MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
MCPS አርማ

አበይት ጉዳዮች

ሜይ 14, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 

ስለ በጀት ውይይት እና MCPS ላይ ሊያስከትል የሚችል ተጽእኖ

ስለ MCPS የሥራ ማስኬጃ በጀት ድምጽ እንደሚሰጥበት ይጠበቅ የነበረው የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል እስከ አርብ፣ ሜይ 15 ድረስ ተላልፏል። ስለ በጀት ይቀነሳል ተብሎ በውይይቱ ላይ የቀረበው $30 ሚሊዮን ዶላር እስከ $90 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ሲሆን በዲስትሪክቱ ውስጥ በሥራ ግብረኃይል፣ በፕሮግራሞች፣ እና በተማሪዎች አገልግሎቶች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ከባድ ውሳኔዎችን ሊያስከትል ይችላል።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ፣ ሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴይለር በካውንቲው ካውንስል በአሁኑ ጊዜ እየተገመገመ ስላለው የበጀት ቅነሳ እና ሊያስከትል ስለሚችለው ተጽእኖ ለሁሉም የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰራተኞች ወቅታዊ መረጃ አጋርተዋል። ማንኛውም ውሳኔ በትምህርት ክፍሎች ላይ የሚያሳርፈውን ቀጥተኛ ተጽእኖ ለመቀነስ ቅድሚያ የሚሰጥ ቢሆንም፣ በዚህ ደረጃ የሚደረጉ ቅነሳዎች ግን ከፍተኛ ተፅእኖ ይኖራቸዋል።

የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አመራር ከሠራተኞች ማህበራት ጋር በመሆን፣ ትምህርት ቤቶችና ተማሪዎች የሚያስፈልጋቸውን የበጀት ድጋፍ ለማግኘት አጥብቆ መከራከርና መሟገቱን ይቀጥላል። የትምህርት ቦርድ በካውንቲው ካውንስል የፀደቁትን ማንኛውንም የበጀት ቅነሳዎች ጨምሮ MCPS በጀት ላይ ሐሙስ፣ጁን 4 ቀን የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ተይዟል፣

ተጨማሪ መረጃ እና ቀጣይ እርምጃዎች ሲኖሩ MCPS ለማህበረሰቡ መረጃ ማጋራቱን ይቀጥላል።

የሱፐርኢንቴንደንቱን መልእክት ያንብቡቪዲዮውን ይመልከቱ

 
  myMCPS Classroom (Canvas) የሳይበር ደህንነት – ሲስተሙ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ይሠራል

myMCPS Classroom (Canvas) MCPS ከተማሪ የመረጃ አያያዝ ስርዓት/ሲስተም ጋር በማሳለጥ አሁን ሙሉ በሙሉ ይሠራል። ይህ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት በትምህርት ዓመቱ መጨረሻ የትምህርት ውጤት አሰጣጥ ወይም የሪፖርት ካርዶች ላይ ምንም አይነት ተጽእኖ ስለማይኖረው ነው።

ባለፈው ሳምንት በመላ አገሪቱ የተከሰተውን Canvas ላይ ተጽዕኖ ያሳደረውን የሳይበር ደህንነት አደጋ ተከትሎ መምህራንን ለመደገፍ፣ MCPS የመምህራንን የትምህርት ውጤት ማስረከቢያ ቀነ-ገደብ እስከ ሰኞ፣ ሜይ 18, 2026 ድረስ አራዝሟል። ለቤተሰብ ParentVUE ተደራሽነት አሁን ሙሉ በሙሉ ተስተካክሏል።

MCPS የቴክኖሎጂ ቡድኖች ሲስተሞችን በቅርበት መከታተላቸውን ይቀጥላሉ፣ እና አቅራቢው ኢንስትራክተር መረጃው ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን እና የሲስተሙ ደህንነት የተጠበቀ መሆኑን አረጋግጧል። ይህንን የሳይበር ደህንነት ክስተት አብረን ስንከታተል ተማሪዎቻችን፣ ሰራተኞቻችን፣ ቤተሰቦች፣ እና በተለይም MCPS የቴክኖሎጂ ሰራተኞቻችን ላሳዩት ትዕግስት፣ እና ትጋት ከልብ እናመሰግናለን። ቤተሰቦች MCPS ቴክኖሎጂን በመጠቀም ረገድ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከሆነ፣ ይህንን የማህበረሰብ የቴክኖሎጂ ድጋፍ ፖርታል ገጽ ይጎብኙ፡- https://montgomery.service-now.com/csm፣ እና ጥያቄ ካለዎት በዚህ አድራሻ ኢሜል ይላኩልን communitytechsupport@mcpsmd.org

 
  ተሻሽሎ የተዘጋጀው ParentVue መተግበሪያ ሜይ 15 ይጀመራል

ParentVUE እና StudentVUE መተግበሪያዎች አዲስ ቅርጸት እና ምቹ አማራጮች አላቸው። የመተግበሪያዎቹ የተሻሻለ ስሪት አርብ፣ ሜይ 15 ጀምሮ ጥቅም ላይ ይውላል። ወላጆች ParentVUE ሞባይል መተግበሪያቸውን ወቅታዊ እንዲያደርጉ ይጠየቃሉ። መመሪያው የማስታወቂያ አማራጮችን፣ የተሻሻለ የአካውንት አያያዝን እና በብዛት የሚጠቀሙበትን ፈጣን ተደራሽነት ጨምሮ ደረጃ በደረጃ ስለ መተግበሪያው ሁሉንም አዳዲስ ለውጦች ያብራራል። ቪዲዮውን ይመልከቱ.

ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ። - Spanish flyer

 
  ከትምህርት ቤት ግቢ ውጭ ስለሚከናወን የኢሚግሬሽን ማስፈጸሚያ እንቅስቃሴን በተመለከተ ለትምህርት ቤት መሪዎች የተጋራ መመሪያ

MCPS በትምህርት ቤት አቅራቢያ፣ በትምህርት ቤቶች ድጋፍ የሚካሄዱ ዝግጅቶች ወቅት ወይም በትምህርት ቤት ትራንስፖርት ላይ ለሚከሰቱ የኢሚግሬሽን ማስፈጸሚያ እንቅስቃሴዎች ምላሽ ለመስጠት ለትምህርት ቤቶች አስተዳዳሪዎች ስለሚጠበቁ ሁኔታዎች መመሪያ ሰጥቷል። መመሪያው የሚያተኩረው በመጀመሪያ የተማሪዎችና የሠራተኞች ደህንነት፣ግልጽ የሆነ ግንኙነት እና MCPS አመራርና የሕግ አገልግሎት ጋር መደረግ ስላለበት ትብብር ላይ ነው። ትምህርት ቤቶች አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ተማሪዎችን ወደ ደህና ቦታዎች ለማዛወር ቅድሚያ እንዲሰጡ፣ የማሳወቂያ ሂደቶችን እንዲከተሉ እና ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ ለቤተሰቦች እና ለሰራተኞች የተረጋገጠ መረጃ በጥንቃቄ እንዲያስተላልፉ ተገልጾላቸዋል። 

መመሪያውን እዚህ መመልከት ይችላሉ [

 
  7ኛ ክፍል ተማሪዎች ቨርቹዋል የሙያ ስራ እና የቴክኒክ ትምህርት ቀን ይሳተፋሉ

7ኛ ክፍል ተማሪዎች ጁን 1–16, 2026 ባለው ጊዜ ውስጥ በሶስተኛው አመታዊ ቨርቹዋል የስራ እና የቴክኒክ ትምህርት (CTE) ቀን ይሳተፋሉ። ተማሪዎች በቪዲዮ እና በተግባቦት በይነመረብ አማካኝነት MCPS የሙያ ዘርፎችን፣ሪጅናል ፕሮግራሞችን፣ የጣምራ ምዝገባ እድሎችን እና በተግባር እየሠሩ የመማር ልምዶችን ይቃኛሉ፤ ይህም የወደፊት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የሙያ አማራጮችን ማሰብ እንዲጀምሩ ይረዳቸዋል።

ልምምዱ በትምህርት ቀን MCPS Clever አማካኝነት የሚካሄድ ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ የሚሰጥ በመሆኑ ተማሪዎች ከፍላጎታቸው ጋር የሚጣጣሙ የሙያ ክላስተሮችን ለመዳሰስ ይጠቅማቸዋል። ቤተሰቦች በሚቀጥሉት ሳምንታት ከልጃቸው ትምህርት ቤት ተጨማሪ ዝርዝሮችን እና የጊዜ ሰሌዳ መረጃን ማግኘት አለባቸው።

 
  የሶስተኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ደብዳቤ–የመልእክት ሳጥንዎን ይመልከቱ

የትምህርት አመቱ ሊጠናቀቅ እየተቃረብን ስለሆነ፣ ተማሪዎ በትክክለኛው መንገድ ላይ መሆኑ(ኗ)ን ማረጋገጥ እንፈልጋለን። በሂሳብ እና/ወይም በንባብ ከክፍል ደረጃቸው በታች የሆኑ ተማሪዎች ያሏቸው ቤተሰቦች MCPS ይህንን መረጃ እና ወደ ትክክለኛው ደረጃ ለመድረስ መውሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች የሚገልፅ (በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የተጠቀሰውን መረጃ እና የተጠቀሰውን እርምጃ የያዘ) ደብዳቤ ደርሷቸዋል። ማሳሰቢያ፡- ደብዳቤው የሚላከው ተማሪዎ ከክፍል ደረጃ በታች ከሆነ(ች) ብቻ ነው። ደብዳቤ ለቤተሰብዎ ተልኮ እንደሆነ ለማወቅ እባክዎን ከሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተላከ ኢሜይል ላይ ያረጋግጡ። ለቤተሰብዎ ደብዳቤ ተልኮ ከሆነ፣ የልጅዎን እድገት እና የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ተጨማሪ እቅድ ወይም ድጋፍ ለመወያየት ወደ ትምህርት ቤቱ(ቷ) መደወል ይችላሉ።

 
  አንፀባራቂ ኮከብ ተማሪዎች

ሜይ 11 በሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተካሄደው 25ኛው አመታዊ የሱፐርኢንቴንደንት "All-County Visual and Performing Arts Celebration" ሥነ ስርአት ላይ በደርዘን የሚቆጠሩ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በዳንስ፣ በቲያትር ትርኢት፣ በቴክኒካል ቲያትር፣ በመዘምራን እና በሙዚቃ መሳሪያ፣ 2D እና 3D ቪዡዋ ስነጥበብ እና በሚዲያ አርት ላሳዩት ስኬት እውቅና ተሰጥቷቸዋል። 

በዝግጅቱ ላይ የቶማስ S. ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቲያትር፣ የኩዊንስ ኦርቻርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቲያትር እና ኦል-ካውንቲ የዳንስ ቡድን ትርኢቶችን አቅርበዋል። 

የፎቶ ጋለሪ እና እውቅና ያገኙትን በሙሉ ይመልከቱ

 
  አትዘግዩ፦ ዛሬውኑ ለመዋዕለ ሕፃናት ወይም ለቅድመ መዋዕለ ሕፃናት አስመዝግቡ

3 እስከ 5 ዓመት ዕድሜ ያላቸው እና MCPS ለመጀመር ዝግጁ የሆነ(ች) ልጅ ወላጅ ነዎት? የቅድመ—መዋዕለ ሕፃናት እና የሄድ ስታርት 4 ዓመት እድሜ ያላቸው ልጆች — እና አንዳንድ 3 ዓመት እድሜ ያላቸው ልጆች - በንባብ፣ በሂሳብ እና በማህበራዊ ልማት የመጀመሪያ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ ይረዷቸዋል። ብቁነት የሚወሰነው በእድሜ እና በቤተሰብ የገቢ መጠን ነው። ልጅዎ በሴፕቴምበር 1 እድሜው(ዋ) 5 ዓመት የሚሞላው/የሚሞላት ከሆነ፣ ለሙሉ ቀን ኪንደርጋርተን ይመዝገቡ። የማስመዝገቢያ ጊዜው አሁን ነው!

ስለ መዋእለ ህጻናት ምዝገባ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ

ስለ ቅድመ መዋዕለ ሕፃናት እና የሄድ ስታርት ምዝገባ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ

የቤተሰብ ተሳትፎ መምሪያ እና የወላጅ አካዳሚ ለኪንደርጋርተን ለሚዘጋጁ ቤተሰቦች የመረጃ አውደ ጥናቶችን እያዘጋጁ ናቸው። የቤተሰብ ተሳትፎ ባለሙያዎች (FESs) በሚቀጥለው የትምህርት አመት ምን መጠበቅ እንዳለባቸው፣ ከልጅዎ አስተማሪ እና ከትምህርት ቤት ሰራተኞች ጋር እንዴት መገናኘት እንደሚችሉ፣ የትምህርት ቀን እና የትምህርት ቤት ልምዶችን ናሙና፣ ትምህርት ቤት ስለመገኘት፣ የትምህርት ቤት ምግቦች፣ በቤት እና በትምህርት ቤት መካከል ስለሚኖር ግንኙነት እና የልጅዎን ትምህርት እንዴት መደገፍ እንደሚችሉ አጠቃላይ መግለጫ ይሰጣሉ።  

ረቡዕ፣ ሜይ 20 ከቀኑ 11 a.m. በኮሪያንኛ።

ረቡዕ፣ ሜይ 20 ከቀኑ 6 p.m. በእንግሊዝኛ፣ በስፓንሽኛ፣ በፖርቱጋልኛ፣ በቻይንኛ

ሰኞ፣ ሜይ 25 ከጠዋቱ 9 a.m. በቬትናምኛ

እዚህ ይመዝገቡ እና አውደ ጥናቱን ለመሳተፍ ሊንኩ ይላክልዎታል።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት እባክዎ፡ Department of Family Engagement በስልክ ቁጥር 240-740-4620 ወይም በዚህ ኢሜል Shannon_R_Flores@mcpsmd.org ይጠይቁ።

 
  ምን አዲስ ነገር እንዳለ ለማወቅ Special Ed Webinar/ልዩ ኢድ ዌቢናር ፕሮግራም አምልጦዎታል? ሪኮርድ የተደረገውን ይመልከቱ

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ፣ የልዩ ድጋፍ አገልግሎት ክፍል ቤተሰቦች በልዩ ትምህርት አገልግሎት፣ በሠራተኞች አደረጃጀት እና በሚሰጡ ድጋፎች ዙሪያ ምን አዲስ ነገር እንዳለ ለመወያየት የዌቢናር ፕሮግራም አካሂዷል። MCPS የልዩ ትምህርት መሪዎች ለውጦቹ ለትምህርት ቤቶች እና ለትምሕርት ክፍሎች ምን ማለት እንደሆኑ ወቅታዊ መረጃ ሰጥተዋል። ምናልባት ካመለጠዎት፣የዝግጅቱን የቪዲዮ ቀረጻ - በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛይመልከቱ። ጥያቄ & መልስ (Q&A) እንግሊዝኛ እናስፓንሽኛበስላይድ የቀረበ

 
  የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ሪፖርት የሚቀርብበት ቀነገደብ አርብ፣ ሜይ 29 ነው።

ከጁን 1, 2025 ጀምሮ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ያጠናቀቁ ተማሪዎች፣ አስፈላጊውን SSL ክንውን ማረጋገጫ ቅጽ ለትምህርት ቤታቸው SSL አስተባባሪ እስከ አርብ፣ ሜይ 29 ድረስ ማቅረብ አለባቸው።

ሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ 75 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል። የሠመር ዕረፍት ተማሪዎች SSL ለመሳተፍ በጣም አመቺ ጊዜ ነው! ስለ ዶኩመንቴሽን የበለጠ ግንዛቤ ይውሰዱ እና በአካል እና ቨርቹዋል SSL እድሎችን እዚህ ይቃኙ። ትርጉሞች እዚህይገኛሉ። ተማሪዎች/ቤተሰቦች ቅጾችን፣መመሪያዎችን እና ሌሎች ሪሶርሶችን MCPS SSL ቋት ላይ ማግኘት ይችላሉ። 

 
  ሂስፓኒክ አሊያንስ ለከፍተኛ የትምህርት ምሁራን እውቅና ሰጥቷል።

ሂስፓኒክ የትምህርት አሊያንስ (HAE) ሜይ 12 ቀን 27 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በ 30ኛው አመታዊ የሂስፓኒክ ምሁራን እውቅና አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ እውቅና ሰጥቷቸዋል። በዝግጅቱ ላይ ለተማሪዎች የአካዳሚክ ልህቀት፣ የአመራር ብቃት፣ እና ላበረከቱት የማህበረሰብ አገልግሎት አክብሮት ተሰጥቷቸዋል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ

 
  የልዩ ትምህርት ወላጆች፡ አስተያየታችሁን እንፈልጋለን

የልዩ ትምህርት ወላጆች፦ የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት መምሪያ (MSDE) ከእናንተ መስማት ይፈልጋል። MSDE በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ የልዩ ትምህርት እና ተዛማጅ አገልግሎቶችን የሚያገኙ ተማሪዎች ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ የሜሪላንድ ልዩ ትምህርት የወላጅ ተሳትፎ ዳሰሳ ጥናት ሞልተው እንዲያቀርቡ እየጠየቀ ነው። የዳሰሳ ጥናቱ የልጅዎ ትምህርት ቤት ከእርስዎ ጋር ምን ያህል በጥሩ ሁኔታ እየሰራ እንደሆነ ለማወቅ ወሳኝ ነው። የሚሰጡት መረጃ ስቴቱ በሕዝብ ትምህርት ቤቶች የሚካሄዱ ልዩ ትምህርትና ተዛማጅ አገልግሎቶችን ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት የሚያግዝ ነው።

የዳሰሳ ጥናቱን እስከ አርብ፣ ጁን 5 ድረስ ሞልተው ይመልሱልን።

ተሳትፎ የሚደረገው በፈቃደኝነት ሲሆን ማንነት ይፋ አይደረግም። አገልግሎቶችን ለሚያገኙ ለእያንዳንዱ ልጅ ወላጆች የተለየ የዳሰሳ ጥናት እንዲሞሉ ይጠየቃሉ።

 
  MCPS ጋር በፈቃደኝነት መሥራት ይፈልጋሉ?

ቤተሰቦች እና የማህበረሰብ አባላት በበጎ ፈቃደኝነት ትምህርት ቤቶችን ለመደገፍ የሚችሉበት ብዙ መንገዶች አሉ። አንዳንድ የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎቶች የበፊት ታሪክ/ዳራ ማጣራት ወይም የጣት አሻራ አያስፈልጋቸውም፣እነርሱም በዚህ ቻርት ላይ ያሉት የተለያዩ አማራጮች ተዘርዝረዋል። 

MCPS ከዳራ ማጣራት ወይም የጣት አሻራ ከመስጠት ወጪ ጋር በተያያዘ የገንዘብ ችግር ለሚኖርባቸው በጎ ፈቃደኞች የክፍያ እርዳታ ይሰጣል። ቤተሰቦች Title I ትምህርት ቤት የሚማር ልጅ ካላቸው ወይም የገንዘብ ችግር ያጋጠማቸው ከሆኑ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። ድጋፍ ለመጠየቅ የፋይናንስ ሰነዶችን ማቅረብ አያስፈልግም።

ስለ በጎ ፈቃደኛ አገልግሎት፣ የበፊት ታሪክ/ዳራ ማጣራት መስፈርቶች እና የክፍያ እርዳታ በሚመለከትMCPS የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ድረ ገጽ ላይ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።በተጨማሪ እነዚህን በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ጥያቄዎች ማንበብ ይችላሉ። 

 
  የትምህርት ጉዞዎን ያቀጣጥሉ - ለሠመር ትምህርት ቤት ይመዝገቡ

ዛሬውኑ ለሠመር ትምህርት ቤት ይመዝገቡ! MCPS በኢግናይት መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካዳሚ አማካኝነት በስድስት ማዕከሎች ላይ የሂሳብ እና የሊተርሲ ችሎታን የማዳበር ፕሮግራም ይሰጣል። ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ይኖራል፤ የትምህርት ሠዓት ካበቃ በኋላ ለሚሰጥ የእንክብካቤ አገልግሎት ክፍያ ይኖራል። ParentVueላይ ይመዝገቡ።

MCPS በአካል እና ቨርቹዋል የሠመር ትምህርት ፕሮግራም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ይሰጣል። የተማሪዎችን በራስ መተማመን በመገንባት እና የፈተና ጭንቀትን በመቀነስ ላይ ያተኮረ አዲስ ተመራጭ — የኮሌጅ ድርሰት ጽሑፍ እና የፈተና ዝግጅት ይመልከቱ። ይህ ኮርስ ከጁላይ 7-21 ወይም ከጁላይ 23 እስከ ኦገስት፤ ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋቱ 8 a.m.–2:30 p.m.,ይካሄዳል። 6. የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ለመመዝገብ ከካውንስለሮቻቸው ጋር መነጋገር አለባቸው።

ተጨማሪ መረጃ

 
  የህዝብ ትምህርት ስለሚኖረው ኃይል— ማወቅ ያለብዎት ጉዳይ

የሕዝብ ትምህርት ኃይል እንዲኖረው የሚያደርገው ምን እንደሆነ አስበውት ያውቃሉ? ሕዝቡ ነው። በየቀኑ፣ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰራተኞች ለዓመታት የማስተማር፣ የስልጠና እና ልምዶቻቸውን ወደ ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ይዘው ይመጣሉ። ተማሪዎች እንዲያድጉ እና ማህበረሰቦች እንዲበለጽጉ የሚያግዙ ጠንካራ ግንኙነቶችን ያስተምራሉ፣ ይደግፋሉ፣ እና ይገነባሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተከበረው የላቀ የትምህርት አገልግሎታችን ጋር ሲነጻጸር ለዚህ ምስጋና ከዚህ የተሻለ ማረጋገጫ የለም—ይኼውም ለውጥ የሚያመጡ ተማሪዎችን፣ ሰራተኞችን እና የማህበረሰብ አባላትን አክብሮት ለመስጠት መልካም እድል ሰጥቶናል። አምልጦታል? እዚህ ይመልከቱ.

Watch in English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese

 
  ማሳሰቢያ
  • ሕያው ቅርስ፡ ወጎችን መጠበቅ፣ Vien An Temple ቤተሰቦችን መደገፍ — AANHPI የቅርስ ወር አካል እንደመሆኑ፣ የትምህርት ቦርድ አባል ጁሊ ያንግ የቬትናም ማህበረሰብ ባህልን እንዴት እንደሚጠብቅ፣ ቤተሰቦችን እንደሚደግፍ እና በቋንቋ፣ በርህራሄ እና በአገልግሎት ግንኙነትን እንዴት እንደሚገነባ ለማሰስ "Vien An Temple" ቤተመቅደስን ይጎበኛሉ። Living Heritage የመጀመሪያውን ክፍል ይመልከቱ። 
  • ሕይወት ለማዳን ዝግጁ ነዎት?፦ ቅዳሜ፣ ጁን 6 በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከጠዋቱ a.m.-1 p.m. ድረስ MedStarHealth 3ኛ አመታዊ Bystander CPR አውደ ጥናት ላይ በእጅ ብቻ CPR እና AED እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ይወቅ። ይመዝገቡ/Register.
  • የልጆች የጎልፍ ውድድር ቅድመ ዝግጅት፡ ሰኞ፣ ጁን 8 በሞንትጎመሪ ካንትሪ ክለብ፣ John L. Gildner Regional Institute for Children and Adolescents ይካሄዳል።
 
  ለተማሪዎች የተዘጋጁ እድሎች
 
  አሁን ደርሷል፡ የጌትስበርግ የመጽሐፍት ፌስቲቫል ቅዳሜ፣ ሜይ 16 ነው

ለመጽሐፍ አፍቃሪዎች የፓርቲ ጊዜ ነው! 17ኛው ዓመታዊ የጌትስበርግ የመጽሐፍት ፌስቲቫል በዚህ ቅዳሜ ከጠዋቱ 10 a.m.-6 p.m. ጌትስበርግ በሚገኘው ቦኽረር ፓርክ ይካሄዳል።አድራሻ፦ Bohrer Park, 506 S. Frederick Avenue in Gaithersburg ፌስቲቫሉ የታላላቅ ደራሲዎች አውደ ጥናቶችን፣ የህፃናት መንደር፣ ደራሲያን የሚገኙበት፣ የመጽሐፍ ፊርማዎችን እና ውይይቶችን፣ የመጽሐፍ ሽያጭ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የግጥም ውድድር አሸናፊዎችን ያካትታል። ከ100 በላይ ደራሲያን እና ሥዕላዊ መግለጫዎች እንደሚቀርቡ ታቅዷል፤ ከእነዚህም ውስጥ የአሁንና የቀድሞ የሞንትጎምሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አስተማሪዎች ይገኙበታል። መግቢያ እና ከሼዲ ግሮቭ ሜትሮ እና ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፌርግራውንድስ የማመላለሻ አገልግሎት ነፃ ነው። 

 
  ከዜና ገፆቻችን
 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ Montgomery County Public Schools
©1995–2026 Montgomery County Public Schools