Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: Aug. 4, 2020


mcps logo

English | español |  中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


የተከበራችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና ሠራተኞች

ዛሬ ይህንን የምጽፍላችሁ ስለ ፎል እሳቤ እና እቅድ ተሻሽሎ የተዘጋጀ ሠነድ ለማጋራት ነው። እንደምታውቁት፥ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ መስፋፋት ምክንያት ባለው ወቅታዊ የጤና ጥበቃ ሁኔታዎችን መሠረት በማድረግ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቨርቹወል ብቻ የማስተማር ሞዴል እስከ አንደኛ ሴሚስተር—ጃኑወሪ 29/2021፣ ወይም የስቴት እና የአካባቢ የጤና ሃላፊዎች ከአንደኛ ሴሚስተር በኋላ ተማሪዎቻችን የሚመለሱበት አስተማማኝ የጤንነት ሁኔታ መኖሩን እስከሚያረጋግጡልን ድረስ ቨርቹወል ብቻ ሞዴል በማስተማር ይቆያል።

Guide Imageየተሻሻለ የ MCPS Fall 2020፦ እንደገና መተለም፣ እንደገና መክፈት፣ እንደገና የማገገም-የማንሠራራት መመሪያ   ይህንን ለውጥ የሚያመለክት ሲሆን ስለ እኛ የአንደኛ ሴሚስተር ቨርቹወል ብቻ መማር-ማስተማር ሞዴል ግንዛቤ ይሰጣል። ከእናንተ—የእኛ ወላጆች፣ የሥራ ባልደረቦች እና ከተማሪዎች ግብረመልስ ስናገኝ በዚህ እቅድ ላይ ማሻሻያዎችን እያደረግን እንቀጥላለን። ሐሙስ፣ ኦገስት 6/2020 ይህንን የተሻሻለ እቅድ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ እናቀርባለን። በዚያን ጊዜ የትምህርት ቦርድ በእቅዱ ላይ ውሳኔ ይሰጣል። ይህንን አስፈላጊ ውይይት እንድትከታተሉ እናበረታታለን። ስብሰባው 3:30 p.m የሚጀመር ሲሆን ፥  በ MCPS ድረ-ገጽ ላይ በቀጥታ ስርጭት  ይተላለፋል እና በ MCPS TV (Comcast 34, Verizon 36, RCN 89) ይተላለፋል። በቀጥታ ስርጭት ለመመልከት ካልቻላችሁ፣ የስብሰባዉ ቀረጻ በ YouTube እና በ MCPS ድረ-ገጽ ላይ ይለጠፋል። በተጨማሪ ለማህበረሰብ—ኦገስት 12 ለወላጆች እና ለሠራተኞች እንዲሁም ኦገስት 13 ለተማሪዎች ሁለት ቨርቹወል ውይይቶችን እናስተናግዳለን። የሁለቱም ቨርቹወል ውይይቶች ዝርዝሮችን ለቤተሰቦች ለማጋራት በቀጣዮቹ ቀኖች በ MCPS ድረ-ገጽ ላይ ይገለጻል።

MCPS FALL 2020: Reimagine, Reopen, Recover--READ THE GUIDE

የደለበ እና በደምብ የሚያሠራ ቨርቹወል ትምህርት ለተማሪዎቻችን ለማቅረብ የተጠቀምነው በስፕሪንግ ወቅት ከነበረው ሞዴል ባገኘነው ተሞክሮ ላይ የተገነባ ነው። የቨርቹወል ትምህርት መርሃግብር በተለይም ተማሪው(ዋ) በትምህርት ቤት ከሚያደርገ-ከምታደርገው ጋር በጣም የተቀራረበ ነው። በቨርቹወል ሞዴል የማስተማር ብቃት-ችሎታቸውን እንዲያሻሽሉ ሠራተኞቻችን ተጨማሪ የሙያ ማዳበር ስልጠና እየተሰጣቸው ነው፣ ተማሪዎቻችን በጠቅላላ ከትምህርት ቤት ህንፃዎች ርቀው በሚገኙበት ወቅት የዲጅታል መገልገያዎች እና የኢንተርኔት ተደራሽነት ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሲስተም አዘጋጅተናል፣ እና ለተማሪዎች የመማር እድሎችን የማዳበር ድጋፍ ለመስጠት ተጨማሪ ጊዜ እያካበትን ነው። የተማሪዎችን፣ የሠራተኞች እና የቤተሰቦችን የመማር ማስተማር ተሳትፎአቸውን ለማቅለል-ለማዳበር የዲጅታል መገልገያዎችን እና መድረኮችን-digital tools and platforms ፍሰት-አገልግሎት እያሻሽልን ነው።

ለወላጆች፣ ለሠራተኞች እና ለተማሪዎች ድጋፍ የሚሰጡ እጅግ ጠቃሚ ሪሶርሶችን-መገልገያዎችን እያዘጋጀን ነው። ስለ ቴክኖሎጂ እና የመማሪያ ቁሳቁሶች ስርጭት እና ስለ ኦንላይን የትምህርት ዝግጅት በመጪዎቹ ቀኖች ተጨማሪ መረጃዎችን እናጋራለን። ስለ መርሃግብር እና ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ "back-to-school information" ጠቃሚ መረጃ በሚመለከት የልጅዎ ትምህርት ቤት ከእርስዎ ጋር ይገናኛል።

በፍጥነት ትምህርት ወደሚጀመርበት ቀን እየተቃረብን ስለሆነ ስጋቶችን እና ጥያቄዎችን ለመመለስ ከማህበረሰቡ ጋር መስራታችንን እንቀጥላለን። የእናንተን ግብረመልስ፣ ጥያቄዎቻችሁን እና የሚያሳስባችሁን ነገር በግብረመልስ ቅጽ ላይ  እንድታቀርቡ እናበረታታለን። ስራችንን መልክ ለማስያዝ እነዚህን የቀረቡ ጉዳዮች ሠራተኞች ይገመግሟቸዋል። የማህበረሰባችንን ፍላጎት ለማሟላት እና የ 2020-2021 የትምህርት ዓመት ስኬታማ እንዲሆን ዝግጅት እያደረግን ባለንበት ወቅት ከእኛ ጋር በመሆን በቀጣይነት ስላደረጉልን ትብብር እና ድጋፍ አመሰግናለሁ።

ከማክበር ሰላምታ ጋር

Jack R. Smith, Ph.D.
Superintendent of Schools 
ጃክ አር. ስሚዝ (ዶ/ር)
የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ