አበይት ጉዳዮች

የትምህርት ቦርድ ወቅታዊ መረጃዎች
ማርች 27, 2026

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ማርች 26 ባካሄደው ስብሰባ ላይ አዲስ የትምህርት ቤት ወሰኖችን እና የሁለተኛ ደረጃ ፕሮግራሞች የሪጅናል እቅድ አጽድቋል፤ ከእነዚህም መካከል የቻርለስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን እንደገና መክፈት፣ የኖርዝውድ እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋት እና የቶማስ S. ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ወደ ክራውን ፋርም ማዛወር ይገኙበታል። ቦርዱ በተጨማሪም በካውንቲ አቀፍ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ወሰኖች ላይ መደረግ ያለበትን የወሰን ጥናት መመሪያ አጽድቋል፣ ሳምንታዊ የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን የድጋፍ ጊዜ ማዕቀፍ አጽድቋል፣ የቶማስ S. ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተግባር ክትትል ሪፖርት ገምግሟል፣ እንዲሁም ከባድ የአየር ሁኔታ በሚከሰትበት ወቅት መከናወን ያለበትን 2026–2027 ቨርቹዋል የማስተማሪያ እቅድ አጽድቋል። ክብረ በዓሉ የሴቶች ታሪክ ወር፣ የወታደር ልጅ ወር፣ ብሔራዊ የትምህርት ቤት ማህበራዊ ስራ ሳምንት፣ እና የስቴት ሻምፒዮና የዋና እና ዳይቪንግ ቡድኖችን ያካተተ ሲሆን ይህም የተማሪዎችን ስኬት፣ የአመራር እና የማህበረሰብ ተጽእኖ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ አጉልቶ ያሳያል።


የድንበር ወሰን እና ፕሮግራሞች/Boundary & Programs | ድህረ ክንውን ሪፖርት/After-Action Report | ድጋፍ የሚሰጥበት ጊዜ/Support Time | ለአርባ ዘጠነኛው ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባልነት እጩዎች/SMOB 49 Candidates | የትምህርት ካለንደር ማሻሻል/Calendar Update | ከባድ የአየር ሁኔታ ሲከሰት ቨርቹዋል ትምህርት የሚሰጥባቸው ቀናት/Virtual Weather Days | ክብረ-በዓላት/Celebrations


የትምህርት ቦርድ ስለ ትምህርት ቤት ወሰኖች እና ለተማሪዎች እድሎችን የማስፋፋት ለውጥ እቅድ አፅድቋል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ተማሪዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የመማር እድሎች እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ለመቀየር፣ አዳዲስ የትምህርት ቤት ወሰኖችን ለማፅደቅ እና ሁሉንም ተማሪዎች ለስኬት ለማዘጋጀት የተነደፉ የሁለተኛ ደረጃ ሪጅናል ፕሮግራሞች ማዕቀፍ በማፅደቅ ወሳኝ እርምጃ ወስዷል። ዕቅዶቹ በቦርዱ አብላጫ ድምጽ ጸድቀዋል። ቦርዱ ይህንን ለእያንዳንዱ ተማሪ ቅልጥፍናን፣ ፍትሃዊነትን፣ እና እድሎችን ሚዛናዊ የትምህርት ተደራሽነት አገልግሎት ከመስጠት አንጻር የዲስትሪክቱ ምርጥና ትክክለኛ ውሳኔ አድርጎ ይመለከተዋል።

የፀደቀው እቅድ ትልቅ እና የተቀናጀ ነው፡ የቻርለስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን እንደገና መክፈት፣ የኖርዝውድ እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋት፣ የቶማስ S. ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ወደ ክራውን ፋርም ማዛወር እና ዲስትሪክቱን ለሁለተኛ ደረጃ ፕሮግራሞች በስድስት ሪጅኖች ማደራጀትን ያካትታል። ይህ ሪጅናል ሞዴል ተማሪዎች ከፍላጎት፣ ከሥራ ግብረ ኃይል ምደባ/መሟላት እና ከተማሪዎች ዝንባሌና ምርጫ ጋር የተጣጣመ ከፍተኛ ተፈላጊነት ላላቸው ፕሮግራሞች ወጥ የሆነ ተደራሽነት እንደሚኖራቸው ያረጋግጣል።

የቦርድ አባላት ድምጽ ከመስጠታቸው በፊት ምክንያቶቻቸውን የሚያብራሩ መግለጫዎችን አጋርተዋል፣ ለውሳኔ የቀረቡትን ጉዳዮች አጣዳፊነት እና አስፈላጊነት አጉልተው አንፀባርቀዋል። የቦርዱ ምክትል ፕሬዝዳንት ብሬንዳ ዎልፍ ወደፊት መራመድ አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል፡- “ለሰባት ዓመታት ቃል ተገብቷል… ፍፁምነት ወደፊት የመራመድ/የእድገት ጠላት መሆን የለበትም።” ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን የቦርዱ ፕሬዝዳንት ለተማሪዎች ያለብንን ኃላፊነት አፅንዖት ሰጥተዋል፡- “አንዳንድ ሰዎች ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፣ ነገር ግን ተጨማሪ ጊዜ መጠበቅ እያጋጠመን ያለውን እውነታ አይለውጠውም… ተማሪዎቻችን የተሻለ የትምህርት አገልግሎት ለማግኘት ከዚህ በላይ መጠበቅ አይኖርባቸውም።”

ተጠያቂነትን እና ግልጽነትን ለማረጋገጥ፣ በቦርዱ የፀደቀው ውሳኔ ሱፐርኢንቴንደንቱ ከ 2026–2027 ጀምሮ እስከ 2030–2031 ሙሉ በሙሉ እስኪተገበር ድረስ ስለ ሁለተኛ ደረጃ ፕሮግራም አተገባበር በየጊዜው ወቅታዊ መረጃዎችን እንዲያቀርቡ ይጠይቃል። በየወቅቱ መቅረብ ያለባቸው መረጃዎች ማካተት ያለባቸው ስኬቶችን፣ ተግዳሮቶችን፣ የበጀት አንድምታዎችን፣ ስለ ሥርዓተ ትምህርት መጎልበት፣ ስለ መምህራን ቅጥር እና የተማሪዎች ተደራሽነት የመሳሰሉ ቁልፍ መለኪያዎችን እንዲሁም ዕቅዱን በትክክለኛው መንገድ ለማስቀጠል የሚመከሩ ማናቸውንም ማስተካከያዎች ማንፀባረቅ አለባቸው።

አዲሱ የድንበር እና የሪጅናል ፕሮግራሞች ሞዴል ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው በ 2027–2028 የትምህርት አመት ነው። MCPS ከቤተሰቦች ጋር ግልጽ የሆነ ግንኙነት ማድረግ፣ የፕሮግራም አቅርቦቶችን ማሻሻል፣ የትምህርት ቤት አመራር መቅጠር እና የትምህርት ቤት ማህበረሰቦችን ለተቀላጠፈ ሽግግር ማዘጋጀት ላይ ያተኩራል።

ቦርዱ የትምህርት ቤቶችን መዋሃድ ወይም መዘጋት ሊያካትት የሚችል በካውንቲ አቀፍ የአንደኛ ደረጃ እና የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የወሰን ጥናት መጀመር አጽድቋል። ይህ ጥናት MCPS የአሠራር ቅልጥፍናውን ከፍ ለማድረግ፣ የትምህርት ቤቶችን አጠቃቀም በእኩል ለማመጣጠን እና የተማሪዎችን የምዝገባ ቁጥር የመቀነስ ተግዳሮት ለመፍታት እንዲረዳ የተዘጋጀ ነው። ጠንካራ የማህበረሰብ ትችቶችን ሊያስከትል ቢችልም፣ ቦርዱ ሆን ተብሎ፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ እና በማህበረሰብ ተሣትፎ ላይ የተመሰረተ ሂደት ለማካሄድ ቁርጠኛ ነው።

ሱፐርኢንቴንደንቱ ያቀረቡትን ምክረሃሳብ እዚህ እና ስለተሰጡት ውሳኔዎች ከዚህ በታች የበለጠ ግንዛቤ ማግኘት ይችላሉ። ውሳኔዎቹ የፀደቁበትን የቦርድ ስብሰባ ሪኮርድ ይመልከቱ።

ውሳኔዎቹን ያንብቡ


ስለ ቶማስ S. ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የድህረ-ትግበራ ሪፖርት የቦርድ ግምገማ

ቦርዱ ፌብሩዋሪ 9በቶማስ S. ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስለተፈጠረው ክስተት በሠራተኞች በኩል በጥልቀት እና በሐቀኝነት የተካሄደውን የግምገማ ሪፖርትተቀብሏል። በጋራ ውይይት፣ የበለጠ አስተማማኝ ሪፖርት ማድረጊያ የግንኙነት ስርዓቶችን ማጠናከር ያለውን አስፈላጊነት አጉልተው አሳይተዋል፣ እና ተማሪዎችን ከወላጆች ጋር ለማገናኘት የተሻለ ዲጂታል "scan-out" ቴክኖሎጂን የሚጠቀሙ ትላልቅ እና ከፍተኛ አቅም ያላቸው ጣቢያዎች እንዲዘጋጁ ጠይቀዋል። በተጨማሪም፣ ቦርዱ "የታመነ ጎልማሳ" ሞዴልን በመላው ስርዓት-አቀፍ መደበኛ ማድረግ ላይ አፅንዖት ተሰጥቷል፣ እና እነዚህ ስትራቴጂካዊ ማሻሻያዎች በቀጣይ የበጀት እና የዕቅድ ዝግጅቶች ላይ ቅድሚያ ትኩረት እንዲሰጣቸው ለማረጋገጥ አበክረው ጠይቀዋል።


የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማሻሻያ፡ አዲስ የተመደበ የድጋፍ ጊዜ

የተማሪዎችን ስኬት እና ፍትሃዊነት ለማጠናከር በሚተገበረው ጉልህ እርምጃ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ የቦርዱ ተማሪ አባል አኑቫ ማሉ/Anuva Maloo ያቀረበውን የተማሪ የትምህርት ድጋፍ ክፍለጊዜ አንቀጽ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። ውሳኔው በሁሉም የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ፣ ሳምንታዊ የምክር ክፍለጊዜ/"Advisory Period" እንዲሰጥ ይጠይቃል።

ይህ ለተማሪዎች ምን ማለት ነው፦

  • የተመደበ ክፍለጊዜ፡የተማሪዎችን ፍላጎቶች ለመመለስ የተመደበ ሳምንታዊ ክፍለጊዜ።

  • እንደሁኔታው የሚመቻች የድጋፍ ክፍለጊዜ፡ ተማሪዎች ይህንን ክፍለጊዜ የአካዳሚክ እርዳታ ለማግኘት፣ የሚወዷቸውን ትምህርቶች በጥልቀት ለመቅሰም ወይም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እድሎችን ለማሰስ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

  • ግልፅ የጊዜ ሰሌዳዎች፡ሁሉም ሰው አስቀድሞ ማቀድ እንዲችል፣ ትምህርት ቤቶች እነዚህን የተመደቡ ክፍለ ጊዜዎች በዝርዝር የሚያሳይ የሩብ ዓመት የጊዜ ሰሌዳ ያዘጋጃሉ።

ይህንን ክፍለጊዜ መደበኛ በማድረግ፣ MCPS የተማሪዎችን አደረጃጀት ለማሳደግ እና እያንዳንዱ የመካከለኛ ደረጃ ተማሪ፣ የትኛውም ሕንፃ ላይ የሚማር ቢሆን፣ ለስኬት የሚያስፈልገውን ድጋፍ እንዲያገኝ ለማድረግ የታለመ ነው። ፕሮግራሙ ያስከተለውን ውጤት እና ተጽእኖ እና ሞዴሉን ወደፊት ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የማስፋት አቅም ካለው ከአንድ አመት በኋላ ሱፐርኢንቴንደንቱ ይገመግማሉ። ይህንን ሜሞራንደምአንብቡ። 


የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) 49ኛው ተማሪ የቦርድ አባል ማን ይሆናል?

ለ 49ኛው ተማሪ የቦርድ አባልነት (SMOB) የመጨረሻ እጩዎችዎን ያግኙ!

በዚህ የእጩዎች መድረክልዑል ዳዊት/Leul Dawit እና ሬሜይ ገርሜይ/Reemey Ghermay ለሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ያላቸውን ራዕይ ያካፍላሉ። በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ሰው ሰራሽ አዕምሮ (AI) የሚያሳድረውን ተፅእኖ እና የትምህርት ቤት ደህንነትን ከመቆጣጠር ጀምሮ እስከ መሠረተ ልማት ማሻሻል እና የተማሪዎችን መብቶች ማስፋፋት ድረስ፣ በትምህርት ቦርድ ውስጥ ድምጽዎን በተሻለ ሁኔታ የሚወክል እጩ ማን እንደሚሆን ይመልከቱ።

ሙሉውን ቪድኦ ይመልከቱ

  • ጥያቄና መልስ/Q&A: ስለ $3.7 ቢሊዮን ዶላር በጀት እና ከትምህርት ቤት ለቆ መውጣት ያላቸው አመለካከት።

  • መብረቃዊ ለውጥ:ተወዳጅ የትምህርት ቤቶች ፉክክር እና ምርጥ የካፊቴሪያ ምግብ።

  • የመዝጊያ/የማጠቃለያ ክርክር፡ ለምን የእርስዎ ድምጽ እንደሚገባቸው እንደሚያምኑ ይገልጻሉ።

የምርጫው ቀን ረቡዕ፣ ኤፕሪል 22 ነው። አሁን ይመልከቱ እና በመረጃ ዕውቀት ላይ የተመሰረተ መራጭ ይሁኑ!


አስፈላጊ ማሳሰቢያ፦ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትምህርት ዓመት የቀን መቁጠሪያ ማሻሻያ

ቦርዱ የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት መምሪያ የትምህርት አመቱ በይፋ ጁን 18 እንዲያልቅ የፈቀደውን የማረጋገጫ ፈቃድ መስጠቱን በደስታ ይገልፃል። በዚህ ክረምት ወቅት በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት በርካታ የት/ቤት መዘጋት ቢኖርም፣ የተስተካከለው የቀን መቁጠሪያ ከስቴት ሕግ ጋር ሙሉ በሙሉ የሚጣጣም ሆኖ ቀጥሏል፣ ይህም ለአንደኛ እና ለመለስተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚያስፈልገውን 1,080 የትምህርት ሰዓት እና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ደግሞ 1,170 ሰዓታት ያሟላል/አልፏል።


ከባድ የአየር ሁኔታ ሲከሰት ለቨርቹዋል የትምህርት ቀናት መዘጋጀት

ማርች 26 የቦርድ መደበኛ ስብሰባ ላይ፣ አባላቱ ስለ 2026–2027 በከባድ አየር ሁኔታ ምክንያት የሚተገበር ቨርቹዋል የማስተማር ዕቅድ ተወያይተው አጽድቀዋል። የቦርድ አባላት እቅዱ በአስቸኳይ የአየር ሁኔታ ጊዜ በት/ቤቶች መዘጋት ወቅት የትምህርት አሰጣጥ ቀጣይነትን ለመጠበቅ የተሰጠውን ትኩረት አድንቀዋል፣ እንዲሁም ለቤተሰቦች ፍትሃዊ የቴክኖሎጂ ተደራሽነት እና ግልጽ የሆነ ግንኙነት አስፈላጊነትን አጉልተው ገልጸዋል። በርካታ አባላት ያልተሣጠ የሽግግር ወቅት ዋጋ እንዳለው አስተውለዋል፣ ይህም ተማሪዎች እና ሰራተኞች የትምህርት ጊዜያቸውን ሳያባክኑ በድንገተኛ የአየር ሁኔታ ምክንያት መስተጓጎልን ለመቋቋም አማራጭ ይሰጣል። እቅዱ በልዩ ፕሮግራሞች ላይ ስላለው ተጽእኖ አንዳንድ ጥያቄዎች ቢነሱም፣ በትምህርት ዓመቱ መጨረሻ ላይ የማካካሻ ቀናትን አስፈላጊነት በመቀነስ ረገድ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት መግባባት ላይ ተደርሷል።

ስለዚህ ፕሮግራም የታቀደው መዋቅር እና አተገባበር ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለማግኘት፣ ሙሉውን 2026–2027 በአካባቢ ከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት ቨርቹዋል የትምህርት ዕቅድ ያንብቡ።


ክብረ በዓላት እና የተሰጡ እውቅናዎች 

የሴቶች የታሪክ ወር

የቦርዱ ምክትል ፕሬዝዳንት ብሬንዳ ዎልፍ የሴቶች የታሪክ ወርን እውቅና በመስጠት፣ የሕዝብ ትምህርትን እና የላቀ ፍትሃዊነትን እና ለሁሉም ሰው ዕድል የፈጠሩትን ድንቅ ሴቶችን አክብረዋል። ክሪስቲን “ቲና” ክላርክ በ 13 ዓመቷ NAACP ከመቀላቀል ጀምሮ እስከ 30 ዓመት ገደማ ድረስ በሕዝብ ጤና አማካሪነት አገልግላለች፣ ይህም በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሰብአዊ መብቶች ፎረም ውስጥ እንድትሳተፍ አስችሏታል። የሜሪላንድ ስቴት ተወካይ ቦኒ ኩሊሰን በሜሪላንድ ውስጥ በህዝብ ጤና፣ ትምህርት እና ፍትሃዊነት ላይ ላሳዩት አመራርም ክብር ተሰጥቷቸዋል፣ በ 2027 ጡረታ ለመውጣት እየተዘጋጁ ሲሆን፣ በሰጡት ዘላቂ አገልግሎት እና መልካም ተፅዕኖ አስደናቂ ውርስ ትተዋል።

የወታደር ልጅ ወር

የቦርድ አባል ላውራ ስቱዋርት የወታደር ልጅ ወርን እውቅና በመስጠት፣ ከወታደራዊ አገልግሎት ጋር የተገናኙ ተማሪዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን ጽናት እና ጥንካሬ አክብሮት ሰጥተዋል። የግሌን ሄቨን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተወካዮች፣ የትምህርት ቤቱን አመራሮች፣ ሰራተኞችን እና የማኮዊን፣ የማርሻል እና የቤይሊ ቤተሰቦችን ጨምሮ፣ ላደረጉት አገልግሎት እና ድጋፍ እውቅና ተሰጥቷቸዋል። ቦርዱ የትምህርት ቤቱን የፐርፕል ስታር ስያሜም አክብሮት ሰጥቷል፣ ይህም ከወታደራዊ አገልግሎት ጋር የተገናኙ ተማሪዎች ዓመቱን ሙሉ ድጋፍ፣ ዋጋ ያላቸው እና ተካፋይነት እንዳላቸው እንዲሰማቸው ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።

ብሔራዊ የትምህርት ቤት ማህበራዊ አገልግሎት ሳምንት

የቦርድ አባል ካርላ ሲልቬስትሬ የብሔራዊ የትምህርት ቤት ማህበራዊ አገልግሎት ሳምንትን እውቅና ሰጥተዋል፣ ይህም ማህበራዊ ሰራተኞች ተማሪዎችን፣ ቤተሰቦችን እና ትምህርት ቤቶችን በመደገፍ ረገድ የሚጫወቱትን ወሳኝ ሚና አጉልቶ ያሳያል። ከዚህ ዓመት “Unite to Ignite: Celebrating Our Impact” በሚል መሪ ቃል፣ ቦርዱ ቪክቶሪያ ኤል. ኢልስን፣ ሊሳ ደብሊው. ኮሎንን፣ ማርጋሬት ኢ. ፍላግን፣ ሺና ሂንን እና ክርስቲና ሂከንን ተማሪዎችን በማበረታታት እና የትምህርት ቤት ማህበረሰቦችን በማጠናከር ላሳዩት ቁርጠኝነት፣ አመራር እና ቁርጠኝነት አክብሮት ሰጥቷል።

የዋና እና ዳይቭ የስቴት ሻምፒዮኖች

የቦርዱ ፕሬዝዳንት ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን የሞንትጎመሪ ካውንቲ የስቴት ሻምፒዮና የዋና እና ዳይቪንግ ቡድኖችን ከዋልተር ጆንሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ከዊንስተን ቸርችል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ከፑልስቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አክብሮትና አድናቆት ሰጥተዋል። ቡድኖቹ ያልተሸነፉበትን የውድድር ዘመናትን፣ ሪከርድ የሰበሩ ስኬቶችን እና በርካታ የስቴት ዋንጫዎችን ማግኘታቸውን ጨምሮ ላሳዩት ልዩ ብቃት እውቅና ተሰጥቷቸዋል። የእነሱ ቁርጠኝነት፣ ጽናት እና ብቃታቸው የተማሪ-አትሌት ከፍተኛውን ደረጃ የሚያንፀባርቁ እና ለመላው ማህበረሰብ ኩራትን የሚያመጡ ናቸው።

ቀጣይ ስብሰባዎች

ሐሙስ፣ ኤፕሪል 16፣ የቦርድ የሥራ ክፍለ ጊዜ (12:00 p.m.)

ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 28፣ የልዩ ማህበረሰብ ኮሚቴ (10:00 a.m.)

ሐሙስ፣ ኤፕሪል 30፣ የቦርድ መደበኛ ስብሰባ (4:00 p.m) 


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ

በህዝባዊ የውይይት መድረኮች እና አስተያየት በመስጠት ከእኛ ጋር ይሳተፉ። 

FacebookInstagramBluesky፣ እና X ላይ ይከታተሉን

ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org


ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org