ወላጆች የእናንተን እርዳታ እንፈልጋለን!

አርብ፣ ፌብሩዋሪ 17

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከትምህርት ቤታቸው ስለተላከው ፀረ-ሴማዊነት ድርጊቶችን የሚያወግዝ ደብዳቤን በሚመለከት እጅግ በጣም ብዙ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች ባለፉት በርካታ ሳምንታት ወደ ቤት ተመልሰዋል። ጥቂት የማይባሉ ተማሪዎች በጠረጴዛ ላይ የናዚ ምልክቶችን ይስላሉ፣ አይሁዳውያን ጓደኞቻቸውን የቃላት ጥቃት ያደረሱባቸዋል፣ ፀረ-አይሁድ ንግግሮችን እያስተጋቡ በማህበራዊ ሚዲያ በሚተላለፉ ሥዕሎች ናዚዝምን አወድሰዋል። እነዚህ ድርጊቶች እኔን እና በጣም ብዙዎቻችሁን - አናደውናል፣ አስደንግጠውናል እና በድንጋጤ ላይ ጥለውናል።

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በሰራሁበት 21 አመት አጋማሽ፣የጥላቻ ማዕበል የትምህርት ስርዓታችንን ሲያውክ አይቻለሁ። እነዚህ የጥላቻ ድርጊቶች የእኛን ማንነታችንን በጭራሽ አይወክሉም። እኛ ከዚህ በጣም የተሻለ እሴት እንዳለን አውቃለሁ። እና እንደ ብዙዎቹ ተግዳሮቶች ሁሉ፣ ማህበረሰባችን ሊነሳ እና በጋራ ዋና እሴቶቻችን ላይ እንደሚሰራ አውቃለሁ፡ መማር፣ ግንኙነት፣መከባበር፣ ልቀት እና ፍትሃዊነት።

ትምህርት ቤቶቻችን እና ሰራተኞቻችን ለእያንዳንዱ ተማሪ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የሚመች ቤት ለመሆን በየቀኑ ቁርጠኝነት አለው። ነገር ግን ያንን ግብ ብቻችንን ማሳካት አንችልም።  እኔ እና እናንተ - ወላጆች፣ አሳዳጊዎች፣ ተንከባካቢዎች እና የማህበረሰብ መሪዎች - ከእኔ ጋር እንድትተባበሩኝ፣ አንድ የሚያደርገን ግኑኝነት ከሚከፋፍሉን ኃይሎች የበለጠ ጠንካራ መሆኑን እንድታስታውሱ እፈልጋለሁ።

ከተከታታይ ፀረ ሴማዊ ክስተቶች በኋላ፣መልዕክት የትምህርት ቦርድ ፕሬዝዳንት እና እኔ ጃኑዋሪ 21 ቀን ባስተላለፍነው መልእክት  “እነዚህን ተደጋጋሚ የጥላቻ ድርጊቶች በምንዋጋበት ጊዜ ፀረ-ሴማዊነት፣ ጥላቻና ዘረኝነት ምን እንደሆነና የሚያስከትለውን ጉዳት ለማሳወቅና ለማስረዳት እርስ በርሳችን ጥረት ማድረግ አለብን። ያ ተግዳሮት እውነተኛ እርምጃ እንድንወስድ ያነሳሳል። ነገር ግን ይህ አስቀያሚ ችግር እስካለ ድረስ፥ የበለጠ መስራት አለብን።

MCPS ምን እየሰራ ነው።
በዲስትሪክቱ ውስጥ ባሉ ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ውስጥ ያሉ መሪዎችና እኛ የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ እና ለማስተማር በአንድነት ቁመናል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መምህራን ተግዳሮቱን ወስደው ከፀረ-ስም ማጥፋት ሊግ (ADL) እና ከአይሁድ ማህበረሰብ ግንኙነት ምክር ቤት (JCRC) እና ሌሎችም ከአቀንቃኞች እና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ፀረ-ሴማዊነት ግንዛቤን ለማዳበር፣ ስለ ሆሎኮስት ከእድሜ ጋር የሚስማማ ስርዓተ ትምህርትን ለማሳደግ፣ ፀረ-ሴማዊ ድርጊቶችን ተከትሎ ማህበረሰቡን ወደነበረበት ለመመለስ የቤተሰብ አሳሳቢ ጉዳዮችን ያድምጡ።

ፀረ-ሴማዊ የጥላቻ አድሎአዊነት ድርጊት ሲከሰት፣ በተማሪ የሥነ ምግባር ደንብ መሠረት ከባድ እና ተገቢ ተግሣጽ እንሰጣለን። ነገር ግን እኛ ከተጋፈጥንበት ሁኔታ ለመውጣት አግባብ ያልሆነ ቅጣት አንቀጣም። በተቻለ መጠን ወደ ማስተማር መዞር አለብን - ምክንያቱም ተማሪዎቻችን በደንብ ሲያውቁ የተሻለ ይሰራሉ።

ግልጽ እንሁንና፣ የፀረ-ሴማዊነት - የጥላቻ ማሳያዎች - ተጠቂዎች አሏቸው።
የናዚን አገዛዝ እና መሪውን አዶልፍ ሂትለርን በማንፀባረቅ የተጻፉ ምልክቶች፣ እና ትርኢታዊ ምስሎች በአይሁዶች ላይ የሚያሳምሙ፣ አስፈሪ እና አሰቃቂ ናቸው። ይህም የሚያመለክተው ከ100 ዓመታት ባነሰ ጊዜ በስድስት ሚሊዮን አይሁዶች ላይ በቀጥታ የተፈፀመውን ስልታዊ፣ የዘር ማጥፋት ጅምላ ግድያ ያስታውሳል። ብዙ አይሁዳውያን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በአያቶች ወይም በሌላ ዘመዶቻቸው በህይወት በተረፉት እና በጠፉት ከሆሎኮስት ጋር ግላዊ፣ እና ቤተሰባዊ ግንኙነት አላቸው። የናዚ የሞት ካምፖች አስፈሪነት ቀደም ሲል ግልጽ ያልሆኑ ፀረ ሴማዊ ምስሎች፣ ምልክቶች እና ቃላቶች መበራከታቸው እና መደበኛ እንዲሆኑ መደረጋቸው -- ተመሳሳይ ምስሎች፣ ቃላት እና ምልክቶች ዛሬ በተማሪዎች እየተመሰለ ነው። ይህ ባህሪ የአይሁድ ተማሪዎች እና ሌሎች ብዙ ሰዎች በራሳቸው ትምህርት ቤቶች እና ማህበረሰቦች ውስጥ ስጋት እና ፍርሃት እንዲሰማቸው ያደርጋል።

ልጆቻችን የዚህ ሰለባ መሆን የለባቸውም
በከፍተኛ ደረጃ ለመማር እና ውጤት ላይ ለመድረስ ሁሉም ተማሪዎች በአካል እና በስሜት ደህንነት ሊሰማቸው ይገባል። በጥላቻ ድርጊቶች ምክንያት የሚፈጠር ጭንቀት ወይም ህመም ተማሪዎች መልካምና ምርጥ ነገሮችን ለመማር እንዳይችሉ ይጋርዳቸዋል። ሁሉም ልጆቻችን፣ በማንኛውም ጊዜ፣ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆን አለበት። ማንም ሰው ሆን ተብሎም ሆነ ባለማወቅ በሌላው ድርጊት ተቀባይነት እንደሌለው ሊሰማው አይገባም።

በቤት ውስጥ ምን ማድረግ ይችላሉ
ቀላል ነው። በልጆቻችን ህይወት ውስጥ እንደ ታማኝ እና ተወዳጅ አዋቂ፣ ልጆቻችንን ለማስተማር ይቀላቀሉን። ተማሪዎቻችንን ለማስገንዘብ ጊዜ ይውሰዱ፡-

  1. ጥላቻ ስህተት ነው።
  2. በጥላቻ ምክንያት ተጠቂዎች ይኖራሉ
  3. ጥላቻ ይከፋፍለናል፥ እና
  4. ጥላቻ በሲቪል ማህበረሰብ ውስጥ መዘዝ አለው።

ልጆችዎን ጭፍን ጥላቻ፣ አድልዎ እና መገለል የጥላቻ ቃላት፣ የጥላቻ ምልክቶች፣ እና በትምህርት ቤት፣ በቤት ወይም በማህበረሰብ ውስጥ ቦታ እንደሌላቸው አስተምሯቸው። ለእንዲህ ዓይነቱ ጥላቻ መፍትሔ የሚመጣው ከጓደኝነት፣ ከፍቅር እና ከመከባበር ኃይል ነው።

ወላጅ እንደመሆንዎ መጠን፣ እርስዎ በዚህ ውስጥ ብቻዎን አይደሉም። በዚህ መልእክት ግርጌ ላይ ያሉት ብዙ መገልገያዎች በእነዚህ አስቸጋሪ ውይይቶች ሊረዱዎት ይችላሉ።

እርስ በርሳችን የተሻለ ነገር ለመስራት/ለማድረግ እንከራከር-እንነጋገር።
እንደ ማህበረሰብ ጮክ ብሎ፣ በግልፅ እና በጋራ ፀረ-ሴማዊነትን እና ሁሉንም የጥላቻ እና የዘረኝነት ድርጊቶችን መቃወም አለብን። ዘር፣ አስተዳደግ፣ የፆታ ማንነት፣ የፆታ ዝንባሌ ወይም ሀይማኖት ምንም ይሁን ምን አካታች እና አቃፊ ተቀባይ ስንሆን፣ በልዩነቶቻችን እንድንከፋፈል ከማድረግ ይልቅ ማህበረሰባችንን ወደ አንድነትና ወደ ሙሉ አቅማችን ለማድረስ አንድ እርምጃ እንቀርባለን። ያንን አቅም እንደምናገኝ አምናለሁ - ይህን ለማድረግ ከፈለግን ግን ለጥላቻ ቦታ አይኖረውም። ፀረ-ሴማዊነትን፣ ጥላቻን እና ዘረኝነትን ለማውገዝ በአንድነት እንቁም። ይህን አብረን እናድርግ።

ከመልካም ወዳጅነት ጋር
Dr. Monifa B. McKnight ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. ማክናይት
Superintendent of Schools የት/ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት
በቤት ውስጥ የሚደረግ ውይይትን የሚደግፉ ሪሶርሶች፡

  1. Policies and Regulations: Detail- Montgomery County Public Schools, Rockville, MD
  2. 5 Tips for Talking with Children About Anti-Semitism | JSSA
  3. Antisemitism Today
  4. ስለ ፀረ-ሰሚትክስ እና ዘረኝነት ማስተማርያ ቁሳቁሶች


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools