የቤተሰብ ደብዳቤ / CEO 2.0 MOU

የማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰር ፕሮግራም መመሪያ አዲስ የተፈረመ ስምምነት

ኤፕሪል 26, 2022

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ለተማሪዎች እና ሰራተኞች ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አካታች እና ምቹ የመማሪያ አካባቢን ለማረጋገጥ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት (MCPD) እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ አስተዳደር የመግባቢያ ሠነድ (MOU) በመባል የሚታወቅ አዲስ ስምምነት ተፈራርመዋል። ይህም በካውንቲው ፐብሊክ ስኩልስ የሕግ አስከባሪ አካላት የሚሰጠውን ፕሮግራም መመሪያ ድጋፍ የሚያጠናክር ነው።

ከሁለት አመት በላይ የወረርሽኝ ተጽእኖና ቨርቹወል እና የተጣመረ ትምህርት እና እንዲሁም የእለት ተእለት የህይወት ተግዳሮቶች ተማሪዎች የፖሊስ አጋሮቻችንን ጨምሮ በታመኑ ጎልማሶች የሚመራ ማህበራዊ-ስሜታዊ እና አእምሯዊ ጤንነት ድጋፍ እና አዎንታዊ ግንኙነት መገንባት ያስፈልጋቸዋል። የማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰር (ዋና ስራ አስፈፃሚ) መርሃ ግብር የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ በመረጃ ላይ የተመሰረተ፣ ጥንቃቄ የተሞላበት እና ሁሉን አቀፍ ምላሽ ለመስጠት አስፈላጊ አካል ነው። ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቹ አካባቢ መኖር ለ MCPS ምርጥ የማስተማር እና የመማሪያ አካባቢ ተልእኮ መሰረት ነው።

ይህ እቅድ የተገለጸው በ MCPD እና MCPS መካከል ባለው የትብብር መርሃግብር ላይ ሲሆን ከትኩረት ቡድኖች፣ ከተማሪዎች፣ ከሰራተኞች፣ ከወላጆች እና ከበርካታ ቁልፍ የማህበረሰብ ባለድርሻ አካላት የተሰበሰበውን የማህበረሰብ ግብአት ያካትታል።

የተሳትፎ ተግባራት የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • ፌብሩዋሪ እና ማርች ላይ በሦስቱም ደረጃዎች የሚተገበር በአስር አመት እድሜ-ክልል ተገቢ የተማሪ ትኩረት ቡድኖችን።
  • በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ባሉ 10 የፖሊስ ዲስትሪክቶች ከ MCPS እና ከፖሊስ ተወካዮች ጋር ተከታታይ የወጣት-ፖሊስ ውይይቶች።
  • ዲሰምበር 2021 ቨርቹወል የቀጥታ ስርጭት የማህበረሰብ ውይይት ስለ ተማሪ ደህንነት ከ1,000 የሚጠጉ ተሳታፊዎች ጋር የተደረገ ውይይት።
  • ፌብሩዋሪ 3 የካውንቲ አቀፍ የተማሪዎች ዉይይት መድረኮች በሁሉም 70 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች።
  • በሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቀጣይነት ያለው የወላጅ ትኩረት ቡድኖች ጋር የሚደረጉ ውይይቶች።

"ከፖሊስ አጋሮቻችን ጋር በዚህ አዲስ ስምምነት እየሰራን ያለው ጠቃሚ የማህበራዊ-ስሜታዊ እና አእምሯዊ ጤንነት ድጋፎች ትክክለኛው መፍትሄ በዚህ ጊዜ ነው" ሲሉ ጊዜያዊ ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ.ማክኒት (Dr. Monifa B. McKnight) ተናግረዋል። "እነዚህ መኮንኖች ታማኝ እና ጠቃሚ የትምህርት ቤታችን ማህበረሰቦች አባላት ይሆናሉ ብለን እናምናለን።"

የፖሊስ አዛዡ ማርከስ ጆንስ (Police Chief Marcus Jones) እንዳሉት፣ “ይህ MOU ለመምሪያችን እና ለህግ አስከባሪ አጋሮቻችን በ MCPS ማህበረሰብ ውስጥ እና ከዚያም ባሻገር የማህበረሰቡን የፖሊስ ዓላማዎች ለማሳካት ያስችላል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት ለሁሉም የ MCPS ሰራተኞች፣ ተማሪዎች እና አጋሮቻችን ደህንነት ለማስጠበቅ ቁርጠኛ ነው። ይህም የማህበረሰባችንን ፍላጎት ለማዳመጥ በተሳተፉ አካላት መካከል የተደረገ እውነተኛ ትብብር ነው።

የ MCPS የማስተማር፣ የመማር እና የትምህርት ቤቶች ዋና ሃላፊ የሆኑት ሩሼል ሩበን (Ruschelle Reuben) የተማሪዎች እና የሰራተኞች ደህንነት እና ሠላም የዲስትሪክቱ ዋና ተቀዳሚ ጉዳይ ነው። "ይህን ፕሮግራም ውጤታማ መሆኑን ለማረጋገጥ እና ማናቸውንም የማሻሻያ ቦታዎችን ለመለየት በየጊዜው እንከታተላለን" በማለት ገልጸዋል። ይህ እቅድ የተለያዩ ፍላጎቶችን እና አስተያየቶችን እንደሚወክል ለማረጋገጥ ከተማሪዎች፣ ከሰራተኞች እና ከቤተሰቦች ጋር ውይይት አድርገናል።

MOU በተጨማሪም የተማሪዎች፣ የሰራተኞች፣ የአስተዳዳሪዎች፣ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት ተወካዮች እና የፖሊስ ዲፓርትመንት ተወካዮች የፕሮግራሙን ቀጣይነት ያለው ግምገማ ያቀርባል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚዎቹ የሚከተሉትን ያደርጋሉ፡-

  • በተመደቡበት ክላስተር ውስጥ ካሉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ጋር አብረው ይሰራሉ።
  • በሚያስፈልገው የ MCPS ሙያዊ እድገት፣ በአመጽ ያልሆነ ቀውስ ሲከሰት ጣልቃ መግባት፣ እና ፍትሃዊ እና ምላሽ ሰጪ ባህልን ያዳበረ ተሳትፎ ያደርጋሉ።
  • ከትምህርት ቤቶች ጋር ቀጥተኛ የግንኙነት መስመር ስለሚኖራቸው በዋና ዋና የት/ቤቶች ዝግጅቶች ላይ ድጋፎችን ያስተባብራሉ፤ ለምሳሌ የአትሌቲክስ ዝግጅቶች፣ ትላልቅ ጭፈራዎች ወይም ሌሎች ተግባራት ሲኖሩ ማለት ነው።
  • ዋና አስፈጻሚዎቹ ለመደበኛ የትምህርት ቤት የዲሲፕሊን ክስተቶች ምላሽ አይሰጡም። እነዚህ ክስተቶች የሚመሩት/የሚስተናገዱት በ MCPS የተማሪ የስነምግባር ህግ ውስጥ በተዘረዘረው ስነ-ስርዓት ነው።

“የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር እንደመሆኔ እነዚህ አዳዲስ መመሪያዎች ለእኛ ትክክለኛ ሚዛን ናቸው። ከፖሊስ አጋሮቻችን ጋር የበለጠ ቀጥተኛ እና የትብብር ግንኙነት መፍጠር ጠቃሚ ይሆናል” ሲሉ የኮ/ኔል ዛዶክ ማግሩደር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር የሆኑት ዶ/ር ሌሮይ ሲ.ኢቫንስ (Dr. Leroy C. Evans) አስረድተዋል። "ይህ በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ያለው ግንኙነት ተማሪዎች እና ሰራተኞች የሚያዩት በመሆኑ በዚህ ምክንያት የበለጠ የደህንነት ስሜት ይኖረናል" ብለዋል።

MOU ወዲያውኑ ተግባራዊ ይሆናል። የማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰሮች በ MCPS ውስጥ ለእያንዳንዱ ክለስተር ይመደባሉ።
የተፈረመውን MOU እዚህ ይመልከቱ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public SchoolsEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools