MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
MCPS Logo

አበይት ጉዳዮች

ኦክቶበር 29, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 

በዚህ የሣምንት መገባደጃ ሰዓት ወደ ኋላ ይመልሱ፦ በዚህ እሁድ (ኖቬምበር 1) ለመደበኛ ሰዓት አቆጣጠር፣ ሰዓትዎን አንድ ሰዓት ወደ ኋላ መመለስ እንዳለብዎት እንዳይዘነጉ። የቀን ብርሃን ወደ ማጠር እና ቀድሞ የመምሽት ጊዜ በሚሸጋገሩበት ወቅት፣ በመንገድ ላይ ሲጓዙ ትኩረት ያድርጉ፤ እንዲሁም ለእግረኞች እና ለብስክሌተኞች ልዩ ጥንቃቄ ያድርጉ።

 
MCPS On The Rise፦ ሁለት-ሶስተኛ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች በትምሕርት ዓመት 2026 የሜሪላንድ ትምህርት ቤቶች አፈጻጸም መግለጫ ከፍተኛ ደረጃ አግኝተዋል   MCPS On The Rise፦ በትምሕርት ዓመት 2026 የሜሪላንድ ትምህርት ቤቶች አፈጻጸም መግለጫ ላይ፣ ሁለት-ሶስተኛ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ደረጃ አግኝተዋል።

በቅርቡ ይፋ የሆነው የትምሕርት ዓመት 2026 የሜሪላንድ ትምህርት ቤቶች አፈጻጸም ሪፖርት ካርድ ውጤት እንደሚያሳየው፣ በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) ውስጥ ከሚገኙት ትምህርት ቤቶች መካከል 134 (67%) ባለ 4 ኮከብ ወይም ባለ 5 ኮከብ ደረጃ በማግኘት፣ በዲስትሪክቱ-ትምህርታዊ ስኬትን በተመለከተ ትልቅ ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል።

ውጤቶቹ፣ በትምህርት አመት 2030 ሁሉም (100%) የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) በሜሪላንድ የትምህርት ቤቶች አፈጻጸም መመዘኛ ሪፖርት ካርድ ላይ አራት ወይም ከዚያ በላይ ኮከቦችን እንዲያገኙ እንደ ዋና ግብ የሚያስቀምጠውን፣ የዲስትሪክቱን "MCPS Future Ready 2025–2030 ስትራቴጂካዊ ዕቅድ" ለማሳካት የተመዘገበ ጉልህ እድገት ያሳያሉ።

በአጠቃላይ 36 ትምህርት ቤቶች ባለ 5-ኮከብ (5-STAR) ደረጃ ያገኙ ሲሆን (ከእነዚህም ውስጥ 20 ት/ቤቶች ከባለ 4 ኮከብ ወደ 5 ኮከብ ደረጃ ያደጉ ናቸው)፣ 98 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ባለ 4-ኮከብ ደረጃ አግኝተዋል፤ (ከእነዚህም ውስጥ 30 ት/ቤቶች ከባለ 3 ኮከብ ወደ 4 ኮከብ ደረጃ ያደጉ ናቸው)፤ በተጨማሪም 17 ትምህርት ቤቶች በስቴት አቀፍ አጠቃላይ የአፈጻጸም ውጤታቸው ላይ በሁለት አሃዝ የሚቆጠር መሻሻል አስመዝግበዋል። ይበልጥ ያንብቡ።

 
የትምህርት ቤቶች መዘጋት እና ማጣመር ጥናት፡ በኦንላይን ስብሰባ ላይ ይሳተፉ፤ አስተያየትዎን ያጋሩ!   የትምህርት ቤት መዘጋት እና ማጣመር ጥናት፡ በኦንላይን ስብሰባ ላይ ይሳተፉ፤ አስተያየትዎን ያጋሩ!

MCPS በአንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት መዘጋት እና ማጠናከሪያ ጥናት ላይ የመጀመሪያውን የማህበረሰብ ተሳትፎ ክፍለ ጊዜዎች እያጠናቀቀ ነው። ስለ ጥናቱ ለመወያየት ከተዘጋጁት እና አሁንም ክፍት ከሆኑት ሁለት የኦንላይን (virtual) መድረኮች በአንዱ ላይ እንዲሳተፉ እንጋብዝዎታለን፦

እነዚህ የውይይት መድረኮች፤ ቤተሰቦች፣ የትምህርት ቤት ሰራተኞች፣ እና የማህበረሰብ አባላት በትምህርት ቤቶቻችን ላይ ስለተደቀኑ ተግዳሮቶች እንዲያውቁ፣ ጥያቄዎችን እንዲያነሱ፣ እንዲሁም እነሱ ትልቅ ቦታ የሚሰጧቸው ጉዳዮችን ለማጋራት እድል ይሰጣሉ። በአሁኑ ወቅት ለመዝጋት ወይም ለማጣመር የተመረጡ ትምህርት ቤቶች የሉም፤ ገና ምንም ዓይነት ምክረ ሐሳቦችም አልቀረቡም፤ እና አስቀድሞ የተወሰነ ውሳኔም የለም። 

ከዚህ ቀደም በአንዱ መርሐ ግብራችን ላይ ተሳትፈው ከሆነ፣ እባክዎ ጊዜ ወስደው አስተያየት መስጫ ቅጻችን ላይ ሐሳብዎን ያጋሩን። የእርስዎ ጠቃሚ አስተያየት በሚቀጥሉት ሳምንታት በሚቀርበው፣ የተሻሻለ በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች (FAQs) ዝርዝራችን ውስጥ ይካተታል። ቅጹ እስከ ረቡዕ፣ ኖቬምበር 4 ድረስ ክፍት ነው።  

ሁለተኛ ዙር የውይይት መድረኮች በኖቬምበር መጨረሻ እና በዲሴምበር መጀመሪያ ላይ ይካሄዳሉ።

ስለ ጥናቱ መረጃ ለመመልከት፣ በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመዳሰስ፣ ስለ ሂደቱ ለመረዳት እና አስተያየትዎን ለማካፈል mcpsstudy.org ይጎብኙ።የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።

 
 መራራው ሐቅ/እውነት፦ መሠረተ ልማት፣ ወጪዎች፣ እና የካፒታል ኢንቨስትመንት ዕቅድ (CIP)   መራራው ሐቅ/እውነት፦ መሠረተ ልማት፣ ወጪዎች፣ እና የካፒታል ኢንቨስትመንት ዕቅድ (CIP)

MCPS የበጀት ዓመት 2028 የካፒታል በጀት ረቂቅ እና ከበጀት ዓመት 2027 እስከ 2032 ያለውን የካፒታል ፕሮግራም (CIP) ማሻሻያዎችን ሲገመግም፣ ዲስትሪክቱ እጅግ አስቸጋሪ ውሳኔዎችን መጋፈጥ ግድ ሆኖበታል። መራራው ሐቅ/እውነት ፦ መሠረተ ልማቶቻችን አርጅተዋል፤ ውጤታማም አይደሉም። ወጪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል፤ የአውቶቡስ መናኸሪያዎቻችን ከአቅማቸው በላይ ተጨናንቀዋል።

ስለ "The Hard Truth" ቪዲዮዎችን ይመልከቱ።

 
የትምህርት ቤቶች የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር የዳሰሳ ጥናት በቅርቡ ስለሚጠናቀቅ ከመዘጋቱ በፊት አስተያየትዎን ያጋሩን!   የየትምህርት ቤቶች የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር የዳሰሳ ጥናት በቅርቡ ስለሚጠናቀቅ፤ ከመዘጋቱ በፊት አስተያየትዎን ያጋሩን!

MCPS የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ 2027-2028 (ካለንደር) እያዘጋጀ ስለሆነ፣ ዲስትሪክቱ ከእርስዎ ተጨማሪ አስተያየትና ግብዓት ማግኘት ይፈልጋል! አርብ፣ ኖቬምበር 6፣ በቀረበው ረቂቅ የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ላይ አስተያየትዎን ማቅረብዎን ያረጋግጡ። ለትምህርት አመቱ የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ቀናትን ነው የሚመርጡት (ሦስቱም ረቂቅ የቀን መቁጠሪያዎች ተመሳሳይ የክረምት/ዊንተር እና የጸደይ/ስፕሪንግ ዕረፍት ጊዜያት አሏቸው)። ፈጣን እና ቀላል ነው — ዛሬውኑ የዳሰሳ ጥናቱን ሞልተው ያቅርቡ !

 
 ጉልበተኝነትን እና ማገባጠርን የመከላከል ወር፡ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ምቹ የትምህርት ቤት ማህበረሰቦችን መገንባት   ጉልበተኝነትን እና ማገባጠርን የመከላከል ወር፡ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ምቹ የትምህርት ቤት ማህበረሰቦችን መገንባት

ኦክቶበር ወር ብሔራዊ የጉልበተኝነትና ማገባጠርን የመከላከል ወር ነው።

ጉልበተኝነት፣ ትንኮሳ፣ ወይም ማስፈራራት ማለት፤ አንድን ግለሰብ ወይም ቡድን ለመጉዳት፣ ለማስፈራራት፣ ወይም ለማዋረድ ታስቦ በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ግለሰቦች የሚፈጸም፣ ተቀባይነት የሌለው፣ ሆን ተብሎ የሚደረግ እና ተደጋጋሚ ባህሪ ነው። በትምሕርት ቤቶቻችን ውስጥ ጉልበተኝነት ቦታ የለውም። በየትምህርት ቤቱ ውስጥ ጠላትነት የተሞላበት ሁኔታ የሚፈጥር፣ የመማር ሂደቱንና የትምህርት ቤት እንቅስቃሴዎችን የሚያስተጓጉል፣ ወይም በአንድ ተማሪ የትምህርት አፈጻጸም፣ ስነ-ልቦናዊ፣ ማህበራዊ፣ ወይም አካላዊ ደህንነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ የሚፈጥር ማንኛውም ዓይነት ባህሪ ተቀባይነት አይኖረውም።

እያንዳንዱ ተማሪ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የተከበረ፣ እና የተካተተ መሆን መሆኑ እንዲሰማው ያስፈልጋል። ይበልጥ ያንብቡ. 

 

 
ኖቬምበር 9 በሚካሄድ የዙም/Zoom ዌቢናር ላይ ስለ "Amplify Desmos Math Curriculum" የሂሳብ ሥርዓተ ትምህርት የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ   ኖቬምበር 9 በሚካሄድ የዙም/Zoom ዌቢናር ላይ ስለ "Amplify Desmos Math Curriculum" የሂሳብ ሥርዓተ ትምህርት የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።

ስለ ተማሪዎ አዲስ "Amplify Desmos Math curriculum" የሒሳብ ሥርዓተ ትምህርት የበለጠ ለማወቅ ይፈልጋሉ? MCPS ሰኞ፣ ኖቨምበር 9 ቀን 6 እስከ 7 p.m. ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቤተሰቦች በዙም/Zoom ዌብናር ስብሰባ (webinar) ያዘጋጃል። (ሊንኩ በሚቀጥለው ሳምንት ይለጠፋል።)

ይህ በዌብናር የሚሰጥ ሴሚናር፤ ስለ ዕለታዊ ትምህርት አወቃቀር፣ ተጨማሪ የትምሕርት ማበልፀግ ተደራሽነት፣ ለቤተሰቦች የተዘጋጁ «Caregiver Hub»ግብዓቶችን እና የቤት ሥራን በተመለከተ ዳሰሳ ይቀርባል። ዌቢናሩ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚቀርብ ሲሆን፤ በስፓንሽኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በአማርኛ፣ በቻይንኛ፣ በፖርቹጋልኛ፣ እና በአሜሪካ የምልክት ቋንቋ የቀጥታ ማስተርጎም አገልግሎት ይሰጣል። 

መገኘት አይችሉም? ከዝግጅቱ በኋላ ሪከርድ የተደረገው MCPS ድረ-ገጽ ላይ ይለጠፋል።

 
ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ…   ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ…

ምናልባት አምልጦዎት ከሆነ፣ «Mental Health Matters» (ስለ አእምሮ ጤና አስፈላጊነት) ፕሮግራም ተከታታይ ዝግጅት በዚህ ወር ይቀጥላል፤ በዚህ ዝግጅት ሱፐርኢንተንደንት ቶማስ ቴይለር፣ ጤናማ ውሳኔዎችን ስለማድረግ እና ከአደንዛዥ ዕፅ ነጻ ሆኖ ስለመኖር አስፈላጊነት የሚያብራራ ቪዲዮ አቅርበዋል።

ስለ ጤናማ ቁመና ደህንነት ቅድሚያ የመስጠት መንገዶችን ማወቅ ይፈልጋሉ? ቅዳሜ፣ ኖቬምበር 14 ከጠዋቱ 10 a.m.-1 p.m. ሲልቨር ስፕሪንግ በሚገኘው ጄምስ ሂውበርት ብሌክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚካሄደው የአእምሮ ጤና እና ደህንነት ኤግዚቢሽን ከእኛ ጋር ይሁኑ። አድራሻ፦ James Hubert Blake High School, 300 Norwood Road in Silver Spring ለሰራተኞች፣ ለተማሪዎች፣ እና ለቤተሰቦቻቸው በነጻ ክፍት የሆነው ይህ መርሐ ግብር፤ የተለያዩ ወርክሾፖችን፣ በተማሪዎች የሚመራ መድረክን እንዲሁም ስለ አእምሮ ጤና እና ደህንነት መረጃ የሚያጋሩ የማህበረሰብ አጋሮችን ያካተተ ይሆናል። ተሳታፊ ተማሪዎች አራት የተማሪዎች አገልግሎት-ትምህርት ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።

 
የቅርብ ጊዜው EdTalk፦ ብዝሃ ቋንቋ ተናጋሪ ተማሪዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን መደገፍ   የቅርብ ጊዜው EdTalk፡ ብዝሃ ቋንቋ ተናጋሪ ተማሪዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን መደገፍ

EdTalk የቅርብ ጊዜ ዝግጅት ላይ፣ የትምህርት ቦርድ ፕሬዝዳንት ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን እና ርእሰ መምህራን አሊሲያ ዲኒ (ከሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) እና ኢዛቤል ሜንሳህ (ከሮሊንግ ቴራስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) በትምህርት ቤቶቻቸው እንዴት ምቹ አካባቢ እንደፈጠሩ፣ ተማሪዎችን እንዴት እንደሚያሳትፉ፣ እና ለብዝሃ ቋንቋ ተናጋሪ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች የቤተሰብ ተሳትፎን እንዴት ከፍ ማድረግ እንደቻሉ ያዳምጡ። EdTalk ይመልከቱ | Vea Educacion al Día

አሁን ሁሉንም EdTalk እና Educación al Día ዝግጅቶችን በአፕል ፖድካስቶች፣ Spotify ወይም የሚወዷቸውን ፖድካስቶች በሚያዳምጡበት ጣቢያ ሁሉ መስማት ይችላሉ።

 
ለተማሪዎች ስኬት በጋራ መስራት፡ የወላጅና መምህራን ውይይቶች ኖቨምበር 23-24 ይካሄዳሉ።   ለተማሪዎች ስኬት በጋራ መስራት፡ የወላጅና መምህራን ውይይቶች ኖቬምበር 23-24 ይካሄዳሉ።

የወላጅና መምህር ውይይቶች ኖቬምበር 23 እና 24 የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህ ውይይቶች ልጅዎ በትምህርትም ሆነ በማህበራዊ ግንኙነት ረገድ ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ ከመምህሩ ጋር ለመወያየት ጥሩ እድል የሚሰጡ ናቸው። ይህ ስጋቶችን የምታጋሩበት ወይም ስለልጃችሁ ፍላጎቶች ለመምህሩ የሚናገሩበት ጊዜ ነው። ወላጆች ከመምህራን ጋር በሚነጋገሩበት ወቅት እንዲያግዟቸው፣MCPS tip sheets አዘጋጅቶ አቅርቧል። ይበልጥ ያንብቡ።

 
መታሰቢያ እና እርቅ የሚዘከርበት ወር   መታሰቢያ እና እርቅ የሚዘከርበት ወር

በኖቬምበር ወር፣ MCPS ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የመታሰቢያ እና የእርቅ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ታሪካዊ የጥቁር ማህበረሰቦች በከተማ እድሳት ምክንያት ስላጋጠሟቸው ለውጦች በሶስት ክፍለጊዜ የዌቢናር ተከታታይ ፕሮግራሞችን እያዘጋጀ ነው። ሌሎችም በቅርቡ የሚከናወኑ «የነጻነት ቀን» (Emancipation Day) ዝግጅቶች አሉ፤ ተማሪዎች በእነዚህ ዝግጅቶች ላይ በመገኘት እንደ «ማህበረሰብ አገልግሎት ትምህርት» የሚቆጠሩ ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ። ይበልጥ ያንብቡ. 

 
በሁለት ፖሊሲዎች ላይ የሚሰጥ የህዝብ አስተያየት እስከ ኖቨምበር 6 ድረስ መቅረብ አለበት   በሁለት ፖሊሲዎች ላይ የሚሰጥ የህዝብ አስተያየት የመጨረሻው ቀን ኖቬምበር 6 ነው።

የትምህርት ቦርድ በሁለት ፖሊሲዎች ላይ በቀረቡት ማሻሻያዎች ላይ የህዝብ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ይፈልጋል—ፖሊሲ IPD: ትምህርታዊ የጉዞ ፕሮግራሞች፣ የመስክ ጉብኝቶች እና የተማሪዎች ድርጅት ጉዞዎች እናፖሊሲ BLB: በይግባኝ እና በችሎት ሂደቶች ላይ ለሚደረጉት የአሰራር ደንቦች።

የህዝብ አስተያየት ፖሊሲዎች

 
የአትሌቲክስ ማጠቃለያ፦ በመላው ካውንቲ የሚሰራ ዳይቪንግ (በውሃ ውስጥ የመጥለቅ ስፖርት) አሰልጣኝ መቅጠር፤ R.A.I.S.E. ሪፖርት እና ወደ ስቴት ሻምፒዮና የሚደረግ ጉዞ!   የአትሌቲክስ ማጠቃለያ፦ በመላው ካውንቲ የሚሰራ ዳይቪንግ (በውሃ ውስጥ የመጥለቅ ስፖርት) አሰልጣኝ መቅጠር፤ R.A.I.S.E. ሪፖርት እና ወደ ስቴት ሻምፒዮና የሚደረግ ጉዞ!

MCPS አትሌቲክስ ለመጪው የዊንተር ወቅት (ከኖቬምበር 14 እስከ ፌብሩዋሪ 10, 2027) በመላው ካውንቲው የሚያገለግል የዳይቪንግ (diving) አሰልጣኝ መቅጠር ይፈልጋል። ሚናው በካውንቲው የዋና ውሃ/county aquatic facilities (ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር) ሶስት ሳምንታዊ 90 ደቂቃ ልምምዶችን መምራትን ያካትታል። የውኃ ዋና ማዕከል፣ የጌትስበርግ የውሃ ዋና ስፖርት ማዕከል እና የጀርመንታወን የቤት ውስጥ የውኃ ዋና ማዕከል)።

ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች MCPS Careers ላይ ማመልከት አለባቸው። ለጥያቄዎች፦ ወደ Kathy Green ኢሜል ያድርጉ።

የኦክቶበር ወር R.A.I.S.E. ሪፖርት

በአትሌቲክስ ፕሮግራሞቻችን ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን የሚያሳዩ ወቅታዊ መረጃዎችን፣ ስኬቶችን፣ እና ዋና ዋና ነጥቦችን ለማግኘት፣ወቅታዊ R.A.I.S.E. ሪፖርት ይመልከቱ።  

ወደ ስቴት ውድድሮች የሚ መንገድ አሁን ይጀምራል!

የመኸር ወቅት ስፖርት ቡድኖች ወደ ስቴት ሻምፒዮና የሚያደርጉትን ጉዞ ሲጀምሩ፣ ደስታና ጉጉት እየጨመረ መጥቷል! የቅርብ ጊዜዎቹን የጥሎ ማለፍ ውድድር ሰንጠረዥ፣ የጊዜ ሰሌዳዎች፣ እና የመግቢያ ቲኬት መረጃ ለማግኘት MPSSAA ድረ-ገጽ ላይ 'ስፖርትስ' (Sports) ይጎብኙ።

 
ማሳሰቢያዎች፦   ማሳሰቢያዎች፦
  • የአውቶቡስ ሹፌሮችን መቅጠር እንፈልጋለን፦ አርብ፣ ኖቨምበር 6 (Nov. 6) ከጠዋቱ a.m.-1 p.m. በሮክቪል Shady Grove Transportation Depot, 16651 Crabbs Branch Way in Rockville የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍል የሚያዘጋጀው የስራ አውደ-ርዕይ እንዳያመልጥዎት። ከመሄድዎ በፊት፣ MCPS Careers ድረ-ገጽ ላይ በኦንላይን መገለጫዎን (profile) ማዘመንዎን ወይም አዲስ ማቅረብዎን ያረጋግጡ። ተጨማሪ መረጃ ይፈልጋሉ? 240-740-6080 ይደውሉ። 
  • ነጻ እና ቅናሽ ዋጋ ያላቸው ምግቦች (FARMS) ማመልከቻዎች፦ ዛሬውኑ ያመልክቱ! ፈጣን እና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው። በቤትዎ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) ተማሪዎች፣ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ቢሆንም፣ የሚያስፈልጋቸው አንድ ማመልከቻ ብቻ ነው። እርዳታ ይፈልጋሉ? ይህንን ደረጃ በደረጃ መመሪያ MySchoolApps ቪዲዮ ይመልከቱ።
 
ከደወል ባሻገር   ከደወል ባሻገር
  • *አዲስ* ሁሉም የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለዘንድሮው የትምህርት አመት ከትምህርት ውጭ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎቻቸው ዝርዝር ላይ የመጨረሻ ማሻሻያዎችን አድርገዋል። ዝርዝሩ እዚህ ይገኛል።
  • *አዲስ* USG Lab Crawl፦ በምህንድስና፣ በቴክኖሎጂ፣ በጤና ወይም በስነ ህይወት ሳይንስ ላይ ፍላጎት ላላቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ክፍት ነው። በተግባር ላይ የተመሰረቱ እንቅስቃሴዎች እና በተግባቦት የማስመሰል ልምምዶች፣ በእነዚህ ዘርፎች መማር እና መስራት ምን እንደሚመስል ይቃኙ። ዝግጅቱ የሚካሄደው ሰኞ፣ ኖቨምበር 2 ከጠዋቱ 9 a.m.-3 p.m. ሮክቪል በሚከተለው አድራሻ ነው፦ Universities at Shady Grove, Building IV, 9631 Gudelsky Drive in Rockville. ይመዝገቡ/Register.
  • የC-SPAN 'StudentCam Documentary Competition' ዶክመንተሪ ውድድር፡ 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች፣ C-SPAN በየዓመቱ በሚዘጋጀው እና ማህበረሰባችንን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በጥልቀትና በሂሳዊ አስተሳሰብ እንዲያስቡ በሚያበረታታው፣ ብሔራዊ የቪዲዮ ዶክመንተሪ ውድድር (StudentCam) ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። በዚህ አመት ተማሪዎች ከውድድሩ ጭብጥ ጋር የሚገናኝ ርዕስ ላይ ከአምስት እስከ ስድስት ደቂቃ የሚፈጅ የቪዲዮ ዶክመንተሪ ሠርተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል፣ የውድድሩ ጭብጥም“Mr. Speaker, I Rise To …”. የመጨረሻ ቀን፡ ረቡዕ፣ ጃንዋሪ 20, 2027።
  • የቪዲዮ ውድድር፦ "ድምጽዎን ያሰሙ፣ ህይወትን ይታደጉ" - በታዳጊዎች ዘንድ እየተስፋፋ ስላለው ህገ-ወጥ ኦፒዮይድስ፣ ከመጠን በላይ ስለመውሰድ (overdose) እና ስለ ፌንታኒል (fentanyl) አደጋዎች ግንዛቤን የሚያሳድግ ኦሪጅናል የቪዲዮ ውድድር ያዘጋጁ። የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች 10 የተማሪ አገልግሎት/ SSL ሰዓቶች ማግኘት ይችላሉ። ቪዲዮዎችን በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ማቅረብ ይቻላል። አንደኛ ለወጣ $5,000፣ ለሁለተኛ $3,000 እና ለሦስተኛ $1,000 ሽልማት ይሰጣል። የመጨረሻው ቀን ሰኞ፣ ኖቬምበር 30ነው።መወዳደሪያውን ያቅርቡ።
  • Capital Weather ከመዋእለ ህጻናት እስከ 8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን፣ ስለ አየር ሁኔታ፣ ስለ ወቅቶች፣ ስለ አየር ንብረት ወይም በተፈጥሮ ተመስጠው የፈጠሯቸው ኦርጅናል ስራዎችን ለልጆች የጥበብ ማሳያ ዝግጅት እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።
 

ዜና አምድ

 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

ከሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) የበለጠ መረጃ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች
©1995–2026 Montgomery County Public Schools