እንግሊዝኛ/English / ስፓንሽኛ/Español / 中文 / ፈረንሳይኛ/Français / ፖርቹጋልኛ/Português / 한국어 / ቬትናምኛ/tiếng Việt / አማርኛ
ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦
ለዊንተር ዕረፍት ስንዘጋጅ፣ ጉንፋን እና እንፍሉዌንዛ በከፍተኛ ሁኔታ የሚበረታበት ወቅት መሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋል! ኮቪድ-19፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ የጉሮሮ ህመም፣ የእጅ፣ የእግር እና የአፍና አፍንጫ መታፈን እና ሌሎች የተለመዱ ኢንፌክሽኖችን ጨምሮ በበርካታ ህመሞች ምክንያት በት/ቤቶቻችን የበርካታ ሰራተኞች እና የተማሪዎች መቅረት እየጨመረ መሄዱን ተመልክተናል። የአካባቢ ሆስፒታሎችም የመተንፈሻ አካላት ህመም ያለባቸውን በተለይም ለከባድ በሽታ ተጋላጭ የሆኑትን ህሙማን በመንከባከብ ላይ የተጠመዱ ናቸው። ይህ ትንንሽ ሕፃናትን እና ልጆችን፣ እንዲሁም አዛውንቶችን እና አንዳንድ የጤና እክል ያለባቸው ግለሰቦችን ያጠቃልላል።
መከላከል
የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቁ ቫይረሶችን እና ሌሎች ኢንፌክሽኖችን ለመከላከል በተለይም በጣም ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ አባሎቻችን ጥበቃ እና ጥንቃቄ ለማድረግ የጤና አጠባበቅ ልማዶችን መከተልና ተግባራዊ ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው። በተደጋጋሚ እጅ መታጠብ፣ ሳል እና ማስነጠስ ሲኖር አፍና አፍንጫን መሸፈን፣ የጋራ እና በርካታ ሰዎች የሚጠቀሙባቸውን ንጣፎችን ማጽዳት እና በታመሙ ጊዜ በቤት ውስጥ መቆየት የበሽታ ስርጭትን ለመከላከል ይረዳል። እንደ ተጨማሪ የመከላከያ ዘዴ ጭምብል ማድረግ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቁ ቫይረሶችን ስርጭት ለመቀነስ ይረዳል፣ እናም የበሽታው ምልክቶች ሲኖሩ የበለጠ ተጋላጭ በሆነ ማንኛውም ሰው አጠገብ እንዳይሆኑ ጥሩ ስለሚሆን ለበሽታው መከላከል ጥንቃቄ ማድረግ ይጠቅማል። የእረፍቱን ወቅት ተከትሎ፣ ሰራተኞች እና ተማሪዎች በቅርብ ጊዜCDC ባዘጋጀው መመሪያ መሰረት ሰዎች ኮቪድ-19 ከያዛቸው ጭምብል እንዲያደርጉ ይጠየቃሉ። ለተጨማሪ መረጃ የእኛን የኮቪድ-19 መረጃ ድረገጽ ይጎብኙ።
ክትባት ወሳኝ የመከላከያ ስልት ነው፣ ስለሆነ፣ አሁንም የጉንፋን ወይም የኮቪድ-19 ክትባት ለመውሰድ ገና አልረፈደም። አንዳንድ ሰዎች የመተንፈሻ አካል በሽታዎችን ለመከላከል "Respiratory Syncytial Virus (RSV)" ክትባት መውሰድ ሊያስፈልጋቸው ይችላል። ስለ ወቅታዊ ክትባቶች ተጨማሪ መረጃ በእኛ ድረገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
ህክምና
ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸው ሰዎች የመተንፈሻ አካል በሽታ ምልክቶች ካሏቸው በፍጥነት የጤና እንክብካቤ ወደሚያገኙበት መሄድ አለባቸው። ለጉንፋን እና ለኮቪድ-19 ኢንፌክሽን የሚደረጉ ሕክምናዎች በሽታው ጉዳት ከማድረሱ አስቀድሞ ሲሰጡ በጣም ጠቃሚ ናቸው። የቤት ውስጥ የህክምና ምርመራ ፕሮግራም ነፃ የቴሌ ጤና ምርመራ ቀጠሮዎችን ስለሚሰጥ ጉንፋን ወይም ኮቪድ-19 ፖዚቲቭ ለሆኑ አዋቂዎች ህክምና ማኘትና መድኃኒት ማዘዝ ይቻላል።
በዓላቱ ለብዙዎች ውጥረት እና የተደበላለቁ ስሜቶችን ሊያመጡ ይችላል፣ ነገር ግን እንደገና ለመታደስ እና በአዎንታዊ መልኩ እርስ በርስ ለመገናኘት በጣም ጥሩ እድል ይሰጣሉ።
ስለ ዕለታዊ የጤና አጠባበቅ የበለጠ ጥንቃቄ በማድረግ ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር ጊዜ ማሳለፍ መልካም ነው። መልካም እንቅልፍ፣ ጥሩ አመጋገብ እና ንቁ መሆን ሁሉም ጤናማ ለመሆን እና ጥሩ ስሜት እንዲኖር መሰረት ናቸው። መልካም እና ጤናማ የዊንተር ዕረፍት ይሁንላችሁ!
Patricia Kapunan፡ M.D., MPH
MCPS Medical Officer
ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org