Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: May 23, 2020


mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞ፡-

በሠላም መቆየታችሁን እና ደህና መሆናችሁን ተስፋ እናደርጋለን። ስለ ኮቪድ-COVID-19 እና በኤኮኖሚያችን፣ በአኗኗር ዘይቤአችን፣ እና እንደቀድሞው ፊት-ለ-ፊት በአካል የመማር ማስተማር ግንኙነት እሳቤ ዲዛይን በተደረጉ የትምህርት ሥርአታችን ላይ ስላስከተለው ጫና እናንተም እንደብዙዎቻችን በሚሠራጩት ተከታታይ ዜናዎች እንደተጥለቀለቃችሁ ይሰማችሁ ይሆናል። ሁላችንም መልካም ነገሮችን የምንፈልግ በመሆኑ፣ አስተሳሰባችንን አዲስ እየተለማመድን ያለውን ክስተት እንድናጤን፣ ከ Fred Rogers ይህንን ጥቅስ አስታውሳለሁ፡- ትንሽ ልጅ በነበርኩ ጊዜ ዜና ላይ የሚያስፈሩ ነገሮችን ስመለከት፣ እናቴ የሚረዱህን ፈልግ ትለኝ ነበር- “When I was a boy and I would see scary things in the news, my mother would say to me, ‘Look for the helpers. ሁልጊዜ የሚረዱ ሰዎችን ታገኛለህ-You will always find people who are helping.’” በ MCPS ማህበረሰባችን ብዙ የሚረዱ ሰዎች አሉ። የትምህርት ቤት ህንፃዎቻችን ከተዘጉ በኋላ በምግብ ማደያ ጣቢያዎቻችን እየሠሩ-እየተጉ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ምግቦችን ለ MCPS ተማሪዎች ስለሰጡት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞችን አስባለሁ። ለተማሪዎች የሚያስፈልጋቸውን ለማሟላት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ስላሉት ስፔሻል ኢጁኬሽን ስለሚያስተምሩት እና የፈጠራ ጥረት ስለሚያደርጉ ሠራተኞቻችን አስባለሁ። በጋራ ተሰባስበው ለሚያስፈልጋቸው ቤተሰቦች የእንክብካቤ ቁሳቁሶችን "care kits" የሚያድሉትን የትምህርት ቤት ማህበረሰቦች አስባለሁ። ብዙዎቻችሁ ሌሎችን ለመርዳት ትኩረት በማድረግ እና የትምህርት ዲስትሪክታችንን በማስተባበር ይህንን ጊዜ መጠቀማችሁን አሳይታችኋል። ስለሚረዱን ሁሉ በማስብበት ጊዜ፣ ወደፊት የሚያጋጥመንን አዳጋች ሁኔታ ለመቋቋም የሚያስችለን አቅም እና ጠንካራ መንፈስ ያለው ማህበረሰብ መኖሩን እገነዘባለሁ።

ስለ 2020 ተመራቂዎች ቨርቹወል የምረቃ ሥነርዓትን መረጃ ጨምሮ፣ ስለ ውጤት እና ሪፖርት አሰጣጥ ቀጣይ እርምጃዎች፣ ስለ ሠመር ስኩል እና ስለ 2020 ተማሪ የቦርድ አባል ምርጫ ከዚህ በታች በርካታ ወቅታዊ መግለጫዎች ይገኛሉ።

ማሳሰቢያ፦ ሰኞ፣ ሜይ 25 በ "Memorial Day" አገራችንን በማገልገል የተሰውትን በምናስብበት ጊዜ MCPS ይህንን ቀን እውቅና በመስጠት የርቀት ትምህርት አይኖርም እና ለተማሪዎች የቤት ሥራ አይሰጥም።

መልካም በዓል ይሁንላችሁ!

ከማክበር ሰላምታ ጋር

Jack R. Smith
Superintendent of Schools 
ጃክ አር. ስሚዝ
የት/ቤቶች ዋና የበላይ ተቆጣጣሪ


Table of Contents

| ስለ 2020 ተመራቂዎች ቨርቹወል የምረቃ ሥርአት | ውጤት አሰጣጥና ሪፖርት አቀራረብ | የሰመር ትምህርት | ከትምህርት ቤቶች እቃዎችን ስለመውሰድ-ስለመቀበል | የአእምሮ ጤንነት ግንዛቤን ለማዳበር በሜይ ወር የሚካሄደውን የ MCPS ጥረት ለመደገፍ MCPS Waymaking Videos ቪድኦችን ያቀርባል። | Nick Asante ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል በመሆን ተመርጧል | ለተማሪዎች ስለ #ThisIsWhy Youth PSA Campaign ውድድር ይካሄዳል | ከምክትል ሱፐርኢንተንደንት መክናይት እና ከተማሪ የቦርድ አባል ናትናኤል ትንቢት - Deputy Superintendent McKnight and SMOB Nate Tinbite ጋር ስለተደረገ ጥያቄና መልስ-Q&A |


ስለ 2020 ተመራቂዎች ቨርቹወል የምረቃ ሥርአት

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የ 2020 ተመራቂዎችን ምረቃ እሑድ፣ ጁን 7 ሲስተም አቀፍ ዩኒቨርሳል የምረቃ ስርዓት " Universal Graduation Celebration" ዝነኛው  "Jose Andres" ታላቁ የምግብ አሠራር ባለሙያ እና የ https://wck.org/ መሥራች በስነሥርአቱ ተጋባዥ ተናጋሪ በሚገኘበት ይካሄዳል።

ሁነቱ በሚካሄድበት ወቅት ከ 10,500 በላይ ለሚሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመራቂዎች እውቅና እና ክብር ይሰጣል። ከ NBC4 ጋር በመተባበር ተዘጋጅቶ ከ 6 p.m. ጀምሮ በ Cozi TV (broadcast over-the-air channel 4.2, Verizon Fios channel 460 and Xfinity channel 208) ይተላለፋል። የሚከበረው ስነሥርአት በኤን ቢ ሲ አንከር ሊኦን ሀሪስ "NBC4 anchor Leon Harris" ፕሮግራም መሪነት ይካሄዳል። ሁነቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የምረቃውን ሥነሥርዓት በድጋሚ ለማየት በ MCPS ድረ-ገጽ እና በ MCPS YouTube ማግኘት ይቻላል።

በተጨማሪ፣ ከ ጁን 8-12 የእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ቨርቹወል የምረቃ ሥርአት ይካሄዳል። ስለ እያንዳንዱ ትምህርት ቤት ቨርቹወል የምረቃ ሥርአት በ MCPS ድረ-ገጽ ላይ ይገለጻል።

በቀጥታ ስርጭት በሚካሄድ የምረቃ ሥነሥርዓት ላይ-The live Universal Graduation Celebration ከትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ጃክ ስሚዝ እና የትምህርት ቦርድ ፕሬዚደንት ሼብራ ኢቫንስ - Superintendent of Schools Jack Smith and Board of Education President Shebra Evans መልእክት ይተላለፋል።

ትምህርት ቤቶች ከ ሜይ 26 እስከ ጁን 5 ባለው ጊዜ ውስጥ የመመረቂያ ካባ እና ቆብ ያሠራጫሉ። የእርስዎ ልጅ ትምህርት ቤት ስለ ስርጭቱ ያለውን እቅድ ዝርዝር ይሰጣል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስለ ህዝብ የጤና ቁጥጥር ክልከላው ከተነሣ በኋላ (once public health restrictions are lifted) ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤት በአካል በመገኘት የሚካሄድ ለውጥ ያለው/የተሻሻለ አይነት የምረቃ ሥርዓቶችን - modified in-person celebrations ለማዘጋጀት ሃሳብ እንዳለን እንዲገነዘቡ እንፈልጋለን።


ውጤት አሰጣጥና ሪፖርት አቀራረብ

ሜይ 12፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ለኤለመንተሪ እና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ተሻሽሎ የቀረበ የውጤት አሠጣጥ መርህ አጽድቋል። የዚህ ለውጥ አካል እንደመሆኑ መጠን፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በእያንዳንዱ ኮርስ ላይ የመጨረሻውን ሁለተኛ ሴሚስተር ውጤታቸውን በፊደል፣ ወይም አልፏል/አልፋለች - “Pass” የሚል ውጤት እንደየምርጫቸው ያገኛሉ። ከዚህ በታች ያለው ስለ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ውጤት አሰጣጥ አሁን በሥራ ላይ ያለውን ፖሊሲ እና ስለቀጣይ እርምጃ ጠቃሚ የሆነ አጭር መግለጫ ነው፦

  • ከ3ኛ የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ያልተጠናቀቁ ነገሮችን ስለማሟላት - Resolving Incompletes from the 3rd Marking Period፦ተማሪዎች በኮርሶቻቸው ላይ ያላጠናቀቁትን የ MP3 ውጤታቸውን ለማስተካከል-ከፍ ለማድረግ እስከ ሜይ 29/2020 ቀሪ የ (MP3) ሥራዎቻቸውን መጨረስ ይኖርባቸዋል። MCPS ከ ሜይ 29 በኋላ፣ ቀሪዎቹን ያልተጠናቀቁትን ኮርሶች በሙሉ ማርች 13/2020 ላይ ወደነበረበት የውጤት ደረጃ ይቀይራል።
  • የ4ኛ ማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ማለፊያ-Passing the 4th Marking Period፦ለ4ኛ የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ፣ የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሙሉ የተዘጋጀውን መሥፈርት መሠረት በማድረግ  "Pass" ወይም "Incomplete" ውጤት ይሰጣቸዋል።
  • ስለ ሴሚስተር የውጤት ስሌት ፦ ስለ መካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የውጤት አሰጣጥ ቦርዱ የሰጠውን ውሳኔ መሠረት በማድረግ፣ ለመካከለኛ ደረጃ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሴሚስተር እና የማጠቃለያ ውጤት ስሌት ከዚህ በታች የሚገኙትን ሠንጠረዦች በጥቅም ላይ ይውላሉ።

HS Courses

ms courses

  • ምርጫ ስለማድረግ፦ ለሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የክሬዲት ኮርሶች፣ ተማሪዎች የመጨረሻ ሴሚስተር ውጤታቸውን በፊደል ወይም እንደየምርጫቸው "አልፏል/አልፋለች" - letter grade, or elect to have a “Pass” ለማግኘት ይችላሉ። በአሁን ወቅት ተማሪዎች ስለ ውጤት አሰጣጥ የሚጠቅማቸውን አማራጭ ለመውሰድ መቻላቸውን ለማረጋገጥ ሲስተሞችን እያዘጋጀን እንገኛለን። በአጠቃላይ፣ ተማሪዎች/ቤተሰቦች መጠበቅ ያለባቸው፦
    • ተማሪዎች/ቤተሰቦች ስለ እያንዳንዱ ኮርስ የውጤት አስጣጥ በድረ-ገጽ ፖርታል ላይ የሚመርጡበት "online portal" ጁን 4 ጀምሮ ይከፈታል እና ጁን 12 ይዘጋል።
    • ከ ጁን 4-12 ባለው ክፍት ጊዜ ተመራቂ የሆኑ ሲንየሮችም ስለውጤት አሰጣጥ ምርጫቸውን ለማሳወቅ ይችላሉ።
    • ተማሪዎች/ቤተሰቦች መረጃዎችን-ኢንፎርሜሽን በትክክል ተረድተው መወሰን እንዲችሉና ለዚህ ሂደት እንዲዘጋጁ በሚቀጥሉት ሁለት ሣምንቶች የበለጠ መረጃ ይላካል።
    • ምርጫዎቻቸውን እንደገና ለመመልከት እና በመጀመሪያ ምርጫቸው ላይ ለውጥ ለማድረግ የሚፈልጉ ተማሪዎች አሁን ስላለው የውጤት ለውጥ ሒደት ከካውንስለሮቻቸው ጋር መሥራት ይችላሉ።
    • ሴሚስተሩን አላጠናቀቀ(ች)ም - Incomplete የሚል የመጨረሻ ውጤት ያገኙ ተማሪዎች በሠመር ትምህርት ፕሮግራም እና/ወይም የማካካሻ ክፍለጊዜ በመማር የማለፊያ ውጤት - passing grade የማግኘት እድል ይኖራቸዋል። ያልተጠናቀቀው-"Incomplete" እስከሚስተካከል ድረስ የውጤት አሰጣጥ ምርጫቸው ተግባራዊ አይደረግም።

ስለ ኤለመንተሪ ትምህርት ቤት ውጤት አሰጣጥ
ለ4ኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ በፊደል ማርክ-ውጤት አይሰጥም። ትኩረት የሚሰጠው ተማሪዎችን በትምህርት ተሞክሮዎች ላይ እንዲሰማሩ ማድረግ እና በተቻለ መጠን ከብዙ ተማሪዎች ጋር በመገናኘት ላይ ይሆናል። ለኤለመንተሪ ተማሪዎች፣ የማጠቃለያው የፊደል ውጤት የሚሰጠው የመጀመሪያውን፣ ሁለተኛውን እና ሦስተኛውን የማርክ መስጫ ክፈለጊዜ ውጤቶችን አማካይ ውጤት መሠረት ያደረገ ነው።


የሰመር ትምህርት

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለኤለመንተሪ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሪጅን፣ እና ትምህርት ቤትን መሠረት ያደረገ እና ሌላ ዲስትሪክት አቀፍ ፕሮግራሞችን ትምህርት እና እውቀትን የማዳበር እድሎችን ይሰጣል። እነዚህ ፕሮግራሞች ትምህርት የሚሰጡት በዋና ዋና ትምህርቶች ዙርያ፣ እና እውቀትን የማዳበር እና ማህበራዊ፣ ስሜታዊ-ስነልቦናዊ ድጋፎችን የማበልጸግ እድሎች ናቸው። እንዳለፉት ዓመታት MCPS በተጨማሪ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ክሬዲት የሚሰጥባቸው የኦንላይን ኮርሶችን-online courses ይሰጣል።

ለተማሪዎች በአካል ፊት-ለ-ፊት ትምህርቶችን ለመስጠት እንችል እንደሆነ ገና አልታወቀም። ስለ አካላዊ-ማህበራዊ ርቀት በስቴት እና በካውንቲ በተጣለው እገዳ፣ የቡድን ቁጥር ማሳነስ፣ እና ስለጤና ግንዛቤ እና ደህንነት መመሪያ መሠረት፣ በመራራቅ —ፊት—ለፊት ወይም ሁለቱን በማቀላቀል ለማድረግ የሚመቸውን ሁኔታ "format—distance, face-to-face or a combination of the two—in the next few weeks ቤተሰቦች ከወዲሁ ለማቀድ እንዲችሉ በሚቀጥሉት ጥቂት ሣምንቶች ውሳኔ እንሰጣለን።

ፕሮግራሞቹ የሚጀምሩት በጁላይ ነው። ስላሉት ፕሮግራሞች ዝርዝር፣ የምዝገባ ቀኖች እና እያንዳንዱ ፕሮግራም ስለሚጀመርበት ቀን ዝርዝር መግለጫ በመጪዎቹ ሣምንቶች ለቤተሰብ ይተላለፋል እና በ MCPS ድረ-ገጽ ላይ ይገለጻል። ለሠራተኞች ለሠመር የሥራ እድሎች እንዴት ማመልከት እንደሚችሉ የሚገልጽ መረጃ በሚቀጥለው ሣምንት ይወጣል።


ከትምህርት ቤቶች እቃዎችን ስለመውሰድ-ስለመቀበል

በቅርቡ የትምህርት ዓመት ስለሚጠናቀቅ የመዝጊያ ሒደት እየተካሄደ ነው። የሠራተኞቻችንን፣ የተማሪዎቻችንን እና የቤተሰቦችን ጤንነት እና ደህንነት ለማረጋገጥ፣ ይህ ሂደት ከሚቀጥለው ሣምንት ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን ምናልባት ከጁን 15 (የትምህርት ቤት የመጨረሻ ቀን) በኋላም ይራዘም ይሆናል። በትምህርት ቤት የተውትን እቃዎች መቼ ለመውሰድ እንደሚችሉ ዝርዝር ቀኖችን የያዘ ማሣወቂያ ወላጆች ከትምህርት ቤታቸው ይደርሳቸዋል። ጤንነት/ደህንነት የቅድሚያ ትኩረታችን ስለሆነ ወደ ትምህርት ቤት ህንፃ ውስጥ እንድትገቡ የማይፈቀድላችሁ መሆኑን ልናስታውሳችሁ እንወዳለን። የመከላከያ አልባሳት ያጠለቁ ሠራተኞች እቃዎቹን አዘጋጅተው በመታጠፊያ አደባባይ ላይ ስለሚያስቀምጡ ንክኪ ሳይኖር መውሰድ ይቻላል። በዚህ ሒደት ላይ ጤንነትን/ደህንነትን ለመጠበቅ በምናደርገው የቅድሚያ ትኩረት የሚያሳዩትን ትእግሥት እናደንቃለን።


የአእምሮ ጤንነት ግንዛቤን ለማዳበር በሜይ ወር የሚካሄደውን የ MCPS ጥረት ለመደገፍ MCPS Waymaking Videos ቪድኦችን ያቀርባል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ተከታታይ ቪድኦ-MCPS “Waymaking” ለሠራተኞች፣ ለተማሪዎች፣ እና ለቤተሰቦች በእለት ተእለት ኑሯችን ላይ መላመድ ያለብን በርካታ ሁኔታዎችን ይዟል። የቪድኦው ትምህርት የሚቀርበው በ Dr. Christina Conolly, director of psychological services for MCPS አማካይነት ነው። ምልከታዎቹ "The shows" የሚከተሉትን በርካታ ርእሶች የያዙ ናቸው፦

  • ካላዊ-ማህበራዊ እርቀትን በመጠበቅ ውጥረትን፣ ፍርሃት እና ጭንቀትን ስለመቋቋም
  • የተማሪዎችን ውጥረት፣ ፍርሃት እና ጭንቀትን መቆጣጠር ስለመቻል
  • ራስን ስለ መግደል የሚታዩ ምልክቶች-ግንዛቤ
  • ስለ ማህበራዊ-ስሜታዊ-ስነልቦናዊ ትምህርት
  • ስለ ሞንጎመሪ ካውንቲ የቀውስ ሁኔታ ማእከል (Montgomery County Crisis Center)
  • ስለ ጥንቃቄ ማድረግ
  • እያንዳንዱን የአእምሮ ጭንቀት መከላከል እና የጣልቃገብ አገልግሎት - Every Mind Crisis Prevention and Intervention Services
  • ስለ ልጅ መበደል-ጉስቁልና
  • ስለ ቤት ውስጥ ግጭት-ጠብ-ጭቅጭቅ-ረብሻ

በ YouTube የምልከታ ዝርዝር ላይ አዳዲስ አርእስቶች በየሣምንቱ ይጨመራሉ። ስለ “Waymaking” ዝርዝሮች በሙሉ እዚህ ይገኛሉ።


Nick Asante ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል በመሆን ተመርጧል

Nick Asante፣ በሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት-Richard Montgomery High School ጁንየር ሲሆን፣ ለ 2020-2021 የትምህርት ዓመት ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል "Student Member of the Board of Education (SMOB)" በመሆን ተመርጧል። የ Mr. Asante የአገልግሎት ጊዜ የሚጀምረው 1/2020 ነው።

ተማሪ የቦርድ አባል (SMOB) የሞንጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ድምፅ የሚሰጥ/የምትሰጥ አባል ነው/ናት። ተማሪ የቦርድ አባል (SMOB) የጋራ ድርድር፣ የካፒታል፣ እና የሥራ ማስኬጃ በጀት እና ት/ቤቶች ሲዘጉ፣ እና ዳግመኛ ሲከፈቱ እና በት/ቤቶች ወሰን-ድንበር ጉዳዮች ላይ ለመወሰን ድምፅ ይሰጣል/ትሰጣለች። ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል "SMOB" በአሉታዊ የሰው ኃይል እርምጃ አወሳሰድ ላይ ድምፅ አይሰጥም-አትሰጥም። ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል "SMOB" አይከፈለው-አይከፈላትም፣ ነገር ግን $5,000 የኮሌጅ ትምህርት ስኮላርሽፕ፣ የተማሪ አገልግሎት ሠዓቶችን፣ እና አንድ የልቀት-ኦነር ደረጃ የማህበረሰብ ጥናት ክሬዲት ያገኛል/ታገኛለች።

Mr. Asante ከ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (John F. Kennedy High School) ጁን ላይ የሚመረቀውን ሲንየር ተማሪ አቶ ናትናኤል ትንቢትን (Mr. Nate Tinbite) ይተካል። የበለጠ ኢንፎርሜሽን ለማግኘት፦ ተማሪ የቦርድ አባል ድረገጽ ይጎብኙ።


ለተማሪዎች ስለ #ThisIsWhy Youth PSA Campaign ውድድር ይካሄዳል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ መዝናኛ (Montgomery County Recreation) እና የጋንዲ ብርጌድ (Gandhi Brigade ) ስለ #ThisIsWhy Youth PSA Campaign ውድድር ማስታወቂያ አውጥተዋል። ለወጣቶች በካውንቲያችን ጠቅላላ ስለ ማህበራዊ-አካላዊ መራራቅ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ይህ ውድድር ተማሪዎች በአርእስቱ ላይ ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ይፈቅዳል። በቤት ውስጥ ታቅቦ ከመቆየትና ምቾት ከማጣት ባሻገር፣ በእነርሱ አማካይነት የሚደረጉት አስተዋጽኦዎችን ጠቃሚነት ይገነዘባሉ … #ThisIsWhy students are choosing to #stayhome #staysafe።

ስለ #ThisIsWhy PSA Video Campaign Contest የውድድር ቪድኦ በዚህ ዓመቱ Gandhi Brigades Youth Media Festival የተካተተ ስለሆነ እስከ ጁን 5 ድረስ ይካሄዳል። በእያንዳንዱ የውድድር አይነት (ኤለመንተሪ ትምህርት ቤት፣ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ልጅግር ጎልማሳ) በአንደኛነት እና በሁለተኛነት ደረጃ ለሚያሸንፉ አሸናፊዎች የገንዘብ ስጦታ ካርዶች ሽልማት ይሰጣቸዋል። ስለ MoCoRec Pick በሣምንቱ ከቀረቡት አንድ ቪድኦ ተመርጦ አርቲስቱ(ቷ) $20 የገንዘብ ስጦታ ካርድ ያገኛል/ታገኛለች።


ከምክትል ሱፐርኢንተንደንት መክናይት እና ከተማሪ የቦርድ አባል ናትናኤል ትንቢት - Deputy Superintendent McKnight and SMOB Nate Tinbite ጋር ስለተደረገ ጥያቄና መልስ-Q&A

ናቲ ትንቢት (Nate Tinbite)፣ ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል፣ ከምክትል ሱፐርኢንተንደት ሞኒፊያ መክናይት (Deputy Superintendent Monfia McKnight) ጋር በመሆን ሜይ 20 የጥያቄ እና መልስ ክፍለጊዜ አካሂደዋል። በወቅቱ፣ Dr. McKnight ዲስትሪክቱ ስለሚያደርጋቸው ጥረቶች መግለጫ የሰጡ ሲሆን ከተማሪዎች የቀረቡላቸውን ጥያቄዎችም መልሰዋል። ክፍለጊዜውን ያልተከታተሉ ከሆነ፣ እዚህ ይመልከቱ


Important Online Resources: