boy in mask at school

የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞች

ስለ MCPS ዳግም የመክፈት እቅድ እና ስለ ወደፊት ማርች 23 የትምህርት ቦርድ ውይይት ማወቅ ያለብዎት አምስት አስፈላጊ ነገሮች እነሆ፦

  1. ስለ ተማሪ ቡድኖች የመመለሻ ጊዜ ቦርዱ አሁን ያለውን የጊዜ ማእቀፍ ለማፋጠን ወስኗል። የፈረቃ II ቡድኖች 2.1 እና 2.2 ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ህንጻዎች በፈረቃ የሚመለሱበት ጊዜ ኤፕሪል 19 ይጀመራል። ቡድን 2.2 እንዲመለሱ ቀደም ሲል ተይዞ የነበረው የጊዜ ሠሌዳ ኤፕሪል 26 ነበር።

    አዲስ የጊዜ ሠሌዳ (የጊዜ ማእቀፍ)

    ፈረቃ II (Phase II)
    ቡድን 2.1(ኤፕረል 19)
    ቡድን 2.2 (ኤፕሪል 19)
    • 8ኛ ክፍል
    • 9ኛ ክፍል
    • 11ኛ ክፍል
    • 7ኛ ክፍል
    • 10ኛ ክፍል
  2. በስፕሪንግ እረፍት ወቅት ጤንነታችሁን ጠብቁ እና የኮቪድ-19 ምርመራ ውሰዱ። የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ማእከል (CDC) እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና ኃላፊዎች በስፕሪንግ እረፍት ወቅት ከስቴት ውጭ መጓዝን አያደፋፍሩም። ከተጓዙ፥ ወደ ትምህርት ቤት ህንፃ ከመመለስህ(ሽ) በፊት ኮቪድ-19 ምርመራ እንድትወስድ(ጂ) አጥብቀን እናደፋፍራለን። ምርመራ ለመውሰድ ጊዜ እንዳለህ(ሽ) ለማረጋገጥ ማክሰኞ፥ ኤፕሪል 6 ሁሉም ተማሪዎች ቨርቹወል የሚማሩበት ቀን ነው። ሮብ፣ ኤፕሪል 7 በመርሃግብሩ መሠረት ቨርቹወል ትምህርት የሚሰጥበት ቀን ይሆናል። ኤፕሪል 6 እንደሚመለሱ የጊዜ ሠሌዳ የተያዘላቸው ተማሪዎች (Group 1.2) ወደ ህንፃዎች የሚመለሱት ሐሙስ፣ ኤፕሪል 8 ይሆናል። የኮቪድ-19 ምርመራ የጤና እንክብካቤ ከምታገኝ(ኚ)በት ወይም በካውንቲ የኮቪድ-19 ምርመራ ጣቢያዎች በነፃ መመርመር ይቻላል። የማህበረሰባችንን ጤንነት ለመጠበቅ እባክህ(ሽ) ይህንን አስፈላጊ እርምጃ መውሰድ አለብህ(ሽ)።
  3. በአካል ትምህርት ላይ ለሚሳተፉ ተማሪዎች እና ለሠራተኞች በቡድን የሚሰጥ የኮቪድ-19 ምርመራ ከስፕሪንግ እረፍት በኋላ ይጀመራል። በትምህርት ቤቶች ፕሮግራማችን የሚጀምረው ኤፕሪል 8 ስለሆነ ምርመራው በፈረቃ ይሰጣል። ጥቂት ትምህርት ቤቶች ከስፕሪንግ እረፍት አስቀድመው የሙከራ ፕሮግራም የጀመሩ ሲሆን፥ ይኼውም ለትምህርት ቤት ማህበረሰብ ተገልጿል። አስፈላጊ የስምምነት ቅጽ ለሚሞሉ ተማሪዎች እና ለሠራተኞች በሙሉ በየሣምንቱ ምርመራ ይኖራል። በግል ለሚደረግ የምርመራ ናሙና መቀበያ የጥጥ መጎርጎሪያ በእያንዳንዱ የመማሪያ ክፍሎች መሰብሰቢያ ቲዩብ ይቀመጣል፥ ከዚያም ወደ ማእከላዊ የምርመራ ላቦራቶሪ ይላካል። በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት የተመደበ(ች) የጤና ባለሙያ የምርመራ አካሄዱን ይቆጣጠራል/ትቆጣጠራለች። በተወሰደው ናሙና ላይ ኮቪድ-19 ቫይረስ መኖር አለመኖሩን በምርመራው ይረጋገጣል። ትምህርት ቤቶች በጥቂት ቀናት ውስጥ ውጤቶቹን ስለሚያገኙ ልጃቸው በሚማርበት/በምትማርበት ክፍል ወይም ከተሰባሰበው ውስጥ ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤት ከተገኘ ለቤተሰቦች ይገለጻል። የስምምነት ቅጽ በሰባት ቋንቋዎች የተዘጋጀ በመሆኑ፥ በዚህ ድረገጽ ላይ ይገኛል። የስምምነት ቅጽ ካልሞሉ የእርስዎ ተማሪ ምርመራ አይደረግለ(ላ)ትም። በትምህርት ቤታችን ስለሚካሄድ የኮቪድ-19 ምርመራ ማወቅ ያለብዎትን አምስት ነገሮች ግንዛቤ ለማግኘት ይህንን ቪድኦ ይመልከቱ - Watch this video። በተጨማሪም፥ ቴርሞሜትሮች "thermometers" ለሁሉም የ MCPS ትምህርት ቤቶች እየተላኩ ስለሆነ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ህንፃ በሚመለሱበት ጊዜ ወደ ቤት ይላካል። ትምህርት ቤቶች ቴርሞሜትሮችን "thermometers" በቀጣዮቹ ሁለት ሣምንቶች ስለሚያገኙ መቼ ወደ ቤት በተማሪዎች እንደሚላክ ለቤተሰቦች ይገልጻሉ።
  4. የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለኤለመንተሪ፣ ለሚድል ስኩል፣ እና ለከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በርካታ የሠመር ፕሮግራሞችን እየታቀደ ነው። ፕሮግራሞቹ በሒሳብ፣ ሊተረሲ፣ ኤለክቲቭስ፣ እና ለሚቀጥለው የክፍል ደረጃ መዘጋጀትን ጨምሮ የባከኑ የትምህርት ጊዜያትን ለማካካስ ይረዳሉ። የኤለመንተሪ እና የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሒሳብ፣ ሊተረሲ እና ስፔሻልስ/ኤሌክቲቭስ ፕሮግራሞችን ይሰጣሉ። በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለመመረቂያ አስፈላጊ በሆኑ በሁሉም ትምህርቶች ዙርያ ዳጋሚ ለሚወሰዱ ወይም ኦርጅናል ክሬዲት ክሬዲቶችን የማግኘት እድሎች ያሉ ሲሆን ክሬዲት የማይኖራቸው አማራጮችንም በአካባቢ ትምህርት ቤቶች መውሰድ ይችላሉ። ፕሮግራሞቹ፦
    • ያለምንም ወጪ ለሁሉም ተማሪዎች የሚሰጡ ሲሆን መጓጓዣም ይኖራል።
    • በሁሉም የአካባቢ ትምህርት ቤቶች/ክለስተሮች ይሰጣል
    • በጠቅላላ-ቨርቹወል እና በአካል አማራጮች ይኖራሉ*

    ምዝገባ ሰኞ፥ ሜይ 3 ይጀመራል የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ፕሮግራሞች ሰኞ፥ ጁን 28 የሚጀመሩ ሲሆን የኤለመንተሪ እና ሚድል ስኩል ፕሮግራሞች ማክሰኞ፥ ጁላይ 6 ይጀመራል። ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል

  5. "The MCPS COVID-19 dashboard" በትምህርት ቤቶቻችን የሚገኙ ማህበረሰቦች ቁልፍ የሆኑ የጤና አጠባበቅ ሜትሪክስ ለመከታተል እና ፖዚቲቭ ኬዞችን ማህበረሰቡ እንዲከታተል ይረዳል። የትምህርት ቤት የማሳወቂያ ደብዳቤዎች እዚህ ላይ ፖስት ይደረጋሉ። የማስታወቂያ ሠሌዳው "dashboard" ለተማሪዎች እና ለሠራተኞች ሪፖርት የተደረገ የተጠራቀመ ፖዚቲቭ ኬዞችን ወቅታዊነቱ ተጠብቆ ይገለጻል። እነዚህ ወቅታዊ መረጃዎች ኤፕሪል መግቢያ ላይ ይፋ ይሆናሉ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከ CDC. የተሰጠውን የተሻሻለውን በትምህርት ክፍል ውስጥ የአካላዊ ርቀት መመሪያ እየቃኘ ነው። በመጪው ስብሰባ ላይ የበለጠ መረጃ ለትምህርት ቦርድ ይቀርባል።

ከእረፍት በኋላ ቀጣዩቹን የተማሪ ቡድኖች በህንጻዎቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ እያልን ለመቀበል በጕጕት እንጠብቃለን። ጤናማ እና መልካም የስፕሪንግ እረፍት እንመኝላችኋለን።


መገልገያዎች/ሪሶርሶች



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools