ለተሻለ ተደራሽነት - ብዙ አማራጮች

ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የታቀዱ ትላልቅ ለውጦች
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራሞች

MCPS በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ላሉ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የአካዳሚክ ፕሮግራሞችን ተደራሽነት ለማስፋት አዲስ ዘይቤ አቅርቧል። እነዚህ ለውጦች የተነደፉት አንድ ግብ በማሰብ ሲሆን፡ ብዙ ተማሪዎች የትም አካባቢ ቢኖሩ የሚፈልጉትን — እና የሚገባቸውን የመማር እድል እንዲያገኙ ለማስቻል ነው።

ወደ ዝርዝሩ ስንግባ፣ እያጋጠመን ያለው የተለመደው አይነት አቅርቦት እና የፍላጎት አመጣጣም ችግር ነው፡ በጣም ብዙ ተማሪዎች በጣም ጥቂት መቀመጫዎችን እያሳደዱ፣ በረጅም ርቀት መጓጓዣዎች እየተመላለሱ እና የፕሮግራም ጥራት አለመስተካከል እና ተደራሽ አለመኖር ናቸው። በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ለየት ያሉ ፕሮግራሞችን ለመከታተል ይመለከታሉ፣ ነገር ግን ያሉት በጣት የሚቆጠሩ ክፍት ቦታዎች ስለሆኑ፣ አብዛኛዎቹ የፍላጎታቸውን ሳያገኙ ወደጎን ይቀራሉ። ይህ ብርቱ ጉዳይ ስለሆነ — ማስተካከል እንፈልጋለን።

ተደራሽነትን የማስፋት እና መሰናክሎችን የማስወገድ አጣዳፊነትን በጉልህ የሚያሳዩ ሁለት እውነተኛ ምሳሌዎችን እንመልከት፦

  • የፑልስቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት – "Global Ecology Program" የ ዓለም አቀፍ ሥነ ምኅዳር ፕሮግራም
    • ያለው 90 መቀመጫዎች ብቻ ሲሆን ከ 800 በላይ ተማሪዎች አመልክተዋል።
  • ሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት – "Countywide International Baccalaureate Program" ካውንቲ አቀፍ የዓለም አቀፍ የባካሎሬት ፕሮግራም
    • ያለው 125 መቀመጫ ብቻ ሲሆን 1,000 ማመልከቻዎችን ተቀብሏል (25 መቀመጫ ብቻ ለአካባቢው ተማሪዎች የተያዘ ነው)።
    • 141 አመልካቾች ያቀረቡት በቀጥታ መጋቢ ት/ቤት ከሆነው ከጁሊየስ ዌስት መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ናቸው።
    • አብዛኛዎቹ የተመዘገቡ ተማሪዎች በካውንቲው ውስጥ ካሉ ሌሎች አምስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የቀረቡ ናቸው፣ አብዛኛዎቹ ያቀረቡት በካውንቲው ውስጥ ካሉ ሌሎች አለም አቀፍ የባካሎሬት ፕሮግራሞችን ያለፉ ተማሪዎች ናቸው።
    • ተማሪዎችን ወደ ፕሮግራሙ ለማጓጓዝ 24 አውቶቡሶች ያስፈልጋሉ።

ለእነዚህ በመመዘኛ-ለሚገቡ ፕሮግራሞች የሚያመለክቱ ተማሪዎች የሚለዩት በጠባብ የአካዳሚክ አፈጻጸም ብልጫ ነው።  ስለዚህ የጎበዝ ተማሪዎችን የማደግ እድል የመንፈግ ልምዳችንን የምንቀጥለው ለምንድነው?

ያለው ፍላጐት ካለው ተደራሽነት እጅግ የላቀ ነው፣ ይህም በትምህርት ስርአቱ ላይ ኢፍትሃዊነትን እና የሎጂስቲክስ አቅርቦት ማነስን እንደሚፈጥር እነዚህ ምሳሌዎች በግልጽ ያረጋግጣሉ። ብቃት እና ጉጉት ያላቸው ተማሪዎችን ለማገልግለል ባለመቻላችን ፍላጎታቸውን ሳናሟላ የተወሰኑ ጥቂት መቀመጫዎችን ብቻ ለማገልገል አውቶቡሶች ካውንቲውን እያቋረጡ እንዲመላለሱ እየተደረገ ነው—ይህ መጥፎ አሠራር ነው። ሪጅናል ፕሮግራሞቻችንን በማስፋት እና ከፍ በማድረግ የተማሪዎችን ፍላጎት ማሟላት፣ አላስፈላጊ ጉዞን መቀነስ እና ለሁሉም ተማሪዎች የበለጠ ፍትሃዊ ተደራሽነት እንዲኖር ማድረግ እንችላለን።

ጉዳዩን በጥልቀት እንመልከት፦

እነዚህ ምክረሃሳቦች ጠንካራ ፕሮግራሞቻችንን ስለማስወገድ አይደሉም። ይልቁንስ እውነታው ተቃራኒው ነው። ይልቁንም በሦስት ቁልፍ ግቦች ላይ ያተኮሩ ናቸው፦ 

  • የአሁኑን ፕሮግራሞቻችንን እና የኮንሶርሽያ ስኬቶችን በማጎልበት ለተጨማሪ ተማሪዎች ሰፊ ተደራሽነት እንዲኖር ማድረግ።

  • ለተማሪዎች በመኖርያቸው አቅራቢያ ፕሮግራሞችን መፍጠር እና በአካባቢያቸው ትምህርት ቤት ክልል እንዲማሩ ማድረግ።

  • በዲስትሪክቱ ውስጥ የፕሮግራም አማራጮችን ማስፋፋትበቁልፍ የትምህርት ጭብጦች ላይ የተመሠረቱ ጠንካራ ኮርሶችን አቅርቦት እና ፕሮግራሞችን በሁሉም አካባቢዎች እና ክልሎች ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ።

የፕሮግራሙ እድሎች ምንድናቸው?

ይህ ሞዴል በማህበረሰብ አስተያየት እና በአምስት የትምህርት መርሃ ግብሮች ላይ የተመሰረተ ነው። እነዚህ አምስት የአካዳሚክ መርሃ ግብር መሪ ሃሳቦች የሚከተሉት ናቸው፦

  • የሕክምና ሳይንስ እና የጤና እንክብካቤ
  • ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና፣ እና ሂሳብ
  • ኢንተርናሽናል ባካሎሬት፣ ሰብአዊነት፣ እና ቋንቋዎች
  • ትምህርትን ጨምሮ አመራር እና ህዝባዊ አገልግሎት
  • ትወና እና ኪነጥበብ፣ ንድፍ/ዲዛይን፣ እና ኮሙኒኬሽን

እያንዳንዱ ፕሮግራም መንገድ የተማሪን ፍላጎት ለማሳካት እና ለድሕረ-ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ዝግጁነት ጥሩ እድሎችን ለመፍጠር ይጠቅማሉ። ለተማሪዎቻችን በምንሰጠው የመሸጋገርያ እድሎች ላይ በመመዘኛ መስፈርት ላይ የተመሰረቱ ፍላጎቶችን እና የተማሪዎችን ዝንባሌና ፍላጎቶች ለማሟላት ያለንን ግልፅ ተነሳሽነት እናረጋግጣለን። እነዚህ ፈለጎች የኢንዱስትሪ ሰርተፊኬቶችን፣ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ የሆኑ ልዩ እድሎችን፣ እና ከትምህርት ቤት ውጭ ያሉ ተጓዳኝ የመማር ተሞክሮዎችን (የሥራ ልምምድ እና አገልግሎት) የመሳሰሉትን ያካትታሉ። 

ቀደም ሲል MCPS ውስጥ ባሉን ተቋሞች፣ እነዚህ ፕሮግራሞች የትምህርት ቤት አቅምን ግምት ውስጥ በማስገባት በአጠቃላይ ወይም በከፊል በሪጅን ተከፋፍለው ሊሰጡ ይችላሉ (ማለትም፦ ከላይ የተዘረዘሩት ፕሮግራሞች በሙሉ ወይም በከፊል ሊሰጡ ወይም በፍላጎት እና በዝንባሌ ላይ ተመስርተው ተከፋፍለው ሊወሰዱ ይችሉ ነበር፤ ለምሳሌ፡  ቪዥዋል እና የትወና ኪነጥበብ በአንድ ሪጅን ውስጥ በአንድ ትምህርት ቤት እንደ አንድ ፕሮግራም ወይም ቪዡዋል ኪነጥበባት ፕሮግራም ብቻ በአንድ ትምህርት ቤት እና ፕሮግራም ተከፋፍሎ ሲሰጥ ቆይቷል)።

ይህ ለውጥ የሚከናወነው በጊዜ ሂደት ነው፦

በእነዚህ ፕሮግራሞች ውስጥ የተመዘገቡ ተማሪዎች ቤተሰቦች በአሁኑ ጊዜ ስጋት ሊኖራቸው እንደሚችል እንረዳለን። እባክዎን የአተገባበሩ የጊዜ ሰሌዳ በነባር የልዩ ወይም የኮንሶርሺያ ፕሮግራሞች ውስጥ ያሉትን ተማሪዎች በማያደናቅፍ ሁኔታ የተነደፈ መሆኑን ይወቁ። ለ 2031 የታቀዱትን ፕሮግራሞች ሙሉ በሙሉ በመተግበር በቅደምተከተል የሚስተካከልበትን አሠራር እያቀድን ነው። አሁን ባለው ፕሮግራም ውስጥ ያሉ ወይም በማዕከል የሚተዳደር ፕሮግራምን በሚቀጥለው አመት የሚቀላቀሉ ተማሪዎች ምርጫቸውን መሙላት ይችላሉ። ይህ በቅደምተከተል የሚተገበር የጊዜ ሠሌዳ 2027-2028 የትምህርት አመት 9ኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ይጀመራል እና 2030-2031 የትምህርት አመት ለሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ይሆናል። 

ስለታቀዱት ፕሮግራሞች እና ስለ አተገባበራቸው ሁሉም ቤተሰቦች የበለጠ እንዲያውቁ እናበረታታለን። እዚህ በይነመረብ ላይ በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎችን ሰነድ(ተደጋጋሚ ጥያቄዎች) ለመገምገም እና በየጊዜው የሚከናወኑ አዳዲስ ማሻሻያዎችን ለማግኘትየሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም ትንተና ድረ-ገጽ መጎብኘት ይችላሉ። በእኛ በኩል እዚህ ያልመለስናቸው ጥያቄዎች ካሉዎት በዚህ የግብረመልስ ቅጽ ጥያቄዎን ማቅረብ ይችላሉ።

ተደራሽነትን ማስፋት፣ አማራጮችን መስጠት፣ እና ይህንን ወደ መኖሪያ አቅራቢያ ት/ቤት በቅርበት እንዲሆን ማድረግ ሁሉም ተማሪዎች ለወደፊት ዝግጁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ MCPS ለሚያደርገው ጥረት ትክክለኛው እርምጃ ነው—በኮሌጅ፣ በስራ ሙያ፣ እና ለበለፀገ ህይወት የተዘጋጁ መሆናቸውን ማረጋገጫ መንገድ ነው።

ይበልጥ በጥልቀት እንመልከት፦

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ


በዚህ አድራሻ ኢሜል አድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org