ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ
ዛሬ የምጽፈው በቅርቡ በአንደኛው የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤታችን አካባቢ የተፈጸመውን የፌደራል የኢሚግሬሽን እርምጃን በሚመለከት ነው። እንደዚህ አይነት ነገር በግልፅ ሁኔታ ሲከሰት እዚያ የነበሩትን ብቻ ሳይሆን ሌሎች በርካታ ሰዎችንም ያናውጣል። በመላው ማህበረሰባችን ይዘዋወራል። የእናንተ ሱፐር ኢንተንደንት እንደመሆኔ መጠን፤ ይንን አይነት ተጽእኖ መገንዘብ እና ትኩረታችንን በጣም አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ላይ የማተኮር ጥልቅ ሀላፊነት ይሰማኛል፡ ትምህርት ቤቶቻችን ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ደጋፊ እና ለእያንዳንዱ ልጅ ምቹ መሆን እንዳለባቸው ይታመናል።
በእኛ ማህበረሰብ ውስጥ ለብዙዎች፣ የኢሚግሬሽን እርምጃ የፖሊሲ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ጥልቅ የሆነ ግላዊ ሁኔታን የሚነካ ነው። እባክዎ ይህንን ይወቁ፡ እርስዎ የ MCPS ቤተሰብ አካል ነዎት። ትምህርት ቤቶቻችን የስደተኝነት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን እያንዳንዱ ልጅ ተቀባይነት ያለው፣ የሚከበርበት፣ የተረጋገ፣ የሚከበርበት እና የሚወደድበት ደህንነታቸው የተጠበቀ የመማሪያ ቦታዎች ናቸው። ይህ ቁርጠኝነታችን ለእያንዳንዱ የተማሪ ቤተሰብ አባል የተረጋገጠ ነው።
የሚከተለውን ቁርጠንነታችንን እና የደህንነት መልእክታችንን ባለፈው ክረምት/ዊንተር ማጋራታችን ይታወሳል፣አሁንም ተመሳሳይ መርሆአችንን እና ተግባራችንን እንደገና እናፀናለን። የዚህ ሁሉ መሠረቱ ለእያንዳንዱ ተማሪ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ደጋፊ እና ምቹ የትምህርት አካባቢ በማቅረብ ላይ ነው፣ ስለሆነም በማህበረሰባችን ብዝሃነት ኩራት ይሰማናል።
የኢሚግሬሽን አስፈጻሚዎች ሲመጡ ጥብቅ ፕሮቶኮሎች ይተገበራሉ
የኢሚግሬሽን አስፈጻሚ ኃላፊዎች ወይም ሌሎች የአካባቢ ህግ አስከባሪ ወኪሎች ወደ ትምህርት ቤት ከመጡ፣ የ MCPS ሰራተኞች ግልጽ፣ ህጋዊ፣ ጤናማ ፕሮቶኮል ይከተላሉ፦
የጎብኚውን ማንነት፣ እና ያላቸውን ህጋዊ ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ።
ለአፋጣኝ መመሪያ ወደ MCPS የህግ አማካሪ/ካውንስል ያሳውቃሉ።
ማንኛውም ተማሪ ተጽዕኖ ካጋጠመው/ካጋጠማት የተማሪው(ዋ)ን ቤተሰብ በመረጡት ቋንቋ ያነጋግራሉ።
የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን ደህንነት ለማረጋገጥ ሁሉንም የትምህርት ቤት የደህንነት ፕሮቶኮሎችን ይከተላሉ።
ትምህርት ማግኘት መብት ነው
የዩናይትድ ስቴትስ ሕገ መንግሥት እና 1982 የጠቅላይ ፍርድ ቤት/ሱፕሪም ኮርት ውሳኔ ሁሉም ልጆች፣ የስደት ሁኔታ ምንም ቢሆን፣ ትምህርት የማግኘት መብት እንዳላቸው ዋስትና ተሰጥቷል።
የቤተሰብ መረጃ ለሦስተኛ ወገን እንዳይሰጥ የተጠበቀ ነው
በቤተሰብ የትምህርት መብቶች እና ግላዊነት ህግ (FERPA) እና በሜሪላንድ ህግ መሠረት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ያላቸው በጣም ውስን ሁኔታዎች ካልሆኑ በስተቀር ትምህርት ቤቶች ያለወላጅ ፈቃድ ከተማሪ ፋይል መረጃን ማጋራት አይችሉም።
ጉልበተኝነትን እና ትንኮሳን አንታገስም
MCPS በስደት ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ወይም በሌላ ምክንያት የሚከሰት ጉልበተኝነትን፣ ትንኮሳን፣ ወይም ማስፈራራትን አይታገስም። ተማሪዎች እንደዚህ አይነት ባህሪ ሲያጋጥማቸው ወዲያውኑ ለሚታመን አዋቂ ሰው ማሳወቅ አለባቸው።
ከሚመለከታቸው ቤተሰቦች ጋር የምናደርጋቸው ግንኙነቶች
መረጃን ለቤተሰቦች ስናጋራ እውነተኛ እና ከመላካችን በፊት ለትምህርት ቤት ስራ ጠቃሚ መሆኑን እናረጋግጣለን። ይህን ማድረግ ከማህበራዊ ሚዲያ ወይም በቃል ከማሠራጨት የበለጠ ጊዜ ሊወስድ ይችላል፣ ነገር ግን ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ ይበልጥ አስፈላጊ ነው። በከፊል-እውነተኛ መረጃን ማጋራት ፍርሃትን ብቻ ከማስፋፋቱም በላይ እኛ ልንጠብቃቸው የምንሞክረውን ሰዎችን ሳናስበው ሊጎዳ ይችላል።
እባካችሁ መቼም ቢሆን ዳር ተመልካች እንደማንሆን እወቁልን። በእንደዚህ አይነት ጊዜያት ከህግ አስከባሪዎች፣ ከካውንቲ ኤጀንሲዎች፣ እና ከማህበረሰብ አጋሮች ጋር በንቃት እንገናኛለን፣ እንተባበራለን። የእኛ ስራ ትክክለኛ መረጃን ማጋራት፣ የተማሪዎችን ግላዊነት መጠበቅ፣ እና ተማሪዎች እና ሰራተኞች ደህንነት እንዲሰማቸው የሚያስፈልጋቸውን ድጋፎች መስጠት ነው።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ለድንገተኛ እና ለአስቸጋሪ ሁኔታዎች ምላሽ ለመስጠት የተማሪዎችን፣ የቤተሰቦችን እና የሰራተኞችን ደህንነት ለማረጋገጥ የተሻሻለ የደህንነት ጥበቃ ፕሮቶኮል ተግባራዊ አድርጓል። መደበኛ የምላሽ አሰጣጥ ፕሮቶኮል (SRP) ደረጃውን የጠበቀ እና ሁሉም ሰው በፍጥነት እና በብቃት እንዴት ምላሽ መስጠት እንዳለበት እንዲያውቅ የአደጋ ጊዜ ቋንቋ ቀላል እንዲሆን ተደርጓል። እነዚህ ፕሮቶኮሎች ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉት በትምህርት ቤቶቻችን አካባቢ የፖሊስ እንቅስቃሴ ሲኖር ነው።
አምስት አይነት ግልጽ እርምጃዎች ይወሰድሉ፦
ባሉበት ክፍል ይቆያሉ – መተላለፊያ ቦታዎች ክፍት እና ነጻ እስከሚሆኑ ድረስ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ይቆያሉ። ይህ ተግባራዊ የሚሆነው በድንገተኛ የህክምና አደጋ ጊዜ ወይም በመተላለፊያ ቦታዎች ላይ አደጋ ሲኖር ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።
ውስጥ ማቆየት - ከውጭ የሚታይ ስጋት ካለ ለምሳሌ፦ በአቅራቢያው የፖሊስ እንቅስቃሴ የሚታይ ከሆነ ሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች ካሉበት ቦታ ወደ ውስጥ ገብተው እንዲቆዩ ይደረጋል፣ የውጪ በሮች ይቆለፋሉ። በህንፃው ውስጥ እያሉ ምን ማድረግ እንዳለባቸው መመሪያዎች ይሰጣሉ።
ሎክዳወን – "በሮች ይቆለፋሉ፣መብራቶች ይጠፋሉ፣ ከእይታ ውጪ ይቆያሉ።" በህንፃው ውስጥ ወይም በህንፃው አቅራቢያ ድንገተኛ ሁኔታዎች/አደጋዎች ሲከሰቱ ጥቅም ላይ ይውላል።
ካሉበት ለቆ መውጣት - ተማሪዎች እና ሰራተኞች ደህንነቱ ወደተጠበቀ ቦታ ህንጻውን ለቀው ይወጣሉ።
መጠለያ መያዝ – በአካባቢው ከባድ የአየር ሁኔታ በሚከሰትበት ጊዜ ጥቅም ላይ ይውላል።
እነዚህ ድርጊቶች በት/ቤቶች አቅራቢያ የኢሚግሬሽን አስፈጻሚዎች የሚገኙት እምብዛም ስለማይሆን ለማንኛውም አይነት ድንገተኛ ሁኔታ በእርጋታ እና በአስተማማኝ ሁኔታ ምላሽ እንድንሰጥ ይረዱናል። ሁሉም የሞንቶጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች እነዚህን ሂደቶች ለመለማመድ እና ከአደጋ ጊዜ በኋላ ቤተሰብን የመገናኘት እቅዶችን ለመገምገም ተከታታይ ልምምዶችን በኦክቶበር ወር መጨረሻ ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል።
ወቅታዊ የአደጋ ጊዜ የግንኙነት መረጃ መስጠት አለባቸው
እባክዎ ስለ ልጅዎ በአስቸኳይ የአደጋ ጊዜ የምናገኝዎትን አድራሻ መረጃ "ParentVUE" ላይ ወይም የወረቀት ቅጹን ሞልተው ለትምህርት ቤትዎ በማስገባት ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ።
የአስቸኳይ አደጋ ጊዜ እቅድ ያዘጋጁ
የኢሚግሬሽን ስጋት ያለባቸው ቤተሰቦች የታመነ ተንከባካቢን ለይተው እንዲያውቁ እና ስለ ሜሪላንድ የተጠንቀቅ ሞግዚትነት ሂደት እንዲያውቁ ይበረታታሉ።
መብትዎን ይወቁ
የስደተኛ የህግ አገልግሎት ማእከል የመሣሰሉ ድርጅቶች የመብት ካርዶችን እና ለቤተሰቦች የማስፈጸሚያ እርምጃዎችን እንዴት ምላሽ መስጠት እንደሚችሉ መመሪያ ይሰጣሉ።
MCPS የህግ አገልግሎቶችን እና ድጋፎችን ከሚሰጡ የአካባቢ ድርጅቶች ጋር ይተባበራል፣ እና ቤተሰቦች መረጃዎችን በማጋራት እንዲገናኙ ያበረታታል።
MCPS የኢሚግሬሽን ድጋፍ ድረ ገጽ ("መብትን ስለማወቅ" መረጃ አለው)
ጊልክረስት የስደተኞች መርጃ ማዕከል/Gilchrist Immigrant Resource Center – 240-777-4940 | ድረ ገጽ
CASA de Maryland – 240-491-5763 | ድረ ገጽ
ሉተራን የማህበራዊ አገልግሎት/Lutheran Social Services – 202-723-3000 | ድረ ገጽ
የሜሪላንድ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ቢሮ/Maryland Office for Refugees and Asylees (MORA) – ድረ ገጽ
ዓለም አቀፍ የነፍስ አድን ኮሚቴ/International Rescue Committee (IRC) – ድረ ገጽ
Ayuda – ድረ ገጽ
የስደተኞች እና የስደተኞች ማቋቋሚያ ማዕከል/Immigrant & Refugee Outreach Center (IROC) – Website
እያንዳንዱ ተማሪ በየቀኑ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጣ፣ እንዲማር፣ እንዲያድግ እና በሁሉም እንቅስቃሴዎች ያለ ፍርሃት እንዲሳተፍ እንፈልጋለን። የእናንተ ደህንነት እና ትምህርት ቅድሚያ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ነው።
በመተባበር፣ MCPS እያንዳንዱ ቤተሰብ ደህንነት የሚሰማው፣ የሚደገፍበት እና የሚታቀፍበት ቦታ መሆኑን እናረጋግጣለን። እርስዎ ወይም ልጅዎ ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች ካሉዎት፣ እባክዎን ትምህርት ቤትዎን ወይም ማእከላዊ ጽ / ቤታችንን ያነጋግሩ - እኛ ለመርዳት እዚህ ነን።
እናመስግናለን
Thomas W. Taylor, Ed.D., M.B.A.
Superintendent of Schools
ቶማስ W. ቴይለር ዶ/ር., M.B.A.
የት/ቤቶች ሱፐር ኢንተንደንት
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
በዚህ አድራሻ ኢሜል ላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org