ስለ ሁከትና ረብሻ ከልጆች ጋር መነጋገር

 

ውድ ወላጆች፣ አሳዳጊዎች እና የማህበረሰብ አባላት

ልጆችን ለመንከባከብ በጣም አስቸጋሪ ጊዜ ነው። በአካባቢዬ የትምህርት ተቋም ውስጥ የሕፃናት ሐኪም እና ወላጅ እንደመሆኔ መጠን፣ ቤተሰቦች፣ የትምህርት ቤት ሰራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት የተለያዩ አይነት አዳጋች ሁኔታዎች ከተከሰቱ በኋላ ተማሪዎቻችንን ሲደግፉ ያላቸውን ጥንካሬ እና ድፍረት በየቀኑ እመሰክራለሁ።

ካልተጠበቀው እና ከሚያስጨንቅ የወረርሽኝ ነውጥ ተቋቁመን ስናበቃ ሌላ የረብሻና ዛቻ ፈተና ሲያጋጥመን ተግዳሮቱ የበለጠ ነው። በማንኛውም መልኩ በግልም ሆነ በቤተሰብ ለጥቃት መጋለጥ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ወይም በሚዲያ ዛቻ የደረሰባቸው ልጆች ተጎጂ ናቸው። ስለ አእምሮ ጤንነታቸው ለመረዳት ስንታገል እያለ በልጆቻችን ላይ ያልተጠበቀ ረብሻ/ዛቻ ሲፈጠር፣ከልጆቻችን ጋር እንዴት እንቋቋመዋለን?   

ወረርሽኙ የልጆችን ደህንነት እንዴት መመልከት እንዳለብን እና እንደምንረዳ ለውጦታል። አንድ የተማርነው ነገር ቢኖር አብረን ካልሰራን ልጆችን በሚገባ ማገልገል/መርዳት እንደማንችል ነው። ሁከት ቤተሰቦችን እና ማህበረሰብን የሚከፋፍል ፈተና ስለሆነ በዚህ ወቅት መደማመጥ እና አብሮ መስራት ለልጆች ደህንነት ወሳኝ ነው። እንደ ታማኝ አዋቂዎች፣ ልጆች በሚኖሩባቸው እና በሚማሩባቸው ቦታዎች ሁሉ ምን እያጋጠሟቸው እንደሆነ በተሻለ ለመረዳት አብረን መስራት አለብን፣ እና እንዴት እንደምንደግፋቸው ይህ መመሪያ ይረዳንል።  

ምናልባት ላይመስል ይችላል፤ ነገር ግን ልጆች ሰለሚሰሙና ስለሚያዳምጡ የታመኑ አዋቂዎች ድምጽ ከፍተኛ ኃይል አለው ወላጆች እና ተንከባካቢዎች፣ የትምህርት ቤት ሰራተኞች፣ የጤና አጠባበቅ ባለሙያዎች እና የማህበረሰብ መሪዎች ሁሉም የልጆችን ደህንነት እና እድገት ለመንከባከብ ልዩ እውቀት እና እድል አላቸው።  

በአጋርነት ለተማሪዎቻችን በቁርጠኝነት፣ በርህራሄ እና በጋራ መከባበር የምንችለውን ሁሉ ማድረጋችንን እንድንቀጥል እያበረታታን ከዚህ በታች ያሉትን መርጃዎች እናቀርባለን።

በየቀኑ ለልጆች ለሚያደርጉት መልካም ነገር ሁሉ አመሰግናለሁ። በዚህ የጋራ ጥረት ውስጥ፣ እርስዎ ብቻዎን አይደሉም።

Dr. Patricia Kapunan
MCPS Medical Officer


ሪሶርሶች







ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)