Community Update

ጃኑወሪ 4, 2022

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ማህበረሰብ፡-

መልካም የዊንተር ዕረፍት ጊዜ እንዳሳለፋችሁ ተስፋ እናደርጋለን። በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር በካውንቲአችን፣ በስቴቱ እና በሀገሪቱ እየጨመረ በሄደ ቁጥር ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች ደህንነቱ የተጠበቀ አመቺ የትምህርት እና የስራ ሁኔታ ለማሰናዳት ቁርጠኛ መሆናችንን ልናረጋግጥልዎ እንፈልጋለን። ይህ መልእክት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ በተማሪዎች እና በሰራተኞች መካከል እየጨመረ ያለ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሁኔታዎችን ተፅእኖ ለመቀነስ በሚቀጥሉት ሳምንታት የሚወስዳቸውን እርምጃዎች ያጠቃልላል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መረጃ
ሰኞ ጃኑወሪ 3 ከጠዋቱ 6 a.m. ድረስ በክረምት እረፍት ወቅት ከ MCPS ተማሪዎች እና ሰራተኞች ሪፖርት የተደረጉ 5,680 በወረርሽኝ የመጠቃት ሁኔታዎች ነበሩ፣ እሁድ ጃኑወሪ 2 በአንድ ቀን ሪፖርት የተደረጉ ሁኔታዎችን ጨምሮ፥ የፖዚቲቭ ሁኔታዎችን ቁጥር ማየት ይችላሉ። በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት የዊንተር ዕረፍት ጊዜ ሪፖርት በዚህ ሊንክ ይታያል።

ዕለታዊ የመረጃ ክትትል
በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት በየቀኑ ሪፖርት የተደረጉ ፖዚቭ ሁኔታዎች ቁጥር በ ኮቪድ-19 ዳሽቦርድ ከረቡዕ፣ ጃንዋሪ 5 ጀምሮ በእያንዳንዱ የትምህርት ቀን በየቀኑ 7 p.m. ላይ ይገለጻል። ዳሽቦርዱ ላይ በጠቅላላ ፖዚቲቭ ሁኔታዎችን እና ራስን ስለ ማግለል (በኳራንቲን መቆየት) በየሳምንቱ ሪፖርት ማድረጉ ይቀጥላል። ቤተሰቦች እና ሰራተኞች ፖዚቲቭ ሁኔታዎችን በዚህ ቅጽ ሪፖርት ማድረጋቸውን መቀጠል አስፈላጊ ነው። መረጃውን በኤሌክትሮኒክስ ማስተላለፍ ካልቻሉ ወደ ትምህርት ቤትዎ ሊደውሉ ይችላሉ።

ትምህርት ቤት በተናጠል ወደ ቨርቹወል ትምህርት የሚሸጋገርበት ሁኔታ
በ MCPS ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች በአካል መማር እንዳለ ይቆያል። ነገር ግን፣ ከሜሪላንድ የጤና ዲፓርትመንት በተገለጸው መሠረት በ14 ቀናት ውስጥ 5% ወይም ከዚያ በላይ ንክኪ የሌላቸው ተማሪዎች/መምህራን/ሰራተኞች በኮቪድ-19 ከተያዙት ውስጥ (ቢያንስ 10 ተማሪዎች/መምህራን/ሰራተኞች) ንክኪ የሌላቸው ስለመሆኑ ከተረጋገጠ ትምህርት ቤት ለ14 ቀናት ወደ ቨርቹወል ትምህርት መሸጋገር አለበት። እባክዎን የ 5% ገደብ የትምህርት ቤት መዘጋትን እንደማያስከትል ያስተውሉ፥ ሊታሰብበት የሚገባው ዋናው ነገር በትምህርት ቤት ውስጥ የቫይረስ ስርጭት ደረጃ ነው።

ወደ ቨርቹወል ትምህርት ለመሸጋገር ውሳኔ ከተወሰነ ወላጆች እና አሳዳጊዎች እንዲያውቁ ይደረጋል። MCPS ወደ ቨርቹወል ትምህርት የሚሸጋገሩ ትምህርት ቤቶች ከተወሰነው የ 14-ቀን ቨርቹወል ትምህርት በኋላ በአካል እንዲመለሱ ማድረግ ይፈልጋል።

ትምህርት ቤት ወደ ቨርቹወል ትምህርት መሸጋገሩን ለመወሰን ግምት ውስጥ መግባት ያለባቸው ነገሮች፦
አንድ ትምህርት ቤት ወደ ቨርቹወል ትምህርት መሸጋገሩን በሚወስኑበት ጊዜ ታሳቢ የሚደረጉ ቁልፍ ነገሮች ፖዚቲቭ የሆኑ የተማሪዎችን ብዛት ያካትታሉ። የምርመራ ውጤታቸው ፖዚቲቭ የሆነ ሰራተኞች ብዛት፣ በኳራንቲን ያሉ ተማሪዎች ብዛት፣ከኮቪድ ጋር በተያያዙ መቅረቶች ምክንያት በትምህርት ቤቱ ውስጥ ያሉ የሰራተኞች ብዛት፣ እና በትምህርት ቤት እና በማህበረሰብ ውስጥ የቫይረሱ ስርጭት ደረጃዎች ይታያሉ።

በተጨማሪም፣MCPS በክፍል ውስጥ የሚያስተምሩ ሰራተኞች፣ የአውቶቡስ ሹፌሮች እና የምግብ አገልግሎት ሰራተኞች መገኘትን ጨምሮ ተግባራዊ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ ማስገባት አለበት።

በትምህርት ቤቶች የኮቪድ-19 ደረጃዎች

በእያንዳንዱ ትምህርት ቤታችን ውስጥ ያለውን የኮቪድ-19 ደረጃ ለመለየት፣ MCPS ትምህርት ቤቶችን በሶስት፣ ባለ ቀለም ኮድ ምድቦች ከፋፍሏቸዋል - አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ።

green circleአረንጓዴ/Green
አረንጓዴ ተብለው በተመደቡ ትምህርት ቤቶች ከ 3% በታች የሆኑ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ባለፉት 14 ቀናት ውስጥ በኮቪድ-19 መያዛቸውን ሪፖርት አድርገዋል።

yellow circleቢጫ/Yellow
በቢጫ በተመደቡ ትምህርት ቤቶች ከ3% በላይ እና ከ5% በታች የሆኑ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ባለፉት 14 ቀናት ውስጥ በኮቪድ-19 መያዛቸውን ሪፖርት አድርገዋል። በእነዚህ የትምህርት ቤት ማህበረሰቦች ውስጥ ያለው የኮቪድ-19 ከፍ ያለ ደረጃ ማለት ቀይ ምድብ ወደሚያደርጋቸው 5% ደረጃ እየተቃረበ ነው።

red circleቀይ/Red
በቀይ በተመደቡ ትምህርት ቤቶች ከ5% በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ባለፉት 14 ቀናት ውስጥ በኮቪድ-19 መያዛቸውን ሪፖርት አድርገዋል።

ትምህርት ቤቶች 5% ደረጃ ላይ ሲደርሱ - እና በቀይ ምድብ ውስጥ ሲገቡ - MCPS መወሰድ ስላለባቸው ቀጣይ ደረጃዎች ከ DHHS ጋር ይወያያል፣ ይህም ትምህርት ቤቱ ወደ 14 ቀናት ቨርቹወል ትምህርት የመሸጋገር ሁኔታን ይጨምራል። ወደ ቨርቹወል ትምህርት የሚደረግ ሽግግር አውቶማቲክ አይደለም።

 የቨርቹወል ማስተማር - መርሐግብር እና እቅድ ማውጣት

  • አንድ ትምህርት ቤት ወደ ቨርቹወል ትምህርት ከገባ፣ የቨርቹወል የትምህርት ቀን በአካል ከመማር ጋር በተመሳሳይ ሰዓት ይጀመራል እና ያበቃል፣ እና የማስተማሪያ መርሃ ግብሩ/ብሎኩ ከተለመደው በአካል-የትምህርት ቀን ጋር በጣም ተመሳሳይ ይሆናል።
  • አስተማሪዎች ሁሉንም ቨርቹወል ትምህርቶችን በቀጥታ ስርጭት (በተሣለጠ ሁኔታ) ያስተላልፋሉ።
  • ተገቢ የስክሪን እረፍት ጊዜ እና ለምሳ እረፍት በእያንዳንዱ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ላይ ጥቂት ማስተካከያዎች ሊኖሩ ይችላሉ።
  • በ14ቱ የካለንደር ቀናት ቨርቹወል ትምህርት የመጀመሪያ ቀን፣ የ MCPS ሰራተኞች በቀጥታ ስርጭት ለሚተላለፍ ትምህርት ይዘጋጃሉ። በዚህ አንድ ቀን መምህራን ለተማሪዎች ራሱን የቻለ (የተቀናጀ) ስራ ሊሰጧቸው ይችላሉ።
  • የአንደኛ ደረጃ አስተማሪዎች እያንዳንዱ ተማሪ Chromebook እንዳለው/እንዳላት እና በካንቫስ (Canvas) ላይ መተግበሪያዎችን ለማግኘት የመክፈቻ እና የይለፍ ቃል እንዳለው/እንዳላት ያረጋግጣሉ።

MCPS ሁሉንም ሰራተኞች እና ተማሪዎች ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ቁርጠኛ በመሆኑ፥ ለተማሪዎቻችን ከፍተኛ ጥራት ያለው የትምህርት ተሞክሮዎችን መስጠቱን ይቀጥላል።

ምርመራ እና ክትባቶች
ፈጣን ምርመራዎች፡- MCPS ከፍ ያለ የኮቪድ-19 ደረጃ ካላቸው ትምህርት ቤቶች ጀምሮ በየትምህርት ቤቱ ላሉ ተማሪዎች ከካውንቲው ፈጣን ምርመራዎችን ይሰጣል - ቢጫ ወይም ቀይ ምድቦች ያሉት፣ ቢያንስ 3% ሰራተኞች እና ባለፉት 14 ቀናት ውስጥ ተማሪዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል ማለት ነው።

ለተማሪዎች በቤት ውስጥ የሚደረግ ምርመራዎችን መስጠት በእነዚህ የት/ቤት ማህበረሰቦች ውስጥ ትክክለኛ የኮቪድ-19 ደረጃዎችን በመግለጥ እና ማንኛቸውም ፖዚቲቭ የሆኑ ተማሪዎችን ከትምህርት ቤቱ አካባቢ በማስወገድ የትምህርት ቤቱን ማህበረሰብ ደህንነት ለማስጠበቅ ይረዳል።

  • ለምርመራው አዎ ይበሉ

ልጃቸው በትምህርት ቤት ምርመራ እንዲወስድ/እንድትወስድ ወላጆች ፈቃድ መስጠት አለባቸው። ይህን ቅጽ በመሙላት መፍቀድ ይችላሉ። ለተጨማሪ ዝርዝሮች፣ እባክዎ የእኛን "Say Yes to the Test" ድረ ገጽ ይጎብኙ

  • በ MCPS የሚካሄድ የኮቪድ ምመራ መጨመር

በትምህርት ቤቶች ውስጥ የዘፈቀደ እና ፈጣን የኮቪድ-19 ምርመራ የማድረግ አቅም ለማሳደግ MCPS ከምርመራ አቅራቢዎቹ ጋር እየሰራ ነው። ይህም በሚቀጥሉት ቀናት እና ሳምንታት ውስጥ ይከናወናል።

  • ክትባት ይውሰዱ።

MCPS ከ DHHS ጋር በመተባበር በት/ቤት የሚደረግ ነፃ የክትባት ክሊኒኮችን ለተማሪዎች ማቅረብ ይቀጥላል። ብዙውን ጊዜ በተመሳሳይ ክሊኒኮች ለአዋቂዎች የመጀመሪያውን፣ ሁለተኛውን እና የማጠናከሪያ (booster) ክትባቶች ሊሰጡ ይችላሉ። ተጨማሪ መረጃ በ ክትባት ድረ ገጽ ላይ ወይም በ DHHS ድረገጽ ላይ ይገኛል።

ስለ ማህበራዊ-ስሜታዊ ስጋቶች
ይህ ወቅት በእኛ ማህበረሰብ ውስጥ ላሉ በርካታ ሰዎች አስቸጋሪ ጊዜ ነው። Omicron variant በጣም በፍጥነት የሚተላለፍ በሽታ ነው። ወረርሽኙ ለብዙዎች የጭንቀት እና የፍርሃት ምንጭ ሆኖ ቀጥሏል እና MCPS ተማሪዎችን፣ ሰራተኞችን እና ቤተሰቦችን ወረርሽኙን እስከምናልፍ ሪሶርሶችን በመስጠት ለመደገፍ ይተጋል። ትምህርት ቤቶች አማካሪዎች እና ሳይኮሎጂስቶች ስላሏቸው ሁሉም ሰራተኞች ድጋፍ እና ሪሶርሶችን ለማግኘት የሰራተኛ ድጋፍ ሰጪ ፕሮግራም/Employee Assistance Programን እንዲያነጋግሩ ይበረታታሉ።

ጠቃሚ መረጃዎች

(እንግሊዝኛ/Englishስፓንሽኛ/Spanishቻይንኛ/Chineseፈረንሳይኛ/Frenchኮርያንኛ/Korean፣ ቬትናምኛ/Vietnameseአማርኛ/Amharic)

መጓጓዣ/ትራንስፖርት
ከፍተኛ የፖዚቲቭ ሁኔታዎች መከሰት አልፎ አልፎ የአውቶቡስ ሹፌር አቅርቦት ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል። በሚቀጥሉት ቀናት ሁሉንም መስመሮች ሙሉ በሙሉ ለማሟላት የተቻለ ጥረት ሁሉ ይደረጋል፥ ነገር ግን አሽከርካሪዎች ከአንድ በላይ መንገድ ማሽከርከር ያለባቸው የጉዞ ጊዜን ሊያራዝም እና በጠዋት እና ከሰአት በኋላ የጉዞ መስመሮች ሊዘገዩ ይችላሉ። ስለልጅዎ የአውቶቡስ መስመር ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት ወይም ያጋጠመዎትን ችግር ሪፖርት ማድረግ ከፈለጉ የትምህርት ቤት መጓጓዣ አውቶቢስ ጣቢያ ቁጥሮችን እነሆ፦

  • ቤተዝዳ የትምህርት ቤት መጓጓዣ አውቶቢስ ጣቢያ (Bethesda Depot): 240-740-6580
  • ክላርክስበርግ የትምህርት ቤት መጓጓዣ አውቶቢስ ጣቢያ (Clarksburg Depot): 240-740-4720
  • ራንዶልፍ የትምህርት ቤት መጓጓዣ አውቶቢስ ጣቢያ (Randolph Depot): 240-740-2610
  • ሼዲ ግሮቭ ኖርዝ የትምህርት ቤት መጓጓዣ አውቶቢስ ጣቢያ (Shady Grove North Depot): 240-740-6220
  • ሼዲግሮቭ ሳውዝ የትምህርት ቤት መጓጓዣ አውቶቢስ ጣቢያ (Shady Grove South Depot): 240-740-6210
  • ዌስት ፋርም የትምህርት ቤት መጓጓዣ አውቶቢስ ጣቢያ (West Farm Depot): 240-740-1851

 

ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ ለማመቻቸት በምናደርገው ጥረት ስለሚያደርጉልን ድጋፍ እናመሰግናለን።

 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools

ሌሎች መገልገያዎች-ሪሶርሶች

  • የአትሌቲክስ ፕሮግራሞች ዝርዝር መረጃ እዚህ ይገኛል።


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools