ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የጤና አገልግሎት ኃላፊ የተላለፈ ጠቃሚ መልእክት

January 17, 2023

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦
ሐሙስ፥ ጃንዋሪ 12 የካውንቲ መሪዎቻችን በማህበረሰባችን ውስጥ ስላለው የኮቪድ-19 ስርጭት መጨመር ስጋታቸውን ገልጸዋል። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ሆስፒታሎች በርካታ ህሙማንን የመቀበል ሁኔታ እየጨመረ ስለሄደ፣ የካውንቲያችን የማህበረሰብ ስጋት ደረጃ አሁን "MEDIUM/መካከለኛ ደረጃ ላይ ነው። ይህ በጣም ተጋላጭ በሆኑ የማህበረሰባችን አባላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል መሆኑን ግንዛቤ መውሰድ እና ከባድ በሽታን የመከላከል አስፈላጊነትን አጉልተን እንድናይ ያደርገናል። በትምህርት ቤቶች የመረጃ ቋት/ዳሽቦርድ ላይ፣ ትምህርት ቤቶች በተከፈቱበት የመጀመሪያው ሳምንት ከፍ ያለ ቁጥር ያላቸው ኮቪድ ፖዚቲቭ ሁኔታዎች የታዩ ሲሆን በቀጣዩ ሳምንት ጥቂት መቀነሱ ሪፖርት ተደርጓል።
ሁሉም ሰውየኮቪድ-19 እና ሌሎች የመተንፈሻ አካል ቫይረሶችን ስርጭት የመከላከል ጤናማ ልምዶችን መተግበር አለበት።ኮቪድ-19 በአካባቢያችን የሚያሳድረውን ተጽእኖ ለመቀነስ ግለሰቦች ሊወስዷቸው የሚችሏቸው ሌሎች እርምጃዎች እነሆ፦

 1. ስለ ጤና ውሳኔዎችን በሚያደርጉበት ጊዜ የኮቪድ-19 ስጋትን ግምት ውስጥ ያስገቡ።
  ከፍተኛ ተጋላጭነት ባለባቸው ሁኔታዎች፣ ለከባድ የኮቪድ-19 ኢንፌክሽን የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ካሉ ወይም ለበሽታው ተጋላጭ በሆነ ሰው አጠገብ ካሉ ተጨማሪ ጥንቃቄዎችን ማድረግ እንዲችሉ ስለ ኮቪድ-19 ስጋትና ጥንቃቄ ሊኖርዎት ይገባል። ከ50 ዓመት በላይ የሆናቸው ጎልማሶች፣ እርጉዝ ሴቶች እና አንዳንድ የጤና መጓደል ሁኔታዎች፣ የስኳር በሽታ እና አስም የመሳሰሉ ህመም ያለባቸው ግለሰቦች በኮቪድ ምክንያት ለከፋ በሽታ የተጋለጡ ናቸው።

 2. የኢንፌክሽን ስርጭትን ለመከላከል፣በተለይም ከፍተኛ ተጋላጭ በሆኑ ሁኔታዎች ለመከላከል ጭምብል ያድርጉ።
  የኛ ካውንቲ የጤና ዲፓርትመንት አፍና አፍንጫን በደንብ የሚሸፍን/የሚከላከል የፊት መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉ በጥብቅ ይመክራል ለበሽታ የሚጋለጡበት ሁኔታ ላይ ካሉ ወይም ከቤተሰብ አባል ጋር በመሆን ለከባድ የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ካሉ ጭምብል ማድረግ እንዳለብዎት ያስታውሱ።  ኮቪድ-19 ካለብዎት ወይም ካለበት ሰው ጋር ቅርብ ለቅርብ ሆነው ከተጋለጡ፣ እባክዎን CDC ራስን ማግለል እና ለበሽታ መጋለጥ መመሪያዎች መሰረት ጭምብል ያድርጉ። በአካባቢያዊ የወረርሽኝ ስርጭት ምክንያት ወይም ሌሎች ከፍተኛ ተጋላጭነት ሁኔታዎች ሲኖሩ ሰራተኞች እና ተማሪዎች በጊዜያዊነት ጭምብል እንዲያደርጉ ሊጠየቁ ይችላሉ።

 3. በተለይ ለከባድ የኮቪድ-19 ኢንፌክሽን የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ካሉዎት ስለሚወሰዱ ክትባቶች ወቅታዊ መረጃ ያግኙ።
  የኮቪድ-19 ክትባቶች ከባድ ኢንፌክሽንን ለመከላከል የሚረዱ ጠቃሚ የመከላከያ መንገዶች ናቸው ስለሆኑ 6 ወር እድሜ በላይ ያሉ ሰዎች ክትባት መውሰድ እንዲችሉ የጸደቁ ናቸው። የክትባቶች በሽታን የመከላከል አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ሊሄድ ስለሚችል የተሻሻለው ቡስተር ክትባት መውሰድ ከፍተኛ ተጋላጭነት ላላቸው ግለሰቦች ተጨማሪ ጠቃሚ በሽታን የመከላከል አቅም ይሰጣል። 

 4. ምልክቶች ካሉዎት ወይም የተጋለጡ ከሆነ ኮቪድ-19 ምርመራ ያድርጉ።
  ምልክቶቹ የኮቪድ-19 ወይም ሌላ ጉንፋን መሰል በሽታ መሆናቸውን ለማወቅ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ምርመራ ማድረግ የኮቪድ-19 ኢንፌክሽን ያለባቸውን ሰዎች ለመለየት ጠቃሚ መንገድ ነው፣ አስፈላጊ ከሆነ የህክምና እንክብካቤ ሊያደርጉ እና ቫይረሱን ወደ ሌሎች ከማስተላለፍ ለመቆጠብ ይረዳል። ከፍተኛ ስጋት ካለው የቤተሰብ አባል ጋር ጊዜ ከማሳለፍዎ በፊት ምርመራ ማድረግ እንዳለብዎት ያስቡበት። 

 5. ኮቪድ-19 የምርመራ ውጤት ፖዚቲቭ ከሆኑ፡
  • ከባድ የሕመም ምልክት ካለዎት ወይም ለከባድ የመተንፈሻ አካላት በሽታ የተጋለጡ ከሆኑ ወዲያውኑ ከጤና ባለሙያ ምክር ይጠይቁ። ከባድ በሽታን ለመከላከል የሚረዱ ሕክምናዎች ስላሉ ቀደም ብለው ህክምና ካገኙ በጣም ይረዳሉ።
  • ወደ ሌሎች ሰዎች ወረርሽኙ እንዳይስፋፋ ለመቀነስ ከበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል "CDC" የሚመከሩትን ራስን የማግለል መመሪያዎችን ይከተሉ።
  • የምርመራ ውጤታቸው ፖዚቲቭ የሆነ ሰራተኞች እና ተማሪዎች MCPS online tool/ኦንላይን ሪፖርት  በመጠቀም የምርመራ ውጤታቸውን ሪፖርት ማድረግ አለባቸው። ወረርሽኝ በትምህርት ቤቶቻችን አካባቢዎች ሲከሰት የምርመራ ውጤቶችን ሪፖርት ማድረግ MCPS የወረርሽኙን ሁኔታ ለመከታተል እና የስርጭቱን መጠን ለመቀነስ እርምጃዎችን እንዲወስድ ይረዳል። 

የስርጭት አዝማሚያዎችን ለመቆጣጠር እና የጤና አጠባበቅ እርምጃዎችን ለማቀድ MCPS ከጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ ጋር በቅርበት መስራቱን ይቀጥላል። በትምህርት ቤቶቻችን ስራዎች ላይ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ተፅእኖ ለመቀነስ የውስጥ መመሪያ እና ለማህበረሰብ የተሰጡ መመሪያዎችን በመከተል እየሰራን ነው። በጋራ እየሠራን የህብረተሰባችንን ጤና ለመጠበቅ በምናደርገው ጥረት ለሚያደርጉት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ሁላችሁንም እናመሰግናለን።

ከልብ

Patricia Kapunan, M.D., M.P.H.
MCPS Medical Officer

 Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools