እንግሊዝኛ/English፣ / ስፓንሽኛ/español፣ / ቻይንኛ/中文 / ፈረንሳይኛ/français፣ / ፖርቹጋልኛ/Português፣ / ኮርያንኛ/한국어 / ቬትናምኛ/tiếng Việt፣ / አማርኛ/Amharic።
በሳምንቱ፣ የትምህርት ቦርድ የልዩ ትምህርት አገልግሎት ለሚያገኙ ተማሪዎች እና ለጀማሪ የብዝሃ ቋንቋ ተናጋሪ ተማሪዎች በተሻለ ሁኔታ የሂሳብ ስትምህርት ማግኘት እንዲችሉ ስለሚሻሻልበት ሁኔታ በዲስትሪክቱ ስትራቴጄክ እቅድ ላይ ተወያይቷል። የወደፊቱን ጊዜ ስንመለከት፣ ቦርዱ በስትራቴጂክ እቅድ አፈጻፀም እና 2025-26 የትምህርት አመት አቆጣጠር ላይ ሪፖርቶችን አድምጧል።
የእኛን ወቅታዊ መረጃዎች እየተከታተሉ ከሆነ፣ ቦርዱ በዚህ አመት የሂሳብ ትምህርትን በሚመለከት የተማሪዎችን አፈጻጸም ለማሻሻል ከፍተኛ ቅድሚያ ትኩረት መስጠቱን ይገነዘባሉ። የልዩ ትምህርት አገልግሎቶችን የሚያገኙ ተማሪዎች እና የመድብለ ቋንቋ ተማሪዎች የሂሳብ ትምህርት አፈፃፀም መስፈርቶችን በማሟላት ረገድ ብዙ ጊዜ አዳጋች ሁኔታ ያጋጥማቸዋል። እነዚህ ተማሪዎች በሂሳብ ስኬታማ እንዲሆኑ ለመርዳት፣ በሚገባ የተሟላ የሒሳብ ትምህርት አሰጣጥ መተግበር ያስፈልገናል።
ይህ አካሄድ ስለ ሂሳብ ትምህርት እና አገልግሎት የሚያገኙ ተማሪዎችን ፍላጎት በመረዳት ላይ ያተኮረ እንደሆነ የዲስትሪክቱ አመራሮች ገልፀዋል። የተማሪዎችን የሒሳብ ትምህርት እና እድገት በብቃት እንደሚደግፉ ለማረጋገጥ እነዚህን ስልቶች መተግበር ውጤታማ መሆናቸውን በየጊዜው መተንተን እና የማስተማር ዘዴዎችን ማስተካከል አስፈላጊ ነው።
ይህ ጠቃሚ ስራ የሚካሄደው በክፍል ውስጥ ብቻ አይደለም። ግንዛቤን ለማሳደግ፣ ኃላፊነትን ለማበረታታት፣ እና በጋራ መሥራትን ለማስፋፋት ህብረተሰቡን በውይይት ላይ ማሳተፍ ይጠቅማል። በተማሪዎች የሂሳብ ችሎታ ላይ እውነተኛ ማሻሻያ ለማድረግ እነዚህ እውነታዎች ሁሉ አስፈላጊ ናቸው።
አገልግሎቶቹን ለሚያገኙ ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማሻሻል MCPS ምን እያደረገ ነው?
አስተማሪዎች ውጤታማ ለመሆን የሚያስፈልጋቸውን በተለይ የተማሪዎች ፍላጎቶች ላይ የሚያተኩሩ ሙያዊ ትምህርቶችን መስጠት - ለአስተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስፈልጉትን መሳሪያዎችን ማቅረብ እና ስልቶችን ማስታጠቅ።
በዲስትሪክት አቀፍ ደረጃመመሪያዎች እና ድጋፎችን ከመስጠት አኳያ አስተማሪዎች አብረው እንዲሰሩ እና-ሁሉም የተማሪ ፍላጎቶች መሟላታቸውን ለማረጋገጥ ተገቢና አስፈላጊ የትምህርት መርጃዎችን መጠቀም።
በሂሳብ ትምህርት ውስጥ ልዩ የቋንቋ ቴክኒኮችን መጠቀም - ትምህርቱን ለሁሉም ተማሪዎች ምቹ ያደርገዋል።
በሂሳብ ትምህርት የተለያዩ ተማሪዎችን ስኬት እንዴት እንደምንደግፍ ለማወቅ፣ ሙሉውን አቀራረብ ይመልከቱ።
የትምህርት አመት የቀን መቁጠሪያ ማዘጋጀት ተማሪዎችን እና ሰራተኞችን የሚነካ ወሳኝ እና ውስብስብ ስራ ነው። በኦክቶበር 22 ስብሰባ ወቅት፣ የ MCPS ሰራተኞች ስለ 2025-2026 የትምህርት ቤት ቀን መቁጠርያ ሁለት አማራጮችን ቦርዱ እንዲወያይበት አቅርበዋል።
ሁለቱ እንዴት ይመሳሰላሉ?
ሁለቱም ረቂቅ የቀን መቁጠሪያዎች 181 የትምህርት ቀናት አላቸው፤ እና አዲስ የተጨመረ የተማሪዎች የሽግግር ቀን ያካትታሉ፣ ይሄ ትምህርት የማይሰጥበት ቀን ነው።
ልዩነታቸው ምንድነው?
የክረምት (ዊንተር) ዕረፍት ጊዜ (8 ቀናት ወይም 10 ቀናት) ሲሆን ለተማሪዎች የመጨረሻው የትምህርት ቀን (ጁን 17, 2026 ወይም ጁን 22, 2026) ይሆናል።
የቀን መቁጠሪያው እንዴት ተዘጋጀ?
የትምህርት ቤት ቀን መቁጠሪያ ያዘጋጀው ቡድን የቦርድ ፖሊሲ IDA በመከተል የሁሉንም ሰው ባህላዊ ዳራ በሚመለከት ከተማሪዎች፣ ከሰራተኞች፣ እና ከማህበረሰብ አባላት ጋር ተሳትፎ አድርጓል። ከዳሰሳ ጥናት ቡድኖች፣ ከትኩረት ቡድኖች፣ እና ከተለያዩ ኮሚቴዎች ግብረመልስ ሰብስበዋል።
የተማሪዎች ሽግግር ቀን ምንድን ነው? ይሄ አዲስ ነው።
ኦገስት 25, 2025 የተማሪዎች የሽግግር ቀን እንዲሆን ተለይቷል። ይህ ዲስትሪክት አቀፍ ትምህርት የማይሰጥበት ቀን ተማሪዎች ከትምህርት ቤታቸው ጋር ትውውቅና ግንኙነት እንዲኖራቸው በማድረግ የትምህርት አመቱን አጀማመር ቀላልና ምቹ በማድረግ ላይ ያተኮረ ነው።
ቀጥሎስ ምን ይደረጋል?
በሁኔታው ላይ አሁን የህዝብ አስተያየት እየተሰበሰበ ነው! ይህንን ቅጽ በመጠቀም ዛሬውኑ ሃሳብዎን ያካፍሉን።
ኖቬምበር 14 የቦርዱየፖሊሲ አስተዳደር ኮሚቴ ግብረመልሶችን ይገመግማል፤ እና ስለ ቀን መቁጠሪያው ይወያያል።
ዲሴምበር 5 ቦርዱ 2025-26 የትምህርት አመት የቀን መቁጠሪያን ያፀድቃል።
የበለጠ ማወቅ እፈልጋለሁ።
እንዲህ እንደሚሉ ተስፋ አድርገን ነበር። ስለ ቀን መቁጠሪያ ዝግጅት ሂደት እና ለቀጣዩ አመት ስለታቀዱት ሁለት ሁኔታዎች የበለጠ ለማወቅየቀረበውንይመልከቱ። እንዲሁም ሁለቱን የታቀዱ የቀን መቁጠሪያ ሁኔታዎች በዚህ ሰነድ (pdf) ላይ ማየት ይችላሉ።
በዚህ አመት፣MCPS እስከ 2026-2030 ድረስ ስራውን የሚመራበትን ስትራቴጂክ እቅድ እያዘጋጀን ነው። ሰራተኞች ከመጀመሪያው ምዕራፍ (1) የተገኙ ልምዶችን እና ቀጣይ እርምጃዎችን ያካተተ ማሻሻያ ለቦርዱ አጋርተዋል።
በመጀመሪያው ምዕራፍ (1)፣ ከተለያዩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ እና የማህበረሰብ አባላት ጋር መተሳሰር በሚከተሉት ሁኔታዎች ላይ ግብረ መልስ አሰጥቷል።
ተማሪዎች የሚያስፈልጓቸው ቁልፍ ክህሎቶች
አስፈላጊ ለውጦች
MCPS ያጋጠሙት ዋና ዋና ተግዳሮቶች
ምዕራፍ 2፣ እስከ ዲሴምበር ድረስ የሚዘልቅ ሲሆን፣ የምዕራፍ 1 መሪ ሃሳቦችን መነሻ-ምክንያት ትንተና ላይ ያተኩራል፣ ለአዲሱ እቅድ ግቦችን ያወጣል፣ እና የእድገት ስልቶችን ይመረምራል።
ሰራተኞች 2026-30 የስትራቴጂክ እቅድ ድረ-ገጽ፣የህዝብ ወቅታዊ መረጃ፣ እና የእቅድ ሂደቱ በሙሉ መስተጋብር የሚከናወንበትን ማዕከላዊ ቋት አስጀምረዋል። ህዝቡ ሂደቱን እንዲከታተል እና በሚገኙበት ጊዜ እንዲሳተፉ እናበረታታለን።
የስትራቴጂክ እቅዱን ለማዘጋጀት አመት የፈጀው ሂደት ከፀረ-ዘረኝነት ስርዓት አቀፍ ኦዲት ግንዛቤዎች ላይ በመነሳት የተገነባ እና ቦርድ ፖሊሲ ABA ውስጥ የተካተቱ ባህላዊ ምላሽ ሰጪ መመሪያዎችን በመከተል የተዘጋጀ ነው።
በብሬንዳ ቮልፍ/Brenda Wolff የሚመራው የቦርዱ ስትራቴጂክ እቅድ አዘጋጅ ኮሚቴ፣ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አቅጣጫ በተሰጡ ምክረሃሳቦች ላይ ከሱፐርኢንተንደንቱ ጋር በመተባበር ይሠራል። የኮሚቴው ሚና የረዥም ጊዜ እይታን፣ የአፈጻጸም ክትትልን፣ እና ተደራሽነትን ያካትታል። ቦርዱ በእቅድ ዝግጅት ሂደት ላይ መደበኛ ማሻሻያዎችን ይቀበላል፣ እና እቅዱ 2025 ላይ ይፀድቃል።
ስለ ምዕራፍ 1 ግብረመልስ እና በእቅዱ ላይ ስለሚያሳድረው ተጽእኖ የበለጠ ለማወቅ የቀረበውን ይመልከቱ።
ኦክቶበር 24, ሐሙስ - ፋሲሊቲዎች እና ድንበሮች የመጀመሪያ አቀራረብ እና የስራ ክፍለ ጊዜ
ኖቬምበር 4 - ሰኞ - ፋሲሊቲዎች እና ድንበሮችን በሚመለከት የማህበረሰብ ውይይት ክፍለጊዜ #1
ኖቬምበር 6 - እሮብ - ፋሲሊቲዎች እና ድንበሮችን በሚመለከት የማህበረሰብ ውይይት ክፍለጊዜ #2
ኖቬምበር 7 - ሐሙስ - መደበኛ የሥራ ስብሰባ
ኖቬምበር 8 - አርብ - ስለ ፋሲሊቲዎች እና ወሰን የስራ ክፍለ ጊዜ
አጀንዳዎችን፣የስብሰባ ግብአቶችን ለመከታተል በቀጥታ ስርጭት ወይም የተቀዳ የስብሰባ ውይይት ለመመልከት የእኛን ድረ ገጽ ይጎብኙ።
ፋሲሊቲዎች እና ወሰኖችን የሚምለከት የማህበረሰብ ውይይት ክፍለጊዜ ኖቬምበር 4 እና 6፣ ማህበረሰቡ ሃሳቡን እንዲያጋራ የተሰጡ እድሎች ናቸው። እነዚህ የማህበረሰብ ውይይት የሚካሄድባቸው ችሎቶች ከሱፐርኢንተንደንት የሚቀርበውን 2026 የካፒታል በጀት እና 2025-2030 የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን በሚመለከት የሚቀርቡ ሃሳቦችን ለመስማት የተዘጋጀ ነው። ሃሳብ ማቅረብ ለሚፈልጉ ሰዎች ምዝገባ ኦክቶበር 24 እኩለ ቀን ላይ ይከፈታል። የበለጠ ለማወቅ እና ሃሳብ ለማቅረብ መመዝገብ ከፈለጉ፣ ድረ ገጻችንይጎብኙ።
ማህበረሰቡ ከቦርዱ ጋር እንዲሳተፍ እና እንዲተባበር እናበረታታለን። በእኛ ድረ ገጽ ላይ መሳተፍ ስለሚችሉባቸው መንገዶች ያንብቡ።
ኢሜል ያድርጉልን፦ boe@mcpsmd.org
ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org