ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች
በቅርብ ጊዜ በአካባቢውም ሆነ በመላ አገሪቱ እየተከናወኑ ያሉት የፌዴራል የኢሚግሬሽን ማስፈጸሚያ እርምጃዎች ለብዙ የማህበረሰባችን አባላት ስጋት መፍጠራቸውን እንገነዘባለን። ለአንዳንዶች፣ ዜናውን ማድመጥና መመልከት እንኳን ከባድ ሊሆን ይችላል። ይህንን የጻፍነው ባለፈው ዓመት እና በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ እንደገለጽነው፣ እሴቶቻችንን ለማጠናከር እና አንዳንድ ጠቃሚ መረጃዎችን ለእናንተ ለማጋራት ነው። በቀላል አነጋገር፣ ተማሪዎቻችንን እና ቤተሰቦችን ለመደገፍ ቁርጠኛ ነን።
ትምህርት ቤቶቻችን ለልጆች ደህንነታቸው የተጠበቀ እና አስተማማኝ ቦታዎች መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰራተኞች በየቀኑ ጠንክረው ይሰራሉ። እያንዳንዳቸው ተማሪዎች፣ የኢሚግሬሽን ሁኔታቸው ምንም ይሁን ምን፣ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ውስጥ ተቀባይነት አላቸው፣ ዋጋ አላቸው፣ እንክብካቤ ይደረግለቸዋል፣ እና የሚወደዱ ናቸው። ይህ በሜሪላንድ እና በመላው ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥም ተግባራዊ የሆነ ሕግ ነው።
ሁሉም ልጆች ሕዝባዊ ትምህርት የማግኘት መሠረታዊ መብት አላቸው፣ እና በፌዴራል ሕግ ድንጋጌ መሠረት እያንዳንዱ ልጅ ከመዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል (K-12) ትምህርት የማግኘት መብት ያለው/ያላት መሆኑን ያረጋግጣል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ በምዝገባ ወቅትም ሆነ በሌላ በማንኛውም ጊዜ ስለ ኢሚግሬሽን ሁኔታ አይጠይቁም። በፌዴራል ሕግ መሠረት የተማሪዎችን ግላዊነት እንጠብቃለን እንዲሁም በቤተሰብ የትምህርት መብቶች እና የግላዊነት ሕግ (FERPA) መሠረት የተማሪዎችን የመረጃ ፋይሎች እና የግል መረጃዎችን በጥብቅ እንጠብቃለን።
ዲስትሪክቱ የኢሚግሬሽን ወይም ሌላ የፌዴራል የህግ አስከባሪ እንቅስቃሴ በትምህርት ቤት አቅራቢያ ወይም በትምህርት ቤት ውስጥ ቢከሰት ግልጽ የሆኑ ተግባራዊ ሂደቶች አሉት። እነዚህ ሂደቶች የተነደፉት እንደሚከተለው ነው፦
የተማሪዎችን ደህንነት እና ሠላም ቅድሚያ መስጠት፣
ሕግ መከበሩን ማረጋገጥ፣ እና
ከቤተሰቦች ጋር ግልጽ የሆነ ግንኙነት ማድረግ።
ህጋዊ የፍርድ ቤት ትዕዛዞችን ማክበር ቢኖርብንም፣ MCPS በኢሚግሬሽን ማስፈጸሚያ እርምጃዎች ውስጥ አይሳተፍም። እናም የኢሚግሬሽን አስከባሪዎችን ወደ የትኛውም ትምህርት ቤቶቻችን በፍጹም አንጋብዝም። ይልቁንም የእኛ ኃላፊነት ሁሉንም ተማሪዎች ማስተማር እና ትምህርት ቤቶቻችን ለተማሪዎችና ለሠራተኞች አስተማማኝ ምቹ ቦታዎች መሆናቸውን ማረጋገጥ ነው።
ቤተሰቦች መረጃ እና አስተማማኝ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው እንረዳለን። MCPS ለቤተሰቦች "መብትዎን ይወቁ"/“Know Your Rights” መረጃ ለመስጠት፣ የህግ አገልግሎት ግብዓቶችን እና ከማህበረሰብ የድጋፍ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ለማገናኘት "CASA and the Gilchrist Immigrant Resource Center" የመሳሰሉ የማህበረሰብ አጋሮች ጋር ይሰራል። አብዛኛው መረጃ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ይገኛል።
ስለዚህ ጉዳይ ከወጣት የቤተሰብ አባላት ጋር መነጋገር አስቸጋሪ ሊሆን ቢችልም፣ እነዚህን ውይይቶች ለማገዝ ከሚታመኑ አጋሮቻችን እና MCPS ሪሶርሶችን እንዲያገኙእናሳስባለን።
ቤተሰቦች በቀጥታ MCPS አለም አቀፍ የተማሪዎች ምዝገባ እና መቀበያ ቢሮ ጋር በመገናኘት ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ እርዳታ ማግኘት ይችላሉ፣ ከዚያም ሰራተኞች መመሪያ ሊሰጡዋቸው እና ተገቢ ድጋፍ ወደሚያገኙበት ሊያገናኙዋቸው ይችላሉ። ይህንን ቢሮ የስልክ ቁጥር 240-740-4500 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፣ ወይም በዚህ አድራሻ ወደቢሮ በመሄድ ሊያገኟቸው ይችላሉ፦ Rocking Horse Road Center (RHRC), 4910 Macon Road - Suite 147, Rockville, MD 20852
የቪዲዮ መልዕክቱን ይመልከቱ
ስለ ቁርጠኝነቶቻችን፣ ፕሮቶኮሎቻችን፣ እና ሪሶርሶቻችን ተጨማሪ መረጃ እና ማረጋገጫ ለማግኘት የቪዲዮ መልዕክቱን እንዲመለከቱ እናበረታታዎታለን።
ከሠላምታ ጋር
Grace Rivera-Oven |
Thomas W. Taylor, EdD MBA |
የቤተሰብ ዝግጅት ሪሶርሶች Family Preparedness Resources
የስደተኛነት ሪሶርሶች Immigrant Resources
ልጆች ስለ ኢሚግሬሽን ማስፈጸሚያ እርምጃዎች የሚሰማችቸውን ስሜት እና ልምዶቻቸውን በተመለከተ ከልጆችዎ ጋር እንዴት መነጋገር እንደሚችሉ፦ UNICEF USA / How to Talk to Your Children About Their Feelings and Experiences Related to Immigration Enforcement Actions
ስለ ስደተኞች መብት የሚገልጹ ግብዓቶች፦ ACLU Immigrants Rights Resources
ስለ አሜሪካ የመምህራን ፌዴሬሽን/የተማሪዎችን ደህንነት መጠበቅ - መብቶችዎን ይወቁ፦ American Federation of Teachers / Protecting Our Students - Know Your Rights
የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ/ቤተሰቦችን በሙሉ መቀበል - ግብአቶች፦ Montgomery County Public Schools / Welcoming All Families - Resources
በሲልቨር ስፕሪንግ የሚገኝ የሉተራን ማህበራዊ አገልግሎቶች፦ Lutheran Social Services in Silver Spring
ቤት አልባነትን ለማስቆም እና ለመከላከል የሚሰጡ አገልግሎቶች፦ Services to End and Prevent Homelessness (SEPH)
የሜሪላንድ የስደተኞች እና ጥገኝነት ፈላጊዎች ቢሮ፣ ቦልቲሞር፦ Maryland Office for Refugees and Asylees (MORA) in Baltimore, MD
ዓለም አቀፍ ስደተኞችን የሚታደግ ኮሚቴ፣ ሲልቨር ስፕሪንግ፦ International Rescue Committee (IRC) in Silver Spring
ስደተኞች እና ለስደተኞች አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል - በጌትስበርግ፦ Immigrant & Refugee Outreach Center (IROC) in Gaithersburg, MD
የካቶሊክ የበጎ አድራጎት ማዕከል:- Catholic Charities Center
በዚህ አድራሻ ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org