MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
MCPS Logo

አበይት ጉዳዮች

ኦክቶበር 15, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 
  ለመቀበል የሚከብደው እውነታ፡ እርጅና የተጫናቸው ትምህርት ቤቶች፣ እየቀነሰ የመጣው የተማሪዎች ምዝገባ እና እየጨመረ የመጣ ወጪ የካፒታል በጀቱን ይወስናሉ።

ዛሬ (ኦክቶበር 15) የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ በተመከረው የበጀት ዓመት (FY) 2028 የካፒታል በጀት እና በ2027-2032 የካፒታል ማሻሻያዎች ፕሮግራም (CIP) ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን በተመለከተ የመረጃ ሪፖርት አግኝቷል/ተቀብሏል። ፕሮፖዛሉ የሚያተኩረው የሁሉም ፕሮጀክቶች አጠቃላይ ግምገማ ላይ ሳይሆን አሁን ባለው የካፒታል ፕላን ላይ ባነጣጠሩ ማስተካከያዎች ላይ ነው። ፕረዘንቴሽኑ በጣም ሰፋ ያለ መልእክት አስተላልፏል፡ ለመቀበል የሚከብደው እውነት MCPS እርጅና የተጫናቸው ትምህርት ቤቶችን፣ እየቀነሰ የመጣው የተማሪዎች ምዝገባን እና እየጨመረ የመጣውን የግንባታ ወጪዎችን በተመለከተ ከባድ ውሳኔዎች ይገጥሙታል። ውስን በሆኑ ሪሶርሶች እና እየጨመረ በመጣው የመሠረተ ልማት ፍላጎት፣ ዲስትሪክቱ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ጤናማ እና ፍትሃዊ የሆነ የመማሪያና የስራ አካባቢ ለመፍጠር በፋሲሊቲዎቹ ላይ ኢንቨስት የሚያደርግበትን መንገድ እንደገና/መለስ ብሎ ማጤን ይኖርበታል። ምንም አለማድረግ አማራጭ አይደለም። ይበልጥ ያንብቡ።

 
  በ2027-2028 የትምህርት ዓመት የቀን መቁጠሪያ ላይ አስተያየት ለመስጠት አንድ ተጨማሪ ዕድል

MCPS የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ 2027-2028 (ካለንደር) እያዘጋጀ ስለሆነ፣ ዲስትሪክቱ ከእርስዎ ተጨማሪ አስተያየት ግብዓት ማግኘት ይፈልጋል!

ለ2027-2028 የትምህርት ዓመት በተመከረው ረቂቅ የተለመደ የቀን መቁጠሪያ ላይ ግብዓትን ለማጋራት እባክዎን ይህንን ሁለተኛ የዳሰሳ ጥናት ይሙሉ። የካላንደር ዝግጅቱን ሂደት ለማዳበር የእርስዎ ግብረመልስ አስፈላጊ ነው። MCPS የትምህርት ፍላጎቶችን፣ ለአሠራር አመቺ ሁኔታዎችን፣ በስቴት ህግ የተደነገጉ ትምህርት ቤቶች መዘጋት ያለባቸውን ጊዜያት፣ ዝቅተኛውን የትምህርት ቀናት እና የክሬዲት ሰዓት መስፈርቶችን ማሟላት፣ ከባድ የአየር ሁኔታ እና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎችን፣ የሰራተኞች የሙያ ማዳበር ቀናትን፣ እና ተማሪዎች ቀደም ብሎ የሚለቀቁባቸውን ቀናት ከግምገማ መርሃ ግብሮች ጋር በተሣለጠ ሁኔታ ይዘጋጃል። የዳሰሳ ጥናቱ አርብ፣ ኖቬምበር 6 ይዘጋል/ያበቃል።

የዳሰሳ #2 ን ይሙሉ

 
  ትምህርት ቤትን የመዝጋት እና የማጣመር ጥናት፡ የማህበረሰብ ውይይቶች ይጀምራሉ

የእናንተን አስተያየት መስማት ይጠቅማል፣ እና ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን! MCPS የአንደኛ ደረጃ እና የመለስተኛ ደረጃ ት/ቤት መዘጋትን እና መጣመርን የሚመለክት ጥናትን ማድረጉን በመቀጠሉ ቤተሰቦች፣ ሰራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት ይበልጥ እንዲማሩ፣ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ እና አመለካከታቸውን እንዲያጋሩ በቀጣይ የሚዘጋጁ የተሳትፎ ስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል። ይበልጥ ያንብቡ።

 
  የተማሪዎ የ2026 የስፕሪንግ ወቅት የ MCAP ውጤቶች አሉ

በ ELA፣ በሂሳብ፣ በሳይንስ (5ኛ እና 8ኛ ክፍሎች)፣ በ LS MISA፣ በስነ መንግስት ወይም በማህበራዊ ጥናቶች (8ኛ ክፍል) ላይ ለተሳተፉ ተማሪዎች የስፕሪንግ 2026 የሜሪላንድ አጠቃላይ ግምገማ ፕሮግራም (MCAP) የሚመለከት የተማሪዎን የግል ሪፖርት (ISR) በኤሌክትሮኒክ መንገድ በ Synergy ላይ ያገኙታል።

ISR ስለ ተማሪዎ አፈጻጸም እና የሜሪላንድ የአካደሚክ መስፈርቶችን ለማሟላት ስላሳየው/ችው እድገት መረጃ ይሰጣል። የልጅዎን ሪፖርት ለማየትወደሚከተለው ይግቡ ParentVUEውጤቶቹን በመረዳት ረገድ እርዳታ ያስፈልግዎታል? ለቤተሰብ ተስማሚ የሆኑ መመሪያዎችን ለማግኘት የMCPS MCAP ድረ ገጽን ይጎብኙ፣ ወይም እርዳታ ለማግኘት የልጅዎን ትምህርት ቤት ያነጋግሩ። በተጠየቀ ጊዜ የታተሙ ቅጂዎችም ይቀርባሉ።

 
  ቦርዱ በሁለት ፖሊሲዎች ላይ የህዝብ አስተያየት ይፈልጋል

የትምህርት ቦርድ በሁለት ፖሊሲዎች ላይ በቀረቡት ማሻሻያዎች ላይ የህዝብ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ይፈልጋል—ፖሊሲ IPD: ትምህርታዊ የጉዞ ፕሮግራሞች፣ የመስክ ጉብኝቶች እና የተማሪዎች ድርጅት ጉዞዎች እናፖሊሲ BLB: በይግባኝ እና በችሎት ሂደቶች ላይ ለሚደረጉት የአሰራር ደንቦች።

በ IPD ፖሊሲ ላይ የተደረጉ ረቂቅ ማሻሻያዎች ከኦክቶበር 9 ጀምሮ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ክፍት የነበሩ ሲሆን፣ አስተያየት የሚሰጥበት ጊዜም አርብ፣ ኖቬምበር 6 ይጠናቀቃል። በ IPD ፖሊሲ ላይ አስተያየቶችን ያቅርቡ።

በ BLB ፖሊሲ ላይ የተደረጉ ረቂቅ ማሻሻያዎች ከኦክቶበር 13 ጀምሮ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ክፍት የነበሩ ሲሆን፣ አስተያየት የሚሰጥበት ጊዜም አርብ፣ ኖቬምበር 6 ይጠናቀቃል።  በ BLB ፖሊሲ ላይ አስተያየቶችን ያቅርቡ።

የህዝብ አስተያየት ፖሊሲዎች

 
  የሂስፓኒክ ቅርሶችን በባህል፣ በምግብ እና በፈጠራ ማጋራት

ብዝሃነትን የሚያከብሩ የሂስፓኒክ ቅርስ ወር ዝግጅቶች በዚህ ወር በMCPS ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ቀጥለዋል። Col. Zadok Magruder ኮ/ል ዛዶክ ማግሩደር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች የእግር ኳስ ውድድርን፣ ምግብ የሚያቀርቡ መኪናዎችን እና ስነ ጥበባትን እና እደ-ጥበባትን አዘጋጅቷል።የሮቤርቶ ክሌሜንቴ መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት ፊየስታ ላቲና በስሙ የሚጠራውን አክብሯል እና የተማሪ ትርኢቶችን፣ እንቅስቃሴዎችን/ተግባሮችን እና ከማህበረሰቡ እና ከአካባቢው ንግዶች የተውጣጡ ተናጋሪዎችን አድምቋል። ተጨማሪ ያንብቡ እንዲሁም ፎቶዎችን ይመልከቱ።

 
  በስርዓተ ትምህርቱ ላይ ቅድመ እይታ በሚደረግበት ቀን (ኦክቶበር 19) ልጅዎ ምን እየተማረ እንደሆነ ያስሱ

በስርዓተ ትምህርቱ ላይ ቅድመ እይታ በሚደረግበት ቀን ይቀላቀሉን እና የማስተማሪያ ማቴሪያሎችን ያስሱ፣ ተማሪዎች የሚማሩትን ይወቁ እና በቤት ውስጥ የሚሰጥ ትምህርትን ለመደገፍ የቀረቡ ሪሶርሶችን ያግኙ። ይህ ዝግጅት ለሁሉም MCPS ትምህርት ዓይነቶች፣ ከመዋዕለ-ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል (K–12 ) ላሉ ቤተሰቦች ክፍት ነው። ሰኞ፣ ኦክቶበር 19 በካርቨር የትምህርት አገልግሎቶች ማዕከል ካፍቴሪያ ከ 11 a.m.-1 p.m. ወይም ከ 5-7 p.m.በሚዘጋጀው ቀጠሮ ሳያሲዙ መምጣት በሚችሉበት ክፍለ ጊዜዎች ላይ ይቀላቀሉን። ቤተሰቦች ከMCPS የትምህርት ስፔሻሊስቶች ጋር መገናኘት፣ ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ የሥርዓተ-ትምህርት ማቴሪያሎችን ማሰስ እና የዲጂታል ትምህርት ሪሶርሶችን ለማግኘት ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።

 
  የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማዕከል ፕሮግራሞች ማሳያዎች እስከ ኦክቶበር ወር መጨረሻ ድረስ ይቀጥላሉ

በስድስቱም ሪጅኖች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የፎል ወቅት ትርኢቶች እየቀጠሉ ሲሆን የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎችን እና ቤተሰቦችን በህክምና ሳይንስ፣ በአለም አቀፍ ባካሎሬት፣ በሰብአዊነት እና ቋንቋዎች ትምሕርት፣ STEM፣ በአመራር እና የሕዝብ አገልግሎት እና በተውኔት እና የስነጥበባት ትምሕርቶች ላይ ሰፋ ካሉ የክልል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የማዕከል ፕሮግራሞች ጋር ያገናኛሉ።

 
  በ Synergy ላይ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ለኦክቶበር 15 ቀጠሮ ተይዟል፡ ምን ይጠበቃል?

Synergy ሐሙስ፣ ኦክቶበር 15 ላይ ማሻሻያ ይደረግበታል። ይህም ለሁሉም ተጠቃሚዎች ቀለል ያለ መሆኑን ያረጋግጣል፣ ነገር ግን ማሻሻያው በሂደት ላይ እያለ የእረፍት ጊዜን ይፈልጋል። በተጨማሪም፣ ማሻሻያው እንደተጠናቀቀ የ iOS እና የ አንድሮይድ የድሮው ParentVUE እና StudentVUE መተግበሪያዎች መስራታቸውን ያቆማሉ።መተግበሪያዎችዎን ማዘመንዎን/አፕዴት ማድረግዎን እና የበፊቶቹን ስሪቶች ማጥፋትዎን ያረጋግጡ።አዲሱን የParentVUE መተግበሪያ እንዴት ማውረድ እንደሚችሉ ይወቁ 

ሲስተሙ ከሐሙስ ኦክቶበር 15, 9 p.m. እስከ አርብ ኦክቶበር 16 ከቀኑ 6 ሰዓት ድረስ አይሰራም።

  • ተጽዕኖ ያደረባቸው አፕሊኬሽኖች፡ Synergy SIS, TeacherVUE, ParentVUE and StudentVUE.
  • መጠንቀቅ ያለባችሁ ነገር፡ በዚህ ዊንዶ ወቅት ሲስተሞቹ ''የሚሰሩ'' ቢመስሉም ቀርፋፋ የመክፈቻ ጊዜያት ወይም ያልተጠበቁ መዘጋቶች ሊያጋጥምዎት ይችላሉ። ብስጭትን ለማስወገድ MCPS አፕዴቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ኦፍላይን እንዲቆዩ ይመክራል።
 
  በ«Game Changer» ኮንፈረንስ ላይ ያነሳሱ፣ ይምሩ እና ትልቅ ህልም ይኑራችሁ

ከ4-12ኛ ክፍል ያሉ ወንድ ተማሪዎች በሚቀጥለው አድራሻ፡ Germantown Campus, Bioscience Education Center, 20200 Observation Drive in Germantown በሞንትጎምሪ ኮሌጅ ኦክቶበር 24, ከ8 a.m.–ቀጥር በሚዘጋጀው በ2026 የስፕሪንግ Game Changer ኮንፍረንስ ለወጣት ወንዶች ጉባኤ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል። ይህ ዝግጅት ተማሪዎች እምቅ ችሎታቸውን እንዲገነዘቡ፣ ታላቅ ግቦችን እንዲያወጡ/እንዲያስቀምጡ፣ ሌሎችን እንዲያበረታቱ እና ህልማቸውን እውን ለማድረግ ስልታዊ እቅዶችን እንዲያዘጋጁ ያበረታታል። ያለው ቦታ ውስን ነው። ይመዝገቡ/Register.

 
  ተዘጋጅ፣ በቦታ፣ ኮሌጅ!

ለኮሌጅ እየተዘጋጁ ነው? FAFSA-readyን ያግኙ፣ የሜሪላንድን የግል ኮሌጅ እና ዩኒቨርሲቲዎችን ያስሱ እና ለኮሌጅ ሲያቅዱ ያለውን ሂደት በልበ ሙሉነት እያሰሱ ማመልከቻዎችን፣ የፈተና ዝግጅትን የኮሌጅ ሜጀሮችን እና ስራዎችን የሚመለከቱ ጠቃሚ ምክሮችን ያግኙ።

  • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲንየር ተማሪዎች ያሏቸው ወላጆች፦ 2027-2028 ለተማሪዎች የፌዴራል የገንዘብ ድጋፍ (FAFSA) ማመልከቻ ቅጽ ሞልተው ለማቅረብ አሁን ክፍት ነው። FAFSAን ከመሙላታቸው በፊት፣ ተማሪዎች እና አስተዋጽኦ አበርካቾች (ለምሳሌ ወላጅ ወይም የትዳር አጋር —አስፈላጊ ከሆነ) የFSA ID ማውጣት አለባቸው፤ ይህም መለያ ወደ FAFSA ለመግባት እና ሰነዱን ለመፈረም እንደ የተጠቃሚ ስም (username) እና የይለፍ ቃል (password) ያገለግላል። የ FSA ID ገና ያላወጡ ቤተሰቦች መዘግየቶችን ለማስቀረት በተቻለ ፍጥነት እንዲያወጡ ይበረታታሉ። ስለ FAFSA ወይም ስለ ፋይናንሻል ኤይድ (የገንዘብ ድጋፍ) ሂደት ጥያቄዎች ካሎዎት፣ የኮሌጅ እና የሙያ መሪዎን (College & Career Navigator - CCN) ወይም የትምህርት ቤት አማካሪዎን ያነጋግሩ።
  • ለሜሪላንድ ስቴት የገንዘብ ድጋፍ ለመጀመሪያ ጊዜ እያመለከቱ ነው? በቅርብ ጊዜ ከሜሪላንድ ከፍተኛ ትምህርት ኮሚሽን (MHEC) በተሰጠው መመሪያ መሰረት፣ የመጨረሻ ዓመት ተማሪዎች በዚህ ጊዜ የMDCAPS አካውንት ማውጣት/መክፈት የለባቸውም። ተማሪዎች በሜሪላንድ የተማሪ መረጃ ስርዓት (MDSIS) በኩል አካውንት ይፈጥራሉ፣ ይህም MHEC ጃንዋሪ ወር ላይይኖራል ብሎ ይገምታል።
  • የተመዘገቡ የሰመር ወቅት የኮሌጅ እና የሙያ ወርክ ሾፖች፡በዚህ ሰመር ወቅት፣ CCNs የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ፣ ለኮሌጅ እና ለሙያ ዝግጁነት የሚሆኑ በርካታ ወርክሾፖችን አዘጋጅተዋል። የተዳሰሱት ርዕሶች የድርሰት አጻጻፍ፣ የፋይናንስ እርዳታ፣ የተለመዱ የመተግበሪያ ምክሮች፣ የፈተና ዝግጅት፣ AI ን በኮሌጅ መተግበሪያዎች ላይ መጠቀም፣ የሥራ/የሙያ ዕቅድ ማውጣት፣ የ NCAA ምልመላ እና ሌሎችም ነበሩ። በተመቻቸዎት ጊዜ ይመልከቱዋቸው። 
  • የግል ኮሌጅ የማመልከቻ ቀናት፡ ከሜሪላንድ የግል ኮሌጆች ወይም ዩኒቨርሲቲዎች በአንዱ የወደፊት ህይወትዎን ለማሰስ ዝግጁ ነዎት? ኦክቶበር 22 እና ኖቬምበር 9 ላይ ምንም ዓይነት የማመልከቻ ክፍያ ሳይከፍሉ ለሜሪላንድ የግል ኮሌጅ ያመልክቱ።
 
  አሁን ማወቅ ያለብዎት — የትምህርት ቤት ምግቦች

የMCPS የምግብ እና የአመጋገብ አገልግሎቶች ክፍል በየዓመቱ ከ18 ሚሊዮን በላይ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምግቦች ያቀርባል። የምግብ ዝርዝሮቹ የተዘጋጁት ፈቃድ ባላቸውና በተመዘገቡ የስነ ምግብ ባለሙያዎች ሲሆን የሀገር ውስጥ የተለያዩ የማህበረሰባችንን የምግብ ጣዕም እና አለም አቀፍ የምግብ ጣዕም ያላቸው የምግብ አይነቶችን ያካትታሉ። የምግብ ዝርዝሮቹ የስነ አመጋገብ መመሪያዎችን የሚከተሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የተገዙ ምግቦች፣የምግቦቹ ንጥረ ነገሮች እና የአዘገጃጀት ዘዴዎች ይገመገማሉ። ቁርስ ወይም ምሳ የሚበላው ምንድን ነው? የትምህርት ቤትዎን ሜኑዎች ከሥዕሎች እና ከአመጋገብ መረጃ ጋር ያግኙ።

ይበልጥ ግንዛቤ ያግኙ፦እንግሊዝኛ/English | ስፓንሽኛ/Spanish |አማርኛ/Amharic | Chinese | French | Korean | Portuguese | Vietnamese

 
  ወደ ስፖርት ጨዋታ ይግቡ፡ የዊንተር ስፖርቶች ምዝገባ አሁን ተከፍቷል

ለዊንተር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አትሌቲክስ የሚደረገው ምዝገባ በParentVUE በኩል አሁን ክፍት ነው።

ተማሪዎ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን/መሆኗን ያረጋግጡ፡

  • አሁኑኑ አካላዊ ምርመራ ያድርጉ፡በሙከራዎች ወይም ልምዶች ላይ ከመሳተፋቸው በፊት ተማሪዎች የተሟላ የቅድመ-ተሳትፎ አካላዊ ምርመራ (MCPS ቅጽ SR-8) በፋይል ላይ ሊኖራቸው ይገባል። የሕክምና ብቁነት ምርመራው ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ለ 13 ወራት ያገለግላል እና በዚያ ጊዜ ውስጥ ያሉ ሁሉንም የስፖርት ዓይነቶች ይሸፍናል።
  • ParentVUEን ለማግኘት ተቸግረዋል?ወደ ParentVue መግባትን አስመልክቶ መረጃ የሚያስፈልጋቸው ወላጆች/አሳዳጊዎች የትምህርት ቤታቸውን ሬጅስትራር (registrar) ማነጋገር አለባቸው።
  • ለወቅቱ/ለሲዝኑ ይዘጋጁ፡ የዊንተር ስፖርት ሙከራዎች እና ልምዶች ኖቬምበር 15 አካባቢ ሊጀምሩ ይችላሉ። እባክዎን ስፖርትን የሚመለከቱ መረጃዎችን እና መርሃ ግብሮችን ለማግኘት የትምህርት ቤትዎን የአትሌቲክስ ክፍል ድህረ ገጽን ይመልከቱ።

ለወንዶችና ለሴቶች የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቅርጫት ኳስ ውድድር ምዝገባ የሚጀምረው ሰኞ፣ ኦክቶበር 26 ቀትር ላይ ነው።

 
  ማሳሰቢያዎች፦
  • የማርቺንግ ባንድ ትርዒት፡ ቅዳሜ ኦክቶበር 24 በ 11:30 a.m በአልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይጀምራል። ጻ እና ለህዝብ ክፍት የሆነ።
  • የሜሪ ሃዋርድ የአገልግሎት ቀን፡ ቅዳሜ ኦክቶበር 24 ከ 8 a.m.-1 p.m። ፕሮጄክቶቹ የአትክልት ቦታዎችን እና ድንኳኖችን ማስዋብን፣ ዱካዎችን መንከባከብን እና የግንባታ ፕሮጀክቶችን ያካትታሉ። ይመዝገቡ/RSVP.  
  • የአእምሮ ጤና እና ደህንነት ኤግዚቢሽን፡ ቅዳሜ ኖቬምበር 14 በጄምስ ሀበርት ብሌክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ 10 a.m.-1 p.m። ነፃ እና ለሰራተኞች፣ ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች ክፍት ነው።
 
  ከመማሪያ ክፍል ውጭ
  • *አዲስ*የ C-SPAN StudentCam ዘጋቢ ፊልም ውድድር፡ ከ6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በC-SPAN ዓመታዊ የቪድዮ ዶክመንተሪ StudentCam ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፣ ይህም ማህበረሰባችን ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድሩ ጉዳዮች በጥልቀት እንዲያስቡ ያበረታታል። በዚህ አመት ተማሪዎች ከውድድሩ ጭብጥ ጋር የሚገናኝ ርዕስ ላይ ከአምስት እስከ ስድስት ደቂቃ የሚፈጅ የቪዲዮ ዶክመንተሪ ሠርተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል፣ የውድድሩ ጭብጥም“Mr. Speaker, I Rise To …”. የመጨረሻ ቀን፡ ረቡዕ፣ ጃንዋሪ 20, 2027።
  • የቪዲዮ ውድድር፦ "ድምጽዎን ያሰሙ፣ ህይወትን ይታደጉ" - በታዳጊዎች ዘንድ እየተስፋፋ ስላለው ህገ-ወጥ ኦፒዮይድስ፣ ከመጠን በላይ ስለመውሰድ (overdose) እና ስለ ፌንታኒል (fentanyl) አደጋዎች ግንዛቤን የሚያሳድግ ኦሪጅናል የቪዲዮ ውድድር ያዘጋጁ። የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች 10 የተማሪ አገልግሎት/ SSL ሰዓቶች ማግኘት ይችላሉ። ቪዲዮዎችን በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ማቅረብ ይቻላል። አንደኛ ለወጣ $5,000፣ ለሁለተኛ $3,000 እና ለሦስተኛ $1,000 ሽልማት ይሰጣል። የመጨረሻው ቀን ሰኞ፣ ኖቬምበር 30ነው።መወዳደሪያውን ያቅርቡ።
  • ለአሜሪካ ያለዎትን ራዕይ ያጋሩ፡ ከ5ኛ-12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች አሁን ፕሬዝዳንት ሆነው እንደተመረጡ እና የመክፈቻ ንግግራቸውን በ2-3 ደቂቃ ቪዲዮ እያቀረቡ እንደሆነ እንዲያስቡ የንግግር ጥሪዎን ያቅርቡ። እስከ 1,000 ዶላር የሚደርሱ ሽልማቶችን ያሸንፉ። የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ። መወዳደሪያው መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን፦ አርብ፣ ኦክቶበር 30ነው።
  • የ Smokey Bear ፖስተር ውድድር፡የሜሪላንድ ደን አገልግሎት ለ7ኛ ክፍል ተማሪዎች የእሳት መከላከል ወር Smokey Bear ፖስተር ውድድር ስፖንሰር እያደረገ ነው። ተማሪዎች "የዱር ሰደድ እሳትን መከላከል የሚችሉት እርስዎ ብቻ ነዎት!"/“Only YOU can prevent wildfires!” የሚለውን ታዋቂ መልእክት መነሻ በማድረግ ኦሪጅናል የጥበብ ሥራ ፈጥረው እንዲወዳደሩ ተጠይቀዋል። የዱር ሰደድ እሳት ደህንነትን እና የደን ጥበቃን ለመዳሰስ የመጨረሻው ቀን፦ ሰኞ፣ ኖቬምበር 2ነው።የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።
  • Capital Weather ከመዋእለ ህጻናት እስከ 8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን፣ ስለ አየር ሁኔታ፣ ስለ ወቅቶች፣ ስለ አየር ንብረት ወይም በተፈጥሮ ተመስጠው የፈጠሯቸው ኦርጅናል ስራዎችን ለልጆች የጥበብ ማሳያ ዝግጅት እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።
 

ዜና አምድ

 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

ከሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) የበለጠ መረጃ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች
©1995–2026 Montgomery County Public Schools