አበይት ጉዳዮች

የትምህርት ቦርድ ወቅታዊ መረጃዎች
ኦገስት 22, 2025

ቦርዱ "ዓላማ ያለው ፖሊሲ" በሚል ርእስ የ 2026 ህጋዊ መድረክ አጽድቋል። እምቅ አቅም አባላቱ በማህበረሰብ አስተያየት ላይ በመመስረት በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የድንበር ጥናቶች ሂደት የሪጅናል ትምህርት ፕሮግራሞችን የማስፋፋት እቅድ ላይ ተወያይተዋል። የወደፊቱን የትምህርት ቤቶች እድሳት አፈጻጸም በተመለከተ የተሻሻለ የካፒታል ፕሮጀክቶች ማዕቀፍ ቀርቧል። ቦርዱ ስለ ቀደምት ትምህርት በማንፀባረቅ ከኮሌጅ ጋርደን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ቤተሰቦች ጋር "የመዋዕለ ህጻናት ወር ዝግጅት" አክብሯል። በተጨማሪም፣ MCAAP ጋር አዲሱን 2025–2028 የጋራ ድርድር ስምምነት አጽድቋል።

የትምህርት ቦርድ "የመዋዕለ ሕፃናት ወር ዝግጅት" በልዩ ክብረ በዓል አስጀምሯል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ኦገስት 21 ለመዋዕለ ሕፃናት ወር ተዘጋጁ የሚለውን አስደሳች በዓል ማዕከላዊ መድረክ በመያዝ መርቷል። ቦርዱ ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች፣ አስተማሪዎች፣ እና የማህበረሰብ አጋሮች በተገኙበት ስለ ቀደምት የህጻናት ትምህርት ያለውን ቁርጠኝነት እና ጠንካራ ጅማሮ አስፈላጊ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል።

የቦርድ አባላቱ ከኮሌጅ ጋርደን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመጡት የመዋለ ህፃናት ተማሪዎች እና ቤተሰቦች እንዲሁም አስተማሪዎች እና የማህበረሰብ አጋሮች ጋር በመሆን ወደ መዋእለ ህጻናት የሚኖረውን ወሳኝ ሽግግር እና  ቤተሰቦች  እና ማህበረሰቦች ለት/ቤት ዝግጁነት እና ስኬት የሚጫወቱትን ጠቃሚ ሚና አንፀባርቀዋል። 

የቦርዱ ፕሬዝዳንት ጁሊ ያንግ "የዛሬው ዝግጅት ከሥነ ሥርዓት ማክበር የበለጠ ነው —ለልጆች፣ ለቤተሰቦች እና ለማህበረሰባችን ትልቅ ምዕራፍ ነው" በማለት ገልፀዋል። "መዋለ ሕጻናት የዕድሜ ልክ የትምህርት ጉዞ ላይ የመጀመሪያው እርምጃ ነው። የማወቅ ጉጉት የሚፈጠርበት፣ ጓደኝነት የሚያብብበት፣ እና ጥያቄዎችን የመጠየቅ ደስታ የሚጀምረው በዚህ ደረጃ ላይ ነው።" 

በክብረ በዓሉ ላይ ስለ ፍትሃዊ የቀዳሚ ትምህርት ተደራሽነት፣ የቤተሰብ ድጋፍ፣ እና ለእያንዳንዱ ልጅ ምቹ፣እና አስደሳች ጅምር ላይ ቦርዱ የሚያደርገውን ትኩረት አጽንኦት ሰጥተዋል።


2026 ህጋዊ መድረክ ፍትሃዊነትን፣ እንደሁኔታው ማመቻቸትን፣ እና የወደፊት ዝግጁነትን ቅድሚያ ይሰጣል

ቦርዱ 2026 ህጋዊ መድረክን ዓላማ ያለው ፖሊሲ በሚል አጽድቋል። ለቀጣዩ የሜሪላንድ አጠቃላይ ጉባኤ ዲስትሪክቱ የሚያቀነቅናቸውና የቅድሚያ ትኩረት የሚሰጣቸውን ጉዳዮች የሚዘረዝር የታመቀ አቅም.,በዝርዝር አስቀምጧል። MCPS በስትራቴጂክ እቅዱ መሰረት፣ የወደፊት ዝግጁነት፡ ለእያንዳንዱ ተማሪ ስኬት ያለውን ጉልህ ራዕይመድረክ ስለ ፍትሃዊነት፣ ተደራሽነት፣ እና ተማሪን ያማከለ ፖሊሲ የቦርዱን ቁርጠኝነት ያንፀባርቃል።

መድረኩ በአራት ቁልፍ ዘርፎች ላይ ያተኩራል፦

  • ከዘመናዊ የተማሪ ፍላጎቶች ጋር በተሻለ ሁኔታ ለማጣጣም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መመረቂያ መስፈርቶችን በየጊዜው መገምገም

  • ፍትሃዊ ተደራሽነትን እና የረጅም ጊዜ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ AP/IB ፈተና የገንዘብ ድጋፍ በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሞዴል

  • የኮሙኒቲ ትምህርት ቤቶች የገንዘብ ድጋፍን እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚያውሉ የበለጠ አመቺነት መፍጠር

  • ዲስትሪክቶች 180 ቀናት ወይም 1,080 ሰዓታት እንዲያሟሉ የሚያስችላቸው የማስተማሪያ ጊዜ ህጎችን መለወጥ

በተጨማሪ የሚቀነቀንባቸው ጉዳዮች የመምህራን ዝግጅት፣ የምረቃ መጠን ሪፖርት፣ እና የትምህርት ቤት ደህንነት ፖሊሲ ማሻሻያዎችን ያካትታሉ።

ይህለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች ምን ማለት እንደሆነ፡
መድረኩ ለምሳሌ፦ ትምህርት ቤቶች በማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች የአካዳሚክ አገልግሎቶችን የመስጠት አቅምን ማሳደግ፣  AP/IB ፈተናዎች ፍትሃዊ የሆነ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግን እና የምረቃ መስፈርቶች ላይ የወቅቱን ተማሪዎች ነባራዊ እውነታዎች የሚያንፀባርቁ ተማሪዎችን በቀጥታ የሚነኩ ፖሊሲዎችን የሚደግፍ ነው። እነዚህ ለውጦች ያሉትን ሪሶርሶች/ሀብት በአግባቡ በመጠቀም የትምህርት ተሞክሮን ለማጠናከር የታለሙ ናቸው።

ቀጣዩስ ምንድነው፦
ሴፕቴምበር 15 በሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በሚደረገው የህግ አውጪዎች መድረክ ላይ እነዚህ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች ለትምህርት ስርዓቱ ምን ማለት እንደሆኑ የበለጠ ለመነጋገር ቦርዱ ከተመረጡት ባለስልጣናት ጋር ይገናኛል።

የኦገስት 21 የቦርድ ስብሰባን ይመልከቱ እና www.montgomeryschoolsmd.org/boe ዘወትር ይከታተሉ።


የትምህርት ቦርድ እና MCAAP አዲስ ስምምነት አድርገዋል።

ቦርዱ ስለ 2025–2028 የትምህርት አመት ከሞንትጎመሪ ካውንቲ አስተዳዳሪዎች እና ርዕሳነ መምህራን (MCAAP) ጋር የተደረገውን አዲስ የህብረት ድርድር ስምምነት አጽድቋል። ሜይ 30, 2025 MCAAP አባላት ያፀደቁት ስምምነት ፍትሃዊነትን እና ፍትሃዊ የስራ ሁኔታዎችን ለማረጋገጥ፣ ግልፅነትን ለማጎልበት፣ እና ሙያዊ ልህቀትን ለመደገፍ የተሻሻለ ቋንቋን የያዘ ውል ነው።

MCAAP ፕሬዝዳንቷ ዶ/ር ክርስቲን ሃንዲ ስምምነቱን የትብብር እና የእድገት ምዕራፍ በማለት አድንቀዋል።

“ይህ ውል MCAAP እና MCPS መካከል ያለውን እውነተኛ ትብብር ያሳያል። ግልጽ የሚጠበቁ ነገሮችን ያስቀምጣል፣ የሰው ሃይል እና የህመም እረፍት ክፍያን የመሳሰሉ ቁልፍ አፈጻፀሞችን ያሻሽላል፣ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ የአባሎቻችንን ደህንነት እና የተሻለ ጥቅም ይጠብቃል። አብረን ስንሰራ ምን ልናሳካ እንደምንችል በእውነት የሚያስደንቅ ነው።

በስምምነቱ ላይ ዳግም የምደባ ሂደቶች፣ የስራ ጫና ስጋቶች፣ እና የድጎማ እና የማሟያ ማሻሻያዎች ተደርገዋል፣ ይህም የት/ቤት አስተዳዳሪዎችን እና ርዕሳነ መምህራንን ለመደገፍ የሚደረገውን አጠቃላይ ጥረት ይወክላል።


ቦርዱ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የድንበር ጥናቶች እና የፕሮግራም ማስፋፋት ሂደት ላይ ተወያይቷል

MCPS ስለወደፊቱ ዝግጁ የሁለተኛ ደረጃ የድንበር ጥናቶች እና የፕሮግራም ትንተና ማሻሻያዎችን ተመልክቷል። ይህ ተነሳሽነት ከፍተኛ ጥራት ያለው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፍትሃዊ ተደራሽነትን ይደግፋል፤ እንዲሁም ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስልታዊ/ስትራቴጂክ እቅድ ጋር ይጣጣማል።

ዋና ዋና ነጥቦቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • 2027–2028 የክራወን እና ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መከፈት እና የኖርዝውድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዳግም መከፈት ጋር የተያያዘ የድንበር ጥናቶችን እርምጃ ያመለክታል።

  • እስካሁን የደረሰውን የማህበረሰብ ግብረመልስ አስተያየቶች እና የተሻሻሉ የድንበር ጥናት አማራጮችን እንዴት እያሳወቀ እንደሆነ አጠቃላይ መግለጫ ይዟል።

  • በካውንቲው ውስጥ በስድስት ዞኖች ውስጥ የታቀዱ የሪጅናል ማግኔት መሰል ፕሮግራሞችን ጨምሮ የተዘረጋ የአካዳሚክ ፕሮግራም እቅድ ቅድመ እይታ፣ የሕክምና ሳይንስ፣ ኢንጂነሪንግ፣ ኢንተርናሽናል ባካሎሬት፣ ስነ ጥበባት እና ሌሎችም ተመሳሳይ ጭብጦችን ያካትታል።

  • በቅርበት፣ የትምህርት ቤት ህንጻዎችን በብቃት መጠቀም፣ ደህንነቱ የተጠበቀ መጓጓዣ እና የቤተሰብ ርቀትን መቀነስ ላይ አጽንዖት የመስጠት መርሆች አሉት።

  • የመጨረሻ ማጠቃለያ ከመደረጉ በፊት ተጨማሪ የማህበረሰብ ግረመልስ ግብአት ለመሰብሰብ በተለያዩ ዝግጅቶች፣ በዳሰሳ ጥናቶች፣ እና በትምህርት ቤት-ተኮር ግንኙነቶች ቀጣይነት ያለው መረጃ የማሰባሰብ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዷል።

2027-2028 የትምህርት አመት አዳዲስ ድንበሮች እና መርሃ ግብሮች ቀስ በቀስ እየጀመሩ ቦርዱ 2026 መጀመሪያ ላይ የመጨረሻውን ማጠቃለያ ይወስናል ተብሎ ይጠበቃል።

በበልግ/ፎል ወቅት በሙሉ ለቤተሰቦች ተጨማሪ መረጃዎችን ማካፈል እና የተሳትፎ እድሎች ይኖራሉ።

የበለጠ ለመረዳት እዚህ የቀረበውን ይመልከቱ።


የካፒታል ፕሮጀክቶች ቅደም ተከተል፦

MCPS በዲስትሪክቱ ውስጥ የካፒታል ፕሮጀክቶች እንዴት ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ለመምራት የተሻሻለ ማዕቀፍ አዘጋጅቷል። እቅዱ የቀድሞ የቁልፍ የፋሲሊቲ አመላካቾችን (KFIs) በፋሲሊቲ ሁኔታ ኢንዴክስ (FCI) እንደ ዋነኛ መለኪያ ይተካል፣ይህ የበለጠ መረጃን መሰረት ያደረገ እና ግልፅነት ይኖረዋል። ማዕቀፉ ስለ ህንጻዎች አጠቃቀም፣ የትምህርት ብቃት፣ እና አጠቃላይ የትምህርት አቀራረብን በተመለከተ በተማሪዎች ፍላጎት ላይ ማተኮር የመሳሰሉ ተጨማሪ መስፈርቶችን ያካትታል። ከ 25 ዓመት በላይ የሆናቸው ከግማሽ በላይ የሚሆኑ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶችን በእድሳት፣ በጥገና እና በመተካት ላይ ያተኮረ መሠረተ ልማትን ለማዘመን እና የመማሪያ አካባቢዎችን ለማሻሻል ባለ 20-አመት ስትራቴጂ ይዘረዝራል። የማህበረሰብ ግብአቶች እና ተሳትፎ የሂደቱ ቁልፍ ምሰሶዎች ሆነው ይቀጥላሉ።

አቀራረቡን በማንበብ ወይም ስለየተቋማትን (ፋሲሊቲ) ሁኔታ ግምገማ በተመለከተ አዲሱን ድረገጽ በመጎብኘት የበለጠ ይወቁ።


አስፈላጊ የሆነውን ማወቅ፡ ጤና እና ቅርስን የሚመለከት የቦርድ ሻምፒዮና

ቦርዱ የትምህርት ቤቶችን ማህበረሰብ ደህንነት ማካተት እና ተሳትፎን የሚያዳብሩ በርካታ ቁልፍ ሥርዓቶችን እውቅና በመስጠት አጽድቋል። እነዚህም አለምአቀፍ ከመጠን በላይ የመውሰድ ግንዛቤ ቀን "International Overdose Awareness Day" (ኦገስት 31) እና ብሄራዊ የተሐድሶ ወር "National Recovery Month" (ሴፕቴምበር) የሚያካትቱ ሲሆን ሁለቱም ስለ አደንዛዥ እፅ አጠቃቀም የመከላከል እና ለተጎጂዎች ድጋፍ የመስጠት ግንዛቤን ለማሳደግ የታለሙ ናቸው። ቦርዱ በአእምሮ ጤና ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመቅረፍ እና መገለልን ለመቀነስ ብሄራዊ ራስን የማጥፋት መከላከል ሳምንት (ሴፕቴምበር 7–13)አለም አቀፍ ራስን የማጥፋት መከላከል ቀን (ሴፕቴምበር 10) አውጇል።

ተጨማሪ ዕውቅና የተሰጣቸው ጉዳዮች፦ ዓለም አቀፍ የንባብ ቀን (ሴፕቴምበር 8)የሂስፓኒክ ቅርስ ወር (ከሴፕቴምበር 15 እስከ ኦክቶበር 15) ያካትታሉ። 15)እና ብሔራዊ የስጥበባት ትምህርት ሳምንት (ሴፕቴምበር 14–20)፣ እያንዳንዱ ስለ ሊተርሲ አስፈላጊነት በማክበር የባህል ቅርስ እና ስነጥበብ በተማሪዎች ስኬት ላይ ያለውን ጠቀሜታ ያከብራል።

ቦርዱ ሴፕቴምበር 26 የማህበረሰብ ተሳትፎን የማጎልበት ቀን እንዲሆን ወስኗል።ይኼውም እንደ ብሄራዊ የትምህርት ቤት የወላጆች ቡድን የምስጋና ቀን፣የወላጅ በጎ ፈቃደኞች ተማሪዎችን እና ትምህርት ቤቶችን በመደገፍ ረገድ ያላቸውን ወሳኝ ሚና በማክበር ላይ የሚያተኩር ነው።


ቀጣይ ስብሰባዎች

ሐሙስ፣ ሴፕቴምበር 4  የቦርድ የስራ ክፍለ ጊዜ


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ

በህዝባዊ የውይይት መድረኮች እና አስተያየት በመስጠት ከእኛ ጋር ይሳተፉ። 

FacebookInstagramBluesky፣ እና X ላይ ይከታተሉን

ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org


ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org