ደህንነት እና ጥበቃ በትምህርት ቤቶቻችን–እያንዳንዳችን የምንጫወተው ሚና አለ

February 13, 2023

ውድ የ MCPS ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ቤተሰቦች፣

ደህንነት እና ጥበቃ በትምህርት ቤቶቻችን ከፍተኛ ተቀዳሚነት የሚሰጠው በመሆኑ በመከላከያ መንገዶች፣ በጠቃሚ አጋርነቶች እና ለማንኛውም ክስተት ፈጣን ምላሽ በመስጠት ለማረጋገጥ የምንሰራው ነገር ነው። የት/ቤት አካባቢዎቻችን ከደህንነት ስጋቶች ነፃ ሲሆኑ፣ ተማሪዎቻችን እና ሰራተኞቻችን ማተኮር እና በከፍተኛ ደረጃቸው/አቅማቸው መስራት ይችላሉ። በቅርቡ በዜናዎች ላይ የሚሰሙ ነገሮች/ታሪኮች በተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ወላጆች የጭንቀት ሀሳቦችን እና ውይይቶችን ፈጥረዋል። ምንም እንኳን እነዚህ በቅርብ የተፈጠሩ አደጋኛ ክስተቶች ቢኖሩም፣ የእኛ 210 ትምህርት ቤቶች ደህንነትን ለመደገፍ በሰጠነው ትኩረት እና በአዋቀርናቸው ሂደቶች የተነሳ ማህበረሰባችን ውስጥ ድህንነታቸው ከተጠበቁት ጥቂት ቦታዎች መካከል ይመደባሉ። ከፍተኛ ደረጃ ያለውን ደህንነት ለማስጠበቅ፣ ሁላችንም እንደ አጋሮች ሆነን መስራታችን አስፈላጊ ነው።

የሁሉንም ተማሪዎቻችንን እና የት/ቤት ሰራተኞች ደህንነት እና ጤናማነት ለማረጋገጥ የእርስዎ ትብብር አስፈላጊ ነው። እኛ ተማሪዎችን እናስተምራለን—እናም ወላጆችን እና አሳዳጊዎችን ለተማሪዎች እንዲነግሩ/እንዲያስታውሱ የምንጠይቀው—ይሄንን ነው፦

  • በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ (የጦር) መሳሪያዎች አይፈቀዱም፣ መቼም ቢሆን። ሽጉጥ፣ ቢላዋ፣ የመጫወቻ ሽጉጥ፣ ጥይቶች ወይም ማንኛውም ጉዳት ለማድረስ የሚውሉ መሳሪያዎች የተከለከሉ ናቸው እና ከፍተኛ የሆነ የትምህርት ቤት እና የወንጀል መዘዞችን የሚያስከትሉ ናቸው።
  • ፈንጂዎች/ተቀጣጣይ ነገሮች አይፈቀዱም። ርችቶች፣ የጭስ ቦምቦች፣ የእሳት ተቀጣጥዮች (flares)፣ ወይም ማንኛውም ተቀጣጣይ መሳሪያዎች የተከለከሉ ናቸው።
  • ማንኛውም አይነት ህገወጥ መድሃኒቶች (ኦፒዮይድ፣ ማሪዋና፣ ወዘተ)፣ የመተንፈሻ/ቬፒንግ (vaping) መሳሪያዎች እና የትምባሆ ምርቶች በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ አይፈቀዱም።
  • እንደ መገፍተር፣ መግፋት ወይም በማንም ሰው ላይ አካላዊ ጥቃትን የመሳሰሉ ድብድቦች/ፀቦች እና አካላዊ ሽኩቻዎች አይፈቀዱም። እና
  • ሁሉም የውጭ በሮች ሁል ጊዜ መዘጋት እና መቆለፍ አለባቸው። መሠረታዊ ቢሆንም፣ ይህ ደህንነትን ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው። ሁሉም ጎብኚዎች የጥበቃ መፈተሻ ቦታዎች ባሏቸው የት/ቤታችን እና የቢሮ ዋና መግቢያዎች ውስጥ ማለፍ አለባቸው። ማንኛውም ግለሰብ ለማንም ሰው የውጭ በር መክፈት የለበትም።

መኖሪያ ቤት ውስጥ ሽጉጦች ካሉ፣ ህጻናት በማይደርሱበት ቦታ መቀመጣቸውን ያረጋግጡ። በBeSmart for Kids መሠረት፣ የጠመንጃ ደህንነት ዘመቻ፣ ወደ 700 የሚጠጉ ልጆች፣ እድሜያቸው 17 እና ከዚያ በታች የሆኑ፣ በየዓመቱ በጠመንጃ ራሳቸውን በማጥፋት ይሞታሉ። የጦር መሳሪያዎችን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ማስቀመጥ እነዚህን አሳዛኝ ሁኔታዎች ለመከላከል እና ልጆችን በቤት እና በትምህርት ቤት ለመጠበቅ ይረዳል።

ስለደህንነቱ የተጠበቀ የጠመንጃ/የጦር መሣሪያ ማስቀመጫ እዚህ የበለጠ ይወቁ።

የትምህርት ቤት መፀዳጃ ቤቶች
አሁን ላይ ለትምህርት ቤት መፀዳጃ ቤቶች የደህንነት እርምጃዎች በተማሪዎች፣ በሰራተኞች እና በወላጆች ግብዓት በመጠቀም እየተመረመሩ ነው። መፀዳጃ ቤቶቻችን ለተማሪዎች ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታዎች መሆን አለባቸው፣ እና የስነምግባር ደንባችንን የሚጥሱ እንደ አደንዛዥ እፅ እና ትምባሆ የመሳሰሉ ድርጊቶች የሚፈጸሙባቸው ቦታዎች መሆን የለባቸውም።

ትምህርት ቤቶች፣ መፀዳጃ ቤቶች ለታሰበላቸው አላማ ጥቅም ላይ መዋል እንዲቀጥሉ ቀኑን ሙሉ በመደበኛነት እንዲፈተሹ እና ክትትል እንዲደረግላቸው እያረጋገጡ ነው። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በሮች ክፍት ሆነው መቆየታቸውን ለማረጋገጥ የውጭ መፀዳጃ ቤት በሮች ላይ ስፕሪንግ ያላቸው መዝጊያዎች (Latches) እየተገጠሙባቸው ነው። በሽግግር/መቀያየሪያ ወቅቶች እና ባልተዋቀሩ ጊዜያት፣ ልክ እንደ ከትምህርት ቤት በፊት፣ ከትምህርት ቤት በኋላ እና ከምሳ ክፍለ-ጊዜ በኋላ ያሉ ጊዜያት ላይ፣ ትምህርት ቤቶች የተዘጋጁ መፀዳጃ ቤቶችን ሊገድቡ ይችላሉ። ሰራተኞች በትምህርት ቀን ውስጥ፣ በክፍል ጊዜያት እና በምሳ ሰአት መካከል በመፀዳጃ ቤት ውስጥ የእይታ ክትትል እና የፍተሻ ድግግሞሾችን እየጨመሩ ነው። እነዚህ እርምጃዎች፣ ከስርዓት-አቀፍ ደህንነት እና ድንገተኛ አደጋ መምሪያ ተጨማሪ ድጋፍ ጋር፣ የተማሪዎችን ምቾት ደረጃ ለማሳደግ እየተተገበሩ ነው። ትምህርት ቤቶች ይሄንን ተቀዳሚ ትኩረት የሚሰጠው ነገር በማድረግ ይቀጥላሉ።

ለአስቸኳይ ሁኔታ ዝግጁነት
ሁሉም ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ቤተሰቦች የከባድ ወይም የድንገተኛ አደጋ መመሪያዎችን ማወቅ እና መከተል መቻላቸው በጣም አስፈላጊ ነው። በመቆለፊያ (Lockdown)፣ በመጠለያ ቦታ መቆየት (Shelter-in-Place) ወይም ቦታውን ለቆ በመውጣት (Evacuation) ጊዜ ሚናዎን ይወቁ። ትምህርት ቤቶች እና ተማሪዎች በዓመት ውስጥ ብዙ ጊዜ በተግባራዊ ልምምዶች ይሳተፋሉ፣ እና ሁሉም ሰው እነዚህን የአሰራር ቅደም ተከተሎች በአደጋ ጊዜያት በትክክል መከተል አለበት። በከባድ ክስተቶች ላይ በተደረጉ ግምገማዎች በተገኘው ትምህርት/ተሞክሮ የተነሳ፣ ወላጆች ስለእነዚህ የአሰራር ቅደም ተከተሎች የበለጠ መረጃ እንዲኖራቸው ትምህርት ቤቶች በግንዛቤ እና በትምህርት ጥረቶች ላይ ተሰማርተዋል።
ስለ ድንገተኛ አደጋ ዝግጁነት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ እነዚህን ምንጮች ይመልከቱ፦

እነዚህ የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት ሂደቶች በብሔራዊ የክስተት አስተዳደር ስርዓት (NIMS) ውስጥ በፌዴራል የደህንነት መመሪያዎች ግንዛቤ የተነገሩ ናቸው እና ያለንን ጥልቅ ቁርጠኝነት እና ለአደጋ ጊዜ ዝግጁነት ይወክላሉ።

ግንኙነት እና አጋርነቶች
በድንገተኛ ጊዜዎች ከማህበረሰቦቻችን ጋር በተደጋጋሚ እና ዝርዝር ግንኙነቶች ለማድረግ የቅርብ ጊዜ ቃል ኪዳኖች ከእርስዎ የተቀበልነውን አስተያየት ማሳያ ቀጥተኛ ምሳሌ ናቸው። ከሁሉም የካውንቲ ፖሊስ ኤጀንሲዎች ጋር ያለው አስፈላጊ ግንኙነት ተዘጋጅቷል ተመድቧል እናም ለትምህርት ቤቶቻችን ከፍተኛ ዝግጁነት እና ምላሽ ለማምጣት እየሰራ ነው። በሁሉም የMCPS አካባቢዎች ለደህንነት አስፈላጊ የሆነ ቁርጠኝነት ስላላቸው ምስጋናችንን እናቀርባለን።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ፖሊሲ JGA፣ የባህሪ ማስተካከያ፣ ደህንነት እና ጠናማነት ዕቅድ የMCPS ትምህርት ቤቶች ውጤታማ ትምህርት ለማግኘት አስፈላጊ የሆኑትን አወንታዊ፣ አክብሮት የተሞላባቸው፣ ሥርዓት የጠበቁ እና ደህንነታቸው የተጠበቁ የትምህርት አካባቢዎች ይሆናሉ የሚለውን ግምት ያስቀምጣል፦ የተማሪ ተሳትፎን መጨመር፤ የተማሪዎችን ስኬት ማሳደግ፤ እና በተቻለ መጠን ከመከሰቱ በፊት የተማሪዎችን ያልተገባ/እኩይ ተግባር የሚከላከሉ ፈጣን ምላሽ ሰጪ/ንቁ የትምህርት ቤት ባህሎችን እና ምህዳሮችን ማሳደግ። እንደ አንድ የተጣመረ የተማሪ፣ የሰራተኞች እና የቤተሰብ ማህበረሰብ በጋራ በመስራት በሁሉም ህንፃዎቻችን ውስጥ ደህንነትን እናረጋግጣለን። ማንኛችንም ብንሆን ለጦር መሳሪያዎች፣ ፀቦች/ድብድቦች፣ አደንዛዥ እፆችን መጠቀም እና ማናችንንም ቢሆን ለሚያስፈራሩ ባህሪዎች ምንም ትእግስት ሊኖረን አይገባም።

ለእያንዳንዳችን የምናቀርበው የትግበራ ጥሪ "አንድ ነገር ካያችሁ፣ አንድ ነገር ተናገሩ፣" ነው፣ ይህን ማድረግ አስፈላጊ እና በዚህ ስራ ውስጥ አጋር ለመሆን ቀላሉ መንገድ ነው።

ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ / Montgomery County Public Schools

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ግብዓቶች፦

  1. ደህንነታቸው የተጠበቁ ትምህርት ቤቶች ሜሪላንድ / SAFE SCHOOLS MARYLAND ነፃ የሪፖርት ማቅረቢያ ስርዓት ነው ለደህንነት ስጋቶች - እባክዎን በመተግበሪያ፣ Safe Schools MD ድረ-ገፅ ወይም 1-833-MD-B-SAFE ሪፖርት ያድርጉ
  2. MCPS የድንገተኛ አደጋ ዝግጁነት ድህረ ገፅ

 Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools