MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
MCPS Logo

አበይት ጉዳዮች

ኦክቶበር 01, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 
  መንገድዎን ይቃኙ፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴንተር ፕሮግራሞችን ያስሱ

በዚህ ወር MCPS በስድስቱም ሪጅኖች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮግራሞችን የሚያስተዋውቁ ዝግጅቶችን (Showcases) ያካሂዳል። እነዚህ ዝግጅቶች 8ኛ ክፍል ተማሪዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን፤ በህክምና ሳይንስ፣ በአለም አቀፍ ባካሎሬት (IB)፣ የሰብአዊነት እና የቋንቋ ጥናት፣ STEM፣ አመራር እና የህዝብ አገልግሎት፣ እንዲሁም ቨርቹዋል እና የትወና አርት ዘርፎች ላይ ከሪጅን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴንተር ፕሮግራሞች ጋር ያገናኛሉ።

የሴንተር ፕሮግራሞቹ በመላው ካውንቲው ለሚገኙ በርካታ ተማሪዎች የተሻለ ተደራሽነት ይሰጣሉ፤ እንዲሁም ውስን የመቀመጫዎችን ብዛት፣ እና አቅምን በማገናዘብ፣ የተጠባባቂዎችን ዝርዝር፣ የትራንስፖርት እና ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ የመሳሰሉ እንቅፋቶችን በመቀነስ፣ ተማሪዎች ከዝንባሌአቸው፣ ከፍላጎታቸውና ከግቦቻቸው ጋር የሚጣጣሙ ፕሮግራሞችን እንዲከታተሉ ያስችላቸዋል።

 

ት/ቤቶችን የመዝጋት እና የማጣመር ሂደትን በተመለከተ የሚደረጉ ቀጣይ የውይይት መድረኮች፡ ምን ይጠበቃል?

ባለፉት ሁለት ሳምንታት፣ MCPS ስለ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መዝጋት እና ማዋሃድ ጉዳይ የሚከተለውን ምክንያት፣ የጊዜ ሰሌዳ፣ እና አሰራር አጋርተናል። በዚህ ሳምንት፣ ቀጣዩን እርምጃ እንወስዳለን፡ ከማህበረሰባችን ጋር የምናደርጋቸውን ውይይቶች እና በሚሳተፉበት ክፍለ ጊዜ ስትገኙ ምን መጠበቅ እንደሚችሉ በአንክሮ ይመልከቱ። ይበልጥ ያንብቡ።

አሁን ያውቃሉ/Now You Know፦እንግሊዝኛ/ English |ስፓንሽኛ/Spanish |አማርኛ/Amharic | Chinese | French | Korean | Portuguese | Vietnamese

 
  ተማሪዎች እርዳታ ለመጠየቅ እንዲቀላቸው ማድረግ

ባለፈው ሳምንት፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ትምሕርት ቤቶች (MCPS) ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ለተማሪዎች ስለሚሰጠው የአእምሮ ጤና ድጋፍ የሚገልጽ ኢሜል ደርሷቸዋል። በዚህ ቪድኦ ላይ ከሱፐርኢንተንደንት ቶማስ ቴይለር/Thomas Taylor የተላለፈ መልእክትእንግሊዝኛ/English እና ስፓንሽኛ/Spanishተካቷል።

ተማሪዎች እርዳታ መጠየቅ የተለመደ ነገር መሆኑን እና እርዳታ ሲያስፈልጋቸው የት ማግኘት እንደሚችሉ ማወቅ አለባቸው። MCPS ተማሪዎች ብቻቸውን እንዳልሆኑ እንዲያውቁ ይፈልጋል። በሁሉም ህንጻዎቻችን ውስጥ፣ እርዳታ ሲፈልጉ ምላሽ የሚሰጡ ታማኝ አዋቂዎች አሉ። በሚቀጥሉት ሳምንታት ቁሳቁሶች ወደ ትምህርት ቤቶች መድረስ የሚጀምሩ ሲሆን፤ ይበልጥ የሚታዩና በቀላሉ ሊገኙ የሚችሉ ናቸው። በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ እና በኮሪደሮች የሚቀመጡ፣ የአደጋ ጊዜ ድጋፍ መረጃዎችን የያዙ፣ ተለጥፈው የሚታዩ፣ ካርዶችን እና መረጃ ሰጪ ፖስተሮችን ያካትታሉ። ተማሪዎችን በቀጥታ ከአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ አገልግሎት ጋር የሚያገናኙ በየትምህርት ቤቱ የተለዩ የኢሜል አድራሻዎች፣ እንዲሁም ስለ አእምሮ ጤና፣ እርስ በርስ ስለመደጋገፍ እና እርዳታ መቼና እንዴት መጠየቅ እንደሚችሉ ትኩረት የተደረገባቸው ትምህርቶችም ይሰጣሉ።

እገዛ ማግኘት “የማወራው ሰው ፈልጋለሁ” የማለት ያህል ቀላል መሆን አለበት። እገዛ ሁልጊዜም በቀላሉ ማግኘት የሚቻል መሆን አለበት።

 
  ParentVue ላይ ለማግኘት የሚጠቅምዎት መመሪያ

ParentVUE በደንብ እየተጠቀሙበት ነው? ይህ የተማሪዎን የትምህርት ቤት ቆይታ ሂደት ለመከታተል እና ከት/ቤቱ ጋር ለመገናኘት ከሚያስችሉዎት እጅግ ቀላል መንገዶች አንዱ ነው። ቤተሰቦች የልጆቻቸውን የትምህርት ውጤቶች እና የቤት ሥራዎችን ለመከታተል፣ ትምህርት ቤት መገኘታቸውን ለማረጋገጥ፣ የት/ቤት አውቶቡስ መጓጓዣ መረጃ ለማግኘት፣ የሪፖርት ካርዶችን እና የትምሕርት ውጤት ግምገማዎችን ለማግኘት፣ የኦንላይን ምዝገባዎችን ለመሙላት እና ከመምህራን ጋር በቀጥታ ለመገናኘት ይጠቅማቸዋል።

አዲሱን ParentVUE መተግበሪያ ማውረድዎን፣ የውጤት ማህደር/Gradebook እና የሚመርጡትን አቋራጭ እንደፍላጎትዎ ማስተካከል፣ እንዲሁም ParentVUE በየጊዜው መመልከትዎን ያረጋግጡ። በመተግበሪያው አማካኝነት በቀጥታ የወላጅ-መምህር ውይይቶችን ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ። ያስታውሱ፦ እያንዳንዱ ወላጅ ወይም አሳዳጊ የራሱን ParentVUE አካውንት/account እና የይለፍ ቃል መጠቀም አለበት።

ይበልጥ ይወቁ፦ English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic

 
  ኦክቶበር 15 በኤዲሰን ት/ቤት በሚካሄድ ዝግጅት ላይ የሙያ ስልጠና ፕሮግራሞችን ይቃኙ።

ቶማስ ኤዲሰን የቴክኖሎጂ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ተቋሙን እንዲጎበኙ፣ 16 የትምህርት መርሃ-ግብሮችን እንዲመለከቱ፣ ከመምህራን ጋር እንዲተዋወቁ እና ተማሪዎች የኮሌጅ ክሬዲት እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ማወቅ የሚያስችል የማስተዋወቂያ ዝግጅት ያካሄዳል። ዝግጅቱ የሚካሄደው ሐሙስ፣ ኦክቶበር 15 ከምሽቱ 6:30 p.m. እስከ 8:00 p.m. ነው። በተጨማሪም ቤተሰቦች ወደ ኤዲሰን ትምህርት ቤት ለማመልከት የጊዜ ሰሌዳና አሰራር መረጃ የሚያገኙ ሲሆን፣ በኢንዱስትሪ እውቅና የተሰጠው ሠርተፊኬት እና በተግባር እየሠሩ የመማር ዕድሎችም ይኖራሉ።

የኤዲሰን ት/ቤት አድራሻ፦ 12501 Dalewood Drive in Silver Spring።

 
  FAFSA ክፍት ነው — ዛሬውኑ ይጀምሩ!

ለከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲንየር ተማሪዎች ወላጆች፦ 2027-2028 (FAFSA) የገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻ ቅጽ አሁን ተከፍቷል። የአሜሪካ የትምህርት መምሪያ የፌዴራል የተማሪዎች ድጋፍ ቢሮ (Office of Federal Student Aid)፣ ተማሪዎች ከድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እንዲያገኙ ለመርዳት በየዓመቱ $120 ቢሊዮን በላይ የገንዘብ ድጋፍ ፣ ብድር እና ከትምህርት ጎን ለጎን እየሠሩ የሚማሩበት የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣል። ለዚህ ብቁ ለመሆን፣ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው የፌዴራል የተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻ (FAFSA) ቅጽ መሙላት አለባቸው።

አብዛኞቹ ተማሪዎች የሚመለከታቸውን ክፍል 12 ደቂቃዎች ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ ውስጥ መሙላት ይችላሉ፤ እንዲሁም ቅጹን ካቀረቡ በኋላ ወዲያውኑ ውጤታቸውን—የፌዴራል ፔል ግራንት (Federal Pell Grant) ተጠቃሚነትን እና የተማሪ የገንዘብ ድጋፍ መመዘኛ (Student Aid Index) ጭምር—ማየት ይችላሉ። ለእርዳታ፣ በትምህርት ቤትዎ የሚገኘውን የኮሌጅ እና የሙያ ቃኚ/ናቪጌተር (College and Career Navigator - CCN) ያነጋግሩ።

 
  ማሳሰቢያዎች፦
  • ለቤተሰቦች የተዘጋጀ የተፋጠነ እና የተጠናከረ ትምህርት (AEI) የዌቢናር ተከታታይ ፕሮግራም፦ ይህ በአራት ተከታታይ ክፍሎች የተከፋፈለ ቨርቹዋል ፕሮግራም፤ ቤተሰቦች ስለ ትምህርት ማበልጸጊያ (enrichment) እና ስለተፋጠነ ትምህርት ዕድሎች፣ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ተማሪዎች የመለየት ሂደት፣ የግንዛቤ ችሎታ ፈተና (CogAT) እንዲሁም ስለ ልጆች መብትና ፍላጎት መሟገት (parent advocacy) የተሻለ ግንዛቤ እንዲያገኙ መረጃዎችን እና ግብዓቶችን ያቀርባል።
    ይበልጥ ግንዛቤ ያግኙ፦እንግሊዝኛ/English | ስፓንሽኛ/Spanish |አማርኛ/Amharic | Chinese | French | Korean | Portuguese | Vietnamese 
  • የቅዳሜ ትምህርት፦ ከመዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የንባብ፣ የቋንቋ ስነጥበብ፣ የሂሳብ፣ ለፈተና የመዘጋጀት እና STEM (ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ) ችልታ የማጎልበት ትምህርቶች ቅዳሜ ጠዋት 8:30 እስከ 11:00 a.m. ይሰጣሉ።ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ እና ይመዝገቡ።
 
  ለአንድ ቀን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እጅጌ አሳጥረው ይዘጋጁ

ላዝሮፕ ኢ. ስሚዝ የአካባቢ ጥበቃ ትምህርት ማዕከል (Lathrop E. Smith Environmental Education Center) ዓመታዊውን "ሜሪ ሃዋርድ የአገልግሎት ቀን" (Mary Howard Day of Service) ዝግጅት ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 24፣ ከጠዋቱ 8 a.m እስከ 1 p.m. ያካሂዳል። የዝግጅት ተግባራቱ የአትክልት ቦታዎችን ማስዋብ፣ የእግር ጉዞ መንገዶችን ጥገና እና የተለያዩ የግንባታ ሥራዎችን ያካትታሉ። ተማሪዎች የአገልግሎት ትምህርት ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ፤ ነገር ግን ከአዋቂ ሰው ጋር መሆን አለባቸው። ቀኑን በሕብረትና በመዝናናት ለማሳለፍ ከእኛ ጋር ይቀላቀሉ! ይበልጥ ግንዛቤ ያግኙ እና RSVPይመዝገቡ።

አድራሻ፦ The Smith Center is located at 5110 Meadowside Lane in Rockville.

 
  ለታሪክ ተናጋሪ ተማሪዎች በሙሉ፦ SLAM ይቀላቀሉ።

በአትሌቲክስ ዲፓርትመንት ስር የሚገኘውና በተማሪዎች የሚመራው የአትሌቲክስ ሚዲያ ቡድን (SLAM)፣ ተማሪዎች በራሳቸው ጥረትና ፈጠራ በሚያዘጋጁት ትክክለኛና ተዓማኒነት ያለው የሚዲያ ይዘት አማካኝነት ስለ MCPS የአትሌቲክስ እንቅስቃሴ ታሪክ እንዲያቀርቡ ይጋብዛል። ተማሪዎች በፎቶግራፍ፣ በማህበራዊ ሚዲያ፣ በጋዜጠኝነት፣ በቪዲዮ ቀረጻ እና በዲጂታል የታሪክ አቀራረብ ዘርፎች ተግባራዊ ልምድ ያገኛሉ፤ በተመሳሳይ ጊዜም የተማሪ አትሌቶችን፣ የተለያዩ ፕሮግራሞችን እና በትምህርት ቤቶች መካከል በሚደረጉ የስፖርት ውድድሮች የሚገኙ አዎንታዊ ውጤቶችን ያንፀባርቃሉ። SLAM ተማሪዎች በሜንቶሽፕ እና በትብብር፤ እንዲሁም በመከባበርና በስፖርታዊ ጨዋነት፣ የአካዳሚክ ብቃት፣ ታማኝነት፣ በከፍተኛ ስሜትና ደህንነት የታጀበ ፉክክር፣ እና ፍትሃዊነትና ተደራሽነት ያለው MCPS የስፖርት ፕሮግራም ዋና እሴቶችን በማስተዋወቅ፤ አዳዲስ ነገሮችን ይፈጥራሉ፣ ሀሳቦችን ይለዋወጣሉ እንዲሁም የሌሎችን ተነሳሽነት ያበተታታሉ።

SLAM ለመቀላቀል ፍላጎት አለዎት? ለተጨማሪ መረጃ፣ ወደLarry Hurd Jr ኢሜል ይላኩ።

 
  PEP ለወላጅነት እና ለቤተሰብ ደህንነት መሻሻል ነጻ ድጋፍ ይሰጣል

MCPS ከወላጆች የማበረታቻ ፕሮግራም (PEP) ጋር ያለውን አጋርነት የቀጠለ ሲሆን፣ለትርፍ ያልተቋቋመ በአካባቢያችን የሚገኝ ድርጅት ለወላጆች እና ለተንከባካቢዎች መገልገያዎችን/ሪሶርሶችን እና ድጋፎችን ይሰጣል። PEP የቤተሰብ ጥንካሬ ግንባታ ፕሮግራም(PEP Family Resiliency Program)፤ ወላጆች እና ተንከባካቢዎች የቤተሰብ ትስስርን ለማጠናከር፣ የልጆችን የአእምሮ ጤና ለመደገፍ እና በትምህርት ቤት ስኬታማ እንዲሆኑ ለማበረታታት የሚያስችሉ ክህሎቶችን እንዲማሩ የሚያግዝ፣ በነጻ የሚሰጥ እና ለስምንት ሳምንታት የሚቆይ የኦንላይን ፕሮግራም ነው። ቢያንስ አምስት ክፍለ ጊዜዎችን በመሣተፍ እና ግምገማውን በመሙላት $50 ዶላር የስጦታ ካርድ ያገኛሉ። ዝግጅቶቹ የሚጀምሩት ኦክቶበር 12 ሲሆን በእንግሊዝኛ፣ በስፓንሽኛ፣ እና በአማርኛ ይካሄዳሉ።

 
  ከመማሪያ ክፍል ውጭ
  • *አዲስ* የወደፊት ድምጽ የመስጠት/የምርጫ ፕሮግራም ፡ 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ክፍት የሆነው ይህ መርሃ ግብር፣ የዜግነት ተሳትፎን እና ዲሞክራሲ በተግባር ሲተገበር የመመልከትን እድል የሚያካትት ነው። ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋን መናገር፣ ማንበብ እና መጻፍ መቻል አለባቸው። ብዝሃ ቋንቋዎችን የመናገር እና የአሜሪካን የምልክት ቋንቋ ችሎታ ያላቸው ተማሪዎች እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ። በጎፈቃደኞች የተማሪ የአገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ያገኛሉ። ለተማሪዎችና ለአሳዳጊዎች ስልጠና ያስፈልጋል። በይነመረብ ላይ ያመልክቱ፦ ለተጨማሪ መረጃ፣ አሳዳጊዎች FV እና ኢሜላቸውን ወደ 77788 መላክ ይችላሉ (ለምሳሌ፦: FV 123@email.com) ወይም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምርጫ ሰራተኞች ፕሮግራም ድረ-ገጽይጎብኙ። ከሐሙስ፣ ኦክቶበር 8 በፊት ይመዝገቡ።
  • *አዲስ* የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለምርጫ ሥራ ሠረተኞችን ይፈለጋሉ፦ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የምርጫ ቦርድ 2026 ዓ.ም አጠቃላይ ምርጫ የሚሰሩ ሰራተኞችን ይፈልጋል። ተማሪዎች ለሰሩበት ለእያንዳንዱ ሙሉ ቀን እስከ $250 ወይም እስከ 25 የSSL ሰዓታት ማግኘት ይችላሉ። አመልካቾች የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው፣ የሜሪላንድ ነዋሪዎች፣ ቢያንስ 16 ዓመት የሞላቸው እና ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው። ስፓንሽኛ ወይም ሌላ ብዝሃ ቋንቋ ችሎታ ያላቸው ተማሪዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ይበረታታሉ። የበለጠ መረጃ ለማግኘት SERVE አጭር የጽሑፍ መልእክት ይላኩ በመቀጠል MCPS ተማሪ ያልሆነ ኢሜል ወደ 77788 (ለምሳሌ፦: SERVE 123@email.com) ወይም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የምርጫ ሥራ ፕሮግራም ድረገጽይጎብኙ። ማመልከቻ መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን፦ ማክሰኞ፣ ኦክቶበር 13 ነው።
  • *አዲስ* "ድምጽዎን ያሰሙ፣ ህይወት ይታደጉ" የቪዲዮ ውድድር፦ በታዳጊዎች ዘንድ ህገ-ወጥ ኦፒዮይድስ (opioids)፣ ከመጠን በላይ መውሰድ እና ፌንታኒል (fentanyl) የሚያስከትሉትን አደጋዎች በተመለከተ ግንዛቤን የሚያሳድግ ኦሪጅናል ቪዲዮ አዘጋጅተው ያቅርቡ። የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች 10 የተማሪ አገልግሎት/ SSL ሰዓቶች ማግኘት ይችላሉ። ቪዲዮዎችን በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ማቅረብ ይቻላል። አንደኛ ለወጣ $5,000፣ ለሁለተኛ $3,000 እና ለሦስተኛ $1,000 ሽልማት ይሰጣል። የመጨረሻው ቀን ሰኞ፣ ኖቬምበር 30ነው።መወዳደሪያውን ያቅርቡ።
  • Design + Build at Blackrock Center for the Arts፦ ይህ ነፃ ፕሮግራም BlackRock Center for the Arts የአካባቢ ጥበቃን የሚያጎለብት የመሬት ገጽታን በመንከባከብ ላይ ያተኩራል፤ ይህም የአካባቢ እፅዋትንና ዛፎችን ያካትታል። ከኦክቶበር 3 ጀምሮ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሴኔካ ክሪክ (Seneca Creek) የውሃ ተፋሰስን ለማሻሻል የሚረዳ ፕሮጀክት በመንደፍና በመትከል ስድስት ተከታታይ ቅዳሜዎችን ያሳልፋሉ። ተማሪዎች እስከ 18 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓት (SSL) ማግኘት ይችላሉ።ያመልክቱ 
  • Latina Legacy Conference፡ ይህ ለላቲኖ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተዘጋጀ ዝግጅት፣ አርብ ኦክቶበር 30 ቀን ከጠዋቱ 10 a.m.-1 p.m. ሮክቪል በሚከተለው አድራሻ ይካሄዳል። አድራሻው፦ 15 W. Gude Drive in Rockville. ለመመዝገብ፣ ተማሪዎች እስከ ሐሙስ፣ ኦክቶበር 15 ድረስ ምክትል ርዕሰ መምህራቸውን ማነጋገር አለባቸው።
  • ለአሜሪካ ያለዎትን ራዕይ ያጋሩ፡ 5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ፕሬዚዳንታዊ ንግግር በመጻፍና በማቅረብ እስከ $1,000 ሽልማት ማግኘት ይችላሉ። "ንግግሩን" ተማሪዎች ፕሬዝዳንት ሆነው እንደተመረጡ በማሰብ የበዓለ ሲመት ንግግራቸውን 2-3 ደቂቃ በሚፈጅ ቪዲዮ እንደሚያቀርቡ ያበረታታል።ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ መወዳደሪያው መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን፦ አርብ፣ ኦክቶበር 30ነው።
  • "Smokey Bear Poster" ፖስተር አዘጋጅቶ የማቅረብ ውድድር፦ 7ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች ክፍት ነው። የሜሪላንድ የደን ልማትና ጥበቃ አገልግሎት 120ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ፣ 7ኛ ክፍል ተማሪዎች የእሳት አደጋ መከላከል ወርን አስመልክቶ "Smokey Bear" የተሰኘ የፖስተር ውድድር አዘጋጅቷል። ተማሪዎች "የዱር ሰደድ እሳትን መከላከል የሚችሉት እርስዎ ብቻ ነዎት!"/“Only YOU can prevent wildfires!” የሚለውን ታዋቂ መልእክት መነሻ በማድረግ ኦሪጅናል የጥበብ ሥራ ፈጥረው እንዲወዳደሩ ተጠይቀዋል። የዱር ሰደድ እሳት ደህንነትን እና የደን ጥበቃን ለመዳሰስ የመጨረሻው ቀን፦ ሰኞ፣ ኖቬምበር 2ነው።የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።
  • Capital Weather ከመዋእለ ህጻናት እስከ 8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን፣ ስለ አየር ሁኔታ፣ ስለ ወቅቶች፣ ስለ አየር ንብረት ወይም በተፈጥሮ ተመስጠው የፈጠሯቸው ኦርጅናል ስራዎችን ለልጆች የጥበብ ማሳያ ዝግጅት እንዲያቀርቡ ይጋብዛል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ።
 

ዜና አምድ

 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

ከሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) የበለጠ መረጃ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች
©1995–2026 Montgomery County Public Schools