አበይት ጉዳዮች
ኖቨምበር 12, 2026
|
|
|
|
ስለ ቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ማሳሰቢያ፦ ከኖቬምበር 23 እስከ 25 ያሉት ቀናት ተማሪዎች ቀደም ብሎ የሚለቀቁባቸው ቀናት ናቸው። የምስጋና በዓልን 'Thanksgiving' ምክንያት በማድረግ፣ ትምህርት ቤቶችና ቢሮዎች ከኖቬምበር 26 እስከ 27 ዝግ ይሆናሉ።
|
|
|
|
|
|
ParentVue ይመልከቱ፦ የመጀመሪያው የውጤት/ማርክ መስጫ ወቅት ሪፖርት ካርዶችን፣ እና የትምህርት እድገት ሪፖርቶችን አሁን ማግኘት ይችላሉ። |
|
የመጀመሪያው የማርክ መስጫ ወቅት የውጤት ሪፖርት ካርዶች ParentVue ላይ ይገኛሉ። እስከ አርብ፣ ኖቨምበር 13 ድረስ፣ ከመዋእለ ህጻናት እስከ 8ኛ ክፍል (K–8) ያሉ ተማሪዎች ወላጆች በንባብ እና/ወይም በሂሳብ ትምህርት የተመዘገበውን ትምህርት የመቅሰም እድገት የሚያሳይ የውጤት መግለጫ ይደርሳቸዋል። የተማሪዎን ስኬቶች ለማክበር እና መሻሻል በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመወያየት ይህ ጥሩ አጋጣሚ ነው። ይበልጥ ያንብቡ.
አሁን ያውቃሉ/Now You Know፦እንግሊዝኛ/ English |ስፓንሽኛ/Spanish |አማርኛ/Amharic | Chinese | French | Korean | Portuguese | Vietnamese
|
|
|
|
|
|
ድምጽዎ ዋጋ አለው! በመላው ዲስትሪክቱ የሚካሄደው የባህልና የሁኔታዎች ዳሰሳ ጥናት አሁን ተጀምሯል። |
|
ቤተሰቦች፣ ተማሪዎች፣ እና የትምህርት ቤት ሰራተኞች በቅርቡ በሚካሄደው በመላው ዲስትሪክቱ የሚከናወን የባህል እና የሁኔታዎች (Culture and Climate) ዳሰሳ ጥናት ላይ በመሳተፍ አስተያየታቸውን እንዲያካፍሉ ተጋብዘዋል። የሚሰጡት አስተያየት ምን ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየተከናወኑ እንዳሉ እና የትኞቹ ላይ መሻሻል እንደሚያስፈልግ ጠቃሚ ግንዛቤ ይሰጣል። ይህ ደግሞ፣ ለእያንዳንዱ ተማሪ የተሻለውን የትምህርት ተሞክሮ ለመስጠት እንዲቻል፣ አመራሩ ምን ነገሮች ውጤታማ እንደሆኑ እና ዲስትሪክቱ በየትኞቹ ዘርፎች ማደግ እንዳለበት በተሻለ ሁኔታ ግንዛቤ ለማግኘት ያግዛል። ዳሰሳው የሚካሄደው በገለልተኛ የምርምር እና የመረጃ አጠናቃሪ ድርጅት አማካኝነት ሲሆን፣ ዳሰሳውን ለመሙላት የሚወስደው ጊዜ ከ 10 ደቂቃ ያነሰ ነው። የሚሰጡት ምላሽ በሙሉ በሚስጥር የሚጠበቅ ነው። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
|
የቀን ብርሃን አነስተኛ በሚሆንበት ወቅት፣ የበለጠ ጥንቃቄ ያድርጉ — ተማሪዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ያግዙ |
|
አንድ ሰዓት ወደ ኋላ መልሰን ስላስተካከልን፣ ፀሐይ ቀደም ብላ እየጠለቀች ነው፤ ይህም ወደ ትምህርት ቤት የሚሄዱና ከትምህርት ቤት የሚመለሱ ተማሪዎችን በተመለከተ ከምንጊዜውም በላይ ጥንቃቄ እንድናደርግ ያስገድደናል። ከሰዓት በኋላ በሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች እና በጉዞ ወቅት የቀን ብርሃን አጠር ስለሚል፣ እባክዎ ፍጥነትዎን ይቀንሱ፣ ንቁ ይሁኑ፣ እና እርስ በርስ ተጠባበቁ።
- አሽከርካሪዎች፦ በትምህርት ቤት አካባቢዎች እና በመኖሪያ ሰፈሮች ውስጥ ፍጥነታችሁን ቀንሱ፤ በእግረኛ መሻገሪያዎች እና በአውቶቡስ ማቆሚያዎች ላይ ተማሪዎች መኖራቸውን በጥንቃቄ ተከታተሉ፤ ትኩረታችሁን የሚከፋፍሉ ነገሮችን አስወግዱ፤ እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የትምህርት ቤት አውቶቡሶች ቀይ ምልክት ዘርግተው ተማሪዎችን ለማሳፈር/ለማውረድ በቆሙ ጊዜ ሁሉ መኪናችሁን አቁማችሁ ጠብቁ።
- ቤተሰቦች፦ ተማሪዎች በእግረኛ መንገድ እና በተለዩ የእግረኛ መሻገሪያዎች ብቻ እንዲሄዱ፣ መንገድ ከመሻገራቸው በፊት ወደ ሁለቱም አቅጣጫዎች እንዲመለከቱ፣ በእግር በሚሄዱበት ጊዜ ስልኮቻቸውን እንዳጠቀሙ፣ እንዲሁም የማየት ሁኔታ ዝቅተኛና ጭጋጋማ በሆነበት ጊዜ ደማቅ ብርሃን የሚያንጸባርቁ ልብሶችን እንዲለብሱ አስታውሷቸው።
ትንሽ ተጨማሪ ትኩረት መስጠት፣ ለሁሉም ሰው ጉዞን ይበልጥ አስተማማኝ ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
|
|
|
|
|
|
ለራስዎ ጊዜ ይስጡ፦ ኖቨምበር 14 በሚካሄደው የአእምሮ ጤና እና ደህንነት ኤግዚቢሽን ላይ እንገናኝ። |
|
ሲልቨር ስፕሪንግ በሚገኘው ጄምስ ሂውበርት ብሌክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ቅዳሜ፣ ኖቨምበር 14 ከጠዋቱ 10 a.m.-1 p.m. የሚካሄደውን የአእምሮ ጤና እና ደህንነት ኤግዚቢሽን እንዳያመልጥዎት።
አድራሻ፦ James Hubert Blake High School, 300 Norwood Road in Silver Spring. ለሰራተኞች፣ ለተማሪዎች፣ እና ለቤተሰቦች በነጻ ክፍት ሲሆን፣ ይህ ዝግጅት ወርክሾፖችን፣ የአካል ብቃት ትምህርቶችን፣ በተማሪ የሚመራ መድረክ፣ እና የማህበረሰብ አጋሮች ስለ አዕምሮ ጤንነት እና ደህንነት መረጃዎችን የሚያጋሩበት ጠቃሚ ዝግጅት ነው። ተሳታፊ ተማሪዎች በመሳተፋቸው አራት የተማሪ አገልግሎት-ትምህርት (Student Service Learning) ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ።
MCPS ተማሪዎች ብቻቸውን እንዳልሆኑ እንዲያውቁ ይፈልጋል። ተማሪዎች ለእርዳታ ጥያቄ በሚያቀርቡበት ጊዜ ምላሽ የሚሰጡ አዋቂዎች በህንጻዎቻችን ውስጥ ይገኛሉ። በመማሪያ ክፍሎችና በኮሪደሮች ላይ፤ በማጣበቂያ የተለጠፉ ነገሮችን፣ ካርዶችን፣ እና መረጃ ሰጪ ፖስተሮችን ጨምሮ፣ ችግር ባጋጠማቸው ጊዜ ድጋፍ ለማግኘት የሚያስችል መረጃ በቀላሉ ማግኘት የሚቻልባቸው ቁሳቁሶች በትምህርት ቤቶቻችን ይገኛሉ። ተማሪዎችን በቀጥታ ከአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ሰጪ አገልግሎቶች ጋር የሚያገናኙ፣ ለየትምህርት ቤቱ የተዘጋጁ የኢሜል አድራሻዎች አሉ፤ እንዲሁም በአእምሮ ጤና፣ እርስ በርስ በመደጋገፍ፣ እና እርዳታ መቼ እና እንዴት መጠየቅ እንዳለባቸው በማሳወቅ ላይ ያተኮሩ የክፍል ውስጥ ትምህርቶች ይሰጣሉ። እርዳታ፣ ድጋፍ፣ እገዛ ሁልጊዜም ይኖራል።
|
|
|
|
|
|
ማመልከቻዎችን ሞልታችሁ/አጠናቃችሁ አቅርቡ፤ 8ኛ ክፍል ሴንተር ፕሮግራሞች እና MSMC የማመልከቻ ማቅረቢያ ቀነ ገደቡ ኖቬምበር 13 ነው። |
|
8ኛ ክፍል ለሴንተር ፕሮግራሞች እና ለመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማግኔት ኮንሶርቲየም ለማመልከት የተሰጠው የመጨረሻ ቀን በፍጥነት እየተቃረበ ነው — አርብ፣ ኖቨምበር 13 ይዘጋል።
የሴንተር ፕሮግራሞች ድረ-ገጽ ላይ ተጨማሪ መረጃ ያግኙ፤ MCPS ውስጥ ሪጅናል እና ሙያ ነክ ጭብጥ ላይ ያተኮሩ ፕሮግራሞች እንዴት እንደተደራጁ ይወቁ፣ የተወሰኑ የሙያ መስኮችን በጥልቀት ለመረዳት የሚያግዙ ግብዓቶችን ያግኙ፣ እንዲሁም በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎችን (FAQs) ይመልከቱ። MSMC ፍላጎት ያላቸው ቤተሰቦች ዝርዝር መረጃዎችን በድረ ገጻቸው ላይ ማግኘት ይችላሉ።
|
|
|
|
|
|
በህይወትዎ ትንሽ ድራማ ይሥሩ! |
|
በመካከለኛ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመኸር ወቅት የቲያትር ዝግጅቶች በከፍተኛ ሁኔታ እየተከናወኑ ናቸው። ድንቅ ትርኢቶችን ይመልከቱ፤ ለሁሉም የሚሆን ነገር አለ።
MCPS የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ይጎብኙ፤ «Fine Arts» በሚለው አማራጭ ይፈልጉ። ከዚያም ተመዝግበው ወደ iCal ወይም Google ካለንደርዎ ማውረድ/መጫን ይችላሉ።
|
|
|
|
|
|
የብዝሃ ቋንቋ ተናጋሪ ቤተሰቦቻችንን ብቃት እንዲያገኝዑ ማስቻል — በምናዘጋጀው መድረክ ላይ ይገናኙን! |
|
MCPS፣ በሂደት ላይ ያሉ ብዝሃ ቋንቋ ተማሪዎችን (EMLs) እና ቤተሰቦቻቸውን ታሳቢ ያደረጉ፣ በተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄዱ ተከታታይ የቤተሰብ ተሳትፎ መርሐ ግብሮችን በማዘጋጀት ቤተሰቦችን እያገናኘ ነው። እነዚህ ከክፍያ ነጻ የሆኑ ዝግጅቶች፣ ቤተሰቦች ከትምህርት ቤት ሰራተኞች ጋር እንዲገናኙ፣ ስለ MCPS ፕሮግራሞች እና የማህበረሰብ ግብዓቶች መረጃ እንዲያገኙ፣ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ እና ከሌሎች ቤተሰቦች ጋር የመተዋወቅ እድል ይሰጣሉ። ልጆችዎ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤት፣ በመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ወይም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ቢሆኑም፣ ለሁሉም የሚሆን ጠቃሚ ነገር አለ! የሚቀጥሉት ሁለቱ ሰኞ፣ ኖቨምበር 16 እና ማክሰኞ፣ ኖቨምበር 17 ይከናወናሉ። ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
|
|
|
|
መራራው እውነት፦ የተማሪዎች ቁጥር መቀነስ፣ ወጪዎች እና CIP |
|
MCPS የበጀት ዓመት 2028 የካፒታል በጀት ረቂቅ እንዲሁም 2027 እስከ 2032 ያለውን የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም (CIP) ማሻሻያዎችን በመገምገም ላይ እያለ፣ ዲስትሪክቱ እጅግ አስቸጋሪ ውሳኔዎችን መጋፈጥ ግድ ሆኖበታል። መራራው እውነት፦ ከትምህርት ዓመት 2019 ጀምሮ የተማሪዎች ምዝገባ ከ 13,000 በላይ ቀንሷል፤ ትንበያዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ቁጥሩ ከዚህም በላይ ይቀንሳል። ነገር ግን፣ ወጪዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ በመጡበት በአሁኑ ወቅት፣ MCPS አሁንም ከ 200 በላይ ያረጁ እና ብቃት የሌላቸውን ተቋማት የመንከባከብ ኃላፊነት አለበት።ስለ "The Hard Truth" ቪዲዮዎችን ይመልከቱ።
|
|
|
|
|
|
ከኖቬምበር 16 እስከ 30 "IXL Challenge" የክህሎት ውድድር ስለሚካሄድ የንባብና የጽሁፍ ክህሎትዎን ያሳድጉ። |
|
በዚህ የመኸር ወቅት፣ MCPS 6ኛ እስከ 11ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች "IXL Challenge" ውድድር ያካሄዳል። ከኖቬምበር 16 እስከ 30 የሚካሄደው ይህ ውድድር፣ የትምህርት ቤት እንቅስቃሴዎች በሚቀዛቀዙበት «Thanksgiving» ዕረፍት ወቅት፣ ተማሪዎች ማንበብ እንዲቀጥሉ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስነጥበት/አርት 'ELA' ክህሎቶቻቸውን እንዲያዳብሩ የሚያግዝ አዝናኝ ስልት ነው። IXL የቋንቋ ስነጥበብ (ELA) ክህሎት ዕቅድ SAT ፈተና ዝግጅትንም ያካትታል። ይህ ለተማሪዎችና ለቤተሰቦች የተዘጋጀ IXL ሊተርሲ ፕሮግራም እና ለዚህ ፕሮግራም የንባብና የጽሕፈት ክህሎቶችን ለማዳበር የሚያቀርባቸውን መገልገያዎች በደንብ ለማወቅ ጥሩ አጋጣሚ ነው። በማንኛውም ሞባይል መገልገያ ከፍተው በመለማመድ ሽልማቶችን ያግኙ።
IXL Flyers:እንግሊዝኛ/English | Spanish |አማርኛ/Amharic | Chinese | French | Korean | Portuguese | Vietnamese
|
|
|
|
|
|
ለፍሪጅ!2ኛ ሩብ ዓመት የትምህርት ከሪኩለም አሁን ይገኛል። |
|
ለትምህርት ዓመት 2026–2027 ሁለተኛ ሩብ ዓመት የሚሆን በፍሪጅ ላይ የሚለጠፍ ሥርዓተ ትምህርት» (Refrigerator Curriculum) አሁን ይገኛል። ይህ ከመዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል (K–12) ያሉ ተማሪዎች በእያንዳንዱ የማርክ መስጫ ወቅት የሚማሩትን የትምህርት ይዘት—ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮችን፣ ጭብጦችን፣ እና የትምህርት ጽሑፎችን ጭምር—በአንድ ገጽ ላይ በቀላሉ ሊነበብ በሚችል መልኩ የሚያቀርብ አጠቃላይ መግለጫ ነው።
|
|
|
|
|
|
ወጣት አንባቢዎችን መገዳደር፦ በክፍል ውስጥ ከመዋእለ ህጻናት እስከ ስምንተኛ በመማሪያ ክፍል "K–8" የሊተርሲ ክህሎትን ማበልጸግ። |
|
Amplify Core Knowledge Language Arts (CKLA) የተሰኘው የቋንቋ ስነጥበብ ፕሮግራም፣ የድምፅ እና የፊደላት ትስስርን (phonics) ከተለያዩ የስሜት ህዋሳት ጋር ከሚያገናኝ አቀራረብ እና ከበለጸጉ ጽሑፎች ጋር በማዋሃድ የተማሪዎችን የይዘት ግንዛቤ ይገነባል። በዚህም ተማሪዎች ማንበብን ከመማር ጎን ለጎን፣ እውቀት ለማግኘት ያነባሉ። MCPS የሊተርሲ ክህሎትን የሚያዳብሩ ተግባራትን በትምህርት ቀን ያካሄዳል። ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
|
በሜሪላንድ ኮሌጆች የኮሌጅ ምዝገባ ውሳኔዎችን ወዲያውኑ ያግኙ |
|
አርብ፣ ኖቨምበር 20 እና አርብ፣ ዲሰምበር 4፣ MCPS ከሜሪላንድ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር፣ ተማሪዎች በቦታው ላይ የምዝገባ ውሳኔ የሚያገኙባቸውን መርሐ ግብሮች ያዘጋጃል። በእነዚህ ዝግጅቶች ወቅት፣ ወደ ትምህርት ተቋሙ ለመግባት የሚፈልጉ ተማሪዎች ከኮሌጅ ምዝገባ ኃላፊ ጋር መገናኘት እና የነጻ ትምህርት ዕድል (ስኮላርሺፕ) ጭምር፣ ስለ ኮሌጅ ምዝገባቸው ፈጣን ውሳኔ ማግኘት ይችላሉ። ቃለ መጠይቆች ዙም/Zoom ላይ በኦንላይን ይካሄዳሉ። ጥያቄዎች ካሉዎት የልጅዎን የኮሌጅ እና የስራ መስክ ናቪጌተር (College & Career Navigator - CCN) ያነጋግሩ።የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።
|
|
|
|
|
|
ያለፈውን እያከበርን፣ በጋራ ወደፊት መጓዝ |
|
በኖቬምበር ወር፣ MCPS ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የመታሰቢያ እና የእርቅ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ታሪካዊ ጥቁር ማህበረሰቦች በከተማ እድሳት ምክንያት ስላጋጠሟቸው ለውጦች ዌቢናሮችን ያስተናግዳል። ሐሙስ፣ ኖቬምበር 19 የሚካሄደው «Changemaker» ወርክሾፕ እንዳያመልጥዎት፤ ተማሪዎች በወርክሾፑ በመሳተፍ «Service Learning» ሰዓት ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
|
Federal Impact Aid ዳሰሳ አሁን ተጀምሯል፤ ParentVUE ላይ ማግኘት ይቻላል። |
|
MCPS ለፌዴራል ኢምፓክት ኤይድ የገንዘብ ድጋፍ ፈንድ 'federal Impact Aid grant funds' ብቁ የሚሆነው ወላጆች/አሳዳጊዎች ዩኒፎርም የለበሱ የአገልግሎት ሰራተኞች ሲሆኑ፣ በፌዴራል ንብረት ላይ የሚኖሩ ወይም በፌዴራል ድጎማ በሚደረግላቸው ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ ልጆች ሲኖሯቸው ወይም በሜሪላንድ ውስጥ ብቁ በሆኑ የፌዴራል ንብረቶች ላይ ተቀጥረው የሚሰሩ ልጆች ሲኖሯቸው ነው። እነዚህ ገንዘቦች ለዲስትሪክቱ እና ለአጠቃላይ የስራ ማስኬጃ በጀት ተጨማሪ ገቢ ያስገኛሉ።
ይህንን የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት፣ ወላጆች/አሳዳጊዎች MCPS ትምህርት ቤቶች ውስጥ ስለሚማሩ እና ከፌዴራል መንግሥት ጋር ግንኙነት ስላላቸው ተማሪዎች መረጃ መሰብሰብ አለባቸው። ይህንን ጥናት MCPS ቅጽ 280-4 'Federal Impact Aid Survey' ወይም ParentVUE በመጠቀም መሙላት ይቻላል። ቅጽ 280-4 ከመረጡ፣ በቤተሰብዎ ውስጥ ለሚገኝ፣ የትምህርት ዕድሜ ላይ ለደረሰ እና ከፌዴራል ግንኙነት ላለው ለእያንዳንዱ ተማሪ አንድ ቅጽ ማቅረብ አለብዎት። ParentVue ላይ መሙላት ከፈለጉ፣ አንድ የኤሌክትሮኒክስ መጠይቅ ብቻ ማቅረብ በቂ ነው።
እባክዎ የዳሰሳ ጥናቱን እስከ አርብ፣ ዲሴምበር 11 ድረስ ሞልተው ያቅርቡ።
በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ጥያቄዎች፦እንግሊዝኛ/English |ስፓንሽኛ/Spanish
ተጨማሪ መረጃ
|
|
|
|
|
|
ከደወል ባሻገር |
- *NEW* Vision Zero Youth Ambassador Program፦ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትራንስፖርት መምሪያ፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ የትራፊክ ደህንነት ጉዳዮችን ለማሻሻል የሚያስችሉ የአመራር ክህሎቶችን እንዲሁም የማህበረሰብ ተሳትፎ እና ግንኙነት ስልቶችን የሚያስተምር፣ በፕሮጀክት ላይ የተመሰረተ የትምህርት ፕሮግራም ለማካሄድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ይፈልጋል። በዚህ ላይ መሳተፍ ከክፍያ ነጻ ሲሆን፣ ተማሪዎች እስከ 46 የተማሪ የአገልግሎት ሰዓት SSL ማግኘት ይችላሉ። የመጨረሻው ቀን ሰኞ፣ ኖቬምበር 30ነው።
- C-SPAN StudentCam Documentary Competition፦6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ክፍት ነው። በዘንድሮው ዓመት፣ ተማሪዎች “Mr. --” ከሚለው ጭብጥ ጋር በተያያዘ ርዕስ ላይ ከ አምስት እስከ ስድስት ደቂቃ የሚረዝም የቪዲዮ ዘጋቢ ፊልም አዘጋጅተው እንዲያቀርቡ ይጠበቃል። አፈጉባኤ፣ ሀሳብ ለማቅረብ እጅ አንስቻለሁ … .” የመጨረሻው ቀን፦ ረቡዕ፣ ጃንዋሪ 20, 2027ነው።
- «ድምጽዎን ያሰሙ፣ ሕይወትን ይታደጉ» የቪዲዮ ውድድር፦ ይህ ውድድር ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ክፍት ሲሆን፣ ተሳታፊዎች 10 SSL (የማህበረሰብ አገልግሎት) ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ። በታዳጊዎች መካከል ህገ-ወጥ ኦፒዮይዶች (opioids) ስለሚያስከትለው አደጋ፣ ከመጠን በላይ ስለመውሰድ (overdose) እና ስለ ፌንታኒል (fentanyl) ግንዛቤን የሚያሳድግ፣ የራስዎ የሆነ ኦሪጅናል ቪዲዮ ያዘጋጁ። ቪዲዮዎችን በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ማቅረብ ይቻላል። የመጨረሻው ቀን ሰኞ፣ ኖቬምበር 30ነው።መወዳደሪያውን ያቅርቡ።
|
|
|
|
|
|
በአካባቢ የሚካሄዱ ዝግጅቶች |
- ሞንትጎመሪ ካውንቲ የመዝናኛ አገልግሎት (Montgomery County Recreation)፡ 2026-2027 የክረምት ወቅት ፕሮግራሞች፣ ትምህርቶች፣ እና የእንቅስቃሴዎች ምዝገባ ማክሰኞ፣ ኖቬምበር 17 ከጠዋቱ 6፡30 a.m. ይጀምራል። ነዋሪዎች ActiveMONTGOMERY.org ድረ-ገጽ ላይ በኦንላይን እንዲመዘገቡ ይበረታታሉ። አካውንት ከሌለዎት ወይም ያለውን አካውንት ማዘመን ከፈለጉ፣ መመሪያዎች እና በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ጥያቄዎች 'FAQs' እዚህ ይገኛሉ።
- የአካባቢን ደራሲያን ማስተዋወቂያ፦ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ቤተ-መጻሕፍት እሁድ፣ ኖቨምበር 22 (Nov. 22) ከቀኑ 1-4 p.m. ዊተን በሚገኘው ቤተ-መጻሕፍት እና የመዝናኛ ማዕከል
አድራሻ፦ Wheaton Library and Recreation Center, 11701 Georgia Avenue in Wheaton
ነጻ የመጻሕፍት ትርኢት እና ከደራሲያን ጋር የመገናኘት መርሐ ግብር ያካሄዳል። 30 የአካባቢ ደራሲያን ጋር መገናኘት፣ በኢንዱስትሪው ውስጥ ስለ ማርኬቲንግ እና ህትመት ፓነሎች፣ ለህጻናት ተስማሚ የሆነ “Read to a Superhero” እንቅስቃሴ እና በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኝ zine አውደ ጥናትን ያካትታል።
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
ከሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) የበለጠ መረጃ
|
|
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች
|
|
©1995–2026 Montgomery County Public Schools
|
|