የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች
 

English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic

 

ስለ ወደፊቱ ማቀድ፦ መረጃ፣ ውይይት፣ እና የማህበረሰብ ድምፅ

40 ዓመታት በላይ በሆነ ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ MCPS የተማሪዎች ምዝገባ ቁጥር እየቀነሰ ነው። በዚህም ምክንያት፣ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከሚያስፈልጋቸው በላይ ቦታ ሲኖራቸው፣ ሌሎች ማህበረሰቦች ግን አሁንም በማደግ ላይ ናቸው። ይህ ማለት፥ ትምህርት ቤቶቻችንን እና የተለያዩ ተቋሞቻችንን እንዴት እየተጠቀምንባቸው እንዳለ በካውንቲው ደረጃ በጥልቀት የምንመረምርበት፣ እንዲሁም ለሁሉም ተማሪዎች የተሻለ የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንዲኖራቸው ለማረጋገጥ የምናቅድበት ጊዜ አሁን ነው ማለት ነው።

ይህ ለምን አስፈላጊ ሆነ? ትምህርት ቤቶቻችንን እና ውስን ሀብታችንን በብቃት መጠቀም ማለት፣ ተማሪዎች በጣም በሚፈልጓቸው ዘርፎች ላይ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች ላይ ማዋል ማለት ነው፤ እነዚህም ጠንካራ የማስተማር ሂደት፣ ውጤታማ የትምሕርት ፕሮግራሞች፣ እንዲሁም እያንዳንዱ ተማሪ እንዲያድግና እንዲሳካለ(ላ)ት የሚያግዙ አገልግሎቶችና ድጋፎችን መስጠት ማለት ነው። በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች እጅግ ጥሩ የሆኑ የትምሕርት ተሞክሮዎችን እንድናቀርብ ያግዘናል።

መታወቅ ያለበት አስፈላጊ ነገር፦ ይህ ስራ በሁለት የተለያዩ ደረጃዎች በሁለት አመት ውስጥ ይከናወናል።

ዘንድሮ = ስለ መዝጋት እና ማጣመር። በሚቀጥለው ዓመት = ስለ ድንበሮች።

በመጀመሪያ ደረጃ፡ መረጃዎችን መገምገምና ትምህርት ቤቶችን ስለመዝጋትና ስለማጣመር ምክረ-ሀሳቦችን ማቅረብ — 2026–2027

በዚህ የትምህርት አመት፥ MCPS በመላው ካውንቲው የሚገኙ አንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ይገመግማል፤ እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን የመዝጋት እና የማጣመር ዕድሎችን ለመመልከት የሚያስችል ግልጽ እና አሳታፊ አሰራር ይዘረጋል። ዓላማውና ግቡ ትምህርት ቤቶችን በማዕቀፍ መሠረት መገምገም እና የትኞቹ ትምህርት ቤቶች መዘጋት ወይም መጣመር እንዳለባቸው — እንዲሁም እንዲህ ዓይነት እርምጃ መወሰድ እንዳለበት — ሱፐርኢንቴንደንቱ ለትምህርት ቦርድ ምክረ ሐሳብ ማቅረብ እንዳለበት መወሰን ነው።

በዚህ ምዕራፍ በመላው ካውንቲው የድንበር ወሰን ጥናት አይካሄድም።

ትምሕርት ቤቶችን ስለ መዝጋት እና ማጣመር የሚወሰነው እንዴት ነው?

አንድ ትምህርት ቤት የመዘጋት ወይም ከሌላ ትምህርት ቤት ጋር የመጣመር ዕድል ከቤተሰቦች አስፈላጊ ጥያቄዎችን እንደሚያስነሳ እናውቃለን። ምንም ዓይነት ውሳኔዎች አልተወሰኑም፤ እንዲሁም ይህ ሂደት ትምህርት ቤቶችን በሚመለከት አስቀድሞ የተወሰነበት ጉዳይ አይደለም። ሥራው የሚጀምረው በመረጃ፣ በመመዘኛዎች እና ከማህበረሰቡ ጋር በሚደረጉ ውይይቶች እና በሚሰበሰብ አስተያየት ነው።

ገለልተኛ አማካሪ፣ ከሜሪላንድ ደንቦች (COMAR)፣ ከትምህርት ቦርድ ፖሊሲ FAA (የአካዳሚክ ተቋማት ህንጻዎች አጠቃቀም ዕቅድ) እና MCPS ደንብ FAA-RA (የአካዳሚክ ተቋማት ሕንጻዎች አጠቃቀም ዕቅድ) ጋር የሚጣጣም ውሳኔ የመስጠት ማዕቀፍ በማዘጋጀት የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶችን (MCPS) ያግዛል። ማዕቀፉ ስለ ትምህርት ቤቶቻችን፣ ስለ መገልገያዎቻችን፣ ስለ ተማሪዎቻችን እና ማህበረሰቦቻችን በርካታ ጉዳዮችን እና ሰፊ የመረጃ አይነቶችን ከግምት ውስጥ የሚያስገባ ሲሆን ይህ ማለት የተማሪዎች ምዝገባን ወይም በየት/ቤቶቹ ያሉትን የመቀመጫ ቦታዎች ብዛት ብቻ የሚመለከት አይሆንም።

ከዚህ ባልተናነሰ አስፈላጊ በመሆኑ፣ ምክረ ሐሳብ ከመቅረቡ በፊት ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች በሂደቱ ውስጥ ተሳታፊ ይሆናሉ። በዚህ የመኸር ወቅት የሚካሄደው ተሳትፎና ውይይት፣ ለውሳኔ አሰጣጥ የሚያገለግሉ መለኪያዎችንና መስፈርቶችን ለመቅረጽ ያግዛል፤ እንዲሁም ስለ ተማሪዎች ተሞክሮ፣ ስለ ማህበረሰቡ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች እና በዚህ ደረጃ ትልቅ ውሳኔዎች ሲወሰኑ ስለሚኖር ጥቅምና ጉዳት በማመዛዘን (trade-offs) ለመወያየት ዕድል ይፈጥራል። ይህ ሂደት፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ማህበረሰቦች ሰፊ ተሳትፎና አስተያየት እንዲሁም የተለያዩ አመለካከቶች እንዲካተቱበት ተደርጎ የተነደፈ ነው።

ያ ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ ሱፐርኢንተንደንቱ ለትምህርት ቦርድ የሚቀርብ ምክረ ሐሳብ ያዘጋጃል፤ እንዲሁም ለሕዝብ ይፋ ያደረጋል። ቦርዱ የመጨረሻ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት፣ ቤተሰቦች እና የማህበረሰብ አባላት በይፋዊ የመስማት ሂደቶች እና በጽሁፍ በሚቀርቡ አስተያየቶች ለመሳተፍ ሌላ ዕድል ይኖራቸዋል።

ሁለተኛ ደረጃ፡ በመላው ካውንቲ የሚካሄድ የድንበር ማካለል ጥናት — 2027–2028

በሚቀጥለው የትምህርት አመት፣ የመጀመሪያው ምዕራፍ ከተጠናቀቀ እና MCPS የተማሪዎቻችንን ብዛትና ያሉትን መገልገያ ሀብት ከግምት ውስጥ በማስገባት ተገቢውን የትምህርት ቤቶች ብዛትና አደረጃጀት ከወሰነ በኋላ፤ MCPS ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመላው ካውንቲው የሚከናወን የአካባቢ ወሰን ጥናት እንዲሁም ለሚመለከታቸው መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የወሰን ማስተካከያ ሥራ ይጀመራል።

ይህ በተለየ ሂደት ይከናወናል፤ ሂደቱም የራሱ የሆኑ የህዝብ መረጃ ልውውጥ መድረኮች፣ የአዋሳኝ መስመር አማራጮች ዝግጅት፣ በርካታ ዙር የማህበረሰብ አስተያየት ማሰባሰቢያዎች፣ የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ምክረ-ሀሳብ፣ የህዝብ አስተያየትና ውይይት መድረኮች፣ እና በትምህርት ቦርድ የሚሰጥ የመጨረሻ ውሳኔን የሚያካትት ነው።

ይህንን በጥንቃቄ እና በአግባቡ ለማከናወን በቂ ጊዜ አለ፤ በዚህ የሁለት ዓመት ሂደት የሚደረጉ ማናቸውንም ለውጦች 2029–2030 የትምህርት አመት ተግባራዊ ለማድረግ ታቅዷል።

የእርስዎ ድምፅ በእያንዳንዱ ምዕራፍ ላይ ወሳኝ አካል ነው፤ ይህም የሚሆነው የውሳኔ አሰጣጥ ምክረ-ሀሳብ ከመቅረቡ በፊት ነው።

ቤተሰቦች፣ የትምህርት ቤቱ ሠራተኞች፣ ተማሪዎች፣ እና የማህበረሰብ አባላት በመላው ካውንቲው በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ የመሳተፍ ዕድል ይኖራቸዋል፤ ዝግጅቶቹ ላይ ሰዎች በቀላሉ እንዲሳተፉ ለማስቻል በአካል እና በኦንላይን (ቨርቹዋል) የተዘጋጁ ናቸው። ከአንድ በላይ በሆኑ ክፍለ-ጊዜዎች መሳተፍ ይችላሉ፤ ነገር ግን በእያንዳንዱ ክፍለ-ጊዜ የሚሸፈነው/የሚቀርበው ተመሳሳይ መረጃ ይሆናል። 

  • አንደኛ ዙር፦ ኦክቶበር 19–ኖቬምበር 2
  • ሁለተኛ ዙር፦ ኖቨምበር 30–ዲሰምበር 10

ብዙ ሥራ — በርካታ ውይይቶች፣ የማህበረሰብ ተደራሽነት፣ እና የመሣተፍ እድሎች— ይጠብቁናል። እነዚህ ውሳኔዎች ለቤተሰቦች እና ለማህበረሰቦች እጅግ ፋይዳ ያላቸው መሆኑን ስለምንገነዘብ በችኮላ አናደርጋቸውም። መረጃዎችን እናጋራለን፣ መስፈርቶቹን እናብራራለን፣ እንዲሁም የማህበረሰባችንን ሐሳብ እናዳምጣለን፤ በተጨማሪም፣ ሂደቱ ከመረጃ እና ከምክክር ወደ ምክረ-ሐሳብ፣ በመጨረሻም ወደ ትምህርት ቦርዱ ይፋዊ ውሳኔ እንዴት እንደሚያልፍ ቤተሰቦች በግልጽ እንዲረዱት/እንዲያውቁት እናደርጋለን።

1ኛ ዙር

ዙር የማህበረሰብ ተሳትፎ ዓይነት የማህበረሰብ ስብሰባ የስብሰባ ቦታ
1 ሰኞ፣ ኦክቶበር 19 ቨርቹወል ከቀትር 12:00 እስከ 1:00 p.m. ዙም (Zoom)
1 ሰኞ፣ ኦክቶበር 19 በአካል 6:30-8:30 p.m. ጌትስበርግ መካከለኛ/ደ/ት/ቤት Gaithersburg MS
1 ማክሰኞ፣ ኦክቶበር 20 በአካል 6:30-8:30 p.m. ኪንግስቪው መካከለኛ ደ/ት/ቤት Kingsview MS
1 ሮብ፣ ኦክቶበር 21 በአካል 6:30-8:30 p.m. ሮዛ ፓርክስ መካከለኛ ደ/ት/ቤት Rosa Parks MS
1 ሐሙስ፣ ኦክቶበር 22 በአካል 6:30-8:30 p.m. ኤ. ማሪዮ ሎይደርማን መካከለኛ ደ/ት/ቤት A. Mario Loiederman MS
1 ኣርብ፣ ኦክቶበር 23 ቨርቹወል ከቀትር 12:00 እስከ 1:00 p.m. ዙም (Zoom)
1 ሮብ፣ ኦክቶበር 28 በአካል 6:30-8:30 p.m. ጁሊዩስ ዌስት መካከለኛ ደ/ት/ቤት Julius West MS
1 ሐሙስ፣ ኦክቶበር 29 በአካል 6:30-8:30 p.m. ኢስተርን መ/ደ/ት/ቤት Eastern MS
1 ኣርብ፣ ኦክቶበር 30 ቨርቹወል ከቀትር 12:00 እስከ 1:00 p.m. ዙም (Zoom)
1 ሰኞ፣ ኖቬምበር 2 ቨርቹወል 6:00-7:00 p.m. ዙም (Zoom)

የቀለም ኮድ፦ አረንጓዴ = በኦንላይን የሚደረግ ቨርቹዋል ስብሰባ፤ ሰማያዊ = በአካል የሚደረግ ስብሰባ

2ኛ ዙር

ዙር የማህበረሰብ ተሳትፎ ዓይነት የማህበረሰብ ስብሰባ የስብሰባ ቦታ
2 ሰኞ፣ ኖቬምበር 30 ቨርቹወል ከቀትር 12:00 እስከ 1:00 p.m. ዙም (Zoom)
2 ሰኞ፣ ኖቬምበር 30 ቨርቹወል 6:00-7:00 p.m. ዙም (Zoom)
2 ማክሰኞ፣ ዲሰምበር 1 በአካል 6:30-8:30 p.m. ኸርበርት ሁቨር መካከለኛ ደ/ት/ቤት Herbert Hoover MS
2 ረቡዕ፣ ዲሰምበር 2 በአካል 6:30-8:30 p.m. ሪጅቪው መካከለኛ ደ/ት/ቤት Ridgeview MS
2 ሐሙስ፣ ዲሰምበር 3 በአካል 6:30-8:30 p.m. ኒውፖርት ሚል መ/ደ/ት/ቤት Newport Mill MS
2 አርብ፣ ዲሰምበር 4 ቨርቹወል ከቀትር 12:00 እስከ 1:00 p.m. ዙም (Zoom)
2 ሰኞ ፣ ዲሴምበር 7 ቨርቹወል ከቀትር 12:00 እስከ 1:00 p.m. ዙም (Zoom)
2 ማክሰኞ፣ ዲሰምበር 8 በአካል 6:30-8:30 p.m. ቤንጃሚን ባንከር መ/ደ/ት/ቤት Benjamin Banneker MS
2 ረቡዕ፣ ዲሰምበር 9 በአካል 6:30-8:30 p.m. ሮኪ ሂል መካከለኛ ደ/ት/ቤት Rocky Hill MS
2 ሐሙስ፣ ዲሰምበር 10 በአካል 6:30-8:30 p.m. ፓርክላንድ መ/ደ/ት/ቤት Parkland MS

የቀለም ኮድ፦ አረንጓዴ = በኦንላይን የሚደረግ ቨርቹዋል ስብሰባ፤ ሰማያዊ = በአካል የሚደረግ ስብሰባ

ጁላይ 16 ከተካሄደው የትምህርት ቦርድ ስብሰባስላይዶችን እና ቪድኦ በማየት ይበልጥ ግንዛቤ ያግኙ።

 

በዚህ አድራሻ ኢሜል አድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org