MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
MCPS አርማ

አበይት ጉዳዮች

ኦገስት 27, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 
  የትምህርት አመት 2026-2027 ለተማሪዎች ስለተደረገላቸው አቀባበል

ኦገስት 25 የትምህርት አመት 2026-2027 መክፈቻ ላይ MCPS በሩን ከፍቶ 150,000 በላይ ተማሪዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት አቀባበል አድርጎላቸዋል። የትምሕርት ቀን ከመጀመሩ አንድ ቀን በፊት፣ ዲስትሪክቱ ሁለተኛውን አመታዊ የሽግግር ቀን አክብሯል (ፎቶዎችን እና ቪዲዮዎችን እንግሊዝኛ | ስፓንሽኛ ይመልከቱ)። 

በመጀመሪያው ቀን የተነሱ ፎተግራፎችን እና ቪዲዮችን እንግሊዝኛ | ስፓንሽኛ ይመልከቱ፣ እና በዚህ አመት MCPS ያለውን ቁርጠኝነት እና ትኩረት የበለጠ ያንብቡ። እናም፣ ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ቀን ላይ እንኳን ደህና መጣችሁ በሚል መልእክት ከተማሪዎች፣ ከሰራተኞች፣ እና ከሱፐርኢንቴንደንት ቴይለር ጋር ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ቀን ለማክበር ትንሽ ጊዜ ይውሰዱ።

 
  በጣም ሞቃት ይሆናል፣ በጣም ይሞቃል!

የአየር ሁኔታ ትንበያዎች በሚቀጥለው ሳምንት በጣም ሞቃታማ የአየር ሁኔታ እንደሚከሰት እየገለጹ ናቸው፣ ይሄ MCPS ባለው የአየር ሙቀት መቆጣጠሪያ/HVAC ሲስተሞች ላይ ተጨማሪ ጫና ይፈጥራል። የሙቀት መጠን ትንበያ 90ዎቹ ላይ ሲሆን፣ MCPS የህንፃዎቻችን ቡድን ምላሽ ለመስጠት በዝግጅት ላይ ናቸው፣ ነገር ግን የሙቀቱ መጠን በመቶ ዲግሪዎች ሲሆን ሕንፃዎቻችን እና በተለይም አሮጌ የሙቀት መቆጣጠሪያ ሲስተሞች ስላሉ፣ ችግሮች ቢከሰቱ ትዕግስታችሁን እንጠይቃለን። እንድንዘጋጅ እርዱን፦

  • በከባድ ሙቀት ሰውነት እንዳይጠወልግ፦ ብዙ ውሃ መጠጣት ያስፈልጋል።
  • ለሙቀት ጊዜ የሚሆን ልብስ ይልበሱ፦ ቀላል/ስስ እና ምቹ የሆኑ ልብሶችን ልበሱ።
  • በንቃት ተከታተሉ፡ ከመጠን በላይ ሙቀት ወይም ህመም ከተሰማችሁ እርዳታ መጠየቅ ያስፈልጋል።
  • መረጃዎችን ተከታተሉ፦ ስለ ማንኛውም የአየር ሙቀት ሁኔታ ወይም HVAC ሲስተም ችግሮች ካሉ እናሳውቃለን።
  • አትሌቲክስ፦ MCPS ከቤት ውጭ ለሚደረጉ ልምምዶች እና ዝግጅቶች የአየር ሙቀት-ደህንነት መመሪያዎችን ይከተላል።

አየሩ በጣም ሞቃት ይሆናል። እየተዘጋጀን ነው፣ እናም ሁሉም ሰው ዝግጁ እንዲሆን እንጠይቃለን።

 
  ደህንነቱ ወደተጠበቀ የትምህርት ዓመት በመሻገር ላይ ነን፡ ስለ ትምሕርት ቤት አውቶቡስ መስመሮች እና የደህንነት ምክሮች

የተማሪዎን የትምሕርት ቤት አውቶቡስ መስመር ለማወቅ ይፈልጋሉ? በትምህርት ቤትዎ አውደመረብ ገጽ ላይ ይገኛል። የጠዋት እና የከሰዓት የትምህርት ቤት አውቶቡስ መስመሮች በእያንዳንዱ የትምህርት ቤት ድረ ገጽ "የትምህርት ቤት መረጃ/School Information" ላይ ይለጠፋሉ። የትምህርት ቤት አውቶቡስ መስመሮች PDFs ህትመት ስለሚገኝ፣ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦

  • በስልክዎ ላይ ገልብጠውመጠቀም ይችላሉ።
  • በወረቀት አትመው ፍሪጅ ላይ መለጠፍ ይችላሉ።
  • አስቀምጠውትበትምህርት ዓመቱ በሙሉ ለመመልከት ቀላል ይሆንልዎታል።

በተጨማሪ፦ MCPS የአውቶቡስ መስመሮችን በሙሉ Division of Transportation Services ድረ ገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ፣ ይኼውም የማግኔት ፕሮግራምን፣ ኢመርሽን፣ እና ሌሎች ልዩ ፕሮግራሞችን ጭምር የሚያገለግሉ ስርዓት አቀፍ ማዕከላዊ መንገዶችን ያካትታል። ስለ መጓጓዣ/ትራንስፖርት ጥያቄ አለዎት? የተማሪዎን መታወቂያ፣ የት/ቤት አውቶቡስ መስመር ቁጥር እና የትምህርት ቤት ስም በመግለጽ የትራንስፖርት አስተዳዳሪዎን ያነጋግሩ።

ደህንነት የሚጀምረው ተማሪዎች አውቶቡስ ላይ ከመሳፈራቸው በፊት ነው

ተማሪዎችን በሠላም ወደ ትምህርት ቤት ማድረስ እና መመለስ የጋራ ኃላፊነት ነው። MCPS በየቀኑ ከ100,000 በላይ ተማሪዎችን የሚያገለግሉ ከ1,200 በላይ የት/ቤት አውቶቡስ መስመሮችን ያንቀሳቅሳል፣ ስለሆነም ጥቂት ቀላል እርምጃዎች የሁሉንም ሰው ደህንነት ለመጠበቅ ይረዳሉ።

  • የት/ቤት አውቶቡስ መስመርዎን ይወቁ። ቤተሰቦች በየቀኑ ጠዋት ከመውጣታቸው በፊት የተማሪዎቻቸውን የአውቶቡስ መስመርና ማቆሚያውን መመልከት፣ እና የጊዜ ሰሌዳውን ማጣራት አለባቸው። 
  • በአውቶቡስ ማቆሚያ ቦታ እና በአውቶቡስ ጉዞ ላይ ደህንነትን መጠበቅ ያስፈልጋል። ተማሪዎች ከመኪና መንገዱ መራቅ መራቅ አለባቸው፣ የአሽከርካሪውን መመሪያ መከተል ይጠበቅባቸዋል፣ አውቶቡስ ጉዞ ጀምሮ መድረሻው ላይ እስከሚቆምበት ጊዜ መቀመጥ እና ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮችን ማስወገድ አለባቸው።
  • አሽከርካሪዎች፦ለት/ቤት አውቶቡስ መቆም አለባቸው። በሜሪላንድ ሕግ መሠረት ሁልጊዜም በትምህርት ቤት አውቶቡሶችና ፌርማታዎች ዙሪያ ፍጥነት መቀነስ፣ የት/ቤት አውቶቡስ መቆሙን የሚያመለክት ቀይ መብራት ሲበራ እና የመቆም ምልክት ሲዘረጋ ህጉን ማክበር ይጠበቅባቸዋል።
  • በትምሕርት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ፣ በትራፊክ ፍሰት፣ በመንገዶች መጨናነቅ ወይም በተማሪዎች ፍላጎት ምክንያት አውቶቡሶች ዘግይተው ሊደርሱ ይችላሉ። ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው።
 
  ህጉን በማክበር መጓዝ እንዳለባችሁ አስታውሱ!
  • በሰዓቱ በት/ቤት አውቶቡስ ማቆሚያ ፌርማታ ላይ ሁኑ እና ከመኪና መንገድ ርቃችሁ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ጠብቁ።
  • ወደ ት/ቤት አውቶቡስ ከመቅረብ በፊት፣ ወይም ከመሻገር በፊት አውቶቡሱ እስኪቆም እና አሽከርካሪው ምልክት እስኪሰጥ ድረስ ጠብቁ
  • በሰላማዊ ሁኔታ ተሳፈሩ—መግፋት፣ መጋፋት፣ ወይም መሽቀዳደም አያስፈልግም።
  • አስተማሪ ወይም የትምህርት ቤት አስተዳዳሪ የሚሰጡትን መመሪያዎች እንደምትከተሉ ሁሉየአውቶቡስ አሽከርካሪውን መመሪያዎች ማድመጥ እና ማክበር ያስፈልጋል።
  • ተቀምጦ መቆየት/መጓዝ፣ የአውቶቡስ ውስጥ መተላለፊያ አለመዝጋት፣ እጆችን፣ እግሮችንና እቃዎችን በአውቶቡሱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ማስገባት አስፈላጊ ነው።
  • ሌሎችን ማክበር ያስፈልጋል—ምንም አይነት ጉልበተኝነት፣ ትንኮሳ፣ ግጭት፣ ተገቢ ያልሆነ ቃላት መሰንዘር ወይም የረብሻ ባህሪ ማሳየት ክልክል ነው።
  • በትምህርት ቤት አውቶቡስ ማቆሚያዎች አካባቢ ያሉትን ሰፈሮች እና ንብረቶች እንዳትነኩ ማክበር እና የአውቶቡሶችን ንጽህና በመጠበቅ መተባበር አስፈላጊ ነው።
  • በሌላ ሁኔታ ፈቃድ ካልተሰጠ በስተቀር በተመደበላችሁ የት/ቤት አውቶቡስ ብቻ መጠቀም አለባቸሁ
  • ስለ አደገኛ ባህሪ ተናገሩ እና ችግር ካለ ለአውቶቡስ አሽከርካሪው(ዋ) ወይም ለታመነ አዋቂ ሰው ንገሩ።
  • አስታውሱ፦ የምታደርጉት ምርጫ አስፈላጊ ነው። ሠላማዊ እና ኃላፊነት የተሞላበት ባህሪ መጠበቅ ሁሉም ሰው በሰላም ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄድ እና እንዲመለስ ይረዳል።

ህጉን ጠብቃችሁ ተጓዙ፡ ሌሎችን አክባሪ ሁኑ። ኃላፊነት ይሰማችሁ። ደህንነታችሁን ጠብቁ።

 
  ስለ ምሳ ማወቅ ያለብዎትን ነገር ሁሉ ያገኛሉ

MealViewer ድረ-ገጽ በመጎብኘት የትምህርት ቤትዎን የቁርስ እና የምሳ ዝርዝር እና የተመጣጠነ አመጋገብ ዝርዝሮችን ማየት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ቀላል እንዲሆን ተደርጓል።

ቤተሰቦች MySchoolBucks ላይ ወደ ልጃቸው አካውንት ገንዘብ እንዴት መጨመር እንደሚችሉ ማወቅ ይችላሉ። ይህ አማራጭ በኦንላይን የመክፈል አገልግሎት ወላጆች/አሳዳጊዎች ለቁርስ፣ ለምሳ፣ እና à-la-carte ለተማሪ የካፊቴሪያ ሂሳብ በክሬዲት ወይም በዴቢት ካርድ ቅድመ ክፍያ እንዲፈጽሙ የተዘጋጀ ነው።በተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ፦

የነፃ እና የቅናሽ ዋጋ ምግብ (FARMS) ማመልከቻ አቅርበዋል? ዛሬውኑ አመልክቱ! ምንም እንኳን ልጆቻችሁ ባለፈው አመት ብቁ ቢሆኑም በየትምህርት አመቱ አዲስ FAARMS ማመልከቻ መቅረብ አለበት። ተደራሽነቱ በቤተሰብ የገቢ መጠን ላይ የተመሰረተ ሲሆን ለማመልከት ቀላል ነው። በኦንላይን FARMS ማመልከቻ MySchoolApps ላይ አቅርቡ (በተለያዩ ቋንቋዎች የተተረጎሙ ቅጾች ይኖራሉ)። ለአንድ ቤተሰብ አንድ ማመልከቻ ብቻ ማቅረብ በቂ ነው። ተጨማሪ መረጃ

አሁን ያውቃሉ ቪድዎች:እንግሊዝኛ/English | español | 中文 | français | Português | 한국어 | tiếng Việt | አማርኛ/Amharic

 
  ወደ ትምህርት ቤት ስለመመለስ መሰረታዊ ነገሮች

የትምህርት አመቱ ሲጀመር ለቤተሰቦች ጥቂት አስፈላጊ ማሳሰቢያዎችን እነሆ፦

  • ፍሪጅ ላይ የሚለጠፍ የሥርዓተ ትምህርት አጭር መግለጫ፡ MCPS ተማሪዎች በእያንዳንዱ የማርክ መስጫ ወቅት ዋና ዋና ርዕሶችን፣ የትምህርት ይዘቶችን በአጭሩ፣ እና ጽሑፎችን ጭምር ምን እንደሚማሩ የሚያሳይ ቀላል፣ አንድ ገጽ ያለው መግለጫ ማጋራቱን ይቀጥላል።
  • ከመጀመሪያው ደወል ጀምሮ እስከ መጨረሻው ከት/ቤት የመሰናበቻ ደወል ድረስ ሞባይል ስልክ መጠቀም አይፈቀድም፦MCPS ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ለትምሕርታቸው ትኩረት እንዲሰጡ እና እርስ በርስ እንዲገናኙ የሚያግዝ አዲስ የሞባይል ስልክ ደንብ ተግባራዊ ያደርጋል። ከመጀመሪያው ደወል ጀምሮ ተማሪዎች እስከሚለቀቁበት ድረስ ሁሉም የግል ተንቀሳቃሽ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች በሁሉም የክፍል ደረጃዎች ከተማሪዎች ርቀው እንዲቀመጡ ይደረጋል። ይህ የትምህርት ሥራ መስተጓጎሎችን ይቀንሳል፣ ተማሪዎች በመማር ላይ በትኩረት እንዲሳተፉ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ያግዛል ተብሎ ይታመናል። ይበልጥ ለመረዳት እዚህ አንብቡ: እንግሊዝኛ/English | español | 中文 | français | Português | 한국어 | tiếng Việt | አማርኛ/Amharic
  • የተማሪዎች የስነምግባር ደንብ ይህ ሰነድ ምቹ የሆነ፣ መከባበር የሠፈነበት፣ ሥርዓት ያለው፣ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ የትምህርት ቤቶችን ሥራዎች ለማካሄድ አስፈላጊ ነው።
  • ተተኳሽ መሣሪያዎችን አስተማማኝ በሆነ ቦታ ማስቀመጥ ይለማመዱ፡ ተተኳሽ የጦር መሳሪያ አለዎት? የጎረሰ ጥይት ካለበት ያውጡ፣ ይቆልፉት እና ጥይቶቹን ለብቻ አስቀምጡ። 
  • ክትባቶች፦ የልጅዎ የክትባት ጊዜ ወቅታዊ መሆኑን ለማረጋገጥ የመስፈርቶችን ዝርዝር ይመልከቱ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ በኦገስት እና ሰፕቴምበር ወር ላይ ክትባት የሚሰጥባቸው ክሊኒኮችን ያካሄዳል።በተጨማሪም፦ MCPS ቅዳሜ፣ ኦገስት 22 በሚካሄደው የሪጅናል ወደ ት/ቤት የመመለሻ ትርኢቶች ላይ ክትባቶችን ለመስጠት አቅዷል።
  • "Check out the MCPS shop" ይመልከቱ፡ ወቅቶች ሲለዋወጡ፣ በኦንላይን ያሉት ምርቶችም እንዲሁ ይሆናሉ፣ ስለዚህ ጊዜውን እየጠበቁ ይመልከቱ። MCPS ብራንድ ላይ የምግብ ዕዳ ለመክፈል (እና MCPS የሚኮሩበት መሆኑን በማሳየት) ያግዙ!።
  • ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ምሽቶች፦ እስካሁን ያላደረጉት ከሆነ በቅርቡ ከትምህርት ቤቶች ስለ ትምህርት ቤት የመመለስ ምሽት መረጃ ይደርስዎታል። የተማሪዎን አስተማሪ ለማግኘት፣ ስለ ክፍል ትምህርት ለመስማት፣ ስለ ትምሕርት ዓመቱ የሚጠበቁ ነገሮች እና ግቦች ለማወቅ እና ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ጥሩ አጋጣሚ ነው። በስፍራው እንደምናገኝዎት ተስፋ እናደርጋለን!
  • MCPS ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ፦ ስለ ኦፊሴላዊ MCPS የአውደመረብ መተግበሪያዎች እና እንዴት ተደራሽ እንደሆኑ ይወቁ። ለሠራተኞች፣ ለወላጆች፣ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የዲስትሪክቱ አጠቃላይ ግንኙነት እና ቀጥተኛ የመልእክት ማስተላለፊያ መድረክ የሆነውን ParentSquare አካውንት እንዲኖራቸው እናበረታታለን። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ፦ 
  • የትምሕርት ቤት ቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ምዝገባ፦ በትምህርት ዓመቱ በሙሉ ለመከታተል ይጠቅምዎታል! አስፈላጊ ቀናትን—በዓላትን፣ የእረፍት ጊዜዎችን፣ ለሙያ ማበልፀግ የተመደቡ ቀናትን፣ እና ሌሎችንም— መዳፍዎ ላይ ለማስቀመጥ MCPS የትምሕርት ቤት ቀን መቁጠሪያ/ካለንደር እንዲኖርዎት ይመዝገቡ። ለመመዝገብ እና የበለጠ ለማወቅ የት/ቤት ቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ገጹን ይጎብኙ።
 
  የቅዳሜ ቀናትን ወደ ስኬት ይለውጡ—ለቅዳሜ ትምህርት ቤት/Saturday School ተመዝገቡ

ልጅዎ በቅዳሜ ትምህርት ቤት/Saturday School (ጆርጅ B. ቶማስ፣ Sr. የትምሕርት አካዳሚ) በራስ መተማመንን እና የትምህርት ስኬትን እንዲያዳብር/እንድታዳብር ያግዙ። ፕሮግራሞች ቅዳሜ ጠዋት ላይ ከመዋእለ ህጻናት እስከ አሥራሁለተኛ (K-12ኛ) ክፍል ላሉ ተማሪዎች የሚሰጡ ሲሆን በንባብ፣ በሂሳብ፣ በፈተና ዝግጅት እና ኮዲንግ እና ሮቦቲክስ የመሳሰሉ STEM ክህሎት ማበልጸጊያዎች ላይ ያተኩራሉ።

ቤተሰቦች እንዲያስመዘግቡ እና ስለ ፕሮግራሙ እንዲያውቁ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ሴፕቴምበር 19 ይካሄዳል። የመጀመሪያው የማስተማር ክፍለ ጊዜ ሴፕቴምበር 26 ከጠዋቱ 8፡30-11 a.m. ይካሄዳል።

  • ክፍያ፦ እስከ ሴፕቴምበር 1 ድረስ $85/በዓመት (FARMS ለሚያገኙ $40)። ማሳሰቢያ፦ ክፍያዎች ከሴፕቴምበር 1 በኋላ ወደ $100 / FARMS ወደ $50 ከፍ ያላሉ።
  • መጓጓዣ፦ ወደ መሀል ቦታዎች መጓጓዣ ነፃ MCPS የአውቶቡስ መስመሮች አሉ።
  • ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እና ለምዝገባ፦ saturdayschool.orgይመልከቱ
 
  ለቀጣዩ የትምህርት ዓመት የትምሕርት ቤት ቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ዝግጅት የእርስዎን አስተያየት ያጋሩን

MCPS የትምህርት አመት 2027-2028 እና 2028-2029 የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ለማዘጋጀት እየሰራ ስለሆነ የእርስዎን አስተያየት መስማት እንፈልጋለን። እባክዎን ይህንን የዳሰሳ ጥናት እስከ ሴፕቴምበር 20 ድረስ ሞልተው በመላክ የእርስዎን አስተያየት ያጋሩ። 

የእርስዎ ግብረመልስ ለዝግጅት ሂደቱ ወሳኝ ነው። MCPS የትምሕርት ቤት ካለንደር በሚያዘጋጅበት ወቅት የትምህርት ፍላጎቶችን፣ የአሠራር ፍላጎቶችን፣ በስቴት ህግ መሰረት የተደነገገ የትምህርት ቤት መዘጋትን፣ አነስተኛ የሚባል የትምህርት ቀናት እና የክሬዲት ሰዓት መስፈርቶችን ማክበር፣ መጥፎና ከባድ የአየር ሁኔታ እና ሌሎች ድንገተኛ ሁኔታዎችን፣ የሰራተኞች የሙያ ቀናትን፣ እና ተማሪዎች ቀደም ብሎ የሚለቀቁበትን ቀናት MCPS የቦርድ ፖሊሲ IDA፣ የትምህርት ዓመት የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ጋር የተጣጣሙ የግምገማ መርሃ ግብሮችን ግምት ውስጥ ያስገባል።

የዳሰሳ ጥናቱን ይሙሉ።

 
  የመኸር ወቅት/Fall የአትሌቲክስ ደህንነት ዕቅድ፡ የአትሌቲክስ ዝግጅቶቻችንን ደህንነቱ የተጠበቀ እና መነቃቃት የሰፈነበት ከማድረግ አንጻር፡

MCPS ተማሪ-አትሌቶች፣ አሰልጣኞች፣ ተመልካቾች እና ማህበረሰባችን ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቹ አካባቢን ለመጠበቅ ቁርጠኛ ነው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምሕርት ቤቶች (MCPS) አትሌቲክስ የትምህርት ዓመቱን በተነቃቃ ስፖርታዊ ጨዋነት እና በተመልካቾች ደህንነት ሳምንት ከሴፕቴምበር 4-11 ባለው ጊዜ ውስጥ ይጀምራል። ወላጆችና ተመልካቾች ጥሩ የስፖርት ጨዋነትን በተምሳሌትነት እና ተማሪ አትሌቶችን፣ አሰልጣኞችን፣ መሪዎችን እና ተቃራኒ ቡድኖችን በማበረታታት ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።

ዲስትሪክቱ የመኸር ወቅትን/Fall ሲጀምር፣ የመኸር /Fall አትሌቲክስ ደህንነት ዕቅድ ለአድናቂዎች አክብሮት የተሞላበት ባህሪ፣ በተመደቡባቸው መቀመጫዎች እና ለተማሪዎች፣ ለሰራተኞች መገናኘት ጭምር፣ የቁጥጥር ሂደቶች እና የጨዋታው መጨረሻ እስከሚጠናቀቅ ጊዜ ያሉትን ሂደቶች ያካትታል። ጥላቻን፣ መድልዎን፣ ወይም ተገቢ ያልሆነ ባህሪን የሚያካትቱ ክስተቶች MCPS ባለው የዲስፕሊን እርምጃ ፕሮቶኮሎች መሠረት ይስተናገዳሉ።

 
  አዳዲስ ቦታዎች፣ አዳዲስ ጅማሬዎች፡ MCPS በሦስት ትምህርት ቤቶች ሪባን ቆርጧል።

ኦገስት 21፣ MCPS በበርተንስቪል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ በጆአን ሌክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ እና በፑልስቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተጠናቀቁ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በይፋ ሪቫን በመቁረጥ አክብሯል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ፕሬዝዳንት ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን እና ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ቶማስ W. ቴይለር የትምህርት ቤት መሪዎች፣ ተመራጭ ባለስልጣናት እና የማህበረሰብ አባላት ጋር በመሆን ዝግጅቱን አክብረዋል። ፎተግራፎችን እና ቪድችን እንግሊዝኛ/English | ስፓንሽኛ/Spanishይመልከቱ።

 
  ተማሪዎችን በራስ በመተማመን እንዲጀምሩ ማዘጋጀት

MCPS ሁለተኛውን አመታዊ የሽግግር ቀን ኦገስት 24 ላይ አክብሯል፣ ይህም ቀኑን ሙሉ የሚፈጅ፣ ትምህርት-አልባ የትምህርት ቤት ልምድ ለመቅሰም ሲሆን ተማሪዎች ከኦፊሴላዊው የትምሕርት መጀመሪያ ቀን በፊት አዳዲስ የሚገቡባቸው ትምህርት ቤቶቻቸውን መቃኘት የሚጀምሩበት በመሆኑ ሰራተኞች ከአዳዲስ አካባቢዎች፣ ከዕለት ተዕለት ተግባሮቻቸው እና ከሚጠበቁባቸው ነገሮች ጋር እንዲላመዱ በመርዳት የተካሄደ ነው። ከርዕሰ መምህራን እና ከአስተማሪዎች ጋር ተገናኝተዋል፣ ህንጻዎችን ጎብኝተዋል፣ የዕለት ተዕለት ተግባራትን ለመለማመድ እና ከክፍል ጓደኞቻቸው ጋር ለመገናኘት እድል አግኝተዋል። ፎተግራፎችን እና ቪድኦ: እንግሊዝኛ/English |ስፓንሽኛ/Spanishተመልከቱ።

 
  አዲስ SSL ቅጾች እዚህ ይገኛሉ፡ ተማሪዎች ማወቅ ያለባቸው ጉዳይ፡

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤት (MCPS) ተማሪዎች በሙሉ ለመመረቅ 75 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ያስፈልጋቸዋል። MCPS = SSL ቅጾችን፣ ወሳኝ በሆኑ አዳዲስ የጊዜ ገደቦች እና የተሻሻሉ አገናኝ ሊንኮችን አሻሽሏል።

በቅጹ ላይ የተደረጉ ቁልፍ የሆኑ ለውጦች

  • MCPS ቅጽ 560-51 (SSL የተግባር ማረጋገጫ ቅጽ) 
    • በተሻሻለው ቅጽ መሠረት፣ ድርጅቶች የአካዳሚክ ዝግጅት እና የአገልግሎት ተግባር ዝርዝሮችን አለባቸው።
    • ተማሪዎች የተገነዘቡትን እና ያስተዋሉትን የቀሰሙትን ትምህርት ነክ ሀሳባቸውን ለመግለፅ እንዲችሉ የበለጠ ተጨማሪ ቦታ ተሰጥቷል።
  • MCPS ቅጽ 560-50 (የግል SSL መጠየቂያ)
    • ተማሪዎች በሞንትጎመሪ ካውንቲ የበጎ ፈቃደኞች ማዕከል ድረ ገጽ ላይ(tinyurl.com/SSLLorganizations) MCPS ፈቃድ የተሰጣቸው SSL ድርጅት ተብሎ ካልተዘረዘረ ማንኛውም የማህበረሰብ ድርጅት ጋር አገልግሎት ለመስጠት ቅጹን ሞልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። 
    • ድርጅቶቹ የአካዳሚክ ዝግጅት እና የአገልግሎት ተግባር ዝርዝሮችን ማቅረብ አለባቸው።

SSL አስተባባሪዎች የቀድሞውን SSL ቅጾች እስከ አርብ፣ ሴፕቴምበር 25 ድረስ ይቀበላሉ። አርብ፣ ሴፕቴምበር 25 በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም አገልግሎት በአዲሶቹ ቅጾች መመዘገብ አለበት።

 
  ከቤት ውጪ የሚከናወን ትምሕርት ይቃኙ፡ የቤተሰብ ኦፕን ሀውስ ለሴፕቴምበር 8 ተዘጋጅቷል።

MCPS የአካባቢ ትምህርት ፕሮግራሞች ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 8 ከቀኑ 6:30-8 p.m. ለመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቤተሰቦች ኦፕን ሀውስ ዝግጅት ያካሄዳል። ሰራተኞች ስለ ስሚዝ ማዕከል የፕሮግራሚንግ አጠቃላይ ገፅታ መግለጫ ይሰጣሉ፣ የካምፓስ ጉብኝት ይደረጋል፣ እና ስለ ስድስተኛ ክፍል የአካባቢ ትምህርት ፕሮግራም መረጃ እና ልምዶችን ያካፍላሉ። አድራሻ፦ The Smith Center is located at 5110 Meadowside Lane in Rockville. ተጨማሪ ይወቁ እና ለመሳተፍ ይመዝገቡ

 

ለውጥ ያድርጉ፦ የመልሶ ማቋቋም ቀለም ሩጫ ላይ ይሳተፉ

አስተማማኝ የአእምሮ ጤናን ለመጠበቅ፣ የአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀምን ለመከላከል፣ እና አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ የእንክብካቤ ተደራሽነት ላይ ያተኮረ ለቤተሰብ ተስማሚ ዝግጅት ላይ ይቀላቀሉን። አንድ ማይል የሚፈጀው ቀለም ሩጫ፣ የእግር ጉዞ እና የማገገም ሚና ለመጫወት የሩጫ ፕሮግራም ቅዳሜ፣ ኦገስት 29 ከጠዋቱ 9-11 a.m. በሮክቪል ከተማ ይካሄዳል። ዝግጅቱ የመታሰቢያ ሥነ ሥርዓት እና የሪሶርስ ትርኢትም ያካትታል፣ በዚህ ዝግጅት ላይ ተሳታፊዎች ከአስተማሪዎች፣ ከማህበረሰብ ግብዓቶች እና ከህክምና ባለሙያዎች ጋር መገናኘት ይችላሉ። የሚሳተፉ ተማሪዎች የአገልግሎት ትምህርት ሰዓት ማግኘት ይችላሉ። ተጨማሪ ይወቁ እና ለመሳተፍ ይመዝገቡ

 
  ማሳሰቢያዎች፦
  • ሰኞ፣ ሴፕቴምበር 7 – የሰራተኞች ቀን፤ ትምህርት ቤቶችና ቢሮዎች ዝግ ናቸው
  • የፋሲሊቲ አማካሪ/አድቫይዘሪ ኮሚቴ፡ MCPS ለትምሕርት አመት 2026-2027 በዚህ ኮሚቴ ውስጥ የሚያገለግሉ የማህበረሰብ አባላትን ይፈልጋል። የኮሚቴ አባላት MCPS የትምህርት ቤት መገልገያዎችን የረጅም ጊዜ እቅድ ሲያዘጋጅ እውቀታቸውን፣ ልምዳቸውን፣ እና አመለካከታቸውን ያካፍላሉ። ፍላጎት ካለዎት፣ እስከ አርብ፣ ሴፕቴምበር 4 ድረስ ማመልከቻ ያስገቡ።
 

ከዜና አምድ

  • ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርኢቶች፡ በሺዎች የሚቆጠሩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ እና የማህበረሰብ አባላት ቅዳሜ፣ ኦገስት 22 ከትምህርት ስርዓት ሰራተኞች እና ከማህበረሰብ አጋሮች ጋር በመሆን 2026-2027 የትምህርት ዓመት በስድስቱ ትርኢቶች ላይ ተሳትፈዋል። ፎተግራፎቹን ይመልከቱ እና ቪዲዮ እንግሊዝኛ | ስፓንሽኛ ይመልከቱ።
  • MCPS ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በዩኤስ የዜና ዘገባዎች ሜሪላንድን ይመራሉ፡ በዩኤስ ኒውስ ኤንድ ወርልድ ሪፖርት በተለቀቁት የቅርብ ጊዜ ዘገባዎች መሠረት አምስት ትምህርት ቤቶች በሜሪላንድ ውስጥ ካሉት ከፍተኛ የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል እንደሆኑ እውቅና አግኝተዋል፣ የፑልስቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ በስቴቱ ሁለተኛ ደረጃ አግኝቷል። ይበልጥ ያንብቡ።
  • MCPS አዳዲስ ርእሰ መምህራንን በደስታ ተቀብሏል፡ የዲስትሪክቱን 26 አዳዲስ ርእሰ መምህራን (አዲስ የተቀጠሩ ወይም ወደ ሌላ ትምህርት ቤት የተዛወሩ) ለትምህርት ቤታቸው ማህበረሰቦች አስደሳች እሳቤዎቻቸውን እውነታ እንዲያካፍሉ ተጠይቀዋል። የተናገሩትን አንብቡ
 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

ከሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) የበለጠ መረጃ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች
©1995–2026 Montgomery County Public Schools