አበይት ጉዳዮች

የትምህርት ቦርድ ወቅታዊ መረጃዎች
 ኦክቶበር 23, 2026

የትምሕርት ቦርድ መልእክት

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ (ቦርዱ)፣ ኦክቶበር 22 በተካሄደው ስብሰባ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶችን (MCPS) የወደፊት ሁኔታ የሚቀርጹ ቁልፍ እርምጃዎችን እና ስትራቴጂካዊ ማሻሻያዎችን በሚመለከት ተወያይቷል። ቦርዱ አጠቃላይ 2027–2028 የጥናት መርሃ ግብር፣ እና ለተማሪዎች የሚቀርቡ ኮርሶችን፣ ቅደም ተከተሎችን፣ እና የአተገባበር መንገዶችን ለመወሰን ድምጽ ሰጥቷል። በተጨማሪም፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) ሰራተኞች በንባብ እና በሂሳብ ትምህርቶች ላይ የተደረጉ የመጀመሪያ ደረጃ የመለኪያ ግምገማ ውጤቶችን በዝርዝር የሚያሳይ፣ የተማሪዎች የትምህርት አፈጻጸም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ሪፖርት አቅርበዋል። በቦርዱ አዳዲስ አጀንዳዎች ስር፣ በቦርዱ ውስጥ የሚገኘው የተማሪ ተወካይ አባል (SMOB) የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት በይፋዊ የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ ውስጥ እንዲካተት የሚያስችል ሀሳብ አቅርቧል። 

የትምህርት ፕሮግራም ማጽደቅ | የትምህርት አፈጻጸም መረጃ | የህዝብ አስተያየት ፖሊሲ | ከቦርድ የሚቀርቡ አዳዲስ ጉዳዮች | EdTalk | ስለ መጪዎቹ ስብሰባዎች |


የትምህርት አመት 2027–2028 የትምህርት ፕሮግራም ማጽደቅ

ቦርዱ ለ 2027–2028 የትምህርት መርሐ ግብር የቀረቡትን የሱፐርኢንተንደንት ምክረ ሐሳቦች በይፋ አጽድቋል፤ ይህም በሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተማሪዎች ለከፍተኛ ደረጃ ትምህርቶች ፍትሃዊ ተደራሽነት እንዲኖራቸው ለማረጋገጥ በመላው ዲስትሪክቱ ተፈጻሚ የሚሆኑ መመዘኛዎችን ያካትታል።

ዋና ዋና ቁልፍ ዝርዝሮች፦

የኮርስ ምድቦች እና GPA ድምር ውጤት ስሌት ማሻሻያ፡ በመደበኛ ደረጃ (0.0 ተጨማሪ ድምር ውጤት ያላቸው)፣ በኦነርስ (Honors) ደረጃ (0.5 ተጨማሪ ድምር ውጤት ያላቸው)፣ እንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ (AP፣ IB እና ጣምራ ምዝገባን ጨምሮ - 1.0 ተጨማሪ ድምር ውጤት ያላቸው) ኮርሶች መካከል ግልጽ ልዩነት ለመፍጠር የኮርስ ትርጓሜዎች ተሻሽለዋል።

መስፈርት በማሟላት በራስ-መመዝገብ፡ ለኮርስ ምርጫ የተማሪዎች ፍላጎት ቀዳሚ ትኩረት ይሰጠዋል። ተደራሽነትን ለማስፋት፣ የተወሰኑ የአካዳሚክ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተማሪዎች (ለምሳሌ፦ በቀድሞው አጠቃላይ ኮርስ 'B' ወይም ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ፣ በስቴት የሚሰጡ ግምገማዎችን ያለፉ፣ ወይም ለከፍተኛ ደረጃ ኮርሶች (AP) ብቃት ያላቸው)፣ የአስተማሪ ምክረ-ሀሳብ ሳያስፈልጋቸው በራሳቸው-'Honors' ወይም በከፍተኛ ደረጃ (Advanced) ኮርሶች ውስጥ ይመዘገባሉ።

AP Capstone ዲፕሎማ ማስፋፊያ፡ በሁሉም ሪጅኖች ዕድሎች መኖራቸውን ለማረጋገጥ፣ በአሁኑ ወቅት ሙሉውን IB ዲፕሎማ ፕሮግራም (IB Diploma Programme) በማይሰጡ ሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ AP Capstone ፕሮግራም (AP Seminar እና AP Research) ይስፋፋል።

የሪጅናል ሴንተር ፕሮግራሞች እና የኮርሶች ማሳለጥ፡ በዋናነት እንደ ስነ-ጥበብ፣ STEM (ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ)፣ እና ከሙያ ጋር የተያያዘ ትምህርት (Career Connected Learning) የመሳሰሉ ዘርፎች የሚገኙት ስድስት የሪጅናል ሴንተር ፕሮግራሞችን ለመደገፍ፣ ወደ 550 የሚጠጉ አዳዲስ ኮርሶች ስራ ላይ እንዲውሉ ተደርገዋል፤ በተመሳሳይ ጊዜ፣ ጊዜ ያለፈባቸው ወይም የተደጋገሙ ወደ 475 የሚጠጉ ኮርሶች ከዝርዝር ውስጥ ተወግደዋል።

የጸደቀውን የትምሕርት አመት 2027-2028 የትምህርት መርሐ ግብር ያንብቡ። 


የተማሪዎች የትምህርት አፈጻጸም መረጃ ላይ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ማሻሻያ

MCPS አመራሩ በንባብ እና በሂሳብ 2026 የመኸር ወቅት የመነሻ መረጃዎችን ያቀረበ ሲሆን፣ የተማሪዎችን የትምህርት እድገት እንዲሁም የማስተማር ሂደቱን ለማጠናከር የታቀዱ ስልቶችን በጉልህ ያንፀባርቃል። የቦርድ አባላት ይበልጥ ግልጽ የሆኑ መረጃዎች፣ የታለሙ ጣልቃ ገብነቶች፣ እንዲሁም በተማሪዎች ውጤት ላይ ሊለኩ የሚችሉ መሻሻሎች እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የመጀመሪያ ደረጃ የሊተርሲ ክህሎት (DIBELS): ከመዋእለ ህጻናት እስከ 3ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች 61.2% የሚሆኑት፣ መሰረታዊ የንባብ መስፈርቶችን አሟልተዋል። በተለያዩ የተማሪዎች ቡድኖች መካከል መሻሻሎች ቢኖሩም፣ አዳዲስ ቋንቋዎችን በመማር ላይ ያሉ ተማሪዎች (Emergent Multilingual Learners) እና ልዩ የትምህርት አገልግሎቶችን በሚያገኙ ተማሪዎች አሁንም ልዩነቶች አሉ።

ሂሳብ (mCLASS እና MAP-M)፦ የመጀመሪያዎቹ mCLASS የሂሳብ ውጤቶች እንደሚያሳዩት፣ ከመዋእለ ህጻናት እስከ 5ኛ ክፍል ካሉት ተማሪዎች መካከል 51.9% የሚሆኑት የተቀመጡትን መመዘኛዎች ያሟሉ ወይም ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ናቸው። በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ MAP-M ውጤቶች ከ 6ኛ ክፍል 27.7% እስከ 8ኛ ክፍል 51.2% የነበሩ ሲሆን፣ ይህም የተማሪዎችን አፈጻጸም እንዲሁም ከአንደኛ ደረጃ ወደ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚደረገውን ሽግግር በተመለከተ ጥያቄዎችን አስከትሏል።

የቦርድ አስተያየት እና ቀጣይ እርምጃዎች፡ የቦርድ አባላት፤ በክፍል ደረጃ እና በተማሪዎች ስብጥር የተከፋፈለ፣ ይበልጥ ዝርዝር የሆነ፣ በትምህርት ቤት ደረጃ የተዘጋጀ እና ለበርካታ ዓመታት የሚዘልቅ መረጃ እንዲቀርብ ጠይቀዋል። በተለይም በጥቁር እና በላቲኖ ተማሪዎች መካከል የሚታየውንየቆየ የአፈጻጸም ልዩነት ለመቅረፍ የሚያስችሉ ተጨባጭ ስልቶችን፣ እንዲሁም የትምህርት ድጋፎች ውጤቶችን እያሻሻሉ መሆናቸውን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ጭምር ጠይቀዋል። አባላቱ በተጨማሪም ከቤተሰቦች ጋር ወቅታዊ ግንኙነት ማድረግ፣ በቤት ውስጥ ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉ የመማሪያ ግብዓቶችን ማቅረብ፣ እንዲሁም የተወሰዱ እርምጃዎችን በዘላቂነት መከታተል አስፈላጊ መሆኑን ቦርዱ አጽንኦት በመስጠት ገልጿል። አስተዳደሩ በክፍል ውስጥ የሚሰጠውን ትምህርት ለማጠናከር፣ ለተማሪዎች የታለሙ ድጋፎችን ለመስጠት፣ ለመምህራን ሙያዊ ድጋፍ (coaching) ለማድረግ፣ እንዲሁም ለቤተሰቦች የተማሪዎችን የእድገት ሁኔታ በዝርዝር የሚያሳዩ ሪፖርቶችን ለማቅረብ የሚያስችሉ ዕቅዶችን ዘርዝሯል።

MCPS ሰራተኞች ለቦርዱ ያቀረቡትን ገለጻ ይመልከቱ። 


የህዝብ አስተያየት እንዲሰጥ ክፍት የሆኑ ፖሊሲዎች

የትምሕርት ቦርድ በአሁኑ ወቅት በሁለት ረቂቅ ፖሊሲዎች ላይ ከህዝብ አስተያየት ማግኘት ይፈልጋል። የማህበረሰብ አባላት የቀረቡትን ለውጦች እንዲመለከቱ እና እስከ ኖቨምበር 6 ቀን 2026 ባለው የመጨረሻ ቀን ድረስ አስተያየቶቻቸውን እንዲሰጡ ይበረታታሉ።

ፖሊሲ IPD (የትምህርት ጉዞ ፕሮግራሞች፣ የመስክ ጉብኝቶች፣ እና የተማሪዎች ድርጅት ጉዞዎች)፦ ለትምህርታዊ ጉዞዎች፣ ከትምህርት ቤት ውጭ ለሚከናወኑ የጥናት ፕሮግራሞች፣ እና ለተማሪዎች ጉዞዎች መመሪያዎችን እና መስፈርቶችን ይደነግጋል።

ፖሊሲ BLB (በይግባኝ እና በይግባኝ ችሎት ላይ የሚተገበሩ የአሰራር ደንቦች)፡ ለቦርዱ ስለሚቀርቡ ይግባኞች እና ይግባኝ የሚሰማበት ችሎት ተፈጻሚ የሚሆኑ የአሰራር ደንቦችን ይዘረዝራል።

ሀሳብዎን እንዴት ማጋራት እንደሚችሉ፦

ሙሉውን የፖሊሲ ረቂቆች ይገምግሙ፤ እና ለህዝብ አስተያየት የቀረቡ MCPS ፖሊሲዎች ድረ-ገጽ ላይ በመግባት አስተያየትዎን በኦንላይን ቅጾች ላይ ማቅረብ ይችላሉ።


የቦርድ አዲስ አጀንዳ፡ በቀን መቁጠሪያ ላይ ስለ ኢትዮጵያ አዲስ ዓመት እውቅና መስጠት

ተማሪ የቦርዱ አባል ልዑል ዳዊት፣ ከ 2027–2028 የትምህርት አመት ጀምሮ እንቁጣጣሽን (የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት) በይፋዊው የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) የትምህርት ካለንደር ውስጥ ለማካተት የሚያስችል የውሳኔ ሀሳብ (አጀንዳ 8.2) አቅርቧል።

ማወቅ ያለብዎት ነገር፦

በቀን መቁጠሪያ ላይ ብቻ የሚካተት፡ ይህ ውሳኔ፣ በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሚገኙትን በርካታ ቁጥር ያላቸው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ባህላዊ ዳራ ለማንፀባረቅና ለማክበር ሲባል፣ «እንቁጣጣሽ»ን በዲስትሪክቱ (district) ይፋዊ የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ላይ በግልጽ እንዲካተት ቀርቧል።

በትምህርት ቀናት ላይ ምንም ተጽዕኖ አይኖረውም፦ ይህ ሀሳብ በቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ላይ እውቅና ለመስጠት እና ግንዛቤ ለመፍጠር ብቻ የታሰበ ነው፤ ትምህርት ቤት እንዲዘጋ፣ ትምህርት የማይሰጥበት ቀን እንዲሆን ወይም የትምህርት ቤት የስራ ሰዓት እንዲቀየር አያደርግም።

ቀጣይ እርምጃዎች፦ አዲስ ጉዳይ ስለሆነ ይህ የውሳኔ ሐሳብ በቦርዱ እንዲገመገም እና ለወደፊት ውይይት እንዲቀርብ ለጊዜው ይቆያል።


ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ…

ሠማያዊ/ብሉ ሪባን ትምህርት ቤቶች

ቤቨርሊ ፋርምስ፣ ሶመርሴት እና ትራቪላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ በስቴት እና በሀገር አቀፍ ምዘናዎች ላሳዩት የላቀ አፈጻጸም እንዲሁም በተማሪዎች መካከል የሚታየውን የትምህርት ውጤት ልዩነት (achievement gap) ከስቴት አማካይ ውጤት አንጻር በማጥበብ ረገድ ላስመዘገቡት ስኬት እውቅና በመስጠት፣ 2026-2027 የሜሪላንድ "ብሉ ሪባን" (Blue Ribbon) ትምህርት ቤቶች ተብለው ተሰይመዋል። የሜሪላንድ "ብሉ ሪባን" (Blue Ribbon) ትምህርት ቤቶች መርሃ ግብር በመላው ስቴቱ የሚገኙ 23 አርአያነት ያላቸውን ትምህርት ቤቶች እውቅና የሰጠ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 12ቱ የመንግስት/የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ናቸው። ትምህርት ቤቶቹ ዜናውን ለተማሪዎቻቸው እንዴት እንዳሳወቁ የበለጠ ያንብቡ/ይመልከቱ።


MCPS የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምዝገባ እና የሴንተር ፕሮግራሞች ቅኝት

edtalk

MCPS ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምዝገባ ሂደት ላይ ትላልቅ ለውጦች ይኖራሉ።

8ኛ ክፍል የሚማር/የምትማር ልጅ ካለዎት፣ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚሆኑ አማራጮችን መርምሮ መወሰን አድካሚ ሊሆን ይችላል። ስለ አዲሶቹ MCPS ሴንተር ፕሮግራሞች (Center Programs) ግልጽ እና ቀጥተኛ መልሶችን ለማግኘት፣ ወቅታዊ EdTalk ይከታተሉ።

በሪጅንዎ ስላሉ የአራት ዓመት የትምህርት ዘርፎች እና ተማሪዎ በዚህ ዓመት እንዴት ማመልከት እንደሚችል/እንደምትችል፣ የትምህርት ቦርድ (BOE) ፕሬዚዳንት ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን (Grace Rivera-Oven) ከፕሮግራም መሪዎቹ አንጃሊ ዌልስ (Anjali Wells) እና ጂኒ ፍራንክሊን (Jeannie Franklin) ጋር የሚያደርጉትን ውይይት ይከታተሉ።


ስለ መጪዎቹ ስብሰባዎች

ሰኞ፣ ኦክቶበር 26፣ የካፒታል በጀት እና CIP የመጀመሪያው የህዝብ አስተያየት የሚደመጥበት ችሎት (5፡00 p.m.)

ማክሰኞ፣ ኦክቶበር 27፣ የካፒታል በጀት እና የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም (CIP) 2ኛው የህዝብ አስተያየት የሚሰጥበት ችሎት *በኦንላይን/ቨርቹዋል* (5:00 p.m.)

ሰኞ፣ ኖቨምበር 2፣ የካፒታል በጀት እና የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም (CIP) የስራ ክፍለ ጊዜ #2 (10:00 a.m.)

ሐሙስ፣ ኦክቶበር 22፣ የቦርድ የስራ ስብሰባ (4፡00 p.m.)

ሰኞ፣ ኖቨምበር 9፣ ልዩ አገልግሎት ስለሚሰጣቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የተቋቋመ ኮሚቴ (9:00 a.m.)

ቦርዱ MCPS የኬብል ቻናሎች እና YouTube ላይ ሁሉንም ወርሃዊ የቦርድ ሥራ ስብሰባዎች እና የስራ ክፍለ ጊዜዎች የስፓንሽኛ ትርጉም ይቀርባል። በተጨማሪም፣ በአካል የተገኙ ተሳታፊዎች ለማንኛውም ስብሰባ የትርጉም አገልግሎቶችን መጠየቅ ይችላሉ። ጥያቄዎች ከስብሰባው ቢያንስ 10 ቀናት ቀደም ብለው መቅረብ አለባቸው። ስብሰባዎቻችንን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ እና ማህበረሰባችን እንዲገናኝ ለማድረግ በጉጉት እንጠብቃለን!


ግንኙነትዎን ይቀጥሉ

በህዝባዊ የውይይት መድረኮች እና አስተያየት በመስጠት ከእኛ ጋር ይሳተፉ። 

Facebook፣ Instagram፣ Bluesky፣ እና X ላይ ይከታተሉን

ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org



ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org