩዋሪ 11፣የቦርድ አማካሪ ኮሚቴ ኮሙኒኬሽን እና የማህበረሰብ ተሳትፎ (6:30 p.m.)

ረቡዕ፣ ፌብሩዋሪ 18፣ የስትራቴጂክ ዕቅድ ኮሚቴ (10:00 a.m.)

ሐሙስ፣ ፌብሩዋሪ 19፣ የቦርድ የሥራ ስብሰባ (4፡00 p.m.) 


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ

በህዝባዊ የውይይት መድረኮች እና አስተያየት በመስጠት ከእኛ ጋር ይሳተፉ። 

FacebookInstagramBluesky፣ እና X ላይ ይከታተሉን

ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org


ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org