Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: July 21, 2020


mcps logo

English | español |  中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በመጀመሪያ ሴሚስተር ቨርቹወል-ብቻ ትምህርት ይሰጣል፥

ስለ ሁለተኛው ሴሚስተር እቅድ ኖቬምበር 2020 ግምገማ ይደረጋል።


የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞች፡-

ይህንን የምጽፈው ስለ ፎል 2020 የመንሠራራት-የማገገም እቅዳችን አስፈላጊ የሆነ ወቅታዊ መግለጫ ለመስጠት ነው። ት/ቤት ዳግም መክፈት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከካውንቲ እና ከስቴት የጤና ሃላፊዎች ጋር በቅርበት እየሠራን ቆይተናል። ትላንት (ጁላይ 20)፣ ከካውንቲ የጤና ኃላፊ ዶ/ር ትራቪስ ገይለስ-Dr. Travis Gayles, county health officer የሚከተለውን ተጨማሪ መመሪያ አግኝተናል "አሁን ባለው የበሽታ ወረርሽኝ እና ቅኝት መረጃ ምክንያት፣ በትምህርት ቤት ህንፃዎች ውስጥ ተማሪዎችን በአካል የማስተማርን እቅድ አልመክርም። እኔ የምመክረው ቢፈጥን ኖቬምበር የመጀመሪያ ሩብ እስከሚጠናቀቅ ድረስ፣ በቨርቹወል ማስተማርን እና የመጀመሪያ ሴሚስተር እስከሚጠናቀቅ ድረስ ቨርቹወል ማስተማርን ግምት ውስጥ በማስገባት በቨርቹወል ማስተማር ሞዴል ላይ ትኩረት ማድረግ-ኢንቨስት ማድረግን ነው።"
ከዚህ በፊት እንደገለጽኩላችሁ፣ በእቅዳችን ሁልጊዜም ቨርቹወል-ብቻ ሞዴልን ስናስብበት ቆይተናል። ነገር ግን፣ ይህ ወቅታዊ መመሪያ ከተሰጠ በኋላ፣ ለዲስትሪክታችን ጤናማው አማራጭ  ለመጀመሪያው ሴሚስተር እስከ—ጃኑወሪ 29/2021 በቨርቹወል ትምህርት መቆየት፣ እና ከመጀመርያ ሴሚስተር በኋላ ተማሪዎች ለጤና በማያሰጋ ሁኔታ እንዲመለሱ የካውንቲያችን ሁኔታ የሚፈቅድ ከሆነ የስቴት እና የአካባቢ የጤና ኃላፊዎች እስከሚወስኑ ድረስ በቨርቹወል ብቻ መማር-ማስተማር ጤናማ አማራጭ ይሆናል። ይህ ውሳኔ የፎል እና የዊንተር ስፖርቶች በጠቅላላ መሠረዛቸውን ጭምር ያካትታል። ከዶ/ር ገይለስ-Dr. Gayles እና ከካውንቲ ተመራጭ ሃላፊዎች ጋር እየሠራን በመጀመሪያው ሩብ ማለቂያ ላይ (ኖቬምበር 9/2020) በርቀት እና በአካል ጣምራ በፈረቃ የመማር-ማስተማር ሞዴልን-phased blended model በሁለተኛው ሴሚስተር (ከፌብሩወሪ 1/2021 ጀምሮ) ተግባራዊ ለማድረግ ይቻል እንደሆነ ለመወሰን ሁኔታዎችን እንገመግማለን። ይህንን በማይታመን ደረጃ ውስብስብ ሁኔታ እየቃኘን ከማህበረሰባችን ጋር የተባበረ ጥረታችንን እቀጥላለን።

በዚህ ሣምንት ገቨርነር ላሪ ሆገን እና የስቴት ትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ዶ/ር ኬረን ሳልመን - Governor Larry Hogan and Dr. Karen Salmon, state superintendent of schools ስለ ስቴቱ የትምህርት ቤቶች መነቃቃት-ማገገም እቅድ ወቅታዊ መግለጫ ይሰጣሉ ብለን እንገምታለን። የእነርሱን መመሪያ ከተመለከትን በኋላ ከመመሪያው ጋር እቅዳችንን እናስተካክላለን።

የቨርቹወል ሞዴል ትምህርት ለማግኘት በጣም አዳጋች የሆነባቸውን ስፔሻል አገልግሎቶችን የሚያገኙ ተማሪዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ የፈጠራ መንገዶችን ማሰስ እንቀጥላለን። ይህ ቨርቹወል ማስተማርን የማራዘም ውሳኔ በካውንቲያችን ውስጥ የበርካታ ወላጆችን የሥራ ጊዜያቸው ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እንደሚያሳድርባቸው እናውቃለን። የምግብ አገልግሎት፣ የቴክኖሎጂ ድጋፍ፣ እና የሌሎች ማቴሪያሎችን ተደራሽነት ለመስጠት እና አንዳንድ የህፃናት እንክብካቤ ሰጪዎች መጠቀምን የመሣሰሉ አንዳንድ አስፈላጊ የሆኑ ተግባሮችን ለማከናወን ዓላማ አንዳንድ ህንፃዎቻችን ክፍት ሆነው እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን።

ኦገስት 6/2020፣ የተሻሻለ እቅድ ለትምህርት ቦርድ እናቀርባለን። በዚያን ጊዜ የትምህርት ቦርድ በእቅዱ ላይ ውሳኔ ይሰጣል። ከአካባቢ የጤና ሃላፊዎች እና ከተማሪዎች፣ ከሠራተኞች እና ከማህበረሰብ በተገኙ ግብረመልሶችና-ምክረሃሳቦች መሠረት የተደረጉትን ለውጦች እና መሻሻሎች ይህ ወቅታዊ መረጃ ያንፀባርቃል።

ለተማሪዎቻችን ጠንካራ-ጤናማ እና አዳዲስ እውቀት የማፍለቅ ሃይል ያለው ቨርቹወል የመማር ተሞክሮዎችን  እየገነባን ያለነው በስፕሪንግ ወቅት ከተማርነው በመነሳት ነው። በቨርቹወል ሞዴል የማስተማር ብቃት-ችሎታቸውን እንዲያሻሽሉ ሠራተኞቻችን ተጨማሪ የሙያ ማዳበር ስልጠና እየተሰጣቸው ነው፣ ተማሪዎቻችን በጠቅላላ ከትምህርት ቤት ህንፃዎች ርቀው በሚገኙበት ወቅት የዲጅታል መገልገያዎች እና የኢንተርኔት ተደራሽነት እንዳላቸው ለማረጋገጥ የሚያስችል ሲስተም ዘርግተናል፣ እና ለተማሪዎች የመማር እድሎችን የማዳበር ድጋፍ ለመስጠት ተጨማሪ ጊዜ እያካበትን ነው። የተማሪዎችን፣ የሠራተኞች እና የቤተሰቦችን የመማር ማስተማር ተሳትፎአቸውን ለማቅለል-ለማዳበር የዲጅታል መገልገያዎችን እና መድረኮችን-digital tools and platforms ፍሰት-እያሻሽልን ነው።

ተማሪዎቻችን ለምንሠራው እና ለመኖራችን የልብ ትርታችን ናቸው። ሁላችንም ለተማሪዎቻችን እጅግ የተሻለ ነገር እንደምንፈልግ ምንም አልጠራጠርም። ተማሪዎቻችን ለአካደሚያዊ ስኬት እና ለማህበራዊ-ስሜታዊነት ደህንነት መዳበር ትምህርት ቤት ምንኛ አስፈላጊ መሆኑን ስለምናውቅ ይህ እጅግ ከባድ ውሳኔ ነው። ተማሪዎቻችንን ስናስተምር ለሁሉም አመቺ እድሎችን በመፍጠር፣ የሠራተኞችን እና የተማሪዎችን ጤንነትና-ሠላም የማረጋገጥ ከፍተኛ ሃላፊነት ወስደን ነው። የተማሪዎቻችንን፣ የሠራተኞችን እና የቤተሰቦችን ፍላጎቶች ለማሟላት በጋራ ተባብረን በምናደርገው ጥረት ስለሚያደርጉት ድጋፍ አመሰግናለሁ።

ከማክበር ሰላምታ ጋር፣
Jack R. Smith, Ph.D.
Superintendent of Schools
ጃክ አር. ስሚዝ (ዶ/ር)
የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ