MCPS የሰራተኛ ዳራ ቁጥጥር፦
ልጆቻችሁ በትምህርት ቤት ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው።

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች እና ማህበረሰብ፣

ይህንን መልክት የማስተላልፈው ከብዙ አመታት በፊት መፍትሄ ማግኘት ስለነበረበት በት/ቤቶቻችን ዲስትሪክት ውስጥ ወሳኝ ስለሆነ ጉዳይ አስፈላጊ መረጃ ለእናንተ ለማካፈል ነው። ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የዋና ኢንስፔክተር ጽ/ቤት ዛሬ የተለቀቀው ዘገባ በትምህርት ድስትሪክታችን ውስጥ ስላለው የማንነት የጀርባ ታሪክ ማጣራት ሂደት ጠቃሚ ጥያቄዎችን አንስቷል። እነዚህ ጉዳዮች ቢያንስ ከ 2019 ጀምሮ በትምህርት ቤቶች አመራር ስርዓታችን ውስጥ ከታዩት ክፍተቶች የመነጩ ሲሆን ይህም ቀደም ባሉት አስተዳደሮች በአግባቡ ስላልተፈቱ ነው። አሁን እነዚህን ጉዳዮች በሙሉ እየገለጥናቸው ስለሆነ እነሱን ለማስተካከል ፈጣን እና ጠንካራ እርምጃዎችን እየወሰድን ነው። 

ዋናው ነገር ይህ ነው።

አዎ—ልጆቻችሁ ሠላም ናቸው። እና ማወቅ ያለብዎት ነገር ይሄ ነው።


1. እያንዳንዱ የ MCPS ሰራተኛ የጀርባ ታሪክ ምርመራ ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል?

አዎ እያንዳንዱ የ MCPS ሰራተኛ እንደ ስራ ሁኔታው(ዋ) በጣት አሻራ ላይ የተመሰረተ የወንጀል ታሪክ ምርመራ ማጠናቀቅ አለበት። የማጣራት ሥራው እስኪጠናቀቅ እና የሚመለከተው ደንብ እና ፖሊሲ እስኪያሟላ ድረስ ማንኛውም ሰራተኛ ስራ እንዲጀምር አይፈቀድለ(ላ)ትም።


2. የእያንዳንዱ የ MCPS ሰራተኛ የወንጀል ታሪክ ምርመራ ተደርጎ ነበር?

ኣዎ አሁን በሥራ ላይ ያሉት የ MCPS ሰራተኞች እያንዳንዳቸው የወንጀል ታሪክ ምርመራ አጠናቀዋል። MCPS የሥራ ቅጥር ከመጀመራቸው በፊት ይህ ሁልጊዜ መደረግ ያለበት ጉዳይ ነው።


3. ታዲያ…ትልቅ ጉዳይ የሆነው ምንድነው?

ሁለት ነገሮች ትልቅ ቁምነር ናቸው።

መጀመሪያ፡በተሻለ ሁኔታ ተከታታይ ክትትል ማድረግ አለብን፣ እና አሁን ያንን እየሰራን ያለነው ከ 2019 በፊት የተቀጠሩ ሰራተኞች በሙሉ እንደገና ማጣራት ተደርጎላቸው RapBack በመባል ወደ ሚታወቀው FBI ቀጣይነት ያለው የክትትል ስርዓት መግባታቸውን ማረጋገጥ ነው። ይህ ስራ ሁሉንም ሰራተኞች በፍጥነት እና በጊዜ መርሐግብር ማጣሪያ ለማድረግ ሁሉን አቀፍ እቅድ ይዟል።

ሁለተኛ፡የህጻናት ጥበቃ አገልግሎቶች (CPS) ሰራተኞች በማንኛውም አይነት የልጅ ጥቃት ወይም በቸልተኝነት ተጠያቂ የሆኑበት ሪፖርት እንደሌለባቸው ለማረጋገጥ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ፖሊሲ ተጨማሪ ማጣራት እንዲደረግ ይፈልጋል። ይህ የማጣራት ሂደት ከረጅም ጊዜ በፊት ማደረግ የነበረበት ሲሆን፣ እነዚህን የማጣራት ሂደቶች ለማጠናቀቅ—በሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ በኩል የሚካሄደው—ከ MCPS ቅጥር ሁኔታ ጋር እኩል አልሄደም። አሁን ይህንንም ለማስተካከል እየፈለግን ነው፣ ነገር ግን በሁለቱ ኤጀንሲዎች መካከል ቀጣይነት ያለው ትብብር ያስፈልገዋል።

በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከተከሰቱት ቁልፍ ብልሽቶች መካከል 2020 ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት እንደገና የጣት አሻራ እና የማጣሪያ ምዝገባን ማቆም እና ማርች 2024 ከተነገረ በኋላ የስቴቱን የኦንላይን ፖርታል CPS የማጣራት ሥራ አለመተግበሩን ያካትታሉ። አሁን እነዚህን ችግሮች በአስቸኳይ እና በግልፅነት እየፈታናቸው ነው።

ስለዚህ ትልቁ ጉዳይ ይህ ነው፡ ባለፈው ጊዜ ሙሉ በሙሉ ወይም በቋሚነት ያልተሰራውን እያስተካከልን እንገኛለን፣ስለዚህ በፍጥነት፣ በግልጽነት፣በማስተካከል ላይ ትኩረት በማድረግ እየሰራን ነው።


በመካሄድ ላይ ያሉ ሌሎች አስፈላጊ እርምጃዎች እነሆ፦

  • ወቅታዊ የማጣራት ክትትል ማድረግ
    ጁላይ 2025 የተጀመረው አዲስ አሰራር ትምህርት ቤቶች የትኛውም የሥራ ተቋራጭ ወይም በጎ ፈቃደኛ ያለ በቂ ፍቃድ ስራ መጀመሩን በቅጽበት እንዲያረጋግጡ ያስችላቸዋል።
  • CPS ማቅረቢያ ማዘመን
    የድሮውን የወረቀት አሠራር ሂደት በዲጂታል ሥርዓት ለመተካት ፈጣን፣ ይበልጥ የተቀናጀ፣ CPS የበፊት ዳራ ማጣሪያ ሂደት ለማዘመን Montgomery County Child Welfare Services ጋር ሠርተናል። ይህ CPS የማጣራት ሂደቱን በሚያስደንቅ ሁኔታ እንዲቀንስ አድርጓል—በፊት ከነበረው 4-6 ሳምንታት ወደ ጥቂት የስራ ቀናት እንዲቀንስ አድርጓል።
  • ስልጠና እና ክትትል ይደረጋል
    ሰራተኞቻችንን በማሰልጠን ላይ ነን እና ለማንኛውም ሰው የኋላ ታሪክን ለሚቆጣጠር የተጠያቂነት አሰራር እየዘረጋን ነው።
  • የቅጥር ፍላጎትን የሚያሟላ የማጣራት ሂደት አጋርነት
    ሌላ ኤጀንሲ CPS የማጣራት ተግባር ስለሚያካሂድ፣ አቅምን ለመጨመር እና የኋላ ተጠራቅሞ የቆየ ሥራን ለመቀነስ ከካውንቲ እና የስቴት ባለስልጣናት ጋር ሠርተናል። እኛ — በህጋዊ መንገድ — እነዚህን የማጣራት ሥራዎች እራሳችን ማከናወን አንችልም፣ ነገር ግን በየደረጃው አሠራሮቹ እንዲሻሻሉ እናበረታታለን።
  • ለሁሉም ሰራተኞች እንደገና መታወቂያ መስጠት
    ሁሉም ሰራተኞች እንደገና ማጣሪያ ከተደረገ በኋላ አዲስ የመታወቂያ ባጆች ይሰጣቸዋል። አዲሶቹ የመታወቂያ ባጃጆች በትምህርት ቤት ደረጃ ደህንነትን ለማጠናከር እና ወቅታዊ ማጣሪያ የተደረገላቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ተጨማሪ የፎተግራፍ መረጃዎች ይኖራቸዋል።

ሙሉ የድርጊት መርሃ ግብሩን እና ለኢንስፔክተር የላኩትን ደብዳቤ እዚህ ማንበብ ይችላሉ። 

እኔ እና ቡድኔ በእነዚህ እርምጃዎች ላይ የምናደርገውን እርምጃ በየጊዜው እናሳውቃለን፣ አንዳንዶቹ በአሁኑ ጊዜ በመካሄድ ላይ ናቸው፣ እና አንዳንዶቹ ደግሞ ጊዜ የሚወስዱ ናቸው። ስርዓታችንን ለመጠገን እና ለማጠናከር ትክክለኛውን ስራ ለመስራት ሙሉ በሙሉ ቁርጠኞች ነን፣ እና እድገታችንን በእውነተኛ ሁኔታ እና በጠንካራ እርምጃዎች በማሳየት እምነትን መገንባት ብቸኛው መንገድ መሆኑን እናውቃለን። ይህንን ተሻግረን የተሻልን እንሆናለን፤ ይህ የትምህርት አመት ጥሩ የትምህርት ዘመን ይሆናል። ይበልጥ ጠንካራ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ MCPS — አብረን እየገነባን ነው።

ከልብ

Thomas W. Taylor, EdD, MBA Superintendent of Schools
የት/ቤቶች ሱፐር ኢንተንደንት

ለበለጠ መረጃ ተዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች (FAQ) ሰነድ እዚህ ማየት ይችላሉ


በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org