አበይት ጉዳዮች
ኖቨምበር 05, 2026
|
|
|
ሀሳብዎን ይግለጹልን! በመላው ዲስትሪክት ውስጥ የሚካሄደው ባህልና ድባብ የዳሰሳ ጥናት ኖቨምበር 8 ይጀመራል |
|
ቤተሰቦች፣ ሰራተኞች፣ እና ተማሪዎች በመጪው የዲስትሪክት አቀፍ ባህል እና ድባብ የዳሰሳ ላይ በመሳተፍ አስተያየት እንዲሰጡ ተጋብዘዋል። የምትሰጡት አስተያየት፣ በዲስትሪክት ደረጃ የሚከናወኑ ፕሮግራሞችን፣ አገልግሎቶችን፣ እና ድጋፎችን ለማጠናከር የምናደርገውን ጥረት ለመቃኘት የሚያግዝ ሲሆን፤ የትኞቹ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየተከናወኑ እንዳሉ እና የትኞቹ ላይ መሻሻል እንደሚያስፈልግ ጠቃሚ ግንዛቤ ይሰጣል። ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
|
|
|
ለተማሪዎች ስኬት በጋራ መስራት |
|
ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ያሏቸው ወላጆች፣ ልጆቻቸው ያሳዩትን እድገት መግለጫ እና የመጀመሪያው የትምህርት ውጤት መግለጫ ሪፖርት ካርድ በቅርቡParentVueላይ ያገኛሉ። ሪፖርቶቹ ልጅዎ በንባብ እና/ወይም በሂሳብ ያሳየ(ች)ውን እድገት አጭር መግለጫ ይሰጣሉ።
ማሳሰቢያ፦ አንዳንድ ወላጆች፣ ልጆቻቸው የዓመቱ መጨረሻ የትምህርት መስፈርቶችን የማያሟሉበት ሁኔታ ስለሚኖር፣ ደብዳቤ ይደርሳቸዋል። ደብዳቤው ላይ ልጅዎን በቤት ውስጥ ለመደገፍ የሚረዱ ስልቶች ተገልጸዋል።
ኖቬምበር 23 እና 24 የሚካሄዱት የወላጅና መምህራን ውይይቶች፣ ስለ ልጅዎ የትምሕርት እድገት ሁኔታ ለመነጋገር እንዲሁም ለማሻሻል የሚያስችል እቅድ በጋራ ከመምህራን ጋር ለማዘጋጀት ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥራሉ። ይበልጥ ያንብቡ.
|
|
|
|
|
|
MCPS ብዝሃ ቋንቋ ተናጋሪ ቤተሰቦችን በልዩ ዝግጅቶች ላይ እንዲሳተፉ ይጋብዛል |
|
MCPS፣ አዳዲስ ብዝሃ ቋንቋዎችን የሚማሩ ተማሪዎችን (EMLs) እና ቤተሰቦቻቸውን በስድስት ዙር የሚካሄዱ ሪጅናል የቤተሰብ ተሳትፎ መርሐ ግብሮችን በማዘጋጀት ቤተሰቦችን አንድ ላይ ያሰባስባል። እነዚህ ከክፍያ ነጻ የሆኑ ዝግጅቶች፣ ቤተሰቦች ከትምህርት ቤት ሰራተኞች ጋር እንዲገናኙ፣ ስለ MCPS ፕሮግራሞች እና የማህበረሰብ ግብዓቶች መረጃ እንዲያገኙ፣ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ እና ከሌሎች ቤተሰቦች ጋር የመተዋወቅ እድል ይሰጣሉ። ልጆችዎ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤት፣ በመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ወይም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ቢሆኑም፣ ለሁሉም የሚሆን ጠቃሚ ነገር አለ! ይበልጥ ያንብቡ.
|
|
|
|
|
|
ቀነ ገደቡ ተራዝሟል፦ MCPS 8ኛ ክፍል ለሴንተር ፕሮግራሞች እና ለመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማግኔት ኮንሶርቲየም የሚቀርቡ ማመልከቻዎች የመጨረሻ ቀን ተራዝሟል። |
|
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመቀጠል ትክክለኛውን መንገድ መምረጥ ለቤተሰብ ትልቅ ውሳኔ መሆኑን እናውቃለን! የተለያዩ አማራጮችን ለመቃኘት፣ ስላሉት ፕሮግራሞች በዝርዝር ለመረዳት፣ እና ማመልከቻዎን አዘጋጅቶ ለማቅረብ ተጨማሪ ጊዜ እንዲያገኙ፣ 8ኛ ክፍል ሴንተር ፕሮግራሞች (8th Grade Center Programs) እና ለመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ማግኔት ኮንሰርትየም/Middle School Magnet Consortium (MSMC) ማመልከቻ መቅረብ ያለበት የመጨረሻው ቀን ተራዝሟል።
አዲሱ የመጨረሻ ቀን፡ አርብ፣ ኖቨምበር 13ነው።
MCPS ሪጅናል እና ትምህርትን፣ ምርምርን፣ ወይም ተግባራትን ከተናጠል የትምህርት ዘርፎች ይልቅ፣ ሁሉንም በአንድ ላይ በሚያገናኝ ማዕከል ማደራጀት ላይ ያተኮሩ ፕሮግራሞች እንዴት እንደተደራጁ ለመረዳት፣ ልዩ የሙያ መስኮችን በጥልቀት ለመዳሰስ የሚያስችሉ ግብዓቶችን ለማግኘት፣ እንዲሁም በተደጋጋሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች (FAQs) መልስ ለማግኘት፤ Center Programs websiteየሚለውን ድረ-ገጽ ይጎብኙ። በመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ማግኔት ኮንሰርትየም (MSMC) ፍላጎት ያላቸው ቤተሰቦች ዝርዝር መረጃ MSMC ድረ-ገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
|
|
|
|
ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ… |
|
ኖቬምበር 4፣ ስለ ጦር መሳሪያ ደህንነት አጠባበቅ፣ ተተኳሽ መሳሪያዎችን በአስተማማኝ ሁኔታ በጥንቃቄ ስለማስቀመጥ፣ እና ይህንን በተመለከተ በቤተሰብ ውስጥ መደረግ ስላለበት ውይይት ለቤተሰቦች መልእክት ተልኳል። አምልጧችሁ ከሆነ እዚህ ማንበብ ትችላላችሁ።
|
|
|
|
|
|
ኖቬምበር 9 በሚካሄድ የዙም/Zoom ዌቢናር ላይ ስለ "Amplify Desmos Math Curriculum" የሂሳብ ሥርዓተ ትምህርት የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ። |
|
ስለ ተማሪዎ አዲስ "Amplify Desmos Math curriculum" የሒሳብ ሥርዓተ ትምህርት የበለጠ ለማወቅ ይፈልጋሉ? MCPS ሰኞ፣ ኖቨምበር 9 ቀን ከሠዓት በኋላ 6 እስከ 7 p.m. ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቤተሰቦች ዙም/Zoom ላይ የኦንላይን ስብሰባ (webinar) ያዘጋጃል።
ይህ በዌብናር የሚሰጥ ሴሚናር፤ ስለ ዕለታዊ ትምህርት አወቃቀር፣ ተጨማሪ የትምሕርት ማበልፀግ ተደራሽነት፣ ለቤተሰቦች የተዘጋጁ «Caregiver Hub»ግብዓቶችን እና የቤት ሥራን በተመለከተ ዳሰሳ ይቀርባል። ዌቢናሩ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚቀርብ ሲሆን፤ በስፓንሽኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በአማርኛ፣ በቻይንኛ፣ በፖርቹጋልኛ፣ እና በአሜሪካ የምልክት ቋንቋ የቀጥታ ማስተርጎም አገልግሎት ይሰጣል።
መገኘት አይችሉም? ከዝግጅቱ በኋላ ሪከርድ የተደረገው MCPS ድረ-ገጽ ላይ ይለጠፋል።
|
|
|
|
|
|
ኖቬምበር 14 በሚካሄደው ስለ አእምሮ ጤንነት እና ደህንነት ኤግዚቢሽን ላይ ከእኛ ጋር ይሳተፉ። |
|
ቅዳሜ፣ ኖቬምበር 14 ከጠዋቱ 10 a.m.-1 p.m. ሲልቨር ስፕሪንግ በሚገኘው ጄምስ ሂውበርት ብሌክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚካሄደው የአእምሮ ጤና እና ደህንነት ኤግዚቢሽን ከእኛ ጋር ይሁኑ።
አድራሻ፦ James Hubert Blake High School, 300 Norwood Road in Silver Spring ለሰራተኞች፣ ለተማሪዎች፣ እና ለቤተሰቦቻቸው በነጻ ክፍት የሆነው ይህ መርሐ ግብር፤ የተለያዩ ወርክሾፖችን፣ በተማሪዎች የሚመራ መድረክን እንዲሁም ስለ አእምሮ ጤና እና ደህንነት መረጃ የሚያጋሩ የማህበረሰብ አጋሮችን ያካተተ ይሆናል። ተሳታፊ ተማሪዎች አራት የተማሪዎች አገልግሎት-ትምህርት ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።
|
|
|
|
|
|
በክፍላቸው ከፍተኛ፡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) ኮከቦቹ አንፀባራቂ ሆነዋል። |
|
'U.S. News & World Report' በሜሪላንድ ስቴት ውስጥ የሚገኙ ምርጥ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችንእና ምርጥ የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን2027 ዓ.ም ደረጃ ይፋ አድርጓል። MCPS ከፍተኛ ደረጃ 25 ምርጥ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 12 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች (ኤለመንተሪ ስኩልስ)፣ እንዲሁም ከ 100 ምርጥ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 40 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አሉት። MCPS ከፍተኛ ምርጥ 25 ትምህርት ቤቶች ውስጥ አምስት የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች (ሚድል ስኩልስ)፣ እንዲሁም ከምርጥ 100 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 15 የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች (ሚድል ስኩልስ) አሉት። ዝርዝሩን ይመልከቱ/See the lists።
|
|
|
|
|
|
መራራው ሐቅ/እውነት፦ መሠረተ ልማት፣ ወጪዎች፣ እና የካፒታል ኢንቨስትመንት ዕቅድ (CIP) |
|
MCPS የበጀት ዓመት 2028 የካፒታል በጀት ረቂቅ እንዲሁም 2027 እስከ 2032 ያለውን የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም (CIP) ማሻሻያዎችን በመገምገም ላይ እያለ፣ ዲስትሪክቱ እጅግ አስቸጋሪ ውሳኔዎችን መጋፈጥ ግድ ሆኖበታል። መራራው ሐቅ/እውነት ፦ መሠረተ ልማቶቻችን አርጅተዋል፤ ውጤታማም አይደሉም። ወጪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል፤ የአውቶቡስ መናኸሪያዎቻችን ከአቅማቸው በላይ ተጨናንቀዋል።
ስለ "The Hard Truth" ቪዲዮዎችን ይመልከቱ።
|
|
|
|
|
|
በሜሪላንድ የተናጠል ኮሌጆች/Maryland Independent Colleges በቦታው ላይ የኮሌጅ መግቢያ ውሳኔ ያግኙ። |
|
አርብ፣ ኖቨምበር 20 እና አርብ፣ ዲሰምበር 4፣ MCPS ከበርካታ የሜሪላንድ ተናጠል ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር፣ ተማሪዎች በቦታው ላይ ፈጣን የመግቢያ ውሳኔ የሚያገኙባቸውን ዝግጅቶች ያካሄዳል። በእነዚህ ዝግጅቶች ወቅት፣ ወደ ትምህርት ተቋሙ ለመግባት የሚፈልጉ ተማሪዎች ከኮሌጅ ምዝገባ ኃላፊ ጋር መገናኘት እና የነጻ ትምህርት ዕድል (ስኮላርሺፕ) ጭምር፣ ስለ ኮሌጅ ምዝገባቸው ፈጣን ውሳኔ ማግኘት ይችላሉ። ቃለ መጠይቆች ዙም/Zoom ላይ በኦንላይን ይካሄዳሉ። ጥያቄዎች ካሉዎት የልጅዎን የኮሌጅ እና የስራ መስክ ናቪጌተር (College & Career Navigator - CCN) ያነጋግሩ። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ
|
|
|
|
|
|
መታሰቢያ እና እርቅ የሚዘከርበት ወር |
|
በኖቬምበር ወር፣ MCPS ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የመታሰቢያ እና የእርቅ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ታሪካዊ የጥቁር ማህበረሰቦች በከተማ እድሳት ምክንያት ስላጋጠሟቸው ለውጦች በሶስት ክፍለጊዜ የዌቢናር ተከታታይ ፕሮግራሞችን እያዘጋጀ ነው። ሌሎችም በቅርቡ የሚከናወኑ «የነጻነት ቀን» (Emancipation Day) ዝግጅቶች አሉ፤ ተማሪዎች በእነዚህ ዝግጅቶች ላይ በመገኘት እንደ «ማህበረሰብ አገልግሎት ትምህርት» የሚቆጠሩ ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
|
ምቾት የሚሰማቸውን ትምህርት ቤቶች መገንባት እና ብዝሃ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ቤተሰቦችን ስለማሳተፍ፡ አዲሱን EdTalk ይመልከቱ። |
|
ቅርብ ጊዜ በተዘጋጀው EdTalk ፕሮግራም ላይ የትምህርት ቦርድ ፕሬዝዳንት ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን (Grace Rivera-Oven) እና ርእሰ መምህራን አሊሲያ ዲኒ (Alicia Deeny) (ከሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) እና ኢዛቤል ሜንሳህ ( Isabelle Mensah) (ከሮሊንግ ቴራስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) በትምህርት ቤቶቻቸው እንዴት ምቹ አካባቢን እንደሚፈጥሩ፣ ተማሪዎችን እንዴት እንደሚያሳትፉ፣ እና ለብዝሃ ቋንቋ ተናጋሪ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች የቤተሰብ ተሳትፎን እንዴት ከፍ እንዳደረጉ ይወያያሉ። EdTalk ይመልከቱ | Vea Educacion al Día
ሁሉንም EdTalk እና Educación al Día ውይይቶች Apple Podcasts፣ Spotify ወይም የሚወዷቸውን ፖድካስቶች በሚያዳምጡበት በማንኛውም መድረክ ማዳመጥ ይችላሉ።
|
|
|
|
|
|
ማሳሰቢያዎች፦ |
- ካውንቲአቀፍ ዳይቪንግ አሰልጣኝ ይፈለጋል፦ ለሚመጣው MCPS የክረምት ወቅት (ኖቨምበር 14 እስከ ፌብሩዋሪ 10, 2027)። ሚናው(ዋ) በካውንቲው የዋና ውሃ/county aquatic facilities (ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር) ሶስት ሳምንታዊ 90 ደቂቃ ልምምዶችን መምራትን ያካትታል። የውኃ ዋና ማዕከል፣ የጌትስበርግ የውሃ ዋና ስፖርት ማዕከል እና የጀርመንታወን የቤት ውስጥ የውኃ ዋና ማዕከል)። ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች MCPS Careers ላይ ማመልከት አለባቸው። ለጥያቄዎች፣ ወደ Kathy Green ኢሜል ይላኩ።
- የአውቶቡስ ሹፌሮች የስራ ቅጥር አውደ ርዕይ፦ MCPS ውስጥ ለመስራት ፍላጎት ያለው ሰው ያውቃሉ? የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍል (Division of Transportation Services)፣ አርብ፣ ኖቬምበር 6፣ ከጠዋቱ 10፡30 a.m. እስከ 1 p.m. በሚከተለው አድራሻ የሥራ አውደ ርዕይ ያዘጋጃል።
አድራሻ፦ Shady Grove Transportation Depot, 16651 Crabbs Branch Way, Rockville
- የህዝብ አስተያየት እንዲሰጥባቸው የቀረቡ ፖሊሲዎች፦ለትምህርት ቦርድ ፖሊሲዎች የህዝብ አስተያየቶችን የማቅረቢያ ጊዜ IPD:የትምህርት ጉዞ ፕሮግራሞች፣ የመስክ ጉብኝቶች፣ እና የተማሪዎች ድርጅት ጉዞዎች እና BLB: በይግባኝ እና በችሎት ሂደቶች ላይ የሚተገበሩ የአሰራር ደንቦች፣ ዓርብ፣ ኖቨምበር 6 ይዘጋል። አስተያየት ያቅርቡ፦ IPD | BLB.
|
|
|
|
|
|
ከደወል ባሻገር |
- *አዲስ* MoCo EmpowHER Passion for Action፦ የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ ረቡዕ፣ ኖቨምበር 11 ከሠዓት በኋላ 6 እስከ 8 p.m. በሚከተለው አድራሻ የሚካሄደውን ዝግጅት እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።
አድራሻ፦ Carver Educational Services Center, 850 Hungerford Drive in Rockville. ይህ በተግባቦት የሚከወን ዝግጅት፤ በተግባር የሚከናወኑ የዕደ-ጥበብ ሥራዎችን፣ በዚህ ዘመን ሴት ተማሪዎችን የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ውይይቶችን ማድረግ እና የግጭት አፈታት ዘዴ አውደ ጥናትን ያካትታል። ይመዝገቡ/Register.
- *አዲስ* KID ሙዚየት BioInnovation Day: እሑድ፣ ኖቨምበር 15 ቀን ከጠዋቱ 10 a.m.-4 p.m. ይካሄዳል። በራሪ ወረቀቱ ላይ ባላእው QR ኮድ ወይም እዚህ በቅድሚያ ለሚመዘገቡ ቤተሰቦች አጠቃላይ የመግቢያ ክፍያ ነፃ ነው
- ሁሉም የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለዘንድሮው የትምህርት አመት ከትምህርት ውጭ የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎቻቸውን በሚመለከት ዝርዝሮቻቸው ላይ የመጨረሻ ማሻሻያዎችን አድርገዋል። ዝርዝሩ እዚህ ይገኛል።
- የC-SPAN 'StudentCam Documentary Competition' ዶክመንተሪ ውድድር፡ 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች፣ C-SPAN በየዓመቱ በሚዘጋጀው እና ማህበረሰባችንን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በጥልቀትና በሂሳዊ አስተሳሰብ እንዲያስቡ በሚያበረታታው፣ ብሔራዊ የቪዲዮ ዶክመንተሪ ውድድር (StudentCam) ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። በዚህ አመት ተማሪዎች ከውድድሩ ጭብጥ ጋር የሚገናኝ ርዕስ ላይ ከአምስት እስከ ስድስት ደቂቃ የሚፈጅ የቪዲዮ ዶክመንተሪ ሠርተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል፣ የውድድሩ ጭብጥም“Mr. Speaker, I Rise To …”. የመጨረሻ ቀን፡ ረቡዕ፣ ጃንዋሪ 20, 2027።
- የቪዲዮ ውድድር፦ "ድምጽዎን ያሰሙ፣ ህይወትን ይታደጉ" - በታዳጊዎች ዘንድ እየተስፋፋ ስላለው ህገ-ወጥ ኦፒዮይድስ፣ ከመጠን በላይ ስለመውሰድ (overdose) እና ስለ ፌንታኒል (fentanyl) አደጋዎች ግንዛቤን የሚያሳድግ ኦሪጅናል የቪዲዮ ውድድር ያዘጋጁ። የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች 10 የተማሪ አገልግሎት/ SSL ሰዓቶች ማግኘት ይችላሉ። ቪዲዮዎችን በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ማቅረብ ይቻላል። አንደኛ ለወጣ $5,000፣ ለሁለተኛ $3,000 እና ለሦስተኛ $1,000 ሽልማት ይሰጣል። የመጨረሻው ቀን ሰኞ፣ ኖቬምበር 30ነው። መወዳደሪያውን ያቅርቡ።
|
|
|
|
|
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የምስጋና በዓል 'Thanksgiving Parade' የሰልፍ ትርኢት ለማሳየት በጎ ፈቃደኞችን ይፈልጋል |
|
የሠልፍ ትእይንትን የማይወድ ማነው?
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ዓመታዊ የምስጋና በዓል የሰልፍ ትርኢት (Thanksgiving Parade) ቅዳሜ፣ ኖቨምበር 21 ቀን፣ ከጠዋቱ 10 a.m. ጀምሮ ይካሄዳል። በሰልፉ ላይ የሙዚቃ ባንዶች (ከጄምስ ሂውበርት ብሌክ፣ ስፕሪንግብሩክ፣ ኖርዝዉድ፣ ክላርክስበርግ፣ እና ጆን ኤፍ. ኬኔዲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡትን ጨምሮ)፣ ደማቅ የዳንስ ቡድኖች፣ ያጌጡ ተንቀሳቃሽ መድረኮች (floats) እንዲሁም አዝናኝ (inflatable) ቅርጻ ቅርጾች ይቀርባሉ። መስመሩ የሚጀምረው ከ Ellsworth Drive እና Fenton Street በ downtown Silver Spring ሲሆን፣ በ Georgia Avenue ወደ ደቡብ አቅጣጫ ይሄድና Silver Spring Avenue ላይ ይቆማል። ዝናብ ቢኖርም ባይኖርም የሰልፍ ትርኢቱ ይካሄዳል።
ሰልፉ የሚካሄደው የተለየ አይነት አለባበስ ኖሯቸው፣ እንደ ቡድን መሪዎች ሆነው የሚያገለግሉ፣ እና ባሉኖችን ተቆጣጣሪዎች የሚሆኑ በጎ ፈቃደኞችን ይፈልጋል። በጎ ፈቃደኞች ከጠዋቱ a.m.-1:30 p.m. ድረስ መገኘት አለባቸው። ዕድሜያቸው 13 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተማሪዎች፣ በመሳተፋቸው ለትምህርት ቤት የማህበረሰብ አገልግሎት (SSL) ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ። ለሰልፍ በጎ ፈቃደኛ ለመሆን ይመዝገቡ።
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
ከሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) የበለጠ መረጃ
|
|
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች
|
|
©1995–2026 Montgomery County Public Schools
|
|