የሠመር መልእክት - ደህንነትዎን ይጠብቁ ፣ ግንኙነትዎ ይቀጥል

June 14, 2023

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

የትምህርት ዓመቱን ስናገባድድ እና የተማሪዎቻችንን፣ የሰራተኞቻችንን እና የቤተሰቦቻችንን ትጋት እና ስኬቶች ስንገነዘብ፣በዚያውም የሠመሩን ወራት በጉጉት እንጠብቃለን! ከቤት ውጭ ብዙ ጊዜ በማሳለፍ፣ ሙቀት እና ትንኞች ሲነድፉን ስንከላከል እና በመዋኛ ገንዳዎች እና መናፈሻ ቦታዎች ላይ መሰብሰብ ስንጀምር ሠመር ቀድሞውኑ የደረሰ ይመስላል።

በሠመር ወራት በደህና ለመደሰት፣ ወላጆች እና ተንከባካቢዎች በሠመር የሚያጋጥሙ ጉዳቶችን መከላከል እና የጤና አጠባበቅን ትኩረት እንዲሰጡ እናበረታታለን። የመጫወቻ ሜዳ፣ ስፖርት እና የውሃ ደህንነት፣ በሙቀት የሚመጣ መጎዳትን መከላከል፣ እና የፀሀይ መከላከያ መጠቀምን የመሳሰሉ ጉዳዮች ከቤተሰብ አባላት እና ሌሎች ተንከባካቢዎች ጋር የሚነጋገሩባቸው አስፈላጊ ጉዳዮች ናቸው። ከጓደኞቻቸው ጋር ጊዜያቸውን የሚያሳልፉ ወይም የሚሰሩ ታዳጊዎች ከመኪና አደጋ ደህንነታቸውን መጠበቅ፣ ከጓደኞቻቸው ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ዙሪያ ስለሚጠበቁ ነገሮች፣ ተጠያቂነት እና እንደ አልኮሆል ወይም ሌላ እጽ መጠቀም የመሳሰሉ አደገኛ ባህሪዎችን በሚመለከቱ ነገሮች ተጨማሪ ውይይቶችን ማድረግ ሊጠቅማቸው ይችላል።

አንዳንድ ቤተሰቦች በትምህርት አመቱ ከሚካሄዱት መርሃ ግብሮች እና ሪሶርሶች ሲለዩ የሠመር ወራት ጫና ሊፈጥርባቸው ይችላል። ተማሪዎች ከእኩዮቻቸው መገለል ሊሰማቸው ይችላል፣ በትምህርት ቤት የሚታመኑባቸውን አዋቂዎች ሊያጡ ይችላሉ፣ ወይም አብዛኛውን ጊዜያቸውን በመገናኛ ብዙሃን ስክሪን እና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተጠደምደው ያሳልፋሉ። በመገናኘት፣ልጆች ከሌሎች ጋር እንዴት እንደሚገናኙ ማስገንዘብ እና በሠመር የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ላይ ጠቃሚ በሆኑ ነገሮች ጊዜንና መዋዕለ ንዋይን ማፍሰስ ስሜታዊ እና አካላዊ ጤንነትን ይረዳል። የተመጣጠነ ምግብ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የእንቅልፍ መርሃ ግብሮች በሠመር ወቅት ስለሚቀያየር ሁሉም ሰው በደንብ ከተመገበ፣ ንቁ እና እረፍት ካደረገ ጥሩ ስሜት ይሰማዋል።

መልካም እና ጤናማ የሠመር ወቅት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

Patricia Kapunan፡ M.D., MPH
MCPS Medical Officer

የአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ የጤናማ ልጆች ድረ ገጽ/American Academy of Pediatrics Healthy Children Website
ከቤት ውጪ በጤንነት መቆየት/Staying Safe Outdoors / Cómo mantenerse seguro al aire libre)
የፀሐይ ሙቀትን መከላከል/Sun Safety and Protection Tips / Consejos de seguridad y protección bajo el sol
ስለ ውኃ ዋና ትምህርት ወላጆች ማወቅ ያለባቸው ነገር (ልጅዎን በውሃ ውስጥ እና በአካባቢው እንዴት እንደሚቆጣጠሩ ያስረዳል
Clases de natación: cuándo comenzar y qué deben saber los padres (y Cómo supervisar su niño cuando está dentro o en cercanías del agua)
ከመገናኛ ብዙሃን ስክሪን ይልቅ: ልጆችዎ ጤናማ የሚዲያ አጠቃቀም ልማዶችን እንዲገነቡ እርዷቸው / Hábitos saludables para el uso de pantallas en la infancia y adolescencia

የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከላትበዚህ ሠመር ለልጆችዎ ጤናማ አካል እና አእምሮ እንዲኖሯቸው ይረዷቸዋል / Este verano, dé a sus hijos un cuerpo y una mente sanos

የልጆች ናሽናል ሆስፒታል አንፀባራቂ ተከታታይ አገልግሎት
የሠመር የዕለት ተዕለት ተግባርን ለማዘጋጀት ስድስት ምክሮች
የሠመር የአስም ትኩሳትን መከላከል
የኦቲዝም ተጠቂ የሆነ(ች) ልጅዎን ለሠመር ዕረፍት ማዘጋጀት

የታዳጊዎች ጤንነት
From KidsHealth.org:  የሠመር ወቅት ደህንነት ለወጣቶች/Summer Safety for Teens
ከወጣት ሴቶች ጤና ማዕከል / የወጣት ወንዶች ጤንነት
 ፓርቲዎች በሚደረጉበት ወቅት ላይ ደህንነትን መጠበቅ
መኪና በሚነዱበት/በሚያሽከረክሩበት ጊዜ ደህንነትን መጠበቅ
የጓደኛ ግፊት/Peer Pressure / Presión de los Pares
ለኮሌጅ ደህንነትን መጠበቅ / Salud Universitaria



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools