skyline

September 10, 2021

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ማህበረሰብ፡-

ቅዳሜ ሴፕቴምበር 11፥ የሽብር ጥቃቶች የተፈጸሙበትና በአሜሪካ ታሪክ የጨለማ ጊዜያት አንዱ የሆነው በዓል 20ኛ ዓመት ይከበራል። በዚያ ቀን በኒውዮርክ ከተማ፣ ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ በፔንታጎን እና በሻንክስቪል ፔንስልቫንያ ወደ 3,000 የሚጠጉ ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በዚያ ማክሰኞ ጠዋት የሁሉም ሰው ሕይወት ተነክቷል።

ይህንን ዓመታዊ በዓል ለማሰላሰል ትንሽ ጊዜ ስንወስድ፥ በሽብር ጥቃቶች እና ከዚያ በኋላ በተወሰዱት ወታደራዊ እርምጃዎች ምክንያት ያጣናቸውን እናስታውስ። ሌሎችን ለማዳን ሕይወታቸውን አደጋ ላይ የጣሉ ሰዎችን እናስታውስ። ከዚያን ቀን የተማርናቸውን ነገሮች በአንድነት እናስብ።

ከተማሪዎቻችን መካከል ሴፕቴምበር 11/2001 በሕይወት የነበሩ በጣም ጥቂቶች (ካሉ) እና ብዙ አስተማሪዎቻችን፣ አስተዳዳሪዎች እና ሰራተኞቻችን ምን እየሆነ እንደነበር ሙሉ በሙሉ ለመረዳት በጣም ወጣት ነበሩ። በዚያ ቀን ምን እንደተከሰተ እና ከዚያ በኋላ ባሉት ሳምንታት፣ ወራት እና ዓመታት ውስጥ ምን እንዳስከተለ በሐቀኝነት መወያየት አስፈላጊ ነው። የ 9/11 መታሰቢያ ሙዚየም መምህራን እና ወላጆች ውይይቶችን ለመጀመር የሚጠቅማቸው ብዙ ሪሶርሶች አሉት። ግን ብዙውን ጊዜ መሆን እንዳለበት፥ የምናስተምረውን ያህል ማዳመጥም አስፈላጊ ነው።

በ MCPS፥ ተማሪዎች የተከሰተውን ሁኔታ እንዲያጤኑ እና ሁላችንም የተሰማንን የፍርሃት እና የተስፋ መቁረጥ ስሜት ለማሸነፍ ሰራተኞቻችን የረዱበትን መንገድ እናስታውሳለን። የ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያሳደረብንን ጫና እና ተጽእኖ ስንመለከት ዛሬም እንደምናስበው ትምህርት ቤቶቻችን የማገገም ሂደቱ አካል ናቸው።

በሴፕቴምበር 11/2001 የሚወዷቸው የሞቱባቸውን የ MCPS ቤተሰቦቻችን እና ባልደረቦቻችን፥ በዚህ ቀን ስለእናንተ እያሰብን ነው። ለሌሎቻችን በሐቀኝነት ለማሰላሰል እና ለመወያየት ቁርጠኝነት ይኑረን። ጥፋትን ወደ ሌሎች የማላከክ እና ጣት የመጠቆም አባዜ እናስወግድ። የ 9/11 ክስተቶችን ያስከተለውን የጥላቻ ሁኔታ እና ከዚያ በኋላ የተፈጸሙትን የጥቃት እና መድሎአዊ ድርጊቶችን እናስወግድ። በ MCPS ማህበረሰብ ውስጥ እርስ በእርስ በመከባበር እና በሰላም ላይ የተመሠረተ አንድነትን፣ ብዙሃነት ያለው ማህበረሰብ ለመፍጠር ቁርጠኛ ነን። መቼም መዘንጋት የለብንም። ይህንን አመታዊ የመታሰቢያ በዓል ስለሌሎች ያለንን ግንዛቤ ለመገንባት፣ መቻቻልን ለማሳደግ እና ሰላምን ለማጎልበት እንደ አጋጣሚ እንጠቀምበት።

ከአክብሮት ሰላምታ ጋር

Brenda Wolff, president, Montgomery County Board of Education
ብሬንዳ ዎልፍ፥ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ፕሬዝዳንት

Monifa B. McKnight, interim superintendent, Montgomery County Public Schools ሞኒፋ ቢ. መክናይት፥ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ጊዜያዊ ሱፐር ኢንተንደንት



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools