አበይት ጉዳዮች
ሴፕተምበር 10, 2026
|
|
|
|
የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ማሳሰቢያ፡ አርብ፣ ሴፕቴምበር 18 ሁሉም ተማሪዎች ቀደም ብሎ የሚለቀቅበት ቀን ነው። ሰኞ፣ ሴፕቴምበር 21 ትምህርት የማይሰጥበት ቀን ነው፤ ለተማሪዎችና ለመምህራን ትምህርት አይኖርም።
|
|
|
|
|
|
በትምህርት ላይ መገኘት (አተንዳንስ) ዋጋ አለው. መገኘት አስፈላጊ ነው። እያንዳንዱ ቀን አስፈላጊ ነው። |
|
ተረድተናል፣ ጠዋት በጣም አድካሚ ሊሆን ይችላል። የማንቂያ ደወል ሰዓቶች አይተባበሩም፣ ጫማዎች ከተቀመጡበት አይገኙም፣ እና አንዳንድ ጊዜ ሁሉንም ሰው አዘጋጅቶ ከቤት ማስወጣት የራሱ የሆነ ሽልማት ይገባዋል። የሆነ ሆኖ ግን ትምህርት ቤት መገኘት በእርግጥ አስፈላጊ ነው።
በየቀኑ በክፍል ውስጥ መሆንና መገኘት አዲስ ነገር ለመማር፣ ጓደኞችን ለማየት፣ ከመምህራን ጋር ለመገናኘት እና ወደፊት ለመራመድ ሌላ ተጨማሪ እድል ነው። እና እነዚያ "አንድ ቀን እዚህ ሌላ ቀን እዚያ" የመሆን መቅረት? በፍጥነት ሊደማመሩ/ሊከማቹ ይችላሉ። በትምህርት ዓመቱ ውስጥ 10% - 18 ቀናት - መቅረት ሥር የሰደደ መቅረት እንደሆነ ይቆጠራል። ያ ጥሩ አይደለም።
MCPS ለመገኘት በጣም ጥሩ ቦታ ነው፤ የራስ ስሜት ያለበት ቦታ ነው። ተማሪዎ በየቀኑ በክፍል ውስጥ እንዲገኝ/እንድትገኝ፣ ከጓደኞች ጋር እንዲሆን/እንድትሆን እና በየቀኑ የትምህርት ቤታችን ማህበረሰብ አካል እንዲሆን/እንድትሆን እንፈልጋለን።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
በትምህርት ቤት መገኘት አስፈላጊ ነው:እንግሊዝኛ/English |ስፓንሽኛ/Spanish
|
|
|
|
|
|
የተሻሻለው የትምሕርት ውጤት አሰጣጥ መመሪያ ቤተሰቦች መረጃ እንዲያገኙ ይረዳል |
|
MCPS ስለ ቤት ሥራ ምደባዎች፣ ስለ ትምህርት ውጤቶች፣ እና የትምህርት እድገትን በሚመለከት ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች ግልጽ እና ወቅታዊ መረጃ ለመስጠት የትምሕርት ውጤት አሰጣጥ እና ሪፖርት አቀራረብ መመሪያውን (በአንድ ገጽ የተጠቃለለ የመረጃ ወረቀት) አሻሽሎ አቅርቧል።
ግቡ ቀላል ነው፤ ግልጽ የሆኑ የሚጠበቁ ነገሮች፣ ወቅታዊ ግንኙነት እና ጠንካራ የአካዳሚክ ድጋፍ ተማሪዎች ምን እንደሚጠበቅባቸው እንዲያውቁ እና ቤተሰቦችም ለመርዳት የሚያስፈልጋቸውን መረጃ እንዲያገኙ ለማድረግ ነው። መመሪያውን ያንብቡ።
|
|
|
|
|
|
የሚቀጥሉትን ሁለት MCPS ትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያዎች/ካለንደሮች ለመቅረጽ ያግዙ |
|
የሚያስቡትን ሊነግሩን እስከ ሴፕቴምበር 20 ጊዜ አለዎት! MCPS የትምሕርት ዓመት 2027-2028 እና የትምሕርት ዓመት 2028-2029 የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያዎችን/ካለንደሮችን ለማዘጋጀት እየሰራ ስለሆነ የእርስዎን አስተያየት ለመስማት እንፈልጋለን። እባክዎ ሀሳብዎን ለማጋራት ይህንን የዳሰሳ ጥናት ቅጽ እስከ ሴፕቴምበር 20 ድረስ ሞልተው ይመልሱ።
የእርስዎ ግብረመልስ ለዝግጅት ሂደቱ ወሳኝ ነው። MCPS የትምሕርት ቤት ካለንደር በሚያዘጋጅበት ወቅት የትምህርት ፍላጎቶችን፣ የአሠራር ፍላጎቶችን፣ በስቴት ህግ መሰረት የተደነገገ የትምህርት ቤት መዘጋትን፣ አነስተኛ የሚባል የትምህርት ቀናት እና የክሬዲት ሰዓት መስፈርቶችን ማክበር፣ መጥፎና ከባድ የአየር ሁኔታ እና ሌሎች ድንገተኛ ሁኔታዎችን፣ የሰራተኞች የሙያ ቀናትን፣ እና ተማሪዎች ቀደም ብሎ የሚለቀቁበትን ቀናት MCPS የቦርድ ፖሊሲ IDA፣ የትምህርት ዓመት የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ጋር የተጣጣሙ የግምገማ መርሃ ግብሮችን ግምት ውስጥ ያስገባል።የዳሰሳ ጥናቱን ይሙሉ።
|
|
|
|
|
|
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የእርስዎን ፈለግ፡ የማዕከል ፕሮግራሞችን ይቃኙ |
|
MCPS በትምህርት አመት 2027–2028 ወደ 9ኛ ክፍል የሚገቡ ተማሪዎች ስለ ማዕከሉ የፕሮግራም ማመልከቻ ሂደት፣ መስፈርቶች፣ እና አቅርቦቶች የበለጠ ለማወቅ ቨርቹዋል የመረጃ ልውውጥ ክፍለ ጊዜዎችን እያዘጋጀ ነው።
ክፍለ ጊዜዎቹ የሚከተሉት ናቸው፦
- ሰኞ፣ ሴፕቴምበር 14 ከሠዓት በኋላ 7 p.m.:እንግሊዝኛ/ English (ASL እና በሚከተሉት ቋንቋዎች ቀጥታ ትርጉም ይሰጣል፦ አማርኛ/Amharic፣ ቻይንኛ/Chinese፣ ፈረንሳይኛ/French)፣ እና | 8 p.m.፣ ስፓንሽኛ/Spanish
- እሮብ፣ ሴፕቴምበር 23 ከቀኑ 7 p.m.: እንግሊዝኛ/English (ASL እና በሚከተሉት ቋንቋዎች ቀጥታ ትርጉም ይሰጣል፦ አማርኛ/Amharic፣ ቻይንኛ/Chinese፣ ፈረንሳይኛ/French) እና | 8 p.m.፣ስፓንሽኛ/Spanish
8ኛ ክፍል ተማሪዎች ያሏቸው ቤተሰቦች፣ በአካባቢ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከሚገኙት የአካዳሚክ፣ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች፣ ከአትሌቲክስ፣ እና ማህበራዊ እድሎች በተጨማሪ፣ ባሉበት ሪጅን የሚሰጡ ልዩ የማዕከል ፕሮግራሞችን መቃኘት ይችላሉ። ፕሮግራሞቹ በአምስት ዘርፎች የተደራጁ ናቸው፡-
- የሕክምና ሳይንስ
- ኢንተርናሽናል ባካሎሬት፣ ሰብአዊነት፣ እና ቋንቋዎች
- ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ፣ እና ሂሳብ (STEM)
- አመራር እና ሕዝባዊ አገልግሎት
- ቪዡዋል እና የትወና አርት
በማዕከል ፕሮግራም ለመግባት ማመልከት ከፈለጉ የሚወስዱት አማራጭ ስለሆነ፣ ተማሪዎች በፍላጎታቸው መሰረት እስከ ስምንት ፕሮግራሞችን ሊመርጡ ይችላሉ። የተማሪዎ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጉዞ በበርካታ እድሎች የታጀበ ነው። በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ይቀላቀሉን እና ተጨማሪ ይወቁ!
|
|
|
|
|
|
ለኮሌጅ ተዘጋጁ፡- አውደ ርዕዮች፣ የፋይናንስ ድጋፍ/Financial Aid እና ሌሎችም ይኖራሉ። |
|
MCPS, Career Council, Inc. እና College Fairs USA
አርብ፣ ኦክቶበር 9 ከጠዋቱ 9:30 a.m.-12:30 p.m. ድረስ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁንየር እና ሲንየር ተማሪዎች በአካል ተገኝተው የኮሌጅ መግቢያ መረጃዎችን የሚያገኙበት አውደ ርዕይ ያስተናግዳሉ። ቦታው፦
at the Activity Center at Bohrer Park in Gaithersburg በትምህርት ቀን በኤግዚቢሽኑ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች በኦንላይን መገለጫቸውን እንዲሞሉ የሚያስችል አገናኝ ሊንክ ያገኛሉ። ለተጨማሪ መረጃ፣ ተማሪዎች የትምህርት ቤታቸውን ካውንስለር ማነጋገር አለባቸው። የአውደ ርዕዩ መግለጫ/Fair Flyer:/እንግሊዝኛ/English
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና ቤተሰቦች ትኩረት ይስጡ፦ የኮሌጅ መግቢያ እና የስኮላርሺፕ ወቅት ሲጀምር፣ MCPS ኮሌጅ እና የስራ ፈላጊዎች (CCNs) ስለኮሌጅ ማመልከቻ ሂደት እና የገንዘብ ድጋፍ ያለዎትን ማንኛውንም ጥያቄ ለመመለስ እና ለመርዳት ዝግጁ መሆናቸውን አስታውሱ። የእንኳን ደህና መጣችሁ ቪዲዮ ይመልከቱ!
የሞንትጎመሪ ኮሌጅም በቅርቡ የገንዘብ ድጋፍ ዝግጅቶችን ያቀርባል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ፦
|
|
|
|
|
|
የትምህርት ቀኑን ጤናማ በሆነ ምግብ ጀምሩ |
|
ቀኑን ጤናማ በሆነ መንገድ መጀመር ትልቅ ለውጥ ሊያስከትል ይችላል። የምግብ እና ስነ አመጋገብ አገልግሎት መምሪያ ተማሪዎቻችን እንዲማሩ፣ እንዲያድጉ፣ እና በእውቀታቸው እንዲበለጽጉ የሚያግዙ ገንቢ የምግብ አማራጮችን ይሰጣል።
ተማሪዎ በትምህርት ቤት ቁርስ ወይም ምሳ ይመገብ/ትመገብ እንደሆነ፣ ስለ ትምህርት ቤት የምግብ ፕሮግራማችን ማወቅ ያለብዎትን ነገር ሁሉ የምግብ እና ስነ አመጋገብ አገልግሎት መምሪያ ድረ ገጽ ላይ ያገኛሉ፣ ይህም የምግብ ዝርዝሮችን፣ የስነ አመጋገብ መረጃ፣ ነፃ እና ቅናሽ ያላቸው (FARMS) የምግብ ማመልከቻዎችን፣ የምግብ ዋጋዎችን እና የክፍያ መረጃዎችን ያካትታል።
ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
|
የቅዳሜ ቀናትን ወደ ስኬት ይለውጡ—ለቅዳሜ ትምህርት ቤት/Saturday School ተመዝገቡ |
|
ልጅዎ በቅዳሜ ትምህርት ቤት/Saturday School (ጆርጅ B. ቶማስ፣ Sr. የትምሕርት አካዳሚ) በራስ መተማመንን እና የትምህርት ስኬትን እንዲያዳብር/እንድታዳብር ያግዙ። ቅዳሜ ጠዋት ከመዋእለ ህጻናት እስከ አሥራ ሁለተኛ ክፍል (K-12ኛ) ላሉ ተማሪዎች የተለያዩ ፕሮግራሞች የሚካሄዱ ሲሆን ንባብ፣ የቋንቋ ስነ ጥበብ፣ ሂሳብ፣ የፈተና ዝግጅት፣ እና ኮዲንግ እና ሮቦቲክስ የመሳሰሉ STEM ማበልጸጊያዎች ላይ ያተኩራሉ።
ቤተሰቦች እንዲያስመዘግቡ እና ስለ ፕሮግራሙ እንዲያውቁ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ሴፕቴምበር 19 ይካሄዳል። የመጀመሪያው የማስተማር ክፍለ ጊዜ ሴፕቴምበር 26 ከጠዋቱ 8፡30-11 a.m. ይካሄዳል።
- ክፍያ፦ $100/በዓመት (FARMS ለተፈቀደላቸው $50)
- መጓጓዣ፦ ወደ መሀል ቦታዎች መጓጓዣ ነፃ MCPS የአውቶቡስ መስመሮች አሉ።
- ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እና ለምዝገባ፦ saturdayschool.orgይመልከቱ
አሁን ያውቃሉ/Now You Know: English | español | 中文 | français | Português | 한국어 | tiếng Việt | አማርኛ ቋንቋዎች ይተላለፋል።
|
|
|
|
|
|
ተማሪዎች በሕገ መንግሥት ቀን ከኮንግረስማን ራስኪን/Raskin ጋር ዌቢናር ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል |
|
ተማሪዎች ሐሙስ፣ ሴፕቴምበር 17 የሕገ መንግሥት ቀን ከቀኑ 4፡30-6 p.m. ባለው ጊዜ ውስጥ ከአሜሪካን ኮንግረስማን ጄሚ ራስኪን/Jamie Raskin ጋር ቨርቹዋል ዌቢናር ላይ እንዲሳተፉ ይበረታታሉ። የሚሳተፉ ተማሪዎች ሁለት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓት (SSL) ማግኘት ይችላሉ። በስፓንሽኛ ማስተርጎም ይኖራል።ይመዝገቡ ስለ መብቶች፣ ዜግነት፣ እና ዲሞክራሲን በሚመለከት ከሕገ መንግሥት የሕግ ምሁር እና የቀድሞ የሕግ ፕሮፌሰር ለመማር ይህንን አጋጣሚ እንዳያመልጥዎት። ተማሪዎች ለኮንግረስማን ራስኪን/Congressman Raskin ጥያቄዎችን እዚህማቅረብ ይችላሉ።
ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ
|
|
|
|
|
|
የላቲና ዝክረ ውርስ ኮንፈረንስ፡ የዘር ሀረግን መታሰቢያ ማክበር፣ የወደፊት ዕጣ ፈንታን መበየን |
|
አምስተኛው አመታዊ የላቲና ሌጋሲ ኮንፈረንስ አርብ፣ ኦክቶበር 30 ከጠዋቱ 10 a.m.-1 p.m. ሮክቪል በሚከተለው አድራሻ ይካሄዳል፦
15 W. Gude Drive in Rockville የዘንድሮው ጭብጥ፣ Raíces & Rising የተሰኘ ሲሆን የመጣንበትን የዘር ሀረግ ስለማክበር ይመለከታል። የወደፊት ሕይወታችንን መተለም፣ ሴቶች ላቲኖ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ያበረታታል፣ ያደፋፍራል፣ እና አንድ ያደርጋል፣ እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት መንገዶችን እና ተደራሽነትን ከፍ ያደርጋል፣ በተጨማሪም የከፍተኛ ትምህርት መስክ እድሎችን ያስሳል። የሚወያዩባቸው ርዕሶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡- የላቲኖዎች ጤና እና የአእምሮ ጤንነት ጉዳይ፤ የላቲኖዎች ትምህርት፤ የላቲኖዎች ማማከር አገልግሎት፣ እና የማህበራዊ ፍትህ እና የላቲኖ ተማሪዎች ድምጽ ይገኝበታል።
ከትምህርት ቤቶች የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል። ለመመዝገብ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ሐሙስ፣ ኦክቶበር 15 ቀን ረዳት ርእሰ መምህራቸውን ማግኘት አለባቸው።
|
|
|
|
|
|
ስፖርት ይወዳሉ? ከበስተጀርባ ይሳተፉ |
|
ስፖርት ባይጫወቱም እንኳ MCPS አትሌቲክስ ለመሳተፍ ብዙ እድሎች አሉት። በማኔጀርነት፣ የውጤት መዝጋቢነት፣ በስታቲስቲክስ ባለሙያነት እና በፎቶግራፍ አንሺነት የማገልገል እድሎች አሉ። ለተጨማሪ መረጃ የትምህርት ቤትዎን የአትሌቲክስ አስተባባሪ (መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) ወይም የአትሌቲክስ ዳይሬክተር (ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) ያነጋግሩ።
|
|
|
|
ቡና፣ ውይይት፣ እና ማህበረሰብ፡- ቤት አልባ ተማሪዎችን መርዳት |
|
MCPS ሁሉንም ተማሪዎች ለመደገፍ ቁርጠኛ ነው፣ ነገር ግን ስራውን ብቻችንን መስራት አንችልም። ጠንካራ የማህበረሰብ አጋርነት ተማሪዎች እንዲያድጉ ለመርዳት ወሳኝ ነው። MCPS McKinney-Vento Unit ለሁለተኛ ጊዜ 'The Coffee Break' ክፍለ ጊዜ እያዘጋጀ ሲሆን ይህም ለትርፍ ያልተቋቋሙ፣ መጠለያ እና ቤት አልባ የሆኑ ተማሪዎችን ለመደገፍ ከማህበረሰብ አጋሮቹ ጋር ቀጣይ ውይይት ለማድረግ የተዘጋጀ ክፍለጊዜ ነው። አዳዲስ ርዕሶችን በጥልቀት ለማየት፣ መገልገያ ሪሶርሶችን ስለማካፈል፣ እና ይህንን ሥራ ከእኛ ጋር ከሚሠሩ ሰዎች ለመማር ነው። McKinney-Vento Act — ምን እንደሆነ፣ ማንን እንደሚደግፍ እና ቤት አልባ ለሆኑ ተማሪዎች የትምህርት መብቶችን እንዴት እንደሚጠብቅ ይገመግማሉ።
ቀኑ፦ እሮብ፣ ሴፕቴምበር 16
ሰዓት፦ 8:45-11 a.m.
ቦታ፦ Rocking Horse Road Center, 4910 Macon Road, Room 108, Rockville
ይመዝገቡ/RSVP
|
|
|
|
ማሳሰቢያዎች እና ተማሪዎች ያሏቸው እድሎች |
- የትምህርት ቤት አውቶቡስ አሽከርካሪነት ሥራ አውደ ርዕይ፦ሐሙስ፣ ሴፕተምበር 17 ከጠዋቱ 10:30 a.m.- 1 p.m. በሚከተለው አድራሻ ይካሄዳል፦ Shady Grove Transportation Depot, 16651 Crabbs Branch Way in Rockville. ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች በራሪ ወረቀቱ ላይ ያለውን QR ኮድ ስካን በማድረግ MCPS ድረ ገጽ ላይ Careers የሚለውን ከፍተው ስለራሳቸው መገለጫ እንዲጽፉ ወይም በፊት አመልክተው ከሆነ እንዲያዘምኑ ይጠየቃሉ።
- ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ብሎክ ፓርቲ፦ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል አባል ማሪሊን ባልኮምቤ/Marilyn Balcombe ይህን ዝግጅት አርብ፣ ሴፕቴምበር 18 ከቀኑ 12:30-3 p.m. ጀርመንታወን ቀጥሎ ባለው አድራሻ ያስተናግዳሉ።
አድራሻ፦ BlackRock Center for the Arts, 12901 Town Commons Drive in Germantown.
- የተማሪ አገልግሎት ትምህርት፦ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ለመመረቅ 75 SSL ሰዓት ያስፈልጋቸዋል። በእነዚህ የሴፕቴምበር እድሎች የተማሪ አገልግሎት ሰዓት ማግኘት ቀጥሉ። ስለ መንገድ ላይ ደህንነት ለሚደረገው PSA ውድድር መወዳደሪያ እስከ እሁድ፣ ኦክቶበር 4 ድረስ በማቅረብ 10 SSL ሰዓቶችን አግኙ።
- የወጣቶች ታወን ሀውስ፦ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል ስብሰባ ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 29 ከቀኑ 6 p.m. ሮክቪል በሚከተለው አድራሻ፦ Council Office Building, Third Floor, 100 Maryland Avenue in Rockville ወይም በዙም ይካሄዳል። የሚሳተፉ ተማሪዎች ጥያቄዎቻቸውን እና ስጋቶቻቸውን ማቅረብ እና ከካውንቲው አመራሮች ጋር በሚደረግ ውይይት መሳተፍ ይችላሉ። ለመሣተፍ ይመዝገቡ.
- ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣት ሴቶች የመኸር/Fall ክፍለ ጊዜ፦ ይህ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚሰጠው ነፃ፣ የኦንላይን፣ 10-ሳምንት የሚፈጅ የስራ ፈጠራ ፕሮግራም ሴፕቴምበር 28 በሚውልበት ሳምንት ይጀመራል። ትምህርቶች ማክሰኞ ከቀኑ 7 p.m.,፣ ረቡዕ ከቀኑ 4፡30 p.m. ወይም ረቡዕ ከቀኑ 8 p.m. ላይ ይካሄዳሉ ይመዝገቡ። የበለጠ መረጃ ያግኙ:እንግሊዝኛ/English | ስፓንሽኛ/Spanish
- ለአሜሪካ ያለዎትን ራዕይ ያጋሩ፡ 5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ፕሬዚዳንታዊ ንግግር በመጻፍና በማቅረብ እስከ $1,000 ሽልማት ማግኘት ይችላሉ። "ንግግሩን" ተማሪዎች ፕሬዝዳንት ሆነው እንደተመረጡ በማሰብ የበዓለ ሲመት ንግግራቸውን 2-3 ደቂቃ በሚፈጅ ቪዲዮ እንደሚያቀርቡ ያበረታታል። ለዴሞክራሲያችን ምርጥ ነው የምትሉትን አንድነትን የሚያበረታታ ራዕይ አቅርቡ።ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ መወዳደሪያው መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን፦ አርብ፣ ኦክቶበር 30ነው።
|
|
|
|
|
|
ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
ከሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) የበለጠ መረጃ
|
|
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች
|
|
©1995–2026 Montgomery County Public Schools
|
|