
አበይት ጉዳዮች
ኦገስት 13, 2026
|
|
|
የቀን ቆጠራው ቀጥሏል… የቀረው ከሁለት ሳምንት ያነሰ ጊዜ ነው! |
- ኮፍያ አንሱ!: MCPS የዘንድሮውን የሠመር ትምህርት ቤት ተመራቂዎች ኦገስት 12 በፔይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አክብሯል። ስለ ከባድ ስራዎቻችሁ እና ስለ ትጋታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ! ፎተግራፎቹን ተመልከቱ።
- ከእኛ ጋር ይቀላቀሉ!: የትምህርት ዓመት 2026–2027 በቅርቡ እንጀምራለን፣ ስለዚህ ቅዳሜ፣ ኦገስት 22 በሚካሄደው ወደ ትምህርት ቤት መመለሻ ትርኢት ላይ መገኘትዎን ያረጋግጡ!፡ በዚህ ዓመት፣ MCPS የትምህርት አመት 2026–2027 ለመጀመር ስድስት ሪጅናል አውደ ርዕዮችን ያስተናግዳል። ትርኢቶቹ ቤተሰቦች ከትምህርት ማህበረሰቦች ጋር እንዲገናኙ እና ለጥያቄዎቻቸው መልስ እንዲያገኙ የበለጠ ይረዳቸዋል። ቤተሰቦች ስለ ትራንስፖርት፣ ስለ ቴክኖሎጂ፣ ስለ ልዩ ትምህርት፣ ስለ ብዝሃ ቋንቋ አገልግሎቶች፣ ስለ አእምሮ ጤና እና ሌሎች ማዕከላዊ ቢሮዎች ላይ የሚገኙ እውቀት ያላቸውን MCPS ሰራተኞችን በቀጥታ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ድጋፍ ሊሰጧቸው ይችላሉ! ትምህርት ቤትዎን ያግኙ፣ ትርኢት የሚካሄድባቸውን ቦታዎች ያግኙ፦
- አልበርት አንስታይን፣ ከጠዋቱ 9 a.m.– እስከ ቀትር (አልበርት አንስታይን፣ ቤቴስዳ-ቼቪ ቼዝ፣ ሞንትጎመሪ ብሌር፣ ኖርዝዉድ፣ ዋልት ዊትማን ክላስተር ትምህርት ቤቶች)
- ፔይንት ብራንች፣ ከጠዋቱ 9 a.m.– እስከ ቀትር (ጄምስ ሁበርት ብሌክ፣ ፔይንት ብራንች፣ ሼርውድ፣ ስፕሪንግብሩክ ክላስተር ትምህርት ቤቶች)
- ዊተን፣ ከቀኑ 3–6 p.m. (ጆን ኤፍ. ኬኔዲ፣ ዋልተር ጆንሰን፣ ዊተን/ቶማስ ኤዲሰን፣ ቻርለስ W. ውድዋርድ ክላስተር ትምህርት ቤቶች)
- ሪቻርድ ሞንትጎመሪ፣ ከቀኑ 1–4 p.m. (ዊንስተን ቸርችል፣ ሪቻርድ ሞንትጎመሪ፣ ሮክቪል፣ ቶማስ S. ውተን ክላስተር ትምህርት ቤቶች)
- ጌትስበርግ፣ ከጠዋቱ 9 a.m.– እስከ ቀትር (ጌትስበርግ፣ ኮሎኔል (ዛዶክ ማግሩደር፣ ኩዊንስ ኦርቻርድ፣ ዋትኪንስ ሚል ክላስተር ትምህርት ቤቶች)
- ሴኔካ ቫሊ፣ ከቀኑ 3–6 p.m. (ክላርክስበርግ፣ ደማስከስ፣ ኖርዝዌስት፣ ፑልስቪል፣ ሴኔካ ቫሊ ክላስተር ትምህርት ቤቶች)
- አሁን ታውቃላችሁ — ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ቀን እየተቆጠረ ነው፡ ማስታወስ ያለባቸው አስፈላጊ ቀናት — የሽግግር ቀን ሰኞ፣ ኦገስት 24 ሲሆን ለሁሉም ተማሪዎች ትምህርት የመጀመሪያው ቀን ማክሰኞ፣ ኦገስት 25 ነው። በቅርቡ እንገናኛለን!
English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese |አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese
- የአትሌቲክስ ማጣሪያ በመካሄድ ላይ ነው፡ በዚህ የመኸር ወቅት ለቡድኖች ማጣሪያ ለሚወዳደሩ ተማሪ-አትሌቶቻችን በሙሉ መልካም ዕድል! ሁሉንም ነገር በመስጠት፣ የቡድን ጓደኞቻችሁን በመደገፍ፣ እና በመከባበር እና ስፖርታዊ ጨዋነት በማሳየት R.A.I.S.E. የቡድን ጨዋነትን እንደምታሳዩ እናበረታታችኋለን።
- የተማሪዎ ክትባቶች ወቅታዊ ናቸው?፦ ወቅታዊ መስፈርቶች እነሆ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ በኦገስት እና ሰፕቴምበር ወር ላይ ክትባት የሚሰጥባቸው ክሊኒኮችን ያካሄዳል።
በተጨማሪም MCPS ቅዳሜ፣ ኦገስት 22 በሚካሄደው የሪጅናል ወደ ት/ቤት የመመለሻ ትርኢቶች ላይ ክትባቶችን ለመስጠት አቅዷል። MCPS ቅዳሜ፣ ኦገስት 22 በሚካሄደው ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ትርኢቶች ላይ ክትባቶችን የመስጠት እቅድ አለው።
- የተማሪዎች መርሃ ግብሮች፦ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች እስከ ረቡዕ፣ ኦገስት 19 ድረስ የክፍል መርሃ ግብራቸውን StudentVue እናParentVue ላይ ይገኛሉ።
|
|
|
|
|
|
ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ… |
|
የትምህርት አመቱ ሊጀመር ሁለት ሳምንት ብቻ የቀረው ሲሆን፣ ከፍተኛ ደስታ እና ጉጉት ይስተዋላል። ከትምህርት ቤት አቅርቦቶች፣ የጊዜ ሰሌዳዎች፣ እና የመጀመሪያ ቀን አልባሳት ጭምር፣ የትምህርት ቤት ደህንነትጉዳይ በሁላችንም አእምሮ ውስጥ አለ። እባክዎ ኦገስት 11 ለቤተሰቦች የተላከውን ይህን የማህበረሰብ መልእክት ይመልከቱ።
ጥቂት ፍንጮች፡
|
|
|
|
|
|
ባለቤትነትን መገንባት፡ ለአዲስ የትምህርት ዓመት መዘጋጀት |
|
የትምህርት አመት 2026–2027 ለመጀመር አስተዳዳሪዎችና ሱፐርቫይዘሮች እየተዘጋጁ ናቸው። ElevatED የትምሕርት ኮንፈረንስ እና ተመሳሳይ የአስተዳዳሪዎች እና ሱፐርቫይዘሮች ኮንፈረንስ፣ መምህራን ትምህርትን በማጠናከር፣ አወንታዊ የትምህርት ቤት ባህሎችን በመገንባት እና የተማሪዎችን የመግባባት ስሜት በመፍጠር ላይ ያተኮሩ አውደ ጥናቶች ላይ ተሳትፈዋል። ዶ/ር ቤቲና ላቭ/Dr. Bettina Love የተባሉ እንግዳ ተናጋሪ እያንዳንዱ ተማሪ የሚታይበት፣ የሚከበርበት እና የሚደገፍበት ትምህርት ቤት አውድ ስለመፍጠር ጠንካራ መልእክት በማቅረብ ሕዝቡን አበረታተዋል። ባደረጉት ገለጻ ጠንካራ አመራር እንዴት ይህ ሥራ ውጤታማ በሆነ ክትትል፣ አዎንታዊ የትምህርት ቤት ባህል፣ እና የጋራ ተጠያቂነት በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲስፋፋ ሁኔታዎችን መፍጠር እንደሚችል ላይ ያተኮረ ነበር።
|
|
|
|
|
|
ጠንካራ አጀማመር፡ ኦገስት 24 የሽግግር ቀን ነው! |
|
የሽግግር ቀን (ሰኞ፣ ኦገስት 24) ወደ ኪንደርጋርተን፣ ስድስተኛ ክፍል እና 9ኛ ክፍል ለሚገቡ ተማሪዎች (በተጨማሪም በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሶስተኛ ክፍል) እና ወደ MCPS አዲስ ለሚገቡ ተማሪዎች የመጀመሪያው ሙሉ የትምህርት ቤት ቀን ነው። ይህ ወደ አዲስ የትምህርት ደረጃ ለሚገቡ ወይም ወደ አዳዲስ የት/ቤት ሕንፃዎች ለሚገቡ ተማሪዎች የሚያደርጉትን ሽግግር ለማቅለል የተነደፈ ሙሉ ቀን የሚፈጅ፣ ትምህርት-የማይሰጥበት የትምህርት ቤት ተሞክሮ ነው። የትምህርት ቤት ውሎአቸውን ለመሞከር ጥሩ ቀን ይሆንላቸዋል። ስለ ሽግግር ቀን የበለጠ ይወቁ፦ እንግሊዝኛ/English | ስፓንሽኛ/Spanish
ተማሪዎች ማክሰኞ፣ ኦገስት 25 ከሚካሄደው የመጀመሪያ የትምህርት ቀን በፊት አዲሱን ትምህርት ቤታቸውን መቃኘት ይጀምራሉ። ከርዕሰ መምህራንና ከመምህራን ጋር ይገናኛሉ፣ ሕንፃዎችን ይጎበኛሉ፣ ስለ ዕለት ተዕለት ተግባሮቻቸው ያውቃሉ፣ እንዲሁም ከክፍል ጓደኞቻቸው ጋር ይገናኛሉ።
|
|
|
|
|
|
የመጫወቻ ጊዜ፦ የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የስፖርት ምዝገባ ክፍት ነው! |
|
MCPS በሌላ አስደናቂ የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል የሚደረጉ የአትሌቲክስ ውድድሮችን ለመጀመር በጣም ጓጉቷል! ከበፊት የተመለሱ ተማሪ-አትሌቶች ይሁኑ ወይም ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሳተፉ ተማሪዎች የአትሌቲክስ ምዝገባ ለማጠናቀቅ እና ለሚመጣው የውድድር አመት ለመዘጋጀት ጊዜው አሁን ነው። ParentVUE ምዝገባ አሁን ክፍት ነው።
በዚህ ዓመት አዲስ የሚጀመር!: የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች አሁን MCPS የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አትሌቲክስ ለመሳተፍ ብቁ ናቸው። የወንዶችና የሴቶች ወጣቶች ሶፍትቦል እና ኮድ ክሮስ ካንትሪ "softball and coed cross country" በመኸር ወቅት የሚካሄዱ ስፖርቶች ናቸው።
ስለ ምዝገባ፣ ስለ ብቁነት ወይም አስፈላጊ ቅጾችን የሚመለከቱ ጥያቄዎች ካሉዎት የትምህርት ቤትዎን የአትሌቲክስ አስተባባሪ ያነጋግሩ።
|
|
|
|
|
|
ጨዋታው እርስዎን ይፈልጋል፡ MPSSAA ኦፊሻል ይሁኑ |
|
ለስፖርት ያለዎትን ፍቅር እውነተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ ለመሆን ወደ አንድ እድል ይለውጡት። የሜሪላንድ የህዝብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአትሌቲክስ ማህበር (MPSSAA) ባለስልጣን ኦፊሻል እና በሜሪላንድ እና MCPS መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአትሌቲክስ ተማሪዎችን ልምድ ለመቅረጽ ይረዱ።
እያንዳንዱ ጨዋታ ውድድሩ ፍትሃዊ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ እና ተወዳዳሪ መሆንን የሚያረጋግጡ፣ በሜዳ እና በትራክ ላይ መሪ እና አርአያ ሆነው የሚያገለግሉ ቁርጠኛ መሪዎችን ይፈልጋል። የዕድሜ ልክ የስፖርት አድናቂ፣ የቀድሞ አትሌት፣ አሰልጣኝ ወይም በቀላሉ ከጨዋታው ጋር ተገናኝተው ለመቆየት መንገድ እየፈለሉ፣ ለመምራትና፣ ንቁ ተሳታፊ የመሆን እና የትልቅ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ አካል ለመሆን እድል ይሰጣል።
በታዳጊ ተማሪዎች-አትሌቶች ህይወት ላይ ዘላቂ ለውጥ እያመጡ የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስፖርቶችን ትክክለኛነት በመጠበቅ ረገድ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ የተከበሩ ማህበረሰቦችን ይቀላቀሉ። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ።
|
|
|
|
MCPS የወደፊት የትምህርት ቤት መገልገያዎችን ሁኔታ ለማሻሻል ያግዙን |
|
MCPS ለትምህርት አመት 2026-2027 በፋሲሊቲ አማካሪ ኮሚቴ ውስጥ ያገለግሉ የማህበረሰብ አባላትን ይፈልጋል። የኮሚቴ አባላት MCPS የትምህርት ቤት መገልገያዎችን የረጅም ጊዜ እቅድ ሲያዘጋጅ እውቀታቸውን፣ ልምዳቸውን፣ እና አመለካከታቸውን ያካፍላሉ። የዚህ ኮሚቴ አባላት ከስድስት ዓመት የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም (CIP) የጊዜ ገደብ ውጭ የሆኑ፣ ነገር ግን ከ10-15 ዓመታት የጊዜ ገደብ ወይም ከዚያ በላይ ትኩረት የሚሹ ሊሆኑ የሚችሉ ማህበረሰቡ ለትምህርት ቤት መገልገያዎች እና እቅድ ካለው ራዕይ ጋር በተያያዙ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ MCPS ጋር የማማከር አገልግሎት።
MCPS የትምህርት መገልገያዎችን የወደፊት ሁኔታ በማዘጋጀት ረገድ የማማከር ፍላጎት ካለዎት፣ እስከ አርብ፣ ሴፕቴምበር 4 ድረስ ማመልከቻ ሞልተው ያቅርቡ።
|
|
|
|
|
|
ማሳሰቢያዎች፦ |
- የቅዳሜ ትምህርት ቤት ምዝገባ አሁን ክፍት ነው፡- የማስተማር ሙያ ሠርተፊኬት ባላቸው መምህራን የሚሰጥ የቅዳሜ ትምህርት ቤት ከመዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል የሂሳብ እና የእንግሊዝኛ/ቋንቋ ስነጥበብ የአካዳሚክ ድጋፍ ፕሮግራሞችን ይሰጣል። በአካል እና ቨርቹዋል አማራጮች አሉት። የትምህርት አሰጣጡ የሚጀምረው ሴፕቴምበር 26 ነው። ክፍያዎች የሚጨምሩት ሴፕቴምበር 1 ላይ ነው። ቀደም ብለው ይመዝገቡ!
- FARMS ማመልከቻዎን እስካሁን አላቀረቡም?: ዛሬውኑ ያመልክቱ! ምንም እንኳን ልጆቻችሁ ባለፈው አመት ብቁ ቢሆኑም በየትምህርት አመቱ አዲስ FAARMS ማመልከቻ መቅረብ አለበት። በኦንላይን FARMS ማመልከቻ MySchoolApps ላይ አቅርቡ (በተለያዩ ቋንቋዎች የተተረጎሙ ቅጾች ይኖራሉ)። በአንድ ቤተሰብ ለሚገኙ ሁሉም ተማሪዎች የሚያስፈልገው አንድ ማመልከቻ ብቻ ነው። ተጨማሪ መረጃ
- MCPS ጋር ስለመሥራት መጥተው ግንዛቤ ያግኙ!: ከኦገስት 14-22 የሚካሄድ የሞንትጎመሪ ካውንቲን የግብርና ትርኢት ይጎብኙ እና MCPS ጋር ስለመሥራት ይወቁ! MCPS የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍል፣ የፋሲሊቲ ጥገና መምሪያ እና የፋሲሊቲዎች ኦፕሬሽን መምሪያ ከትልቁ ቢጫ የትምህርት ቤት አውቶቡስ አጠገብ Chestnut Street መግቢያ አጠገብ መረጃዎችን ያገኛሉ።
|
|
|
|
|
|
ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
ከሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) የበለጠ መረጃ
|
|
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች
|
|
©1995–2026 Montgomery County Public Schools
|
|