አበይት ጉዳዮች

የትምህርት ቦርድ ወቅታዊ መረጃዎች
ጁላይ 17,2026

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ጁላይ 16 ባካሄደው ስብሰባ፤ በቅርቡ ስለሚካሄደው የአንደኛ ደረጃ እና የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የወሰን ጥናት የመጀመሪያ ምልከታ ተቀብሏል፣ ስለዚህ ከመዋእለ ህጻናት እስከ ስምንተኛ ክፍል (K-8) ተማሪዎች ስክሪን መጠቀም ያለባቸውን የጊዜ ርዝመት እና የዲጂታል መሳሪያ አጠቃቀም አጠቃላይ ግምገማ አጽድቋል። በስብሰባው ላይ በተጨማሪም የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ አስደናቂ ስኬቶች ተንፀባርቀዋል፣ ይኼውም "Scripps National Spelling Bee" ከሰጠው ብሔራዊ እውቅና ጀምሮ የተማሪዎቻችንን እና የሰራተኞቻችንን ተሰጥኦ እና የፈጠራ ችሎታ የሚያሳዩ የአሸናፊዎች ስራ ሽልማትን ያከተተ ነው።


ስክሪን ይመልከቱ | የአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶችን ማካለል | የመመሪያ መጽሄት ወቅታዊ ማሻሻያ | የተካሄዱ ሥነ ስርአቶች | የሠመር ወቅት ማሳሰቢያዎች | 49ኛው ተማሪ የቦርድ አባል/SMOB


የቦርዱ ከመዋእለ ህጻናት እስከ ስምንተኛ ክፍል (K-8) ተማሪዎችን የስክሪን ሰዓት አጠቃቀም ግምገማ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

ቦርዱ MCPS በአንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን የስክሪን አጠቃቀም ጊዜ እና የዲጂታል መሳሪያዎችን አጠቃቀም አጠቃላይ ግምገማ እንዲያካሂድ የሚደነግግ ውሳኔ አጽድቋል።

ግምገማው ተማሪዎች በትምህርት ቀን በትምህርት ቤት በሚሰጡ ዲጅታል መሳሪያዎች ላይ ምን ያህል ጊዜ እንደሚያሳልፉ ይገመግማል፣ በትምህርት አሰጣጥ እና ከትምህርት ጋር ያልተገናኘ አጠቃቀም መካከል ያለውን ልዩነት ይመለከታል፣ አላስፈላጊ የስክሪን አጠቃቀም ጊዜን ለመቀነስ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ይገመግማል፣ እና ተማሪዎችን ተገቢ ካልሆኑ የበይነመረብ መረጃዎች ለመጠበቅ የሚረዱ የይዘት ማጣሪያዎችን ውጤታማነት ይገመግማል።

ሪፖርቱ ለቦርዱ የሚቀርበው እስከ ማርች 2027 ድረስ ሲሆን፣ ለተማሪዎች የዕድሜ ደረጃ ተስማሚ የሆነ የሚጠቀሙበት ጊዜ መመሪያ ምክሮችን ያካትታል፤ እንዲሁም የታቀዱት ለውጦች የሚያስከትሉትን ወጪዎች እና የሚያሳድሩ ተፅእኖዎችን ይዘረዝራል።

ከመዋእለ ህጻናት እስከ ስምንተኛ ክፍል (K–8) የተማሪዎች የስክሪን ሰዓት አጠቃቀም ኦዲት ሙሉውን ውሳኔ ያንብቡ።


ወደፊት የሚከናወኑ ጉዳዮች፡ የአንደኛ ደረጃ እና የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የወሰን ጥናት

MCPS ለቦርዱ የቀረበውን የአንደኛ ደረጃ እና የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የወሰን ጥናት፣ የወደፊት የት/ቤቶች ማጣመር ውሳኔዎችን፣ የትምህርት ቤቶችን መዘጋት እና የትምህርት ቤት ወሰኖችን በተመለከተ የሚደረጉ ውሳኔዎችን ለመምራት የሚረዳውን የአፈጻጸም ዕቅድ በዝርዝር አቅርቧል።

የቀረበው የታቀደውን የጊዜ ሰሌዳ፣ የውሳኔ አሰጣጥ ማዕቀፍ እና የወደፊት ምክሮችን የሚያሳውቅ መረጃ አጠቃላይ እይታ የሚመለከት ሲሆን፣ ይህም የምዝገባ ሁኔታዎችን፣ የትምህርት ቤት አቅምን፣ የህንጻዎቹን/የፋሲሊቲዎችን ሁኔታዎች እና ለተማሪዎች ያላቸውን ተደራሽነት ያካትታል፤ ነገር ግን በእነዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም። MCPS በሂደቱ ውስጥ የማህበረሰብ ግብዓት እንዴት እንደሚካተት፣ ቤተሰቦች፣ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት በማህበረሰብ ስብሰባዎች፣ በመረጃ ልውውጥ ክፍለ ጊዜዎች እና ግብረመልስ በመስጠት የመሳተፍ እድሎች መኖራቸውን አጋርቷል።

በዚህ ስብሰባ ወቅት ምንም አይነት የወሰን ለውጦች ወይም የትምህርት ቤት ማጣመር ሁኔታዎች አልቀረቡም። ይህ አቀራረብ MCPS ለወደፊቱ እንዴት ማቀድ እንደሚችል እና ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ትምምህርት የመቅሰም ልምዶችን ማቅረባቸውን ለማረጋገጥ ረጅም ውይይት መደረጉን የሚያሳይ ነበር። ማንኛውም ምክረ ሀሳብ የሚዘጋጀው ግልጽ በሆነ፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ሂደት እና ሰፊ የማህበረሰብ ተሳትፎ ባለው ሂደት ሲሆን፣ ማናቸውም የሚጸድቁ ለውጦች እስከ 2029–2030 የትምህርት አመት ድረስ ተግባራዊ አይሆኑም።

ስለ ጊዜ ሰሌዳ፣ የዕቅድ አፈጻጸም ሂደት፣ እና ስለ ማህበረሰብ ተሳትፎ እድሎች የበለጠ ለማወቅ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የወሰን ጥናት አቀራረብ ይመልከቱ


የቦርድ መመሪያ/Handbook ግምገማ ወቅታዊ መረጃ

ቦርዱ ፖሊሲዎቹ፣ አሠራሮቹ/አፈጻጸሞቹ፣ እና የመደበኛ ሥራ ስብሰባዎች አሠራር ወቅታዊ ሆነው እንዲቀጥሉ እና ግልጽነትን፣ ውጤታማ አስተዳደርን፣ እና ትርጉም ያለው የህዝብ ተሳትፎን መደረጉን ለማረጋገጥ በየዓመቱ የመመሪያ መጽሐፉን/handbook ይገመግማል።

2026–2027 የትምህርት አመት የታቀደው የቦርድ መመሪያ መፅሐፍ/Board Handbook ማሻሻያዎች ግምገማ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል። የታቀዱት ማሻሻያዎች እየተገመገሙ ባሉበት ጊዜ አሁን እየተሠራበት ያለው የቦርድ መመሪያ መጽሐፍ/Board Handbook ተግባራዊነቱ ይቀጥላል። ግምገማው ከተጠናቀቀ በኋላ፣ የታቀዱት ማሻሻያዎች ለቦርዱ እንዲቀርቡና እንዲጸድቁ ይደረጋል።

 


ሥነ ሥርዓቶች እና የተሰጡ እውቅናዎች

የሮበርት ፍሮስት ተማሪ "Scripps Spelling Bee" ብሔራዊ እውቅና አግኝቷል

ማርክ ማን የልህቀት ሽልማት/Mark Mann Excellence Award

የቦርድ አባል ናታሊ ዚመርማን/Natalie Zimmerman ስለ MCPS አስደናቂ ስኬት አክብሮት ሰጥተዋል፡- የሮበርት ፍሮስት መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነችው ሎረን ሜሪላና/Lauren Merillana 2026 ስክሪፕትስ ናሽናል ስፔሊንግ ቢ ግማሽ ፍፃሜ "2026 Scripps National Spelling Bee" ውድድር 10 ከፍተኛ ደረጃ ካገኙት አንዷ በመሆን አሸናፊ ሆናለች። በመላ አገሪቱ በሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ ተወዳዳሪዎች መካከል ጎልታ የምትታየው ሎረን በውድድሩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ብቸኛ ተወካይ ነበረች፣ የተማሪዎቻችንን ቁርጠኝነት፣ ተሰጥኦ፣ እና የትምህርት ልህቀት በአገር አቀፍ ደረጃ ማሳየት ችላለች።

ቦርዱ ሎረንን እና ቤተሰቧን በዚህ አስደናቂ ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ ሲል የሮበርት ፍሮስት መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑትን ዶ/ር ጆይ ጆንስን/Dr. Joey Jones የተማሪዎችን ስኬት በመደገፍ እና የትምህርት ልህቀትን በማሳደግ ላሳዩት አመራር እውቅና ሰጥቷል።

MCPS ፕሮዳክሽን "Capital Emmy Award" ሽልማት እውቅና አግኝቷል

ማርክ ማን የልህቀት ሽልማት

የቦርዱ ፕሬዝዳንት ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን/Grace Rivera-Oven “አቅምን በተግባር ማዋል - የወደፊት ዝግጁነት” የተሰኘውን "2026 Capital Emmy Award" አጭር ይዘት ዝግጅት ሽልማት አሸናፊነት ሽልማት አግኝተዋል።

ቦርዱ የቪዲዮ ፕሮዲዩሰር ብራያን ባብኮክን/Bryan Babcock፣ የሙዚቃ ዳይሬክተሮችን አቪ ሲልበርን፣ ጄኒፈር ቤሪን እና ካንግ ኢዊምቢን/Avi Silber, Jennifer Berry, Kang Ewimbi እንዲሁም የኖርዝዌስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ስኮት ስሚዝን/Scott Smith በዚህ አነቃቂ ፕሮዳክሽን ላይ ላደረጉት ትብብር አድናቆት ሰጥቷቸዋል። ቦርዱ የፈጠራ ችሎታቸውንና ቁርጠኝነታቸውን በመጠቀም ለፕሮጀክቱ ሕይወት የዘሩትን ተማሪዎች እውቅና ሰጥቷል፤ ከእነዚህም መካከል አቢ፣ አዳም፣ አፊያ፣ አሌክሲስ፣ ኤሚ፣ ካምሪን፣ ዲማሪ፣ ዳሻ፣ ዴዚሪ፣ ኤሜሊ፣ ኢሲያ፣ ይስሐቅ፣ ኬልሲ፣ ሊያም፣ ፒየር፣ ሮሃን፣ ሮክሳን፣ ሺሎ እና ሲራ "Abby, Adam, Afia, Alexis, Amy, Camryn, D’mari, Dasha, Desiree, Emely, Iysiah, Isaac, Kelsey, Liam, Pierre, Rohan, Roxane, Shiloh, and Syra" ይገኙበታል። 

ሽልማት ያገኘው ፕሮዳክሽን የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎችን እና አስተማሪዎችን አስደናቂ ተሰጥኦ ያንፀባርቃል፣ የትብብር፣ የፈጠራ፣ እና የተማሪዎች ድምጽ ያለውን ኃይል በጉልህ ያሳያል።


 


የሠመር ወቅት ማሳሰቢያዎች

  • ነፃ የሠመር ምግቦች አሁንም በመላው ሞንትጎመሪ ካውንቲ ከ 100 በላይ የምግብ ማደያ ቦታዎች ላይ ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ምግብ ያገኛሉ። ለቤተሰቦች ለእያንዳንዱ ብቁ ልጅ ለሠመር ግሮሰሪ $120 ዶላር "Maryland SUN Bucks" ይሰጣል። የሠመር ምግቦች የሚታደሉበትን ቦታዎች ለማወቅ እና ስለ ብቁነት መረጃ ለማግኘት MCPS የሠመር ምግብ ድረ ገጽ ይጎብኙ።

አምልጦዎት ከሆነ፡ ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል SMOB ስልጣን የመረከብ ሥነ ሥርዓት ይመልከቱ።

ልዑል ዳዊት 49ኛው የትምህርት ቦርድ ተማሪ አባል በመሆን ስለተሾምክ እንኳን ደስ አለህ! ሙሉውን የሲመት ሥነ ሥርዓትMCPS ድረ ገጽ ላይ ይመልከቱ፣ ወይም የሥነ ስርዓቱን አፈጻጸም ለማየት የእኛን ኢንስታግራም/Instagram ይመልከቱ።

ማርክ ማን የልህቀት ሽልማት/Mark Mann Excellence Award

ቀጣይ ስብሰባዎች

ሐሙስ፣ ኦገስት 20፣ የቦርድ መደበኛ ስብሰባ (ከሰዓት በኋላ 4፡00 p.m.)
ሰኞ፣ ኦገስት 31፣ ልዩ የማህበረሰብ ኮሚቴ (10:00 a.m.)
ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 1፣ የስትራቴጂክ እቅድ ኮሚቴ (10:00 a.m.)


ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ

በህዝባዊ የውይይት መድረኮች ላይ አስተያየት ለመስጠት ይሳተፉ። 

FacebookInstagramBluesky፣ እና X ላይ ይከታተሉን

ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org


ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org