ስለ ኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በህብረተሰቡ ውስጥ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑ ታይቷል።  ካለፈው አርብ ጀምሮ፣ ተጨማሪ ተማሪዎች እና ሰራተኞች አዲስ በኮቪድ-19 መያዛቸውን ሪፖርት አድርገዋል፣ በካውንቲው በሚገኙ ጥቂት ትምህርት ቤቶችም የመማሪያ ክፍሎችን መዘጋት አስከትሏል።  የሠመር ወቅትን ተከትሎ ማህበረሰባችን አንድ ላይ ሲሰባሰብ ይህ መጠነኛ የሆነ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መጨመሩ ያልተጠበቀ አይደለም።  የተመሠረተውን አሰራር በመከተል፣በመማሪያ ክፍል ውስጥ 3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የወረርሽኝ ሁኔታዎች ከተከሰቱ ትምህርት ቤቶች በክፍል ውስጥ ለሚገኙ ሰራተኞች እና ቤተሰቦች በቀጥታ እንዲያውቁት ያደርጋሉ።

እጅን በደንብ መታጠብ፣ ሳል እና ማስነጠስ ሲኖር አፍና አፍንጫን መሸፈን እና ሲታመሙ ቤት መቆየትን የመሳሰሉ ጤናማ ልማዶችን ሁሉም ሰው ማድረጉን መቀጠል አስፈላጊ ነው።   እነዚህ ወሳኝ የጤና ጥበቃ ስልቶች እና ክትባቶች በየትምህርት ቤቶቻችን የበሽታ ስርጭትን ለመከላከል በየእለቱ የምንጠቀማቸው ቁልፍ የሆኑ የመሽታ ስርጭትን የመከላከል እርምጃዎች ናቸው። ለኮቪድ-19፣ ወረርሽኙ በሚከሰትበት ጊዜ ሌሎች እርምጃዎች በጊዜያዊነት ሊተገበሩ ይችላሉ፣ ይህም ስርጭቱ ከፍተኛ በሆነበት የተወሰነ ቦታ ላይ የማጣሪያ ምርመራ ማድረግ፣ ርቀትን መጠበቅ እና ጭንብል መጠቀምን የመሳሰሉ ወረርሽኙን የመቆጣጠር ስልቶችን ይጨምራል። ብዙ ስልቶች ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ፣ በለጋ እድሜ ምክንያት፣ በህክምና ሁኔታ ወይም በእድገት እክል ምክንያት በአስተማማኝ ሁኔታ በተከታታይ ጭምብል ማድረግ የማይችሉ ተማሪዎች ይህን ማድረግ አይጠበቅባቸውም።

በትምህርት ቤት፣ የወረርሽኙን ሁኔታ በጊዜ/አስቀድሞ መለየት እና ምላሽ መስጠት ሰራተኞች እና ተማሪዎች ለማስተማር እና ለመማር ዝግጁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ቁልፍ እርምጃ ነው። 

ለመላው የትምህርት ቤቶቻችን ማህበረሰብ በጤና አጠባበቅ ረገድ ስለምታደርጉት አጋርነት እና ቁርጠኝነት እናመሰግናለን።

Patricia Kapunan, MD, MPH

Medical Officer


በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች/FAQ

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስለ ኮቪድ-19 ሁኔታ መረጃ የት አገኛለሁ?

የኮቪድ-19 የጤና አጠባበቅ እና የደህንነት ሂደቶችን ለመወሰን MCPS ምን አይነት መመሪያ ይከተላል?

MCPS የሚከተለው ከሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት እና ከሜሪላንድ የጤና መምሪያ (MDH) እና MDH ከመዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል (K-12) ትምህርት ቤቶች የተሰጠ መመሪያየጋራ መመሪያ CDC ስለ ተላላፊ በሽታዎች ከመዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል (K-12) ትምህርት ቤቶች ስለ ኮቪድ-19 የሚሠጣቸውን የጤና ጥበቃ ምክሮችን ይከተላል።  የማህበረሰብ ጤና ጥበቃ ስልቶች የታቀዱት ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት ጋር በመቀናጀት ነው።

ስለ ጭምብል መጠቀም/ፊት መሸፈን የMCPS ፖሊሲ ምንድነው?

  • ጭንብል ማድረግን ጨምሮ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አሠራር በኮቪድ-19 የመረጃ ቋት/ፖርታል ላይ ተገልጸዋል

  • በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች ጭምብል መጠቀም የግዴታ አይደለም።  ልዩ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፦

    • በቅርቡ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ከ5ኛው ቀን በኋላ ወደ ስራ እና ወደ ትምህርት ቤት የሚመለሱ ሲሆን CDC ባስቀመጠው መመሪያ መሠረት እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ጭምብል ማድረግ አለባቸው 

    • በጊዜያዊ የወረርሽኙ ሁኔታዎች፣ በክፍላቸው ውስጥ ብዙ ጊዜ የተጋለጡ ሰዎጭ ጭንብል ማድረግ ከበርካታ የመከላከያ ስልቶች አንዱ ነው 

በዚህ የትምህርት አመት MCPS ኮቪድ-19 የጤና አጠባበቅ ሂደቶች ላይ ምን ለውጦች ተደርገዋል?

በመረጃ ቋት/ፖርታል ላይ ያለው ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ መልዕክት በዚህ የትምህርት ዓመት ስለ ኮቪድ-19 የትምህርት ቤት አሠራር ላይ የተደረጉ ለውጦችን ይገልጻል። ትልቁ ለውጥ ተማሪዎች እና ሰራተኞች በኦንላይን ሪፖርት ማድረጊያውን መጠቀም አያስፈልጋቸውም፣ እና በቀላሉ በኮቪድ-19 ምክንያት መቅረታቸውን ለት/ቤታቸው ወይም ለፕሮግራማቸው ማሳወቅ ይችላሉ።  ተላላፊ በሽታን ለመከላከል ዋና የጤና አጠባበቅ ስልቶቻችን መተግበር እንቀጥላለን፣ እና በከፍተኛ አስጊ ሁኔታዎች ወይም የተጠረጠረ የወረርሽኝ ስርጭትን ለመገደብ የኮቪድ-19 ልዩ እርምጃዎችን በጊዜው እንተገብራለን።

የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽንን ለመከላከል የፊት መሸፈኛዎችን ስለመጠቀም የበለጠ ማወቅ የምችለው የት ነው?

Healthy Children.org: Mask Mythbusters: Common Questions about Kids & Face Masks / Rompe mitos sobre la mascarilla: preguntas frecuentes sobre el uso del tapabocas en niños

CDC፡ ኮቪድ-19 - ጭምብል መጠቀም እና እንክብካቤ/CDC: COVID-19 - Use and Care of Masks /



ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)